ዶ/ር ፍሬው ለማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
በኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ፍሬው ለማ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማህበር አሳውቋል።
ዶ/ር ፍሬው እ.ኤ.አ. ከ1993 አንስቶ የማህበሩ አባል ነበሩ።
የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማህበር በዶ/ር ፍሬው ለማ ህልፈት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገልፆ ፤ የቀብር ስነስርዓታቸው በነገው ዕለት እንደሚፈፀም አሳውቋል።
@tikvahethiopia

#RosewoodFurniture
< ሮዝውድ ፈርኒቸር>
በዘመናዊ ማሽነሪ እና በ3D ዲዛይን የታገዘ,
ለኣጠቃቀም ምቹ እና ወቅቱን የጠበቁ ዘመናዊ የፈርኒቸር ስራዎች !
👉🏼 ስልክ : 0921346038
👉🏼 ሜሴጅ @Rosewo0d
👉🏼 ኣድራሻ : ኣዲሱ ገበያ ኣደባባይ
ስራዎቻችንን ለማየት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.iss.one/R0seWood

አምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
በደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ በሚኖሩበት ሀገር አሜሪካ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል።
በታጠቅ ጦር ሰፈር፣ ህፃናት አምባ ፣ ጀግኖች አምባ መቋቋም ላይ ድርሻ እንደነበራቸውና በኢሰፓ ውስጥ የጎላ ሚና እንደነበራቸው ይነገራል።
አምባሳደር ዶ/ር ካሳ በጄኔቫ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በሂብሪው ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ጀሩሳሌም የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ምሩቅ ነበሩ።
አምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ በደርግ ስርዓት ግንቦት 19/1983 ከሀገር ለቀው የወጡ የመጨረሻው ከፍተኛ ባለስልጣን ናቸው።
NB : ከ3 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ለውጥ ተከትሎ መንግስት ባቀረበው ጥሪ ከ27 ዓመት የስደት ኑሮ በኃላ ወደኢትዮጵያ መጥተው እንደነበር ይታወሳል።

TIKVAH-ETHIOPIA
ዶ/ር ፍሬው ለማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ፍሬው ለማ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማህበር አሳውቋል። ዶ/ር ፍሬው እ.ኤ.አ. ከ1993 አንስቶ የማህበሩ አባል ነበሩ። የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማህበር በዶ/ር ፍሬው ለማ ህልፈት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገልፆ ፤ የቀብር ስነስርዓታቸው በነገው ዕለት እንደሚፈፀም አሳውቋል። …
#DrFerewLemma
" ከባድ እና ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶኛል " - ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በዶ/ር ፍሬው ለማ ህልፈት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው ገለፁ።
ሚኒስትሯ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ " የሥራ ባልደረባችንና በጤና ሚኒስቴር ለረጅም አመታት የምግብና ስርዓተ ምግብ ከፍተኛ አማካሪ ሆነው ሲያገለግሉ በነበሩት የህብረተሰብ ጤና እና የስነ-ምግብ ባለሙያ ዶ/ር ፍሬው ለማ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት ከባድና ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶኛል " ብለዋል።
ዶ/ር ፍሬው ለማ ፤ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት በመምህርነት ለረጅም አመታት ያገለገሉ ሲሆን በጤናው ዘርፍ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ መሆንን ጨምሮ በርካታ ስራዎችን ሰርተዋል።
በለንደን ሳውዝ ባንክ ዩንቨርስቲ ከፍተኛ ተመራማሪ ሆነው የሰሩ ሲሆን በኢትዮጵያ ስርዓተ-ምግብን ለማሻሻል በትጋት እና ቁርጠኝነት በብዙ አለም አቀፍ እና ሀገራዊ መድረኮች አገልግለዋል።
ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፥ " በዚህ ከባድ ጊዜ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻው እንዲሁም ለስራ ባልደረቦቻቸዉ በሙሉ ፈጣሪ ልባዊ መጽናናትን እንዲሰጥ እመኛለሁ " ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

#UPDATE😷
የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ፦
🇫🇷 ፈረንሳይ በ24 ሰዓት ከ100 ሺ በላይ የኮቪድ-19 ኬዝ ተመዝግቧል፤ በሀገሪቱ 104,611 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
🇮🇳 በህንድ ከጃንዋሪ 3 ጀምሮ እድሜያቸው 15 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የኮቪድ-19 ክትባቶች ማግኘት እንደሚችሉ ጠ/ሚ ናሬንድራ ሞዲ አሳውቀዋል።
🇮🇱 እስራኤል 100,000 ዩኒት የPfizer ፀረ-ቫይረስ ኮቪድ-19 ክኒን Paxlovid አዛለች። ትዕዛዙ ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ለከባድ ህመም ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች የሚውል መሆኑን ከባለስልጣናት ተሰምቷል።
🇩🇴 የዶሚኒካን ሪፐብሊክ የመጀመሪያውን የኦሚክሮን ኬዝ ሪፖርት አድርጋለች።
🇵🇹 ፖርቹጋል ኦሚክሮን ልውጥ ቫይረስ በሀገሯ በዋነኝነት እየተሰራጨ የሚገኘው ዝርያ መሆኑን አሳውቃለች፤ ትላንት ከ10,000 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።
🇹🇭 ታይላንድ የመጀመሪያው የኦሚክሮን የሀገር ውስጥ ስርጭትን ሪፖርት አድርጋለች።
🇪🇹 ኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ-19 ስርጭት በአስከፊ ሁኔታ እየተሰፋፋ ስለመጣ ሁሉም ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በቢሾፍቱ ከተማ በነበረ አንድ የውይይት መድረክ ላይ አሳስበዋል።
🇨🇳 የ13 ሚሊዮን ሰዎች መኖሪያ በሆነችው የቻይናዋ ከተማ ዢያን ሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ከተላለፈ ዛሬ 4ኛ ቀን ሲሆን የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱ ተነግሯል።
🇪🇹 የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ህብረተሰቡ በኮቪድ -19 ክትባት ዙሪያ የሚወሩ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ፣ አሉባልታዎችን እና ኢ-ሳይንሳዊ የሆኑ መረጃዎችን ወደ ጎን በመተው በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራታቸው የተረጋገጠ ክትባቶችን በመውሰድ ጤንነቱን እንዲጠብቅ ብለዋል።

ዴዝሞንድ ቱቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
የደቡብ አፍሪካ ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ዴዝሞንድ ቱቱ በደቡብ አፍሪካ የጨቋኙን አፓርታይድ ስርዓት እንዲወገድ የታገሉና የኖቤል የሰላም ተሸላሚ ነበሩ።
የሊቀ ጳጳሱን ከዚህ አለም በሞት መለየት ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ አረጋግጠው መግለጫ አውጥተዋል።
በመግለጫቸው የእሳቸው ማረፍ " ነፃ የወጣች ደቡብ አፍሪካን በውርስ ያበረከቱልን ያ ድንቅ ትውልድ አካል ስንብት አንድ ምዕራፍ መሆኑን ማሳያ ነው " ብለዋል።
ዴዝሞንድ ቱቱ በአገራቸው ደቡብ አፍሪካ ሆነ በተለያዩ አገራት ስመ ጥር የሆኑና በሰላም ምልክት ከሚታወቁ ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበሩ።
በደ/ አፍሪካ ውስጥ አናሳ ነጭ መንግሥት ሲተገበር የነበረውንና በጥቁሮች ላይ ከፍተኛ ጭቆና ፣ ግፍ እና አድሏዊነት በፖሊሲ ደረጃ የጫነውን የአፓርታይድ ስርዓት በመቃወም ከነበረው ትግል ጀርባ አንቀሳቃሽ ግለሰቦች አንዱ ነበሩ። #ቢቢሲ

" የተላለፈውን ውሳኔ አትቀበልም፤ አታስፈፅምም፤ የትኛውንም አይነት ትብብር አታደርግም " - ኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ዙሪያ ያካሄደውን ልዩ ስብሰባና በምክር ቤቱ የጸደቀውን የውሳኔ ሀሳብ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫው፥ ኢትዮጵያ ም/ ቤቱ አንዳንድ አገራት የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያና መጠቀሚያ መሆኑ እጅጉን እንዳሳዘናት ገልጿል። …
" በህግ ደረጃ ኢትዮጵያ እስካልተስማማች ድረስ ወደ ሀገር የመግባት መብት የላቸውም " - ዶ/ር አደም ካሴ
የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በ08/04/2014 ዓ/ም በአብላጫ ድምፅ ያሳለፈውን ውሳኔ (ዓለም አቀፍ የመርማሪ ቡድን በኢትዮጵያ እንዲሰማራ) ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው ፤ እንደማታስፈፅም፤ የትኛውም አይነት ትብብር እንደማታደርግ ማሳወቋ ይታወሳል።
የተመርማሪ ሀገር ፍቃድ በሌለበት የመርማሪ ቡድኑ ዕጣ ምን ሊሆን ይችላል ? ኢትዮጵያ ተገዳ መርማሪዎችን የምታስገናግድበት አሰራር ወይም ዓለም አቀፍ ህግ አለ ?
በዚህ ጉዳይ #ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡት ዶክተር አደም ካሴ (በተለይ በአፍሪካ የህግ እና ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ) ተከታዩን ብለዋል ፦
" በዓለም አቀፍ ህግ ይሄን ኮሚሽን በሚመለከት አንድ ሀገር ውስጥ ሊገባ የሚችለው / በሀገሪቱ ገብቶ ሊመረምር የሚችለው በሀገሪቱ ፍቃድ ከተሰጠው ብቻ ነው።
ኢትዮጵያን ሊያስገድዳት የሚችል ስርዓት የለም። ምንም እንኳን የህግ ስርዓት ባይኖርም በፖለቲካ ደረጃ ጫና ሊያመጣ የሚችል ፤ ምን የምትደብቁት ነገር አለ ? እየተባለ ፖለቲካዊ ጫናዎችን ሊያመጣብን ይችላል።
በህግ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት እስካልተስማማ ድረስ ወደ ሀገር የመግባት መብት የላቸውም።
ሌላው ጉዳይ በአጠቃላይ በዓለም ደረጃ ከውሳኔ ሰጪ አካላት በተጨማሪ እነዙህ ውሳኔ አካላትን እየተጠቀሙ አንዳንድ ሀገራት እነሱ የሚደግፉትን አቋም ለማራመድ ይጠቀሙበታል።
በተለይ አሜሪካ እና ምዕራባውያን ኢትዮጵያ ይሄን ቡድን የማታስገባ ከሆነ አንዳንድ ጫናዎች ለማስረግ ለምሳሌ ማዕቀቦችን ለመጫን እና ግፉቶችን ለማድረግ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
ኢትዮጵያ በህግ ደረጃ ወደ ኢትዮጵያ ውስጥ የማስገባት ግዴታ ባይኖርባትም በተመድም ከዛም አልፎ ውሳኔውን የሚደግፉ ሀገራት ምዕራባውያን ሀገራትም ያንን ተጠቅመው ጫና ሊያደርጉ ይችላሉ።
ነገር ግን ወደ ኢትዮጵያ አይገቡም ማለት ምርመራውን ማድረግ አይችሉም ማለት አይደለም። ምርመራውን ማካሄድ ይችላሉ፤ ይቀጥላሉ በስልክም በሌላም መንገድ አካሂደው አለ የሚሉትን መረጃ ለምክር ቤቱ ያቀርባሉ። "

" የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት የሚገለጽበት ጊዜ አልተወሰነም " - አቶ ረዲ ሽፋ
ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎች ለ @tikvahuniversity ደርሰዋል።
የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ "ፈተናው ገና እየታረመ" መሆኑን ለቲክቫህ ገልጸዋል።
የፈተናው ውጤት የሚገለጽበት ጊዜ አለመወሰኑንም ነግረውናል።
"የፈተናው ውጤት በዚህ ቀን ይገለጻል ተብሎ የተቀመጠ ቀነ ገደብ የለም። ስለዚህ በዚህ ቀን ይፋ ይደረጋል ልንል አንችልም" ብለዋል ዳይሬክተሩ።
የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ለፈተናው ያልተቀመጡ ተማሪዎች ከአንድ ወር በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ ይደረጋል ተብሎ የነበረ ቢሆንም አሁን ባለው ሁኔታ ፈተናውን መስጠት እንደማይቻል ገልጸዋል።
አካባቢዎቹ ገና እየተረጋጉ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ተማሪዎቹ ፈተናውን ለመውሰድ በስነ ልቦና መዘጋጀት እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል።
More : @tikvahuniversity

#GoodayOn Mobile App
የፈለጉትን ባለሙያ ካሉበት ሆነው አማርጠው የሚያገኙበት መተግበሪያ!
አስጠኚ ፣ ሹፌር ፣ ቧንቧ ሰራተኛ ፣ ኤሌክትሪሺያን ፣ ዲሽ ጥገና ፣ መካኒክ ፣ የግንባታ ፊኒሺንግ ፣ ሽያጭ ፣ የሂሳብ ባለሞያ እና ...ሌሎችም
ከGoodayOn መተግበሪያ በተጨማሪ ፤ ወደ 9675 ጥሪ ማእከል በመደወል አገልግሎታችንን ማግኘት ይችላሉ።
GoodayOn መተግበሪያን ለማውረድ ፤ https://cutt.ly/JWR6vZb
ቴሌግራም ቻናል ፤ @goodayOn #ጉዳይ 9675
የፈለጉትን ባለሙያ ካሉበት ሆነው አማርጠው የሚያገኙበት መተግበሪያ!
አስጠኚ ፣ ሹፌር ፣ ቧንቧ ሰራተኛ ፣ ኤሌክትሪሺያን ፣ ዲሽ ጥገና ፣ መካኒክ ፣ የግንባታ ፊኒሺንግ ፣ ሽያጭ ፣ የሂሳብ ባለሞያ እና ...ሌሎችም
ከGoodayOn መተግበሪያ በተጨማሪ ፤ ወደ 9675 ጥሪ ማእከል በመደወል አገልግሎታችንን ማግኘት ይችላሉ።
GoodayOn መተግበሪያን ለማውረድ ፤ https://cutt.ly/JWR6vZb
ቴሌግራም ቻናል ፤ @goodayOn #ጉዳይ 9675
#UPDATE😷
የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ፦
🇮🇷 ኢራን በኮቪድ-19 ኦሚክሮን ዝርያ ስጋት ከብሪታንያ ፣ ፈረንሳይ ፣ ዴንማርክ እና ኖርዌይ የሚመጡ መንገደኞችን ለ15 ቀናት ያህል አግዳለች። በህዳር ወር መጨረሻ በደቡብ አፍሪካ እና በሰባት ጎረቤት ሀገራት ተጓዦች ላይ የተጣለው ተመሳሳይ እገዳ ለ15 ቀናት ተራዝሟል።
🇯🇴 ጆርዳን 295 የኦሚክሮን ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ሪፖርት አድርጋለች።
🇴🇲 ኦማን ወደሀገሪቱ ለመግባት ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የውጭ አገር ተጓዦች ቢያንስ ሁለት የኮቪድ-19 ክትባት መከተብ እንዳለባቸው አሳውቃለች። በሌላ በኩል በደቡብ አፍሪካ፣ ናሚቢያ፣ ቦትስዋና፣ ዚምባብዌ፣ ሌሶቶ፣ ኢስዋቲኒ እና ሞዛምቢክ የተጣለድ እግድ ተነስቷል።
🇹🇷 በቱርክ እስካሁን ከ128.6 ሚሊዮን በላይ ክትባቶች ተሰጥተዋል።
🇵🇸 የፍልስጤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በጋዛ ሰርጥ የመጀመሪያውን የኦሚክሮን ኮቪድ-19 ልውጥ ቫይረስ ሪፖርት አድርጓል።
🇪🇹 በኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት (ከሰኞ - እሁድ ባሉት ቀናት) 22,321 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በተጠቀሰው ጊዜ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል።
🇺🇸 በአሜሪካ በዚህ የበዓላት ሰሞን እጅግ በጣም ተላላፊ የሆነው የኦሚክሮን ልውጥ ቫይረስ በመላው ሀገሪቱ መስፋፋት መቀጠሉ ተገልጿል።

#እድንታውቁት
የኤክሳይዝ ታክስ ፈቃድ ፦
ማናቸውም ሰው ከገቢዎች ሚኒስቴር የተሰጠ የኤክሳይዝ ታክስ ፈቃድ ሳይኖረው በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 የተዘረዘሩ ሥራዎችን ሊያከናውን አይችልም፡፡
የኤክሳይዝ ታክስ ፈቃድ ኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ምርቶች ለማምረት በተፈቀደለት አምራች እና በታክሱ መስሪያ ቤት መካከል እንደተፈፀመ ውል ይቆጠራል፡፡
በፈቃዱ የተመለከቱ የውል ቃሎችንና ሁኔታዎችን የሚጥስ የተፈቀደለት አምራች በወንጀል ተጠያቂ ይሆናል፡፡
የኤክሳይዝ ታክስ ፈቃድ የሚከተሉትን መረጃዎች የሚይዝ ሊሆን ይገባል:-
1. የተፈቀደለትን አምራች ስም፤
2. የተፈቀደለትን አምራች የግንኙነት አድራሻ (ኢሜይል፣ ፋክስና ስልክ)፤
3. ፈቃዱ ተፈፃሚነት መሆን የሚጀምርበትን ቀን፤
4. የተፈቀደለት አምራች የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ምርቶች የሚያመርትበትን ፋብሪካ እና የዋናው መሥሪያ ቤት አድራሻ፤
5. የተፈቀደለት አምራች በፋብሪካው ውስጥ እንዲጠቀምባቸው በታክሱ ባለሥልጣን የተፈቀደለትን መሣሪያዎች ዝርዝር እንዲሁም፤
6. የሚያመርተው ምርት ዓይነት፡፡
የኤክሳይዝ ታክስ ፈቃድ የተፈቀደለትን አምራች የሥራ አፈፃፀም መሠረት በማድረግ የንግድ ሥራውን የሚያካሂድባቸውን ሁኔታዎች የሚይዝ ሊሆን ይችላል፡፡
የተፈቀደለት አምራች በፈቃዱ በተዘረዘሩ መሣሪያዎች ለመጠቀም የሚችለው በፋብሪካው በተመለከተው አድራሻ ብቻ ነው፡፡
የተፈቀደለት አምራች የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ምርቶች የሚመረቱበትን አድራሻ / መሣሪያ ከመለወጡ በፊት፣ ይህንኑ ለታክስ መስሪያ ቤቱ በማስታወቅ በፈቃዱ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ መጠየቅ አለበት፡፡
የኤክሳይዝ ታክስ ሚከፈልባቸው ምርቶች የሚመረቱበትን አድራሻ ወይም የመሣሪያዎች ለታክሱ መስሪያ ቤት ሳያስታውቅ እና በፈቃዱ ላይ ማሻሻያ ሳይደረግ አድራሻቸውን ወይም መሣሪያዎችን የለወጠ ባለፈቃድ በኤክሳይዝ ታክስ አስተዳደር አዋጅ መሠረት በወንጀል ተጠያቂ ይሆናል፡፡
የተፈቀደለት አምራች ፋብሪካ እና የማምረቻ መሣሪያዎች በአዋጁ የተደነገገውን የሚያሟሉ መሆኑ በታክሱ መስሪያ ቤት ባለሙያዎች ጉብኝት ሳይረጋገጥ የኤክሳይዝ ፈቃድ ሊሰጥ አይችልም፡፡
ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር

" ያለንበት ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ ነው " - በሳዑዲ የታሰሩ ዜጎች
በሳዑዲ እስር ቤት እየተሰቃዩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ግፋቸውን ህዝብ እንዲሰማላቸውና የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲሰጣቸው ተማፀኑ።
ለበርካታ ወራት በአሰቃቂ ሁኔታ በእስር ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያውኑ ያሉበት ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ መሆኑን ገልፀዋል።
በእስር ቤቱ በርካታ ቁጥር ያለው እስረኛ እንደሚገኝ የገለፁት ታሳሪዎቹ ከነዚህ ታሳሪዎች ውስጥ አቅመ ደካሞችና ሴቶች እንዲሁም ህፃናት ሳይቀር እንደሚገኙበት አሳውቀዋል።
አሁን ላይ ትኩረት የሚሰጣቸውን አካል በማጣታቸው እንግልቱ መጨመሩንና ተስፋቸው መሟጠጡን በመግለፅ ለህዝብና ለመንግስት አቤት እያሉ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
እስር ቤቱ ደረጃውን ያልጠበቀና እስር ቤት ሊባል የማይችል ማጎሪያ እንደሆነ የገለፁት ታሳሪዎቹ በታሰሩ ወቅት የለበሱትን ልብስ ብቻ እንደለበሱ አመታትን ሳይቀር ሊያሳልፉ የሚችሉበት ዘግናኝ ቦታ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል።
ይህን አስከፊ ሁኔታ በመመልከት የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይሰጣቸው ዘንድ ተማጽነዋል።
ሳዑዲ አረቢያ እስር ላይ ሚገኙ ወገኖች ባስተላለፉት መልዕክት " አንድ ነጭ በሌላ ሀገር ቢታሰር የዓለም ሚዲያዎች እያብጠለጠሉ ቢያስወሩት ነጩ ተፈቷል ይባላል ፤ እኛ ግን በመቶ ሺዎች የምንቆጠር ኢትዮጵያውያን መብታችን የአንድ ነጭ ያህል እንኳን አልሆነም " ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ " ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪ ነን የሚሉት አካላት በማያገባቸው ነገር በየሀገሩ የሚዳክሩ ለምን ወደ ሳዑዲ ጎራ አይሉም፤ ለምን መጥተው እስር ቤቱን አይጎበኙም ? እስር ቤቶች በኢትዮጵያውያን እና በሌሎችም ሀገራት ዜጎች ተጨናንቋል በተለይ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርደው ስቃይ የከፋ ነው " ሲሉ ወቅሰዋል።
Credit : ሀሩን ሚዲያ

#NBE
ባንኮች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሚያስቀምጡት መጠባበቂያ ገንዘብ ላይ ለቡና ላኪዎችና አቅራቢዎች ብድር እንዲሰጡ በብሔራዊ ባንክ የተላለፈው መመርያ ከታኅሳስ 13/2014 ዓ.ም. ጀምሮ መተግበር መጀመሩን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
በኢንዱስትሪው ውስጥ እስካሁን ባልተለመደ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን ከብሔራዊ ባንክ በተላለፈው መመርያ መሠረት ባንኮች በብሔራዊ ባንክ ከሚያስቀምጡት የአሥር በመቶ መጠባበቂያ ገንዘብ ላይ ሁለት በመቶውን ወጪ በማድረግ ለዚሁ ዘርፍ ብድር እንደተጠቀሙበት አስታውቋል፡፡
በተለይ የቡና የወጪ ንግድ እንዳይስተጓጎል ባንኮችም የጥሬ ገንዘብ ችግር እንዳይገጥማቸው ታሳቢ ተደርጎ ተግባራዊ እንዲሆን በተላለፈው መመርያ መሠረት፣ ለቡና ላኪዎችና አቅራቢዎች ብድር ማቅረብ ይችላሉ፡፡
ባንኮቹ ለነዚህ ዘርፎች የሚሰጡት ብድር እያንዳንዱ ባንክ ባለው መጠባበቂያ ገንዘብ ልክ መጠን የሚወሰን ነው፡፡
የተሰጠው ብድር የመመለሻ ጊዜ ገደብ የተቀመጠለት ሲሆን፣ ባንኮቹ ለነዚህ ዘርፎች የሰጡትን ብድር እስከ ነሐሴ 2014 ዓ.ም. መልሰው ወደ ብሔራዊ ባንክ ማስገባት እንደሚኖርባቸው ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

#AGOA የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያ ፣ ማሊ እና ጊንን ከAGOA እንዲሰረዙ ፈርመዋል። ከእኤአ ከጥር 1 ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል። ኢትዮጵያ የተሰረዘችው ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ተፈፅሟል ለተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው ፤ በተጨማሪ ከህወሓት ጋር ለድርድር እንድትቀመጥ ለማስገደድ በማለም ጭምር ነው። አሜሪካ ፥ ኢትዮጵያን ጨምሮ ማሊን እና ጊኒን ከAGOA የሰረዘችው ፍላጎቶቼን…
" አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ ተጠቃሚነት ያስወጣችብትን ውሳኔ ልታጤነው ይገባል " - የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ ተጠቃሚነት ያስወጣችብትን ውሳኔ አጥብቃ ልታጤነው እንደሚገባ ኢትዮጵያ አመልክታለች።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ የንግድ ስርኣት ያስወጣችብትን ውሳኔ በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።
የአፍሪካ ሀገራትን በንግድና ስራ እድል ተጠቃሚ ከሚያደርገው የአጎዋ ንግድ ስርኣት አሜሪካ ኢትዮጵያን ማስወጣቷ የኢትዮጵያን መንግስት እንዳሳዘነው ሚኒስቴሩ አመልክቷል።
የኢትዮጵያ መንግስት ሰላምና መረጋጋትን ፣ ፖለቲካዊ መግባታትና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ሊያመጡ የሚችሉ ስራዎችን ባለፉት ሦስት ዓመታት ማከናወኑን ያመለከተው መግለጫው በተለይ ደግሞ የሁለቱን አገራት ረጅም ጊዜ የቆየ ግንኙነት ያማከለ የለውጥ ስራዎች ማከወኑንም አንስቷል።
ከአሜሪካ ልዩ ልዩ ተቋማት ጋር ደግሞ የሁለትዮሽ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ መልኩ ግንኙነቱን ለማጠንከር እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ አብራርቷል።
ኢትዮጵያን ከአጎዋ ማስወጣት በአጎዋ የስራ እድል የተፈጠረላቸውን በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን የሚጎዳ ተግባር ከመሆን ባለፈ በእነሱ ስር ተጠቃሚ የሆኑ ዜጎችንም ኑሮ የሚያመሳቅል መሆኑን አስታውቋል።
በዚህም አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ ተጠቃሚነት ያስወጣችብትን ውሳኔ አጥብቃ ልታጤነው እንደሚገባ መጠየቁን ኢዜአ ዘግቧል።