TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ቶታል አካባቢ የትራፊክ አደጋ የደረሰ ሲሆን የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

የከባድ እና ቀላል ጉዳት መጠን ቁጥር ለጊዜው አልታወቀም።

የተገጩ ተሽከርካሪዎች ከመንገዱ እስኪነሱ ተዘግቶ የነበረው መንገድ አሁን ክፍት መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" ፈያ ዳኢ " ለኦስካር ሽልማት ታጨ።

በኢትዮጵያዊ - ሜክሲኳዊቷ ፊልም ሠሪ ጀሲካ በሽር የተዘጋጀው ፈያ ዳኢ 'የሐረር' ፊልም በ94ተኛው የኦስካር ሽልማት በዘጋቢ ፊልም ዘርፍ ነው ለሽልማት የታጨው።

የኦስካር ሽልማት (አካዳሚ አዋርድስ) ትላንት በ10 ዘርፎች የሚያወዳድራቸውን ፊልሞች ይፋ ሲያደርግ የጀሲካ ፊልም መታጨቱ ታውቋል።

ጀሲካ በሽር ይህንን ዘጋቢ ፊልም ለማጠናቀቅ 10 ዓመታት እንደወሰደባት በያዝነው ዓመት መባቻ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ባደረገችበት ወቅት ተናግራ ነበር።

' ፈያ ዳኢ ' ፊልም ስለሱስ፣ ስደት፣ ንግድ ፣ ልጅነት፣ መንፈሳዊነት፣ ፍቅር፣ ተፈጥሮ፣ የፖለቲካ እስር፣ ሴትነት ፣ የነጻነት ትግል፣ ሞት፣ ወጣትነት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ብቸኝነት፣ ህልም፣ ቤተሰብ፣ ማንነት ጉዳዮችን ያነሳል።

ሁለት ሰዓት ገደማ የሚወስደው 'ፈያ ዳኢ' በፊልሙ ዓለም ገናና ስም ያላቸው ሰንዳንስ እና ትሩ/ፎልስ ፌስቲቫሎችን ጨምሮ በበርካታ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ታይቷል፤ ተደንቋል፤ ተወዷል።

ስዊዘርላንድ ውስጥ የሚዘጋጀው ታዋቂው 'ቪዥን ዱ ሪል' የዘጋቢ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ተሸልሟል። በፉል ፍሬም እና ሆትዶክስ ፌስቲቫሎች ላይም ተሸልሟል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UNSC ከዚህ በፊት ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ከአስር ጊዜ በላይ ስበስባ የተቀመጠው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመነጋገር ስብሰባ እንደሚቀመጥ ታውቋል። ምክር ቤቱ ዛሬ በ “any other business” ስር በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ የሚወያይ ሲሆን ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት ፦ 🇪🇪 ኢስቶኒያ 🇫🇷 ፈረንሳይ 🇮🇪 አየርላንድ 🇳🇴 ኖርዌይ 🇬🇧 ዩናይትድ…
" የተመድ ፀጥታው ም/ቤት ስብሰባ ያለ ውጤት ነው የተጠናቀቀው "- አቶ ከበደ ዴሲሳ

ከአንድ ቀን በፊት በተወሰኑ ሀገራት ሀሳብ አመንጪነት ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ ስበስባ የተቀመጠው የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባውን ያለ ምንም ውጤት ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ ከበደ ዴሲሳ በመግለጫቸው፥ ከአንድ ቀን በፊት የተመድ ፀ/ቤት በተወሰኑ ሀገራት ሀሳብ አመንጪነት ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ ተቀምጦ እንደነበርና ስብሰባው ያለውጤት መጠናቀቁን ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው፥ " የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት ስብሰባው ያለ አግባብ የተጠራ እና ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር ታስቦ የተጠራ መሆኑን በመረዳት ጣልቃገብነቱን ባለመቀበላቸው ጠንከር ያለ ውሳኔ እንዲተላለፍ ተብሎ የተደረገው ስበስባ ያለውሳኔ የተጠናቀቀና ውጤት ያላስገኘላቸው ሆኖኗል " ብለዋል።

አቶ ከበደ ዴሲሳ፥ ከዚህ በፊትም የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ስበስባ ሲያደርግ ነበር ሲሉ ያስታወሱ ሲሆን ባልተለመደ ሁኔታ ከ12 ጊዜ በላይ ስብሰባ አድርጓል ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው፥ "ም/ቤቱ አንድ ጊዜ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ስም ሌላ ጊዜ በታላቁ ህዳሴ ግድብ የማይመለከተው ጉዳይ ውስጥ እየገባ አንዳንድ ኃያላን ሀገራት የፖለቲካ ማስፈፀሚያ/ፍላጎታቸውን በተቋማቱ በኩል ለማስፈፀም ስብሳባ ሲጠሩ ቆይተዋል፤ ከአንድ ቀን በፊትም የተደረገው ስብሰባ ያለ ውጤት ነው የተጠናቀቀው" ብለዋል።

የፀጥታው ም/ቤት ሰኞ በ“any other business” ስር ስለኢትዮጵያ እንደሚወያይና ስብሰባ እንዲካሄድ የጠየቁት ኢስቶኒያ፣ ፈረንሳይ፣ አየርላንድ፣ ኖርዌይ ፣ ዩኬ፣አሜሪካ እንደነበሩ መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
' የውሃ ማቆራረጥ በሰመራ ሎግያ '

የሰመራ ሎግያ ውሃና ፈሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ፥ በአሁኑ ሰአት የተፈጠረው የውሃ የመቆራረጥ ችግር የተፈጠረው በዋነኝነት በኤሌክትሪክ መብራት ምክንያት ነው ሲል አሳውቋል።

ፅ/ቤቱ ለወራት ተቋርጦ የነበረው የመብራት አገልግሎት በአፋር ክልል በተጀመረበት ጊዜ የኤሌክትሪክ ሀይል የውሃ ፓምፖችን ማንቀሳቀስ አልተቻለም ብሏል።

በዚህ ምክንያት የተፈጠረው የኤሌክትሪክ የሀይል መዋዠቅ ችግር ከኮምቦልቻ ማከፋፈያ በአጭር ጊዜ እንዲስተካከል ከአፋር ክልል መብራት ሀይል አገልግሎት ጋር እየተነጋገርን እንገኛለን ሲል አሳውቋል።

ጽ/ቤቱ የኤሌክትሪክ ችግር እስኪፈታ ድረስ ለደንበኞቹ ውሃ ለማቅረብ ክፍተቱን ነዳጅ በመገዛት በጄኔሬተር ለመሙላት ጥረት እያደረገን መሆኑን ገልፆ ትልልቅ የውሃ ፓምፖችን ግን በጄኔሬተር ማንቀሳቀስ እንዳልተቻለ አስረድቷል።

ፅህፈ ቤቱ ችግሩ እስኪፈታ ድረስ ድንበኞቹ በትዕግስት እንዲትጠባበቁ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
" የAMISOM ቆይታ ለ3 ወር ተራዝሟል " - የተመድ ፀጥታው ም/ ቤት

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃው ምክር ቤት የAMISOM የሶማሊያን የቆይታ ጊዜ በ3 ወራት አራዝሞታል።

ይህ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ የተላለፈው AMISOM የተልዕኮ ሊጠናቀቅ ሳምንት ሲቀረው ነው።

የAMISOM ቆይታ ጊዜ እንዲራዘም ምክንያት የሆነው በአገሪቱ ደህንነት ላይ ክፍተት እንዳይፈጠር ታስቦ እንደሆነ ተገልጿል።

Credit : Abdiirizak Mohamed

@tikvahethiopia
#ተሳተፉ

" ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን "

ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዙር አንደኛ አመት የስራ ዘመኑ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለማቋቋም የቀረበውም ረቂቅ አዋጅ ለህግ ፣ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶ ነበር።

ህብረተሰቡ መሳተፉን ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የመጀመሪያ ዙር የህዝብ አስተያየት መሰብሰቢያ መድረክ ተዘጋጅቶ ከህዝቡና ከተለያዩ ተቋማት የተወከሉ ተሳታፊዎች በተገኙበት በረቂቅ አዋጁ ላይ አስተያየት ተሰብሰቧል።

በተጨማሪ የህዝቡን አስተያየት ከፍ ለማድረግ ሁለተኛ ዙር የህዝብ አስተያየት መሰብሰቢያ መንገድ ቅዳሜ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ/ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከጥዋቱ 3 ሰዓት ላይ የህዝብ መድረክ ተዘጋጅቷል።

አስተያየት ያላቸው አካላት እንዲሁም ግለሰቦች ተገኝተው እንዲሳተፉም ይፋዊ ጥሪ ቀርቧል።

በአካል መሳተፍ የማይችሉ በስልክ ቁጥር 0111225853 ወይም 0913760561 / 0913395495 ላይ በመደወል መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል።

ረቂቅ አዋጁን በዚህ ያግኙ👉 t.iss.one/tikvahethiopia/65861

@tikvahethiopia
#Update

በመሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች እንዲሁም የመሠረተ ልማት ቅንጅት ሥራዎች ላይ ጥሎት የነበረው ዕግድ ማንሳቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታውቋል።

ዕግዱ ከታህሳስ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ መነሳቱን የከንቲባ ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ በሆኑት አቶ ጥላሁን ወርቁ ሮቢ ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤ ተገልጿል።

ዕግድ ተጥሎባቸው ከነበሩት ውስጥ ፦

- በሊዝ ይዞታዎች አዲስ የግንባታ ፈቃድ የመስጠት፣
- የፕላን ስምምነት፣
- የግንባታ ማሻሻያ፣
- ለነባር ይዞታ ካርታ ያላቸው በመልሶ ማልማት ውስጥ (Regulation) የተጠናላቸው፣
- የሊዝ ይዞታዎች፣
- የምትክ ቦታ መሬት ሲረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ፣
- የዕድሳት ፈቃድ መስጠት፣
- የግንባታ ማስጀመሪያ የመስጠትና አገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ፣
- የግንባታ ማስጀመሪያ ክትትል ውስጥ የነበሩ በዕርከን የአገልግሎት ገቢ የመሰብሰብ፣
- ለተለያዩ አካላት የግንባታ መረጃ የመስክ ሪፖርት የመስጠትና የአገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ፣
- የሕንፃ መጠቀሚያ ፈቃድ መስጠትና ክፍያ የመሰብሰብ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ መገለፁን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
" አብዛኛዎቹ ተፈናቃዮች ወደ የቀያቸው ተመልሰዋል " - ሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት

የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ከሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖችና ከሌሎችም አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን በ12 መጠለያ ጣቢያዎችና ከዘመድ ጋር የነበሩ ተፈናቃዮች አብዛኛዎቹ ወደ የቀያቸው መመለሳቸውን አስታውቋል።

ፅ/ቤቱ ለጀርመን ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል፥ በጦርነቱ ውስጥ ከነበሩ 441,650 ተፈናቃዮች መካከል አብዛኛዎቹ ወደ አካባቢያቸው ተመልሰዋል።

አሁን ከ50 ሺህ የማይበልጡ ተፈናቃዮች ብቻ ደብረ ብርሃን ውስጥ እንደሚገኙ እና አስፈላጊው እገዛ እተደረገላቸው መሆኑን አመልክቷል።

በጦርነቱ ምክንያት በአማራ ክልል ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው እንደነበር ሪፖርት መደረጉን ሬድዮ ጣቢያው በዘገባው አድታውሷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ቶታል አካባቢ የትራፊክ አደጋ የደረሰ ሲሆን የአንድ ሰው ህይወት አልፏል። የከባድ እና ቀላል ጉዳት መጠን ቁጥር ለጊዜው አልታወቀም። የተገጩ ተሽከርካሪዎች ከመንገዱ እስኪነሱ ተዘግቶ የነበረው መንገድ አሁን ክፍት መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳውቋል። @tikvahethiopia
የዛሬው የቦሌ መንገድ የትራፊክ አደጋ ፦

አደጋው የደረሰው ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ እየተጓዘ የነበረው ሸገር አውቶቡስ መንገዱን ስቶ ወደ መስቀል አደባባይ በሚጓዙ ተሽከርካሪዎች መንገድ ላይ በመግበት ነው፡፡

በአደጋው መንገድ በማቋረጥ ላይ የነበረች አንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በአንድ ሰው ላይ የአካል ጉዳት ድርሷል፡፡

ሸገር ባስን ጨምሮ 8 ተሽከርካሪዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡

በአጠቃላይ በደረሰው አደጋ የተጋጩ ተሽከርካሪዎች ፦
- ሸገር አውቶብስ
- አምስት የቤት መኪናዎች
- አንድ ላዳ
- አንድ የመንግስት መኪና
- አንድ ሞተር ሳይክል ናቸው።

የአደጋው መንስኤ በፖሊሲ በመጣራት ላይ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመት ኤጀንሲ ፦

• ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በላይ ባለማሽከርከር፣
• ርቀትን እና ረድፍን ጠብቆ በማሽከርከር
• ጠጥቶ ባለማሽከርከር
• ለተሽከርካሪዎች ተገቢውን የቴክኒክ ምርመራ ሳያስደርጉ ባለማሽከርከር
• የትራፊክ ህግ እና ስርዓቶችን በማክበር ተጠንቅቆ በማሽከርከር ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት ከትራፊክ አደጋ ሞት ይታደጉ ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#Update

ሀገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች የሰቆጣ ከተማን መቆጣጠራቸውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

ሀገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች አብዛኞቹ የዋግ ኅምራ አካባቢዎች ነጻ በማውጣት የዞኑን ዋና ከተማ ሰቆጣን መቆጣጣራቸውን ተገልጿል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ " አካባቢው ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በሚወጣበት ጊዜ የዋግ ኅምራ ሚሊሻዎች አስደናቂ ጀብዱ የፈጸሙ ሲሆን፣ የአካባቢው ሕዝብም ከመከላከያ ሠራዊትና ከአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመጣመር ደጀንነቱን በብቃት አሳይቷል " ብሏል።

አክሎም ፥ " የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ የጸጥታ ኃይሎች ቀሪዎቹን ሥፍራ እያጸዱ፣ የፈረጠጠውን የአሸባሪውን ጀሌ እየደመሰሱ፣ ወደ አበርገሌ በመገሥገሥ ላይ ይገኛሉ " ሲል አሳውቋል።

በተያያዘም በቆቦ ግንባር በአንድ በኩል ሙጃና ጥሙጋ ላይ የሠፈረውን የጠላት ኃይል በመጥረግ ወደ አላማጣ ከተማ ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ተኩለሽን ተቆጣጥረው በማጽዳት፣ ወደ መረዋና ኮረም እየገሠገሡ ይገኛሉ ብሏል።

@tikvahethiopia
#UNSC

ዛሬ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት #በአፍጋኒስታን ጉዳይ በአሜሪካ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ።

የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ረቡዕ ባካሄደው ስብሰባ ለአፍጋኒስታን ሰብአዊ ርዳታ የሚያመቻች በአሜሪካ የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ በመሉ ድምፅ አጽድቋል።

የውሳኔ ሀሳቡ፥ "የገንዘብ ክፍያ፣ ሌሎች የፋይናንስ ሀብቶች ወይም የኢኮኖሚ ሀብቶች እና እንዲህ ዓይነቱን እርዳታ በወቅቱ ለማድረስ ወይም መሰል ተግባራትን ለመደገፍ አስፈላጊ የሆኑ እቃዎችና አገልግሎቶች አቅርቦት ይፈቀዳል " ነው የሚለው።

እንዲህ ያለው እርዳታ " አፍጋኒስታን ውስጥ ያሉ መሰረታዊ የሰው ልጆች ፍላጎቶችን " የሚደግፍ እንጂ ከታሊባን ጋር በተገናኙ አካላት ላይ የተጣለውን ማዕቀብ " መጣስ አይደለም " ሲልም ያክላል።

አፍጋኒስታን በከፋ የኢኮኖሚ ውድቀት አፋፍ ላይ ትገኛለች።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 2,992 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 10,828 የላብራቶሪ ምርመራ 2,992 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ3 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ወረርሽኙን ለመከላከል የምታደርጉትን ጥንቃቄ እርምጃ ከመቼውም ጊዜ በላይ ታጠናክሩ ዘንድ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
#AFRICA🏆

ከጥር 1 - ጥር 29 ቀን 2014 ድረስ በካሜሩን በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የእግር ኳስ ውድድር ላይ ሀገራቸው 🇪🇹 ኢትዮጵያን ወክለው የሚፋለሙ ተጨዋቾች ይፋ ሆነዋል።

(ዝርዝሩ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል)

More : @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተመጣጣኝ የአፀፋ እርምጃ እንሰጣለን " - ፑቲን የሩሲያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ በዩክሬን ጉዳይ ይዛዋለች ላሉት የኃይል አቋም መንግስታቸው ተመጣጣኝ አፀፋዊ እርምጃ እንደሚሰጥ ዝተዋል። ሩሲያ ጦሯን ወደ ዩክሬን ድንበር ካስጠጋች በኃላ አሜሪካ የምትመራቸው ምዕራባውያን መንግስታት ከሩሲያ ጋር የገቡት አተካራ እየተካረረ መጥቷል። ፑቲን ዛሬ ከመከላከያ ሚኒስቴር ሹማምንት ጋር ባደረጉት ውይይት…
የሩሲያ እና የNATO ፍጣጫ ወዴት ያመራ ይሆን ?

" ተጨባጭ የሆነ ወታደራዊ አጸፌታ ጀምሬያለሁ " - NATO

ሩስያ እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /NATO/ ጦራቸውን ወደ ዩክሬን ድንበር ማስጠጋታቸው በአካባቢው ላይ ወታደራዊ ፍጥጫ ከምን ጊዜውም በላይ እንዲያይል አድርጓል።

ሩስያ ጦሯን ወደ ዩክሬን ድንበር በማንቀሳቀሷ NATO ተጨባጭ የሆነ ወታደራዊ አጸፌታ ጀምሬያለሁ ብሏል።

ይህንንም " Die Welt "የተሰኘው በጀርመንኛ ቋንቋ የሚታተመው መጽሄት ዘግቧል።

አንድ የNATO ዲፕሎማት ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ የድርጅቱ ተወርዋሪ አጥቂ ጦር ቁጥር በአካባቢው ጨምሯል። " የጦር ጫፍ " በሚል የሚታወቀው የNATO አጥቂ ኃይል ከሰኞ ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ በተጠንቀቅ እንዲቆም ትእዛዝ ተሰጥቶታል።

ጦሩ የተጠንቀቅ ትእዛዝ የተላለፈለት በእነዚህ 5 ቀናት ውስጥ ወደ ግጭት ቀጠና ሊሰማራ ይችላል በሚል ነው።

ይሄው ጦር በአሁኑ ወቅት በሚቀጥሉት 7 ቀናት ለግዳጅ ዝግጁ ሆኖ እንዲቆይም ተነግሮታል።

ምዕራቡ ዓለም ሩስያ ዩክሬንን ልትወር እያሴረች ነው ሲል ይከሳል።

ሩስያ በበኩሏ አሜሪካ እና NATO በምስራቅ በኩል የሚያደርጉት መስፋፋት ለመገታቱ ዋስትና ሊሰጠኝ ይገባል ትላለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፦ በሩስያ እና አሜሪካ መካከል በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የአካባቢው ደህንነትን በሚመለከት ውይይት ሊኖር እንደሚችል ተጠቁሟል።

ውይይቱ በአዲስ ዓመት (እ.ኤ.አ. 2022) የመጀመሪያ ወር ከNATO ጋርም ይደረጋል ተብሏል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ

@tikvahethiopia