TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ተባብረንና ተቀናጅተን መስራት ከቻልን የማንፈታው ችግር የለም " - ዋና ሳጅን አናቶ አርጎ

በሐዋሳ ከተማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ አካባቢ 12 ሺህ ብር ሰርቆ የተሰወረውን ሌባ ለያዘ ፓሊስ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረ/ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ምስጋና አቀረቡ።

ከቀኑ 7:00 ሰዓት አካባቢ በኢንዱስትሪያል ፓርክ አካባቢ 12 ሺህ ብር ነጥቆ የውሃ መውረጃ ቦይ ውስጥ የገባውን ሌባ ለመያዝ የ3 መቶ ሜትር ርቀት በመሄድ የያዘው ዋና ሳጅን አናቶ አርጎ ነው።

ዋና ሳጅን አናቶ ተከታትሎ የገባው የውሃ መውረጃ ቦይ ርቀት፣ ጥልቀትና በውስጡ የነበረው ሙቀት ትንፋሽ የሚያሳጣ መሆኑን ይገልጻል።

በውስጡ የነበረውን የድንጋይ ውርወራ ተቋቁሞ ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠትና ሙያዊ ግዴታውን ለመወጣት ሲል የሚወደስ ተግባር ፈጽሟል።

ዋና ሳጅን አናቶ እንደገለጸው አጋዥ የሆኑ ልጆች፣ የአካባቢው ህብረተሰብ እና በፖሊሶች ጥረት የተገኘ ውጤትም ነው ብሎታል።

በዚህ አይነት ተባብረንና ተቀናጅተን መስራት ከቻልን የማንፈታው ችግር የለም ሲልም ገልጿል።

መረጃው የሐ/ክ/የመ/ኮ/መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
#Awaqi

አዋቂ በወጣቶች ላይ ያተኮረ የአስተሳሰብ ክህሎት ስልጠና እና የመረጃ ልውውጥ ቻናል ነው። አጭር አነቃቂ ቪዲዮዎችን፣ ስልጠናዎችን እና ለወጣቶች የስራ እድሎችን ያካትታል።

ለተለያዩ የህይወት ክህሎቶች እና የስራ እድሎች ለማግኝት የአዋቂን ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ይቀላቀሉ!

Follow @awaqiethiopia

Join our Telegram Channel
https://t.iss.one/+oIKaBr97Xn40OGM0
#Update😷

የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ፦

🇺🇸 አሜሪካ በአዲሱ አመት ዋዜማ ወደ 8 የደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት ላይ የጣለችውን የጉዞ ገደብ እንደምታነሳ ታውቋል። ሀገራቱ ደቡብ አፍሪካ፣ ቦትስዋና ፣ ዚምባብዌ ፣ ናሚቢያ ፣ ሌሶቶ፣ ኢስዋቲኒ ፣ ሞዛምቢክ እና ማላዊ ናቸው።

🇮🇪 አይርላንድ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ በቀን ከፍተኛውን ኬዝ ያስመዘገበች ሲሆን 11,182 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።

🇹🇷 ቱርክ በአገር ውስጥ የተሰራውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት 'Turkovac' በቅድሚያ ለዜጎቿ በኃላም ክትባት ለማግኘት ለሚቸገሩ ሀገራት ጋር እንደምታካፍል ፕሬዜዳንት ኤርዶጋን ተናግረዋል።

🇫🇷 ፈረንሳይ ትላንት አርብ ወደ 100,000 እተቃረበ ኬዝ ሪፖርት አድርጋለች፤ በአንድ ቀን 94,124 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል። አሁን እየታየ ያለው አዝማሚያ ፕሬዝዳንት ማክሮን ሰኞ የመንግስት ሚኒስትሮችን ለልዩ ስብሰባ እንዲጠሩ ገፍቷቸዋል።

🇯🇵 የጃፓን ተቆጣጣሪዎች በMerckና Co Inc የተሰራውን የኮቪድ-19 ፀረቫይረስ ኪኒን አገልግሎት ላይ እንዲውል አፅድቀዋል።

🇮🇳 የህንድ ፍርድ ቤት የጠ/ሚር ናሬንድራ ሞዲ መንግስት ምርጫ ሊካሄድ በተያዘባቸው ግዛቶች የፖለቲካ ሰልፎችን እና ምርጫ ቅስቀሳዎች እንዲቆም እንዲያደርጉ አሳስቧል። በኦሚክሮን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ 3ኛውን የኮቪድ-19 ማዕበል እንዳያስናሳ ተሰግቷል።

🇲🇪 የሞንቴኔግሮ ፕሬዝዳንት ሚሎ ጁካኖቪች በኮቪድ-19 መያዛቸው ታውቋል፤ ፕሬዜዳንቱ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንደነበራቸው ከተረጋገጠ በኃላ ነው በቫይረሱ መያዛቸው የታወቀው።

🇪🇹 በኢትዮጵያ ባለፉት 3 ቀናት ብቻ 11,358 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopia
#Japan

ጃፓን በWFP፣ IOM፣ UNHCRና UNMAS በኩል በአፋር ፣ አማራ እና ትግራይ ክልል ላሉ ወገኖች የምታደርገውን የ12 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር የአደጋ ጊዜ እርዳታ ለማራዘም መወሰኗን አሳውቃለች።

ጃፓን ፥ ለ270 ሺህ ሰዎች የምግብ ፣ ለ19 ሺህ ቤተሰቦች የእርዳታ እቃዎች፣ ለ14 ሺ ቤተሰቦች መጠለያና ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች ፣ ለ10 ሺ ሴቶች የንፅህና መጠበቂያዎች ከድጋፎቼ መካከል በምሳሌነት ይጠቀጠሳሉ ብላለች።

@tikvahethiopia
#Sudan

በሱዳን መዲና ካርቱም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚደረግ ተሰምቷል።

የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪውን ያስተላፉት የሱዳን የተቃዋሚዎች እና የፖለቲካ ሀይሎች ኮሚቴ ነው።

ሰልፉ በሌተናል ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና በጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ መካከል የተደረሰውን ስምምነት በመቃወም ነው የሚካሄደው።

የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪውን ተከትሎ በካርቱም ውስጥ የሚገኘው የደህንነት ኮሚቴ፤ ከህላፋያና ሶባ ድልድዮች ውጪ በ3 አቅጣጫዎች ወደ ከተማይቱ የሚያስገቡ ድልድዮችን ከትናንት ምሽት ጀምሮ እንዲዘጉ ውሳኔ አሳልፏል።

ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ ተቋማት ጥበቃ እንደሚደረግላቸው ያሳሰበው ኮሚቴው፤ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ በመብት ቢሆንም፤ አመጽ እና ሁከት መቀስቀስን ግን እንደማይታገስ አስታውቋል።

በካርቱም የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪውን በመከተል የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡንም አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
#አደይ #DStv

ዘወትር ከሰኞ-አርብ ማታ በ2:00 ሰዓት በድጋሚ ከረፋዱ 4:30 እና ከሰዓት በ9:30 እንዲሁም እሁድ ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ የሳምንቱ አምስት ተከታታይ ክፍሎች በአቦል ቻናል (146) ይቀርባሉ።

#DStvየራሳችን
ጋዜጠኛ እና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ጋዜጠኛ እና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ በ53 ዓመት ዕድሜው ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የቅርብ ቤተሰቦቹ ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል።

ተስፋዬ ገብረአብ ለወራት በህመም ላይ የቆየ ሲሆን ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ ህክምና ሲከታተል ቆይቶ ነው አርብ ከሰዓት በኋላ ታኅሣሥ 15/2014 ዓ.ም ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጋዜጠኛ እና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ጋዜጠኛ እና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ በ53 ዓመት ዕድሜው ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የቅርብ ቤተሰቦቹ ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል። ተስፋዬ ገብረአብ ለወራት በህመም ላይ የቆየ ሲሆን ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ ህክምና ሲከታተል ቆይቶ ነው አርብ ከሰዓት በኋላ ታኅሣሥ 15/2014 ዓ.ም ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው። @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ እና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ማን ነው ?

- ነሐሴ 22/1960 ዓ.ም ከኤርትራውያን ቤተሰቦቹ ቢሾፍቱ ከተማ ነበር ተወልዶ ያደገው።

- በደርግ ዘመን ማብቂያ አካባቢ ላይ ወደ ጦር ሠራዊቱ ተመልምሎ ሥልጠና ከወሰደ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ወታደራዊው መንግሥት ወድቆ ከኢህአዴግ ጋር ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ በጋዜጠኝነት ሲያገለግል ቆይቷል።

- ዕለታዊ የመንግሥት ጋዜጦችን የሚያሳትመው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ አገልግሏል።

- ከኢህአዴግ ፓርቲ ጋር ጥብቅ ቁርኝት የነበረው "እፎይታ" መጽሔትን መርቷል።

- ኢትዮጵያ ውስጥ እያለ ከጋዜጠኝነት ሙያው ጎን ለጎን መጽሐፍቶችን አሳትሟል፣ ከገዢው ፓርቲ ጋር በነበረው አለመግባባት ኢትዮጵያን ጥሎ ከወጣ በኋላ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኔዘርላንድስና ሌሎችም አገራት ውስጥ ኗሯል።

- የጋዜጠኝነት ሥራውን ካቆመ በኋላ አስከ ህይወቱ ፍጻሜ ድረስ የሙሉ ጊዜ ፀሐፊ በመሆን ከ8 በላይ ሥራዎችን ለአንባቢያን አድርሷል።

- ከ8 በላይ ስራዎችን በአማርኛ ቋንቋ ያሳተመ ሲሆን በአንባቢያን ዘንድ በስፋት ያስተዋወቀው " የቡርቃ ዝምታ " የተሰኘው ረዥም ልብ ወለዱ ነው። ይህ የልብወለድ መጽሐፉ በበርካታ የአማርኛ ልብወለድ አንባቢያን ዘንድ ነቀፌታን አሰንዝሮበታል።

- የግል ማስታወሻዎችን፣ ልብወለድ፣ አጫጭር ልብወለድ እንዲሁም ወጎችን በመጻፍ አድናቆትን አትርፏል።

- ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት (ህወሓት) ትግል ጅማሬ አስከ ኢህአዴግ አዲስ አበባ መግባት ድረስ ያለውን ዋና ዋና ታሪክ እና ገድል የሚተርከውን ተከታታይ ቅጽ ያለውን " ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ " መጽሐፍትን አሳትሟል።

- በጋዜጠኝነቱና በሥነ ጽሁፉ ዘርፍ የገዢው ኢህአዴግ ዋነኛ ሰው በመሆን የተለያዩ ሥራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፤ እሱ እንደሚለው ከአገሪቱ ዋነኛ ፖለቲከኞች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ኢትዮጵያን ለቅቆ ለመሰደድ በቅቷል።

- ከአገር ለቆ ከወጣ በኋላ ብዙ መነጋገሪያ የሆኑ በወቅቱ ገዢ ፓርቲ የነበረው ኢህአዴግና የባለሥልጣናቱ የውስጥ ምስጢር የሆኑ ጉዳዮችን የያዙ "የጋዜጠኛው ማስታወሻ" እና "የደራሲው ማስታወሻ" የተሰኙ መጽሐፎችን ለንባብ አብቅቷል።

ጋዜጠኛ እና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በ53 ዓመት ዕድሜው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sudan በሱዳን መዲና ካርቱም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚደረግ ተሰምቷል። የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪውን ያስተላፉት የሱዳን የተቃዋሚዎች እና የፖለቲካ ሀይሎች ኮሚቴ ነው። ሰልፉ በሌተናል ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና በጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ መካከል የተደረሰውን ስምምነት በመቃወም ነው የሚካሄደው። የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪውን ተከትሎ በካርቱም ውስጥ የሚገኘው የደህንነት…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪድዮ - #የሱዳን_ተቃውሞ

የሱዳን ጸጥታ ሃይሎች በሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኮሱ።

ዛሬ በሱዳን መዲና ካርቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ጥቅምት ወር የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።

የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች ብሄራዊ ቤተ መንግስት አቅራቢያ በነበሩ ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸውን ኤኤፍፒ የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ከካርቱም በተጨማሪ በተለያዩ የሱዳን ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ እየተደረገ ነው።

Video Credit : UoKEN

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተሳተፉ " ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን " ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዙር አንደኛ አመት የስራ ዘመኑ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለማቋቋም የቀረበውም ረቂቅ አዋጅ ለህግ ፣ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶ ነበር። ህብረተሰቡ መሳተፉን ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የመጀመሪያ ዙር የህዝብ አስተያየት መሰብሰቢያ መድረክ ተዘጋጅቶ ከህዝቡና ከተለያዩ ተቋማት የተወከሉ ተሳታፊዎች…
#ETHIOPIA

" የሚቋቋመው ኮሚሽን እውነተኛ ችግር ፈቺ ሊሆን ይገባል " - የውይይቱ ተሳታፊዎች

የአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ሁለተኛው ዙር ይፋዊ የህዝብ ውይይት ዛሬ ቅዳሜ ተካሂዷል።

የሚቋቋመው ኮሚሽን እውነተኛ ችግር ፈቺ ሊሆን ይገባል ተብሏል።

በውይይቱ የፍትህ ሚኒስቴር ሚንስትር ጌዲዮዎን ጢሞቲዮስ (ዶ.ር) የእጩ ኮማሽነሮችን ሹመትን በተመለከተ በጠቅላይ ሚንስትሩ አቅራነት በህ /ም/ቤት የሚጸድቅ ሲሆን ኮሚሽነሮቹ መሉ ጊዜያቸውን ስራ ላይ የሚያውሉ እንደሆነ አስረድተዋል።

አገራዊ የምክክር መድረኩ ዋና አላማ አገራዊ መግባባትን ለመፍጠር እሰከሆነ ድረስ በርዕሱ ላይ ማሻሻያ ሊደረግበት አንደሚችል ተናግረዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች የሚቋቋመው ኮሚሽን የህዝብን አንድነት ለማስቀጠልና አገሪቱ ከገባችበት ውስብስብ ችግር ማውጣት የሚያስችል መሆን አለበት ብለዋል።

ኮሚሽኑ ነጻና ገለልተኛ አንዲሆን በጀቱ ከገንዘብ ሚኒስቴር መውጣት እንዳለበት እና እጩ ኮሚሽነሮች በጠቅላይ ሚንስትር ይቀርባሉ የሚሉ ሀሳቦች ከረቂቅ አዋጁ መውጣት አንዳለባቸው የውይይቱ ተሳታፊዎች አስተያየት ሰጥተዋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ከፖለቲካ፣ ከሀይማኖት እና ከብሄር ወገንተኝነት የፀዱ፣ ችሎታቸው እና ብቃታቸው የተረጋገጠ፣ እንዲሁም አገርና ህዝብን ለማሻገር ቁርጠኛ የሆኑ ህዝብ ያመነባቸው ሊሆኑ እንደሚገባ አንስተዋል።

አገር በቀል እውቀቶች እና እሴቶች በረቂቅ አዋጁ መካተት እንዳለበት የውይይቱ ተሳታፊዎች ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል የረቂቅ አዋጁን ርዕስ አገራዊ የምክክር መድረክ ከማለት ይልቅ ‹‹ብሄራዊ የመግበባት መድረክ›› መባል አንዳለበት ሀሳባቸውን ገልጸዋል፤ ረቂቅ አዋጁ ቋንቋን ታሳቢ ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል።

#HPR

@tikvahethiopia
" ሃገራዊ ዉይይቱ በርካታ ድምጾችና ፍላጎቶች የሚንጸባረቁበትና የሚሰሙበት ሊሆን ይገባል "- ክቡር ዶ/ር ሌንጮ ለታ

አንጋፋው ፖለቲከኛ ክቡር ዶ/ር ሌንጮ ለታ በኦሮሚያ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በተዘጋጀው የ18ኛ ዙር የ'ጉሚ በለል' የውይይት መድረክ ተሳታፊ ነበሩ።

የዛሬው ውይይት መድረክ " የብሔራዊ ዉይይቱ አንኳር ጉዳዮችና ሃገራዊ ፋይዳዉ" በሚል ርዕስ ነበር የተካሄደው።

ክቡር ዶ/ር ሌንጮ በመድረኩ የመወያያ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በሃገራዊ ወይይቱ አስፈላጊነትና በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ዙሪያ አንኳር ነጥቦችን አንስተዋል።

ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን መገንባት የሚቻለዉ በትጥቅ ትግል ሳይሆን በበሰለና በሰለጠነ ወይይት ብቻ ነዉ ብለዋል።

ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት ከጦርነት ይልቅ ሰላማዊ ወይይት ተመራጭ መሆኑን ጠቅሰዋል።

" ሃገራዊ ዉይይቱ ለኦሮሞ ህዝብ በጣም አስፈላጊ ነው " ያሉት ክቡር ዶ/ር ሌንጮ " ሃገራዊ ዉይይቱ በርካታ ድምጾችና ፍላጎቶች የሚንጸባረቁበት እና የሚሰሙበት ሊሆን ይገባል" ብለዋል።

ክቡር ዶ/ር ሌንጮ ፥ " እኩልነት በሌለበት አንድነትን መፍጠር አይችልም " ያሉ ሲሆን " ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ለመፍጠር ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ራሳቸዉን የሚመለከቱባትን ኢትዮጵያን መገንባት ይገባል " ብለዋል።

ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን በሂደት እንጂ በአንድ ጊዜ መገንባት እንደማይቻል የገለፁት ክቡር ዶ/ር ሌንጮ ለታ " እንከን የሌለበት ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን መፈለግ የተሳሳተ አስተሳሰብ ነዉ" ብለዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ ከተሳታፊዎች በኩል የተለያዩ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፤ ሁሉም አካል ለሀገራዊ ውይይቱ ስኬት የድርሻውን እንዲወጣ መጠየቁን ከኦቢኤን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ🕊

ብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ስለኢትዮጵያ ሰላም ጸሎት አቀረቡ። 

ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዛሬ ታኅሣሥ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. በአውሮፓውያንን የልደት በዓል "Urbi et Orbi" የተሰኘውን ሐዋርያዊ ቡራኬ ባቀረቡበት ወቅት ስለኢትዮጵያ ሰላም ጸሎት አድርሰዋል።

በጸሎታቸውም "የሰላም ንጉሥ ሆይ ኢትዮጵያ ወደ ከምንም በላይ የሕዝቦች ፍላጎት  እርቅ እና ሰላማዊ የኑሮ ጎዳና እንድትመለስ እርዳት" ብለዋል።

በተመሳሳይ ለሌሎች ግጭት ስላለባቸው ሃገሮችም ጸሎት አድርሰዋል።

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

#EthiopianCatholicSecretariat 

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 5,013 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 14,027 የላብራቶሪ ምርመራ 5,013 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ6 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

193 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ከፍተኛ_ጥንቃቄ

@tikvahethiopia