TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ALERT🚨

በሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 2,992 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 10,828 የላብራቶሪ ምርመራ 2,992 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ3 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ወረርሽኙን ለመከላከል የምታደርጉትን ጥንቃቄ እርምጃ ከመቼውም ጊዜ በላይ ታጠናክሩ ዘንድ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
#AFRICA🏆

ከጥር 1 - ጥር 29 ቀን 2014 ድረስ በካሜሩን በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የእግር ኳስ ውድድር ላይ ሀገራቸው 🇪🇹 ኢትዮጵያን ወክለው የሚፋለሙ ተጨዋቾች ይፋ ሆነዋል።

(ዝርዝሩ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል)

More : @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተመጣጣኝ የአፀፋ እርምጃ እንሰጣለን " - ፑቲን የሩሲያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ በዩክሬን ጉዳይ ይዛዋለች ላሉት የኃይል አቋም መንግስታቸው ተመጣጣኝ አፀፋዊ እርምጃ እንደሚሰጥ ዝተዋል። ሩሲያ ጦሯን ወደ ዩክሬን ድንበር ካስጠጋች በኃላ አሜሪካ የምትመራቸው ምዕራባውያን መንግስታት ከሩሲያ ጋር የገቡት አተካራ እየተካረረ መጥቷል። ፑቲን ዛሬ ከመከላከያ ሚኒስቴር ሹማምንት ጋር ባደረጉት ውይይት…
የሩሲያ እና የNATO ፍጣጫ ወዴት ያመራ ይሆን ?

" ተጨባጭ የሆነ ወታደራዊ አጸፌታ ጀምሬያለሁ " - NATO

ሩስያ እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /NATO/ ጦራቸውን ወደ ዩክሬን ድንበር ማስጠጋታቸው በአካባቢው ላይ ወታደራዊ ፍጥጫ ከምን ጊዜውም በላይ እንዲያይል አድርጓል።

ሩስያ ጦሯን ወደ ዩክሬን ድንበር በማንቀሳቀሷ NATO ተጨባጭ የሆነ ወታደራዊ አጸፌታ ጀምሬያለሁ ብሏል።

ይህንንም " Die Welt "የተሰኘው በጀርመንኛ ቋንቋ የሚታተመው መጽሄት ዘግቧል።

አንድ የNATO ዲፕሎማት ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ የድርጅቱ ተወርዋሪ አጥቂ ጦር ቁጥር በአካባቢው ጨምሯል። " የጦር ጫፍ " በሚል የሚታወቀው የNATO አጥቂ ኃይል ከሰኞ ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ በተጠንቀቅ እንዲቆም ትእዛዝ ተሰጥቶታል።

ጦሩ የተጠንቀቅ ትእዛዝ የተላለፈለት በእነዚህ 5 ቀናት ውስጥ ወደ ግጭት ቀጠና ሊሰማራ ይችላል በሚል ነው።

ይሄው ጦር በአሁኑ ወቅት በሚቀጥሉት 7 ቀናት ለግዳጅ ዝግጁ ሆኖ እንዲቆይም ተነግሮታል።

ምዕራቡ ዓለም ሩስያ ዩክሬንን ልትወር እያሴረች ነው ሲል ይከሳል።

ሩስያ በበኩሏ አሜሪካ እና NATO በምስራቅ በኩል የሚያደርጉት መስፋፋት ለመገታቱ ዋስትና ሊሰጠኝ ይገባል ትላለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፦ በሩስያ እና አሜሪካ መካከል በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የአካባቢው ደህንነትን በሚመለከት ውይይት ሊኖር እንደሚችል ተጠቁሟል።

ውይይቱ በአዲስ ዓመት (እ.ኤ.አ. 2022) የመጀመሪያ ወር ከNATO ጋርም ይደረጋል ተብሏል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የሱዳን ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ስልጣን ሊለቁ ነው። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በሚቀጥሉት ሰዓታት ውስጥ ስልጣን ለመልቀቅ እንዳሰቡ ለፖለቲከኞች ቡድን መናገራቸውን ሮይተርስ ለሃምዶክ ቅርብ ከሆኑ ሁለት ምንጮች መስማቱን ዘግቧል። ቡድኑ በቦታቸው ላይ እንዲቆዩ ቢጣይቃቸውም እሳቸውን ግን ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ነግረዋቸዋል። ጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሀምዶክ በጥቅምት ወር በሌ/ጄነራል…
#UPDATE

የሱዳን ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ የስልጣን መልቀቂያ ለማስገባት የደረሱበትን የውሳኔ ሀሳብ ማጠፋቸው/ማንሳታቸው ተሰምቷል።

ከሳዑዲ ጋዜጣ ላይ እንዳነበብነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ የደረሱበትን የውሳኔ ሀሳብ አንስተውታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ሀሳባቸውን ያነሱት ከሌ/ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ውይይት ካደረጉ በኃላ መሆኑን ጋዜጣው ምንጮቹ እንደነገሩት አስነብቧል።

በሌላ በኩል የአሜሪካ 🇺🇸 አፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ዛሬ ከጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ እና ከአል ቡርሃን ጋር ጠቃሚ ውይይት ለማድረግ እድል በማግኘቱ አመስግኖ " አሜሪካ የሱዳን መሪዎች የሱዳንን ህዝብ የነጻነት ፣ የሰላም እና የፍትህ ምኞት ለማሳካት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ማበረታቷን ቀጥላለች ሲል " ገልጿል።

ትላንት ምሽት የሱዳኑ ጠ/ሚ አብደላ ሃምዶክ በሰዓታት ውስጥ ስልጣን ለመልቀቅ እንዳሰቡ ለፖለቲከኞች ቡድን መናገራቸውን ሮይተርስ ለሃምዶክ ቅርብ ከሆኑ 2 ምንጮች መስማቱን መዘገቡ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#Update😷

የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ፦

🇦🇺 አውስትራሊያ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ባከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑ ተዘግቧል።

🇻🇪 የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ በሀገራቸው 7 የኦሚክሮን ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ መገኘቱን ሪፖርት አድርገዋል።

🇺🇸 አሜሪካ እድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ከፍተኛ ተጋላጭነት ላላቸው ሰዎች የPfizer ፀረ-ኮቪድ ክኒን ፈቃድ ሰጥታለች።

🇳🇬 ናይጄሪያ ከ1 ሚሊዮን የሚበልጡ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው የአስትሮዜኔካ ክትባቶችን ትላንት አስወግዳለች።

🇨🇳 በቻይና ሰሜናዊ ከተማ ዢያን አዲስ በተከሰተ የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት 13 ሚሊዮን ነዋሪዎች በሙሉ ቤታቸው እንዲቆዩ ታዟል። ሁሉም አባወራዎች በየ2 ቀን አንድ ጊዜ አንድ የቤተሰብ አባል ወደ ውጭ መላክ እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን ከድንገተኛ አደጋዎች በስተቀር ሁሉም ሰው በቤት ውስጥ እንዲቆይ ታዟል።

🇫🇷 ፈረንሣይ በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 84,272 አዳዲስ የኮቪድ-19 ኬዝ ሪፖርት አድርጋለች፤ ቁጥር ኖቬንበር 2020 ላይ ከተመዘገበው ከፍተኛ ኬዝ 87,000 የሚጠጋ ነው።

🇬🇧 ብሪታንያ ከ5 እስከ 11 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ተጋላጭ ሕፃናትን የኮቪድ-19 ክትባት መከተብ እንደምትጀምር ተሰምቷል። ውሳኔው የተላለፈው የሀገሪቱ የመድኃኒት ተቆጣጣሪ አነስተኛ የPfizer-BioNTech ዶዝ በእዛ እድሜ ክልል መጠቀም እንደሚቻል ከገለፀ በኃላ ነው።

🇹🇷 ቱርክ በሀገሯ የተሰራውን የኮቪድ-19 ክትባት Turkovac ለአደጋ ጊዜ አገልግሎት እንዲውል መፈቀዷን አስታውቃለች።

🇯🇵 ጃፓን ኦሳካ ውስጥ የመጀመሪያ የታወቀ (የዛው የሀገር ውስጥ) የኦሚክሮን ቫይረስ ስርጭትን አረጋግጣለች። ቫይረሱ የተገኘባቸው 3 ሰዎች ሲሆኑ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም።

@tikvahethiopia
#AGOA

ኢትዮጵያ በAGOA ላይ እንድትቆይ ተሰሚነት ያላቸው የኮንግረስ መሪዎች ለአሜሪካ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ደብዳቤ አስገቡ።

የኢትዮጵያ-አሜሪካውያን የዜጎች ም/ቤት ኢትዮጵያ በAGOA እንድትቆይ ግፊት እያደረገ ይገኛል።

ይህን ተከትሎ ለዋይትሃውስ ድምፃቸውን እንዲያሰሙ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው ኮንግረስ መሪዎች የም/ቤቱን ደብዳቤ ተከትሎ ለፕሬዜዳንት ባይደን ኢትዮጵያ በAGOA ላይ እንድትቆይ ደብዳቤ አስገብተዋል።

@tikvahethiopia
#Amhara

በአማራ ክልል የሰዓት እላፊ ገደብ ላይ ማሻሻያ ተደረገ።

የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃለፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የክልሉ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ በተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ መወሰኑን ተናግረዋል።

ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ጠዋት 12 ሰዓት የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ በክልሉ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እየተሻሻለ በመምጣቱ የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴዎች እንዳይዳከሙ እና በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ዲያስፖራዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ማሻሻያ ተደርጓል ነው ያሉት።

በዚህም መሠረት የሰዓት እላፊ ገደቡ ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋት 11 ሰዓት ድረስ ማሻሻያ መደረጉን አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ አሚኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ችሎት ! አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ እንዲገደል ቦታ አመቻችታለች ተብላ በሽብር ወንጀል የተከሰሰችውን እና የክሱ አንቀጽ ተቀይሮ በዋስ የተፈታችው ላምሮት ከማል የመከላከያ ማስረጃ የለኝም በአቃቢህግ ማስረጃ ይፈረድብኝ ስትል ፍርድ ቤቱን መጠየቋ ተሰምቷል። በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት የተከሰሰችበት የሽብር ወንጀል ተቀይሮ አደጋ ላይ ያለ ሰውን በቸልተኝነት ያለመርዳት የወንጀል ህግ…
ችሎት !

አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ በሽጉጥ በተመታበት ወቅት በቸልተኝነት እርዳታ እንዳያገኝ ባለማድረግ ወንጀል ላምሮት ከማል ጥፋተኛ ተባለች።

የጥፋተኝነች ፍርዱን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረሽብርና የህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ከሳሽ ዓቃቢህግ ተከሳሿ ከአንድ የኦነግ ሸኔ አባል ጋር ሜክሲኮ አካባቢ በመገናኘት መንግስትን ከስልጣን ለማውረድ ታዋቂ ሰዎችን ለማስገደል ማቀዳቸውንና ከነዚህ ታዋቂ ሰዎች መካከል አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መሆኑን ግለሰቡ ገልጿላት አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ እንዲገደል ቦታ እንድታመቻች በተነጋገሩት መሰረት የግድያ ቦታ አመቻችታለች ብሎ ክስ አቅርቧባት የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ግን የተከሰሰችበት ወንጀል በቂ ማስረጃ አልቀረበም ሲል በነጻ አሰናብቷት ነበር።

ዓቃቢህግ በውሳኔው ቅር በመሰኘት ለጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ያለ ሲሆን ይግባኙን የመረመረው የጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍ/ቤት ነጻ በማለት የሰጠውን ውሳኔን በመሻር አርቲስት ሀጫሉ በሽጉጥ በተከሳሽ ጥላሁን ያሚ ተመቶ ደም ሲፈሰው በቸልተኝነት እርዳታ እንዲያገኝ ባለማድረግ የወንጀል ህግ አንቀጽ 575 ንዑስ ቁ1 በመተላለፍ እንድትከላከል ትዛዝ ሰቶ ነበር።

ይህን ትዕዛዝ ተከትሎ ለመደበኛ ፍርድ ቤት ተከሳሿ መከላከያ ማስረጃ የለኝም ዓቃቢህግ ባሰማው ማስረጃ ይፈረድብኝ ማለቷን ተከትሎ ፍ/ቤቱ ዛሬ በቸልተኝነት ሰውን ባለመርዳት በወንጀል ህግ አንቀጽ 575 ንዑስ ቁ1 በመተላለፍ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰቶባታል።

ተከሳሿ 1 ገጽ ቅጣት ማቅለያ በጽሁፍ አቅርባለች።

ፍ/ቤት የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት በይደር ቀጥሯል። ተከሳሽ ላምሮት ከማል የቅጣት ውሳኔ እስኪሰጥ እስከ ነገ ፖሊስ ጣቢያ እንድትቆይ ታዟል።

ምንጭ፦ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
" ከማሽከርከራችሁ በፊት የተሽከርካሪያችሁን ደህንነት ፈትሹ ፤ ተገቢውን ጥንቃቄም አድርጋችሁ አሽከርክሩ " - ፖሊስ

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በደረሰ የትራፊክ አደጋ በአንድ ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደረሰ።

በዛሬው ዕለት በደብረ ማርቆስ ከተማ ከጠዋቱ 1፡4ዐ ላይ ቀበሌ ዐ5 ልዩ ቦታው ታቦቱ መውረጃ መስቀለኛ መንገድ አካባቢ ከከተማው ወደ ኬላ መስመር ይጓዝ የነበረ ኮድ (3) የሰሌዳ ቁጥር 20975 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዙ ተሽከርካሪ ልጆችን ትምህርት ቤት ለመሸኘት ከመንገድ ውጭ በቆመች አንድ ግለሠብ በሁለት እግሯ ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል።

ተጎጂዋ ደ/ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ገብታ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ይገኛል።

አሽከርካሪው አደጋውን ካደረሠ በኃላ በመሠወሩ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል አስፈላጊውን ክትትል እያደረገ መሆኑን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታውቋል።

የደ/ማርቆስ ፖሊስ አሽከርካሪዎች ከማሽከርከራቸው በፊት የተሽከርካሪያቸውን ደህንነት እንዲፈትሹ እና ተገቢውን ጥንቃቄ አድርገው እንዲያሽከረክሩ መልዕከት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#Bank_of_Abyssinia

ወደ ሃገር ቤት በ " ካሽ ጎ " ገንዘብ ለመላክ አስበዋል ? ቪዛ ካርድ ወይም ማስተር ካርድዎን ተጠቅመው ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡

ይከፈል የነበረው የ1.5% የመላኪያ ክፍያ በነፃ መደረጉን ስንገልጽሎት በደስታ ነው። የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ https://t.iss.one/BoAEth
#አቢሲንያ #የሁሉም_ምርጫ
#MinistryFinance

በሀገሪቱ 🇪🇹 ኢኮኖሚ ላይ የደረሰውን ጉዳት መልሶ ለመገንባት የሚያስችል እና ዜጎች ለማቋቋም የሚውል አዲስ በጀት ሊያጸድቅ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ በጠ/ሚ ጽ/ቤት በተዘጋጀው " የአዲስ ወግ " መርሃ ግብር ላይ መስሪያ ቤታቸው በጦርነት ምክንያት የተጎዳውን ኢኮኖሚ ለማካካስ ብሎም መልሶ ለመገንባት ተጨማሪ በጀት እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡

የሚያስፈልገው ገንዘብን በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ተሰርቶ ረቂቁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን አስታውቋል።

አቶ አህመድ ሽዴ በቅርቡ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብም የገለፁ ሲሆን ከጸደቀ በቀጥታ ወደ ስራ እንደሚገባ መናገራቸድን አል ዓይን ድረገፅ አስነብቧል።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
#Amhara #Tigray #Afar

የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ 🇪🇹 በግጭት በተጎዱ ክልሎች ላለው የጤና እና ሰብዓዊ ፍላጎቶች ምላሽ እየሰጠ መሆኑን አሳውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት አካላት ከ2 ቀን በፊት #በአማራ ክልል የወደሙ ሆስፒታሎችን በአካል የተመለከቱ ሲሆን የ2 ሚሊዮን ሰዎችን አስቸኳይ የጤና ፍላጎት ለማሟላት ወደ 100 ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ መድሀኒትና የህክምና ቁሳቁሶችን እንዳስረከቡ ድርጅቱ ገልጿል።

ተጨማሪ የህክምና ቁሳቁሶች ወደ #አፋር#ትግራይ እና ሌሎችም ክልሎች መላኩን ድርጅቱ አመልክቷል።

@tikvahethiopia
#Afar #Tigray #Amhara

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ምክትል ቃል አቀባይ የሆኑት ፈርሐን ሐቅ በሰሜን ኢትዮጵያ አንዳንድ መሻሻሎች መኖራቸውን የሚያመላክቱ ሪፖርቶች መኖራቸውን ገልፀዋል።

አሁንም ግን ከሰሞኑን በአካባቢው በተከሰተ ግጭት ሳቢያ ያለው ሁኔታ ተለዋዋጭ እንዲሁም ሊገመት የማይችል ነው ብለዋል።

ቃል አቀባዩ ፥ በአማራ እና አፋር ክልል ተፈናቅለው የነበሩ አንዳንድ ነዋሪዎች ወደ ቄያቸው እየተመለሱ መሆናቸውን በአካባቢው ከሚገኙ ባልደረቦቻችን ተረድተናል ብለዋል።

በአካባቢው ባለው የተደራሽነት ችግር የተመላሾችን ቁጥር ለማወቅ አዳጋች መሆኑን ገልፀዋል።

በአፋር እና ትግራይ ምዕራባዊ ክፍል አሁንም የሚፈናቀሉ አንዳንድ ሰዎች መኖራቸውን አመልክተዋል።

ቃል አቀባዩ ፥ በስፍራው ያሉት የሰብዓዊ ድጋፍ አጋሮቻችን እኤአ ከታህሳስ 15-17 ባሉ ጊዜያት ውስጥ የአየር ድብደባ መካሄዳቸውን ፤ ብዙ ሰዎች መሞታቸውን እና ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል ብለዋል። ይሁን እንጂ ድርጊቱን ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ እንዳልተቻለ አስረድተዋል።

ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በአፋር በኩል ወደ ትግራይ መቐለ የደረሰ ምንም አይነት እርዳታ የጫነ ተሽከርካሪ አለመኖሩን ተናግረዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው በርካታ ተግዳሮት አሁንም ድረስ ያለ መሆኑን ጠቁመው ሁሉም ወገኖች ግጭት አቁመው የእርዳታ አቅርቦት እና የእርዳታ ሰራተኞች ወደ ትግራይ ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች በነፃነት እንዲቀሳቀሱ እንዲደረግ ጥሪ እናቀርባለን ማለታቸውን ቬኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia