TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Amhara #Tigray #Afar

የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ 🇪🇹 በግጭት በተጎዱ ክልሎች ላለው የጤና እና ሰብዓዊ ፍላጎቶች ምላሽ እየሰጠ መሆኑን አሳውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት አካላት ከ2 ቀን በፊት #በአማራ ክልል የወደሙ ሆስፒታሎችን በአካል የተመለከቱ ሲሆን የ2 ሚሊዮን ሰዎችን አስቸኳይ የጤና ፍላጎት ለማሟላት ወደ 100 ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ መድሀኒትና የህክምና ቁሳቁሶችን እንዳስረከቡ ድርጅቱ ገልጿል።

ተጨማሪ የህክምና ቁሳቁሶች ወደ #አፋር#ትግራይ እና ሌሎችም ክልሎች መላኩን ድርጅቱ አመልክቷል።

@tikvahethiopia
#Afar #Tigray #Amhara

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ምክትል ቃል አቀባይ የሆኑት ፈርሐን ሐቅ በሰሜን ኢትዮጵያ አንዳንድ መሻሻሎች መኖራቸውን የሚያመላክቱ ሪፖርቶች መኖራቸውን ገልፀዋል።

አሁንም ግን ከሰሞኑን በአካባቢው በተከሰተ ግጭት ሳቢያ ያለው ሁኔታ ተለዋዋጭ እንዲሁም ሊገመት የማይችል ነው ብለዋል።

ቃል አቀባዩ ፥ በአማራ እና አፋር ክልል ተፈናቅለው የነበሩ አንዳንድ ነዋሪዎች ወደ ቄያቸው እየተመለሱ መሆናቸውን በአካባቢው ከሚገኙ ባልደረቦቻችን ተረድተናል ብለዋል።

በአካባቢው ባለው የተደራሽነት ችግር የተመላሾችን ቁጥር ለማወቅ አዳጋች መሆኑን ገልፀዋል።

በአፋር እና ትግራይ ምዕራባዊ ክፍል አሁንም የሚፈናቀሉ አንዳንድ ሰዎች መኖራቸውን አመልክተዋል።

ቃል አቀባዩ ፥ በስፍራው ያሉት የሰብዓዊ ድጋፍ አጋሮቻችን እኤአ ከታህሳስ 15-17 ባሉ ጊዜያት ውስጥ የአየር ድብደባ መካሄዳቸውን ፤ ብዙ ሰዎች መሞታቸውን እና ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል ብለዋል። ይሁን እንጂ ድርጊቱን ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ እንዳልተቻለ አስረድተዋል።

ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በአፋር በኩል ወደ ትግራይ መቐለ የደረሰ ምንም አይነት እርዳታ የጫነ ተሽከርካሪ አለመኖሩን ተናግረዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው በርካታ ተግዳሮት አሁንም ድረስ ያለ መሆኑን ጠቁመው ሁሉም ወገኖች ግጭት አቁመው የእርዳታ አቅርቦት እና የእርዳታ ሰራተኞች ወደ ትግራይ ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች በነፃነት እንዲቀሳቀሱ እንዲደረግ ጥሪ እናቀርባለን ማለታቸውን ቬኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Update

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

ዶ/ር ሊያ በመግለጫቸው በአፋር እና በአማራ ክልሎች በህወሓት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ሥራ ለማስጀመር በተደረገ እንቅስቃሴ እስካሁን 64 የሚሆኑ የጤና ተቋማት በድጋሚ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ መቻሉን መናገራቸውን ዋልታ ዘግቧል።

በሁለት ክልሎች ላይ የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ሥራ ለማስጀመር እና ለማደራጀት በተለያዩ መንገዶች የሀብት ማሰባሰብ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ዶ/ር ሊያ ታደሰ በመግለጫቸው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥርጭት በከፍተኛ ሁኔታ በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ህብረተሰቡ ለኮቪድ-19 ወረርሽኝን የመከላከያ እንደሁም የመቆጣጠሪያ መንገዶችን መተግበሩ ላይ ከፍተኛ መዘናጋት እያሳየ እንደሆነ አመልክተዋል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ : ወደ ድብድብና ቡጢ መሰናዘር የተቀየረው የጋና ፓርላማ ክርክር 👊

ከቀናት በፊት ሰኞ በጋና ፓርላማ በኤሌክትሮኒክ ግብይት ላይ ሊጣል በታቀደ ታክስ ላይ ፓርላማው ለሁለት ተከፍሎ ከፍተኛ ክርክር ሲደረግ ነበር።

ይኸው ክርክር ወደ ከፍተኛ ፍጥጫ ተቀይሮ ተከራካሪዎቹ ወደ ድብድብ እና ቡጢ🤜 🤛መሰናዘር አድርሷቸዋል ፤ የፓርላማው ክስተት ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ነው ያለፈው።

በዚህ ጥል አንድ ሰው መጎዳቱ ተሰምቷል።

@tikvahethiopia
#UPDATE

" ሰራዊቱ ባለበት እንዲቆይ ተወስኗል " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዶ/ር ለገሰ፥ " በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የተመራው 'ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት' በአሸባሪው ሃይል የተወረሩ አካባቢዎችን በማስለቀቅና ተልዕኮውን በማሳካት የመጀመሪያው ምዕራፍ ተጠናቋል" ሲሉ አሳውቀዋል።

በዘመቻው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ታላቅ ጀብዱ የሰሩበትና በታሪክ ወርቃማ ሆኖ የሚጻፍ ስራ የሰሩበት ነው ያሉ ሲሆን የአማራና አፋር ክልል የፀጥታ ሃይሎችም የራሳቸውን ጥረት አድርገው አኩሪ ድርሻ ተወጥተዋል ሲሉ ተናግረዋል።

"አሁን ላይ የጠላት መሻት፣ ፍላጎትና የማድረግ አቅም ክፉኛ ተመቷል ያሉት ሚኒስትሩ፥ "ይሁን እንጂ የጠላት ሃይል ፍላጎት ዳግም እንዳይቀሰቀስ መንግስት በቀጣይ በጥናት ላይ ተመስርቶ እርምጃ ይወስዳል" ብለዋል።

የወገን ሃይል ጥንካሬውን ይዞ እንዲቀጥል ጠንካራ ስራ ይሰራል ሲሉ የተናገሩት ሚኒስትሩ ህብረተሰቡ እስከዛሬ ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ዶ/ር ለገሰ፥"ወራሪውን ሃይል በገባበት የደመሰሰው የመከላከያ ሰራዊትም ባለበት እንዲቆይ ተወስኗል" ሲሉ አሳውቀዋል።

"ለዚህም ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል ካጋጠሙ ችግሮች መማር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ በተጠና መልኩ የፀጥታ ሃይሉ እርምጃ እንዲወስድ እንዲሁም በሽብር ቡድኑ ሴራና ወጥመድ ላለመግባት በማሰብ ነው ውሳኔው የተወሰነው" ሲሉ አስረድተዋል።

በምዕራብ አማራ ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ መንግስት ወደፊት መረጃዎችን እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ፥ "በኦሮሚያ ክልል በንጹሃን ላይ በአሸባሪው ሸኔ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል" ሲሉ ማስገንዘባቸውን ፋና ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Attention

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዝ ዛሬ ማምሻውን ባደረገው ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ አፈጻጸሙን ገምግሟል፡፡

ዕዙ ከግምገማው በኃላ የተለያዩ ትዕዛዝትን አስተላልፏል።

* ከላይ ያንብቡ !

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 3,793 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 13,147 የላብራቶሪ ምርመራ 3,793 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ5 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

በሌላ በኩል ፤ ኦሚክሮን የተሰኘው የኮቪድ-19 አዲሱ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ መከሰት አለመከሰቱን ለማረጋገጥ ናሙና በመውሰድ ምርምር እየተካሄደ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ዛሬ አስታውቀዋል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ (ዩኤኢ) ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት ጋር በተያያዘ ከኬንያ፣ #ኢትዮጵያ ፣ ታንዛኒያ እና ናይጄሪያ ወደ ሀገሯ የሚገቡ መንገደኞችን አገደች።

እግዱ ከታህሳስ 16 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ነው።

እግዱ ወደ ተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ከመምጣታቸው 14 ቀናት በፊት በአራቱ ሀገራት የነበሩ ተጓዦችን እንዳይገቡ ማገድን የሚያካትት ነው።

ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ወደ እነዚህ ሀገራት የሚደረገው በረራ በተያዘለት መርሃ ግብር ይቀጥላል ተብሏል።

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ዜጎችና የመጀመሪያ ደረጃ ዘመዶቻቸው (FDR) ፣ ወርቃማ ቪዛ (የረጅም ጊዜ የመኖሪያ ቪዛ) ያላቸው ፣ በእነዚህ ሀገራት መካከል ያሉ የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች እንዲሁም ኦፊሴላዊ ልዑካን ከአዲሱ የጉዞ ህግ / እገዳ ነፃ መሆናቸው ተናግሯል።

ነገር ግን ከመነሳታቸውን ከ48 ሰዓት በፊት የኮቪድ-19 ምርመራ ተመርምረው ነፃ መሆናቸው የሚያረጋግጥ ውጤት ማቅረብ ፣ ኤርፖርት ላይ ፈጣን የPCR ምርመራ በስድስት ሰዓት ውስጥ ማድረግ እንዲሁም ዩኤኢ ሲደርሱ ኤርፖርት ላይ የPCR ምርመራ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ዜጎችና የመጀመሪያ ደረጃ ዘመዶቻቸው ፣የረጅም ጊዜ የመኖሪያ ቪዛ ያላቸው እና የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች የ10 ቀን ኳራንቲን እና ወደ ሀገር በገቡ በ9ኛው ቀን የPCR ምርመራ ማድረግ አለባቸው ተብሏል።

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ዜጎች ወደ አራቱ የአፍሪካ ሀገራት እንዳይጓዙ የተከለከሉ ሲሆን ክልከላው የሀገሪቱ የድንገተኛ ህክምና ጉዳዮች ፣ ይፋዊ ልዑካን እንዲሁም ከሶኮላርሺፕ ጋር በተያያዘ የሚጓዙትን አይጨምርም።

ምንጭ፦ https://www.wam.ae/en/details/1395303005869

@tikvahethiopia
#Awaqi

⚡️ምንም ቢሆን ምንም ⚡️
አላማችንን ለማሳካት ወደፊት እንራመድ ✊🏾
.
.
የተለያዩ ለወጣቶች የተዘጋጁ የህይወት ክህሎቶችን እና የስራ እድሎችን ለማግኘት አዋቂን ይቀላቀላሉ 👇🏾

Follow @awaqiethiopia

👇🏾Join our Telegram Channel
https://t.iss.one/+oIKaBr97Xn40OGM0
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AGOA

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያ ፣ ማሊ እና ጊንን ከAGOA እንዲሰረዙ ፈርመዋል።

ከእኤአ ከጥር 1 ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል።

ኢትዮጵያ የተሰረዘችው ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ተፈፅሟል ለተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው ፤ በተጨማሪ ከህወሓት ጋር ለድርድር እንድትቀመጥ ለማስገደድ በማለም ጭምር ነው።

አሜሪካ ፥ ኢትዮጵያን ጨምሮ ማሊን እና ጊኒን ከAGOA የሰረዘችው ፍላጎቶቼን ማሟላት አልቻላችሁም በሚል ነው።

ከመሰረዟ በፊትም የሁለት ወራት የማሰቢያ ጊዜ ገደብ ሰጥታ ነበረ።

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በAGOA ላይ እንድትቆይ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው ኮንግረስ መሪዎች ለባይደን ደብዳቤ ቢፅፉም እሳቸው ግን ኢትዮጵያን ከAGOA ሰርዘዋታል።

ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ያህል ከቆየችበት የAGOA ተጠቃሚነት እንዳትሰረዝ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ካውንስል ከፍተኛ ግፊት ሲያደርግ ነበር።

የፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ውሳኔ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰራተኞችን እንዲጎዱ የሚያደርግ ነው።

ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያን AGOA ተጠቃሚነት ውጭ ማድረግ፤ ከግጭቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙት የሌላቸውን ከ200 ሺህ በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የበርካታ ሴቶች ኑሮ ላይ ተጽእኖ እንደሚኖረው ማሳወቋ ይታወሳል።

በግበዓት አቅርቦት ሰንሰለት የሚሳተፉትን የ1 ሚሊዮን ሰዎች ህይወት በእጅጉ እንደሚጎዳው መግለጿ አይዘነጋም።

AGOA ምንድነው?

African Growth and Opportunity Act (AGOA) የግብይት ስርዓት ነው፤ ይህ የግብይት ስርዓት የተወሰኑ የብቃት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ከሳሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ሸቀጦችን ያለቀረጥ ለአሜሪካ ገበያ እንዲሸጡ የሚፈቅድ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE " ሰራዊቱ ባለበት እንዲቆይ ተወስኗል " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ መግለጫ ሰጥተዋል። ዶ/ር ለገሰ፥ " በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የተመራው 'ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት' በአሸባሪው ሃይል የተወረሩ አካባቢዎችን በማስለቀቅና ተልዕኮውን በማሳካት የመጀመሪያው ምዕራፍ ተጠናቋል" ሲሉ አሳውቀዋል። በዘመቻው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ታላቅ…
#USA

አሜሪካ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደ ትግራይ ክልል እንደማይቀጥል መገለፁን እንደምትቀበለው በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል አስታውቃለች።

ሀገሪቱ ፥ የኢትዮጵያ መንግስት የአየር ጥቃትን እንዲያቆም እና ኤርትራ ጦሯን ከኢትዮጵያ እንድታስወጣ በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን ብላለች።

አሜሪካ ፥ በኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ ያሉ ሁሉም ወገኖች ጦርነቱን ማቆም፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲያበቁ ማድረግ፣ ሰብዓዊ አቅርቦቶችን መፍቀድ ፣ ለመደራደርም መቀመጥ አለባቸው ብላለች።

ለግጭቱ ምንም አይነት የወታደራዊ መፍትሄ የለም ስትል አሜሪካ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ገልፃለች።

@tikvahethiopia
#Update😷

የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ፦

🇮🇹 ጣሊያን ከቤት ውጪ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ማድረግ ግዴታ አድርጋለች።

🇪🇨 ኢኳዶር የኮሮና ቫይረስ ክትባትን መከተብ አስገዳጅ አድርጋለች።

🏴󠁧󠁢󠁳󠁣󠁴󠁿 ስኮትላንድ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት ለመዋጋት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የምሽት ክለቦችን እንደምትዘጋ አስታውቃለች።

🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ከኮቪድ-19 ስጋት ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ናይጄሪያ ወደሀገሯ የሚገቡ ተጓዦችን አግዳለች።

🇪🇸 የስፔኗ ካታሎኒያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመዋጋት ከገና ዋዜማ ጀምሮ የምሽት የሰዓት እላፊ ገደብ ልታውጅ መሆኗ ታውቋል።

🇩🇰 ዴንማርክ ወደሀገሯ የሚገቡ መንገደኞች የኮቪድ-19 ምርመራ ነፃ ውጤት ማቅረብ እንዳለባቸው አሳውቃለች።

🇲🇦 የሞሮኮ መንግስት በአገር አቀፍ ደረጃ የጤና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እስከ ጥር 31 (እኤአ) አራዝሟል።

🇷🇺 በሩሲያ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ600,000 አልፏል። በሩሲያ የ600,434 ሰዎች ሞት የተመዘገብ ሲሆን ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአሜሪካ (813,000 ሞት) እና ብራዚል (618,000 ሞት) ቀጥላ 3ኛ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ አድርጓታል።

🇪🇹 በሀገራችን ኢትዮጵያ ኦሚክሮን መከሰት አለመከሰቱን ለማረጋገጥ ናሙና በመውሰድ ምርምር እየተካሄደ ነው።

🌎 የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ የኦሚክሮን ዝርያ በዓለም ዙሪያ መስፋፋቱን የቀጠለ መሆኑን እና በርካታ አገሮች ይህን በፍጥነት እየተሰራጨ የሚገኘውን ኦሚክሮን ልውጥ ቫይረስ ሪፖርት እያደረጉ መሆኑን አመልክቷል። እስከ ሰኞ ድረስ ባለው በ106 አገራት ልውጡ ቫይረስ መገኘቱ ተረጋግጧል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዝግጅት ምን ይመስላል ?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ለኢ.ፕ.ድ. በሰጠው ቃል የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጥሪ ተከትሎ ወደ አገር ቤት ለመምጣት ዝግጅት ላይ ያሉ በሁሉም አህጉራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቀልጣፋ አገልግሎት እንደሚሰጥ አሳውቋል።

🛫በቀጥታ በረራ፣ በአጋሮቹ በኩልና በቻርተሩ በረራ አማካኝነት ቀልጣፋ አገልግሎት የሚያገኙበት ሁኔታ ላይ ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል።

🏨 እንግዶች ወደ አገር ሲገቡ የአየር መንገዱ ንብረት የስካይላይት ሆቴል በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቷል።

🚖 ከኤርፖርት ወደ ተለያዩ የሆቴል ማረፊያዎች ለሚሄዱ የዲያስፖራው ወገኖች ከበቂ የሰው ሀይል ጋር የትራንስፖርት አገልግሎት ተዘጋጅቷል።

127 የዓለም አገራትና 5 አህጉራትን እንዲሁም ከ60 በላይ የአፍሪካ አገራት መዳረሻ ያደረገው ግዝፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው ለሚመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የ30 በመቶ ቅናሽ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

(ኢፕድ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ችሎት

ላምሮት ከማል በነጻ ተሰናበተች።

ፍ/ቤቱ ዛሬ ከሰዓት ጥፋተኛ በተባለችበት አንቀጽ በ3 ወር ቀላል ዕስራት እንድትቀጣ የወሰነ ሲሆን ከቅጣቱ በላይ በዕስር በመቆየቷ በነጻ እንድትሰናበት አዟል።

ተከሳሿ በቁጥጥር ስር ከዋለችበት ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ /ም ጀምሮ 3 ወራት በፖሊስ ጣቢያ 1 አመት ከ5 ወራት ደግሞ በማረሚያ ቤት በዕስር መቆየቷን ተከትሎ ነው በነጻ ከስር እንድትሰናበት ነው የተወሰነው።

ላምሮት ከማል በመጀመሪያ ከተከሰሰችበት አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ እንዲገደል የግድያ ቦታ ማመቻቸት ሽብር ወንጀል በቂ ማስረጃ አልቀረበም ተብሎ በዚሁ ፍርድ ቤት በነጻ መሰናበቷ ይታወቃል።

ዓቃቤህግ ነጻ መባሏን በመቃወም ለጠ/ፍ/ ቤት ይግባኝ መጠየቁን ተከትሎ የይግባኝ ሰሚ ችሎቱ መዝገቡን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት የነጻ ውሳኔን በመሻር ላምሮት ከማል አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ በሽጉጥ በተመታበት ጊዜ በቸልተኝነት እርዳታ ባለመስጠት በወንጀል ህግ አንቀጽ 575 ንዑስ ቁ 1 እንድትከላከል ትዛዝ የሰጠ ሲሆን።

መዝገቡ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት ከተመለሰ በኋላም እንድትከላከል በዠየተደረገ አንቀጽ ዋስትና አያስከለክልም ሲል ችሎቱ በ5 ሺህ ብር ዋስ ከዕስር እንድትፈታ ወስኖ ከስር ተፈታ ነበር።

መከላከያ እንድታቀርብ በተሰጠ ቀጠሮ በጽፈት ቤት ቀርባ በጽሁፍ መከላከያ ማስረጃ የለኝም በዓቃቢህግ ባሰማው ማስረጃ ይፈረድብኝ ስትል ፍርድ ቤቱን ጠይቃ ነበር።

በዚህ ጥያቄ መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ትናንት በነበረ ቀጠሮ እንድትከላከል በተባለችበት አንቀጽ መከላከል ባለመቻሏ የጥፋተኝነት ፍርድ በመስጠት በይደር ለቅጣት ውሳኔ መቅጠሩ ይታወሳል።

በዚህም ፍ/ቤቱ በዛሬ ቀጠሮ ዓቃቤ ህግ ወንጀሉ በጭካኔ እና በለሊት የተፈጸመ መሆኑን ጠቅሶ ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃ ውድቅ አድርጓል።

ተከሳሿ የቀደመ የወንጀል እሪከርድ እንደሌለባትና የልጅ እናት መሆኗን ጠቅሳ ያቀረበችውን የቅጣት ማቅለያ አስተያየት ፍርድ ቤቱ ተቀብሏታል።

በሶስት (3) ወር ቀላል እስራት እንድትቀጣ የወሰነ ቢሆንሞ ከቅጣት ውሳኔው በላይ በስር ማሳለፏ ተጠቅሶ በነጻ እንድትሰናበት ተደርጓል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
#DebreBrehan

' ትምህርት ሠኞ ይጀምራል '

በደብረ ብርሃን ከተማ ተፈናቃዮች ተጠልለውባቸው በነበሩ ትምህርት ቤቶች ከሰኞ ጀምሮ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንደሚቀጥል የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ፅህፈት ቤት ማሳወቁን ፋና ዘግቧል።

ህወሓት በአማራ ክልል ላይ በከፈተው ጦርነት ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖችን በመጠለያነት ሲያገለግሉ የነበሩ ትምህርት ቤቶች ከሰኞ ጀምሮ በተያዘላቸው መርሃ ግብር ሁሉም የመማር ማስተማር ሂደታቸውን ይቀጥላሉ ተብሏል።

አሁን ላይ ለት/ ቤቶቹ ተገቢው የፅዳት ስራ ተሰርቶላቸውና መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ስለተሟሉ ተማሪዎች በመማሪያ ክፍላቸው በመገኘት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ጥሪ ቀርቧል።

በደብረ ብርሀን ከተማ ሶስት አንደኛ ደረጃ እና ሶስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፥ በአጠቃላይ በስድስት የትምህርት ተቋማት ተፈናቃዮች ተጠልለው ይገኙ እንደነበር ፋና ብሮድካስት በዘገባው አስታውሷል።

@tikvahethiopia
#Dibate

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ለአመታት ያክል ተቋርጦ የቆየዉን የመብራት አገልግሎት ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

የድባጤ ወረዳ መሪ ማዘጋጃ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አርጌታ ወይላ ፥ ለበርካታ ጊዜያት ተቋርጦ የቆየዉን የመብራት አገልግሎት ለማስጀመርና ማህበረሰቡ የመብራት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።

ሀላፊዉ በመብራት ገመድ ዝርጋታ ስራ ላይ ተገኝተው የተሳተፉትን የወረዳው በጎ አድራጎት ወጣቶችንና ሰላም በማስከበር ረገድ የተሳተፉ የመከላከያ ሰራዊት፣ ለክልሉና ሌሌሎች ክልል ልዩ ሀይሎች ምስጋና አቅርበዋል።

ብልሽት የገጠሙባቸዉን ቦታዎች ላይ ጥገና ተደርጎ በአጭር ጊዜ አገግሎት እንደሚያስጀምሩ የመብራት ሀይል ባለሙያዎች ተናግረዋል።

መረጃው የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው።

@tikvahethiopia