#EthiopiaAirlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተከታታይ 4 ዓመታት የአለም አየር መንገዶች ብቃት መዛኝና ደረጃ መዳቢ በሆነው ስካይትራክስ የሚሰጠውን "የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማት" አሸነፈ።
ይህ ሽልማት በብዙዎች ዘንድ "የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ኦስካር" በመባል ይታወቃል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tikvahethiopia

በ2021 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ደረጃ ፦
1. Ethiopian Airlines 🇪🇹
2. South African Airways
3. Kenya Airways
4. Royal AirMaroc
5. Air Mauritius
6. Air Seychelles
7. RwandAir
8. FlySafair
9. Egyptair
10. Fastjet
#SKYTRAX #World_Airline_Award
@tikvahethiopia
1. Ethiopian Airlines 🇪🇹
2. South African Airways
3. Kenya Airways
4. Royal AirMaroc
5. Air Mauritius
6. Air Seychelles
7. RwandAir
8. FlySafair
9. Egyptair
10. Fastjet
#SKYTRAX #World_Airline_Award
@tikvahethiopia
#Update
አቶ አብርሃ ደስታ ከእስር ተፈቱ።
የዓረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ (ዓረና) አመራር የሆኑትና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ያገለገሉት አቶ አብርሃ ደስታ ዛሬ ከእስር ተፈተዋል።
አቶ አብርሃ ከእስር የተፈቱት በ10 ሺ ብር ዋስ መሆኑ ታውቋል።
አቶ አብርሃ ደስታ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ " ከ82 ቀናት በኋላ በፍርድ ቤት የአሰር ሺ ብር የዋስትና ብይን መሰረት ከእስር ተለቅቄያለሁ " ሲሉ ፅፈዋል።

#ETHIOPIA
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ኤስያ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከአምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጡ።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ?
- የፖለቲካ ፍላጎትን መሠረት አድርጎ በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ኢትዮጵያ አትቀበልም ብለዋል። የፖለቲካ ፍላጎት ባላቸው አካላት ገፋፊነት እና አስተባባሪነት የተላለፈው ውሳኔ በኢትዮጵያ ምድር ተፈፃሚ እንደማይሆን አስረግጠው ተናግረዋል።
- የህወሓት አሸባሪ ሀይል በደረሰበት ምት ይዟቸው የነበሩ አብዛኛው የአፋር እና የአማራ አካባቢዎችን በማስለቀቅ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ገልፀዋል። ይህም ቡድኑ ለሰላም ሲል በወረራ ከያዝኳቸው አካባቢዎች ለቅቂያለሁ ማለቱ ከተጨባጩ እውነታ ጋር የሚቃረን ነው ብለዋል።
- መንግስት ቡድኑ (ህወሓት) በሚሸሽባቸው እያንዳንዱ #የትግራይ_መንደሮች እግር በእግር በመከተታል የመግባት ፍላጎት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል፤ ነገር ግን ቡድኑ መቸውም ቢሆን መልሶ ጥቃት የማድረስ አቅሙ የተዳከመ መሆኑ ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
- የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትን ማስጠበቅ የመንግስት ኃላፊነት እንደመሆኑ መጠን፣ ትግራይን ጨምሮ #በማንኛውም_ሀገሪቱ_አካባቢዎች ሰራዊቱን የማስፈር መብት እንዳለው ተናግረዋል።
- በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያለመ ሁሉን አካታች ዉይይት እንዲኖር ማንኛዉም በአገሪቱ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል አካል የሚሳተፍበ የህገ መንግስት ማሻሻያን ጨምሮ በሀገሪቱ ስምምነት ያልተደረሰባቸው ጉዳዮችን የተመለከቱ ጉዳዮች ለውይይት ክፍት እንደሚደረጉ ገልጸዋል።
ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Minstry-of-Foreign-Affairs-of-Ethiopia-12-21

Telegraph
Minstry of Foreign Affairs of Ethiopia
#AmbassdorRedwanHussien የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ኤስያ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከአምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጡ። አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የፖለቲካ ፍላጎትን መሠረት አድርጎ በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ኢትዮጵያ እንደማትቀበል…
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ኤስያ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከአምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጡ። አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ? - የፖለቲካ ፍላጎትን መሠረት አድርጎ በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ኢትዮጵያ አትቀበልም…
" መንግስት ትግራይን ጨምሮ በማንኛውም ሀገሪቱ አካባቢዎች ሰራዊቱን የማስፈር መብት አለው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
የኢትዮጵያ መንግስት ህወሓት በሚሸሽባቸው እያንዳንዱ የትግራይ መንደሮች እግር በእግር በመከታተል የመግባት ፍላጎት የሌለው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናገሩ።
አምባሳደር ሬድዋን ይህን የተናገሩት ዛሬ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ኤስያ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።
አምባሳደር ሬድዋን ፥ መንግስት ህወሓት በሚሸሽባቸው እያንዳንዱ የትግራይ መንደሮች እግር በእግር በመከታተል የመግባት ፍላጎት የሌለውም፤ ነገር ግን ቡድኑ መቸውም ቢሆን መልሶ ጥቃት የማድረስ አቅሙ የተዳከመ መሆኑ ማረጋገጥ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትን ማስጠበቅ የመንግስት ኃላፊነት እንደመሆኑ መጠን፣ ትግራይን ጨምሮ በማንኛውም ሀገሪቱ አካባቢዎች ሰራዊቱን የማስፈር መብት እንዳለው አስገዝበዋል።

#ALERT🚨
በሀገራችን ኢትዮጵያ በቀን 2,323 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 10,016 የላብራቶሪ ምርመራ 2,323 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
በተመሳሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ የ5 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

" ተመጣጣኝ የአፀፋ እርምጃ እንሰጣለን " - ፑቲን
የሩሲያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ በዩክሬን ጉዳይ ይዛዋለች ላሉት የኃይል አቋም መንግስታቸው ተመጣጣኝ አፀፋዊ እርምጃ እንደሚሰጥ ዝተዋል።
ሩሲያ ጦሯን ወደ ዩክሬን ድንበር ካስጠጋች በኃላ አሜሪካ የምትመራቸው ምዕራባውያን መንግስታት ከሩሲያ ጋር የገቡት አተካራ እየተካረረ መጥቷል።
ፑቲን ዛሬ ከመከላከያ ሚኒስቴር ሹማምንት ጋር ባደረጉት ውይይት እንደተናገሩት አሜሪካ እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት (NATO) የሩሲያን ፀጥታ እንደማይጋፉ አስገዳጅ ማረጋገጫ መስጠት አለባቸው ብለዋል።
NATO ወደ ምስራቅ አውሮፓ መስፋፋቱን እንዲያቆም በተለይ ዩክሬንን አባሉ እንደማያደርግ ማረጋገጫ እንዲሰጣት ሩሲያ በተደጋጋሚ ጠይቃለች።
ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ እና NATO ማረጋገጫውን ካልሰጡ መንግስታቸው ተመጣጣኝ ወታደራዊ እና ቴክኒካዊ የአፀፋ እንደሚሰጥ አስጠንቅቀዋል።
ፕሬዜዳንቱ ምዕራባውያን መንግስታት ዩክሬን ውስጥ የሚያደርጉትንና ሊያደርጉ የሚፈልጉትን ጉዳይ በተመለከተ የምናፈገፍግበት ስፍራ እንደሌለ ሊገነዘቡት ይገባል ብለዋል።
ፑቲን " አሁን ዩክሬን ውስጥ የሚደረጉት፣ ሊደረጉ የሚሞከሩት ወይም ያቀዱት ከኛ የመንግስት ድንበር በሺህ ኪ/ሜ ርቀት ላይ አይደለም ደጃፋችን ላይ እንጂ፤ የምናፈገፍግበት ስፍራ እንደሌለ ሊገነዘቡት ይገባል " ሲሉ ነው የተናገሩት።
NATO በቅርቡ ከሩሲያ ጋር ትርጉም ያለው ድርድር እንደሚያደርግ አስታውቋል። የሩሲያ እና የNATO ምክር ቤት ስብሰባ በፈረንጆቹ 2022 አዲስ አመት መጀመሪያ እንደሚካሄድ NATO አሳውቋል።
ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ

#BREAKING
የሱዳን ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ስልጣን ሊለቁ ነው።
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በሚቀጥሉት ሰዓታት ውስጥ ስልጣን ለመልቀቅ እንዳሰቡ ለፖለቲከኞች ቡድን መናገራቸውን ሮይተርስ ለሃምዶክ ቅርብ ከሆኑ ሁለት ምንጮች መስማቱን ዘግቧል።
ቡድኑ በቦታቸው ላይ እንዲቆዩ ቢጣይቃቸውም እሳቸውን ግን ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ነግረዋቸዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሀምዶክ በጥቅምት ወር በሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በሚመራው ጦር መፈንቅለ መንግስት ተደርጎባቸው ለቁም እስር መዳረጋቸው በኃላም በተደረገ ስምምነት ከሳምንታት በፊት ወደ ስልጣናቸው መመለሳቸው አይዘነጋም።

የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ ፦
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ 91,743 ኬዝ ተመዝግቧል። ይህ ወረርሽኙ ከተካሰተ ጊዜ አንስቶ የተመዘገበ ሁለተኛው ከፍተኛ ቁጥር ነው።
🇺🇸 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የዋይት ሀውስ የመካከለኛ ደረጃ ሰራተኞቻቸው በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ የኮቪድ-19 ምርመራ አድርገው ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።
🇬🇧 ለንደን የአዲስ አመት ዝግጅትን ሰርዛለች።
🇲🇦 ሞሮኮ በኮሮና ቫይረስ መባባስ ምክንያት የአዲስ ዓመት ዋዜማ ዝግጅቶችን አግዳለች። የሰዓት እላፊ ገደብም ታውጇል። ከቀናት በፊት ኦሚክሮን በሀገሪቱ መገኘቱ ተረጋግጧል።
🇳🇿 ኒውዚላንድ ኦሚክሮን እንዳይስፋፋ በመስጋት ድንበሮቿ የመክፈት እቅዷን እስከ የካቲት ወር መጨረሻ አዘግይታለች።
🇮🇷 በየመን የኢራን ልዩ መልዕክተኛ በኮቪድ-19 ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል፤ መልዕክተኛው ከሰነዓ ከወጡ በኃላ መሞታቸው ነው የተሰማው።
🏴 በስኮትላንድ ከገና በዓል ጋር ተያይዞ ገደቦች ተጥሏል፤ ከዲሴምበር 26 ጀምሮ ለሶስት ሳምንታት በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ የሚገኙ ሰዎች ላይ ገደብ እንዲኖር እና አካላዊ መራራቅ አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል።
🇩🇰 ኦሚክሮን ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ዴንማርክ ውስጥ በዋነኝነት እየተስፋፋ ከሚገኙ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች አንዱ መሆኑ ተሰምቷል።
🇮🇳 ህንድ ኦሚክሮን በእጥፍ መጨመሩን ተከትሎ ሁሉም ክልሎች ንቁ እንዲሆኑ አሳስባለች።
🇮🇱 እስራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሚክሮን ልውጥ የኮሮና ቫይረስ መሞቱ የተረጋገጠ ሰው ሪፖርት አድርጋለች።
ምንጭ፦ የየሀገራቱ የጤና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች/ የዜና ተቋማት

" እዳ መክፈያ ጊዜው ለ3 ወር ተራዝሟል " - IMF
የዓለም ገንዘብ ድርጅት (IMF) አነስተኛ ገቢ ላላቸው 25 ተበዳሪ ሀገራት ተጨማሪ የእዳ አገልግሎት መክፈያ ጊዜ ፈቅዷል።
ከ25ቱ ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት። ከ25ቱ መካከል 20ው የአፍሪካ ሀገራት ናቸው።
የድርጅቱ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ ተሰብስቦ ባሳለፈው ውሳኔ 25ቱ ሀገራት ለድርጅቱ መክፈል የሚገባቸውን ክፍያ በሶስት ወር አራዝሞታል።
ድርጅቱ የእዳ መክፈያ ጊዜ ሲያራዝም ይህ ለ5ኛ ጊዜ ሲሆን የመጨረሻው መሆኑን አሳውቋል።
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ምክንያት በማድረግ 4 ጊዜ የእዳ መክፈያ ማራዘሚያ ጊዜ ሰጥቶ ነበር።
ምንጭ፦ www.imf.org/en/News/Articles/2021/12/20/pr21390-imf-executive-board-extends-debt-service-relief-for-25-eligible-low-income-countries & Deutsche Welle

#AddisAbaba
ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ቶታል አካባቢ የትራፊክ አደጋ የደረሰ ሲሆን የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።
የከባድ እና ቀላል ጉዳት መጠን ቁጥር ለጊዜው አልታወቀም።
የተገጩ ተሽከርካሪዎች ከመንገዱ እስኪነሱ ተዘግቶ የነበረው መንገድ አሁን ክፍት መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳውቋል።

" ፈያ ዳኢ " ለኦስካር ሽልማት ታጨ።
በኢትዮጵያዊ - ሜክሲኳዊቷ ፊልም ሠሪ ጀሲካ በሽር የተዘጋጀው ፈያ ዳኢ 'የሐረር' ፊልም በ94ተኛው የኦስካር ሽልማት በዘጋቢ ፊልም ዘርፍ ነው ለሽልማት የታጨው።
የኦስካር ሽልማት (አካዳሚ አዋርድስ) ትላንት በ10 ዘርፎች የሚያወዳድራቸውን ፊልሞች ይፋ ሲያደርግ የጀሲካ ፊልም መታጨቱ ታውቋል።
ጀሲካ በሽር ይህንን ዘጋቢ ፊልም ለማጠናቀቅ 10 ዓመታት እንደወሰደባት በያዝነው ዓመት መባቻ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ባደረገችበት ወቅት ተናግራ ነበር።
' ፈያ ዳኢ ' ፊልም ስለሱስ፣ ስደት፣ ንግድ ፣ ልጅነት፣ መንፈሳዊነት፣ ፍቅር፣ ተፈጥሮ፣ የፖለቲካ እስር፣ ሴትነት ፣ የነጻነት ትግል፣ ሞት፣ ወጣትነት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ብቸኝነት፣ ህልም፣ ቤተሰብ፣ ማንነት ጉዳዮችን ያነሳል።
ሁለት ሰዓት ገደማ የሚወስደው 'ፈያ ዳኢ' በፊልሙ ዓለም ገናና ስም ያላቸው ሰንዳንስ እና ትሩ/ፎልስ ፌስቲቫሎችን ጨምሮ በበርካታ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ታይቷል፤ ተደንቋል፤ ተወዷል።
ስዊዘርላንድ ውስጥ የሚዘጋጀው ታዋቂው 'ቪዥን ዱ ሪል' የዘጋቢ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ተሸልሟል። በፉል ፍሬም እና ሆትዶክስ ፌስቲቫሎች ላይም ተሸልሟል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ

#UNSC ከዚህ በፊት ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ከአስር ጊዜ በላይ ስበስባ የተቀመጠው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመነጋገር ስብሰባ እንደሚቀመጥ ታውቋል። ምክር ቤቱ ዛሬ በ “any other business” ስር በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ የሚወያይ ሲሆን ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት ፦ 🇪🇪 ኢስቶኒያ 🇫🇷 ፈረንሳይ 🇮🇪 አየርላንድ 🇳🇴 ኖርዌይ 🇬🇧 ዩናይትድ…
" የተመድ ፀጥታው ም/ቤት ስብሰባ ያለ ውጤት ነው የተጠናቀቀው "- አቶ ከበደ ዴሲሳ
ከአንድ ቀን በፊት በተወሰኑ ሀገራት ሀሳብ አመንጪነት ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ ስበስባ የተቀመጠው የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባውን ያለ ምንም ውጤት ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
አቶ ከበደ ዴሲሳ በመግለጫቸው፥ ከአንድ ቀን በፊት የተመድ ፀ/ቤት በተወሰኑ ሀገራት ሀሳብ አመንጪነት ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ ተቀምጦ እንደነበርና ስብሰባው ያለውጤት መጠናቀቁን ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው፥ " የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት ስብሰባው ያለ አግባብ የተጠራ እና ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር ታስቦ የተጠራ መሆኑን በመረዳት ጣልቃገብነቱን ባለመቀበላቸው ጠንከር ያለ ውሳኔ እንዲተላለፍ ተብሎ የተደረገው ስበስባ ያለውሳኔ የተጠናቀቀና ውጤት ያላስገኘላቸው ሆኖኗል " ብለዋል።
አቶ ከበደ ዴሲሳ፥ ከዚህ በፊትም የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ስበስባ ሲያደርግ ነበር ሲሉ ያስታወሱ ሲሆን ባልተለመደ ሁኔታ ከ12 ጊዜ በላይ ስብሰባ አድርጓል ሲሉ ተናግረዋል።
አክለው፥ "ም/ቤቱ አንድ ጊዜ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ስም ሌላ ጊዜ በታላቁ ህዳሴ ግድብ የማይመለከተው ጉዳይ ውስጥ እየገባ አንዳንድ ኃያላን ሀገራት የፖለቲካ ማስፈፀሚያ/ፍላጎታቸውን በተቋማቱ በኩል ለማስፈፀም ስብሳባ ሲጠሩ ቆይተዋል፤ ከአንድ ቀን በፊትም የተደረገው ስብሰባ ያለ ውጤት ነው የተጠናቀቀው" ብለዋል።
የፀጥታው ም/ቤት ሰኞ በ“any other business” ስር ስለኢትዮጵያ እንደሚወያይና ስብሰባ እንዲካሄድ የጠየቁት ኢስቶኒያ፣ ፈረንሳይ፣ አየርላንድ፣ ኖርዌይ ፣ ዩኬ፣አሜሪካ እንደነበሩ መገለፁ አይዘነጋም።