TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AGOA
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያ ፣ ማሊ እና ጊንን ከAGOA እንዲሰረዙ ፈርመዋል።
ከእኤአ ከጥር 1 ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል።
ኢትዮጵያ የተሰረዘችው ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ተፈፅሟል ለተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው ፤ በተጨማሪ ከህወሓት ጋር ለድርድር እንድትቀመጥ ለማስገደድ በማለም ጭምር ነው።
አሜሪካ ፥ ኢትዮጵያን ጨምሮ ማሊን እና ጊኒን ከAGOA የሰረዘችው ፍላጎቶቼን ማሟላት አልቻላችሁም በሚል ነው።
ከመሰረዟ በፊትም የሁለት ወራት የማሰቢያ ጊዜ ገደብ ሰጥታ ነበረ።
ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በAGOA ላይ እንድትቆይ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው ኮንግረስ መሪዎች ለባይደን ደብዳቤ ቢፅፉም እሳቸው ግን ኢትዮጵያን ከAGOA ሰርዘዋታል።
ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ያህል ከቆየችበት የAGOA ተጠቃሚነት እንዳትሰረዝ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ካውንስል ከፍተኛ ግፊት ሲያደርግ ነበር።
የፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ውሳኔ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰራተኞችን እንዲጎዱ የሚያደርግ ነው።
ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያን AGOA ተጠቃሚነት ውጭ ማድረግ፤ ከግጭቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙት የሌላቸውን ከ200 ሺህ በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የበርካታ ሴቶች ኑሮ ላይ ተጽእኖ እንደሚኖረው ማሳወቋ ይታወሳል።
በግበዓት አቅርቦት ሰንሰለት የሚሳተፉትን የ1 ሚሊዮን ሰዎች ህይወት በእጅጉ እንደሚጎዳው መግለጿ አይዘነጋም።
AGOA ምንድነው?
African Growth and Opportunity Act (AGOA) የግብይት ስርዓት ነው፤ ይህ የግብይት ስርዓት የተወሰኑ የብቃት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ከሳሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ሸቀጦችን ያለቀረጥ ለአሜሪካ ገበያ እንዲሸጡ የሚፈቅድ ነው።
@tikvahethiopia

#UPDATE " ሰራዊቱ ባለበት እንዲቆይ ተወስኗል " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ መግለጫ ሰጥተዋል። ዶ/ር ለገሰ፥ " በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የተመራው 'ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት' በአሸባሪው ሃይል የተወረሩ አካባቢዎችን በማስለቀቅና ተልዕኮውን በማሳካት የመጀመሪያው ምዕራፍ ተጠናቋል" ሲሉ አሳውቀዋል። በዘመቻው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ታላቅ…
#USA
አሜሪካ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደ ትግራይ ክልል እንደማይቀጥል መገለፁን እንደምትቀበለው በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል አስታውቃለች።
ሀገሪቱ ፥ የኢትዮጵያ መንግስት የአየር ጥቃትን እንዲያቆም እና ኤርትራ ጦሯን ከኢትዮጵያ እንድታስወጣ በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን ብላለች።
አሜሪካ ፥ በኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ ያሉ ሁሉም ወገኖች ጦርነቱን ማቆም፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲያበቁ ማድረግ፣ ሰብዓዊ አቅርቦቶችን መፍቀድ ፣ ለመደራደርም መቀመጥ አለባቸው ብላለች።
ለግጭቱ ምንም አይነት የወታደራዊ መፍትሄ የለም ስትል አሜሪካ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ገልፃለች።

#Update😷
የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ፦
🇮🇹 ጣሊያን ከቤት ውጪ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ማድረግ ግዴታ አድርጋለች።
🇪🇨 ኢኳዶር የኮሮና ቫይረስ ክትባትን መከተብ አስገዳጅ አድርጋለች።
🏴 ስኮትላንድ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት ለመዋጋት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የምሽት ክለቦችን እንደምትዘጋ አስታውቃለች።
🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ከኮቪድ-19 ስጋት ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ናይጄሪያ ወደሀገሯ የሚገቡ ተጓዦችን አግዳለች።
🇪🇸 የስፔኗ ካታሎኒያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመዋጋት ከገና ዋዜማ ጀምሮ የምሽት የሰዓት እላፊ ገደብ ልታውጅ መሆኗ ታውቋል።
🇩🇰 ዴንማርክ ወደሀገሯ የሚገቡ መንገደኞች የኮቪድ-19 ምርመራ ነፃ ውጤት ማቅረብ እንዳለባቸው አሳውቃለች።
🇲🇦 የሞሮኮ መንግስት በአገር አቀፍ ደረጃ የጤና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እስከ ጥር 31 (እኤአ) አራዝሟል።
🇷🇺 በሩሲያ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ600,000 አልፏል። በሩሲያ የ600,434 ሰዎች ሞት የተመዘገብ ሲሆን ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአሜሪካ (813,000 ሞት) እና ብራዚል (618,000 ሞት) ቀጥላ 3ኛ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ አድርጓታል።
🇪🇹 በሀገራችን ኢትዮጵያ ኦሚክሮን መከሰት አለመከሰቱን ለማረጋገጥ ናሙና በመውሰድ ምርምር እየተካሄደ ነው።
🌎 የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ የኦሚክሮን ዝርያ በዓለም ዙሪያ መስፋፋቱን የቀጠለ መሆኑን እና በርካታ አገሮች ይህን በፍጥነት እየተሰራጨ የሚገኘውን ኦሚክሮን ልውጥ ቫይረስ ሪፖርት እያደረጉ መሆኑን አመልክቷል። እስከ ሰኞ ድረስ ባለው በ106 አገራት ልውጡ ቫይረስ መገኘቱ ተረጋግጧል።

#ETHIOPIA
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዝግጅት ምን ይመስላል ?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ለኢ.ፕ.ድ. በሰጠው ቃል የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጥሪ ተከትሎ ወደ አገር ቤት ለመምጣት ዝግጅት ላይ ያሉ በሁሉም አህጉራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቀልጣፋ አገልግሎት እንደሚሰጥ አሳውቋል።
🛫በቀጥታ በረራ፣ በአጋሮቹ በኩልና በቻርተሩ በረራ አማካኝነት ቀልጣፋ አገልግሎት የሚያገኙበት ሁኔታ ላይ ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል።
🏨 እንግዶች ወደ አገር ሲገቡ የአየር መንገዱ ንብረት የስካይላይት ሆቴል በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቷል።
🚖 ከኤርፖርት ወደ ተለያዩ የሆቴል ማረፊያዎች ለሚሄዱ የዲያስፖራው ወገኖች ከበቂ የሰው ሀይል ጋር የትራንስፖርት አገልግሎት ተዘጋጅቷል።
127 የዓለም አገራትና 5 አህጉራትን እንዲሁም ከ60 በላይ የአፍሪካ አገራት መዳረሻ ያደረገው ግዝፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው ለሚመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የ30 በመቶ ቅናሽ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
(ኢፕድ)

#ችሎት
ላምሮት ከማል በነጻ ተሰናበተች።
ፍ/ቤቱ ዛሬ ከሰዓት ጥፋተኛ በተባለችበት አንቀጽ በ3 ወር ቀላል ዕስራት እንድትቀጣ የወሰነ ሲሆን ከቅጣቱ በላይ በዕስር በመቆየቷ በነጻ እንድትሰናበት አዟል።
ተከሳሿ በቁጥጥር ስር ከዋለችበት ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ /ም ጀምሮ 3 ወራት በፖሊስ ጣቢያ 1 አመት ከ5 ወራት ደግሞ በማረሚያ ቤት በዕስር መቆየቷን ተከትሎ ነው በነጻ ከስር እንድትሰናበት ነው የተወሰነው።
ላምሮት ከማል በመጀመሪያ ከተከሰሰችበት አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ እንዲገደል የግድያ ቦታ ማመቻቸት ሽብር ወንጀል በቂ ማስረጃ አልቀረበም ተብሎ በዚሁ ፍርድ ቤት በነጻ መሰናበቷ ይታወቃል።
ዓቃቤህግ ነጻ መባሏን በመቃወም ለጠ/ፍ/ ቤት ይግባኝ መጠየቁን ተከትሎ የይግባኝ ሰሚ ችሎቱ መዝገቡን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት የነጻ ውሳኔን በመሻር ላምሮት ከማል አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ በሽጉጥ በተመታበት ጊዜ በቸልተኝነት እርዳታ ባለመስጠት በወንጀል ህግ አንቀጽ 575 ንዑስ ቁ 1 እንድትከላከል ትዛዝ የሰጠ ሲሆን።
መዝገቡ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት ከተመለሰ በኋላም እንድትከላከል በዠየተደረገ አንቀጽ ዋስትና አያስከለክልም ሲል ችሎቱ በ5 ሺህ ብር ዋስ ከዕስር እንድትፈታ ወስኖ ከስር ተፈታ ነበር።
መከላከያ እንድታቀርብ በተሰጠ ቀጠሮ በጽፈት ቤት ቀርባ በጽሁፍ መከላከያ ማስረጃ የለኝም በዓቃቢህግ ባሰማው ማስረጃ ይፈረድብኝ ስትል ፍርድ ቤቱን ጠይቃ ነበር።
በዚህ ጥያቄ መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ትናንት በነበረ ቀጠሮ እንድትከላከል በተባለችበት አንቀጽ መከላከል ባለመቻሏ የጥፋተኝነት ፍርድ በመስጠት በይደር ለቅጣት ውሳኔ መቅጠሩ ይታወሳል።
በዚህም ፍ/ቤቱ በዛሬ ቀጠሮ ዓቃቤ ህግ ወንጀሉ በጭካኔ እና በለሊት የተፈጸመ መሆኑን ጠቅሶ ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃ ውድቅ አድርጓል።
ተከሳሿ የቀደመ የወንጀል እሪከርድ እንደሌለባትና የልጅ እናት መሆኗን ጠቅሳ ያቀረበችውን የቅጣት ማቅለያ አስተያየት ፍርድ ቤቱ ተቀብሏታል።
በሶስት (3) ወር ቀላል እስራት እንድትቀጣ የወሰነ ቢሆንሞ ከቅጣት ውሳኔው በላይ በስር ማሳለፏ ተጠቅሶ በነጻ እንድትሰናበት ተደርጓል።
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

#DebreBrehan
' ትምህርት ሠኞ ይጀምራል '
በደብረ ብርሃን ከተማ ተፈናቃዮች ተጠልለውባቸው በነበሩ ትምህርት ቤቶች ከሰኞ ጀምሮ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንደሚቀጥል የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ፅህፈት ቤት ማሳወቁን ፋና ዘግቧል።
ህወሓት በአማራ ክልል ላይ በከፈተው ጦርነት ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖችን በመጠለያነት ሲያገለግሉ የነበሩ ትምህርት ቤቶች ከሰኞ ጀምሮ በተያዘላቸው መርሃ ግብር ሁሉም የመማር ማስተማር ሂደታቸውን ይቀጥላሉ ተብሏል።
አሁን ላይ ለት/ ቤቶቹ ተገቢው የፅዳት ስራ ተሰርቶላቸውና መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ስለተሟሉ ተማሪዎች በመማሪያ ክፍላቸው በመገኘት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ጥሪ ቀርቧል።
በደብረ ብርሀን ከተማ ሶስት አንደኛ ደረጃ እና ሶስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፥ በአጠቃላይ በስድስት የትምህርት ተቋማት ተፈናቃዮች ተጠልለው ይገኙ እንደነበር ፋና ብሮድካስት በዘገባው አስታውሷል።

#Dibate
በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ለአመታት ያክል ተቋርጦ የቆየዉን የመብራት አገልግሎት ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
የድባጤ ወረዳ መሪ ማዘጋጃ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አርጌታ ወይላ ፥ ለበርካታ ጊዜያት ተቋርጦ የቆየዉን የመብራት አገልግሎት ለማስጀመርና ማህበረሰቡ የመብራት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሀላፊዉ በመብራት ገመድ ዝርጋታ ስራ ላይ ተገኝተው የተሳተፉትን የወረዳው በጎ አድራጎት ወጣቶችንና ሰላም በማስከበር ረገድ የተሳተፉ የመከላከያ ሰራዊት፣ ለክልሉና ሌሌሎች ክልል ልዩ ሀይሎች ምስጋና አቅርበዋል።
ብልሽት የገጠሙባቸዉን ቦታዎች ላይ ጥገና ተደርጎ በአጭር ጊዜ አገግሎት እንደሚያስጀምሩ የመብራት ሀይል ባለሙያዎች ተናግረዋል።
መረጃው የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው።

በአፍሪካ ቀዳሚ #EthiopianAirlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) በፋርማሲዩቲካል ሎጅስቲክስ የገለልተኛ ገምጋሚ (CEIV Pharma) የልህቀት ማዕከልነት ሰርተፍኬት አግኝቷል።
የኢትዮጵያ 🇪🇹 አየር መንገድ ይህንን ሰርተፍኬት በማግኘት ከአፍሪካ ቀዳሚው አየር መንገድ ነው፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) በፋርማሲዩቲካል ሎጅስቲክስ የገለልተኛ ገምጋሚ (CEIV Pharma) የልህቀት ማዕከልነት ሰርተፍኬት አግኝቷል።
የኢትዮጵያ 🇪🇹 አየር መንገድ ይህንን ሰርተፍኬት በማግኘት ከአፍሪካ ቀዳሚው አየር መንገድ ነው፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE " ሰራዊቱ ባለበት እንዲቆይ ተወስኗል " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ መግለጫ ሰጥተዋል። ዶ/ር ለገሰ፥ " በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የተመራው 'ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት' በአሸባሪው ሃይል የተወረሩ አካባቢዎችን በማስለቀቅና ተልዕኮውን በማሳካት የመጀመሪያው ምዕራፍ ተጠናቋል" ሲሉ አሳውቀዋል። በዘመቻው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ታላቅ…
#Update
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደትግራይ ክልል እንዳይገባ በተወሰነው ውሳኔ ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጠ/ሚኒስትሩ ለዚህ ውሳኔ መደረስ ብዙ ምክንያቶች እንዳሉ አስገንዝበው “ውሳኔዎቻችን በስሜት የሚወሰኑ ሳይሆን ዘላቂ ጥቅምን ያገናዘቡ ናቸው” ብለዋል።
የማንኛውም ውሳኔያችን መርህ ኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ድል እንድትጎናፀፍ ማስቻል ነው ፤ ግዛታዊ አንድነታችን የሚጠበቅበትና በዘላቂነት ኢትዮጵያ አሸናፊ የምትሆንበትን መንገድ መቀየስ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ዶ/ር ዐቢይ፤ "ህወሓት እና አፈቀላጤዎቹ መንግስትንና ሰራዊቱን ለመክሰስ ወደአዘጋጁት የሴራ ወጥመድ መግባት እንደሌለብን እናምናለን" ያሉ ሲሆን "በዚህ ወቅት የእኛ ወደክልሉ መግባት ከጥቅሙ ጉዳቱ ነው የሚያመዝነው" ሲሉ ገልፀዋል።
ጠ/ሚስትሩ መከላከያ ሰራዊት ለኢትዮጵያ የግዛት አንድነትና ሉአላዊነት የሚያሰጋ ነገር ከገጠመ በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ወደ ትግራይ ክልል ገብቶ የሀገራን ደህንነት የማስከበር ህገመንግስታዊ መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታም አለበት ብለዋል።
ሰራዊቱ ስትራቴጂክ በሆኑ ቦታዎች ሰፍሮ የጠላትን እንቅስቃሴ በአንክሮ እየተከታተለ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የትግራይ እናቶች አሁን ላይ ያለው ይሄ ሁሉ ምስቅልቅል ያመጣባቸውንና ልጆቻቸውን ነጥቆ ያስጨረሰባቸውን አሸባሪ ኃይል መጠየቅ አለባቸው ብለዋል።
ዶ/ር ዐቢይ "ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይሄንን አሸባሪ ከጫንቃው ላይ ያስወገደው በመራር ትግሉ ነው" ያሉ ሲሆን " የትግራይ ህዝብም እንደሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ይሄንን አሸባሪ ታግሎ የማስወገድ አቅምና ችሎታ አለው፤ ድጋፍና እርዳታ በአስፈለገ ጊዜም የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ከክልሉ ህዝብ ጎን ይቆማል " ብለዋል።
* ሙሉ ማብራሪያው ከላይ ተያይዟል።

#SituationReport
#Tigray #Amhara #Afar
የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ /UN OCHA/ ሪፖርት ፦
- ከጥር ወር ጀምሮ በትግራይ እና በአማራ ክልል 728 ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተለያዩ ህጻናት ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተገናኙ ሲሆን ይህም ከጠቅላላው 9 በመቶውን ብቻ የሚወክል ነው ተብሏል።
- ግጭቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ ህዳር ወር መጨረሻ ድረስ በሰሜን ኢትዮጵያ በሶስቱ ክልሎች ከ1,000 የሚበልጡ ከፆታ ጥቃት በህይወት የተረፉ ሴቶች በጤና አገልግሎት ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል።
- 500,000 የሚገመቱ ህጻናት ላይ ትኩረት ያደረገ ሰፊ የአመጋገብ ዘመቻ ለማካሄድ ከ5,700 በላይ እሽጎች ቫይታሚን ኤ ወደ አፋር ተልኳል።
- ይህ ሪፖርት በተዘጋጀበት ሳምንት በአማራ ከ 560 ሺህ በላይ ሰዎች የምግብ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል ፤ በአፋር ከ88 ሺህ በላይ ሰዎች እንዲሁም በትግራይ ከ138 ሺህ በላይ ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል።
- በትግራይ ባለው የነዳጅ እጥረት ምክንያት አንዳንድ አጋሮች ከታህሳስ 10 ጀምሮ የምግብ አቅርቦትን አቁመዋል።
ሙሉ ሪፖርት : https://reports.unocha.org/en/country/ethiopia/

#ALERT🚨
በሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 4,573 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 12,348 የላብራቶሪ ምርመራ 4,573 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ3 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

" ተባብረንና ተቀናጅተን መስራት ከቻልን የማንፈታው ችግር የለም " - ዋና ሳጅን አናቶ አርጎ
በሐዋሳ ከተማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ አካባቢ 12 ሺህ ብር ሰርቆ የተሰወረውን ሌባ ለያዘ ፓሊስ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረ/ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ምስጋና አቀረቡ።
ከቀኑ 7:00 ሰዓት አካባቢ በኢንዱስትሪያል ፓርክ አካባቢ 12 ሺህ ብር ነጥቆ የውሃ መውረጃ ቦይ ውስጥ የገባውን ሌባ ለመያዝ የ3 መቶ ሜትር ርቀት በመሄድ የያዘው ዋና ሳጅን አናቶ አርጎ ነው።
ዋና ሳጅን አናቶ ተከታትሎ የገባው የውሃ መውረጃ ቦይ ርቀት፣ ጥልቀትና በውስጡ የነበረው ሙቀት ትንፋሽ የሚያሳጣ መሆኑን ይገልጻል።
በውስጡ የነበረውን የድንጋይ ውርወራ ተቋቁሞ ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠትና ሙያዊ ግዴታውን ለመወጣት ሲል የሚወደስ ተግባር ፈጽሟል።
ዋና ሳጅን አናቶ እንደገለጸው አጋዥ የሆኑ ልጆች፣ የአካባቢው ህብረተሰብ እና በፖሊሶች ጥረት የተገኘ ውጤትም ነው ብሎታል።
በዚህ አይነት ተባብረንና ተቀናጅተን መስራት ከቻልን የማንፈታው ችግር የለም ሲልም ገልጿል።
መረጃው የሐ/ክ/የመ/ኮ/መምሪያ ነው።