TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከአናዶሉ ኤጀንሲ ጋር ልዩ ቃለ ምልልስ አድርገዋል። የተነሱ ጉዳዮች ፦

• የግጭቱ ወቅታዊ ሁኔታ
• የውጭ ጣልቃገብነት
• የኢትዮ-ቱርክ የሁለትዮሽ ግንኙነት
• የኢትዮጵያ እና የሱዳን የድንበር ግጭትና ሌሎች ጉዳዮች ተነስተዋል።

ቃለምልልሱ ከላይ በቪድዮ (4 MB) ታያይዟል።

Credit : Anadolu Agency

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያላሳደሱ የጉምሩክ አስተላላፊዎች የተሰጠው ቀነ ገደብ ሊሰጠናቀቅ 3 ቀን ቀርቶታል።

የጉሙሩክ አስተላላፊዎች የሞያ እና የብቃት ማረጋገጫ አሰጣጥና አስተዳደር በተመለከተ በወጣው መመሪያ ቁጥር 153/2011 በማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 170/2013 መሰረት የጉሙሩክ አስተላላፊዎች የስራ ብቃት ማረጋገጫ መውሰድና በወቅቱ ማሳደስ ይጠበቅባቸዋል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ከዚህ ቀደም በተለያዩ በሚዲያዎች ዝርዝር መስፈርቶችን በማየት እና በማሟላት ከህዳር 15 - ታህሳስ 15 /2014 ድረስ እንዲወስዱ / እንዲያሳድሱ አሳውቆ ነበር።

የተሰጠው ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ሶስት ቀናት ብቻ የቀረው ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ የማይፈፅሙ ኮሚሽኑ እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ_አገራዊ_ምክክር_ኮሚሽን_ማቋቋሚያ_አዋጅ_Amhaic.doc
143 KB
#ያንብቡ

በኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ እና የሃሳብ መሪዎች እንዲሁም የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል እጅግ መሠረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የሃሳብ ልዩነት እና አለመግባባት የሚታይ በመሆኑ ይህን ልዩነት እና አለመግባባት ለማርገብና ለመፍታት ሰፋፊ አገራዊ የሕዝብ ምክክሮችን አካታች በሆነ መንገድ በማካሄድ አገራዊ መግባባት መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል።

መሠረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ አካታች አገራዊ ምክክሮችን ማካሄድ የተሻለ አገራዊ መግባባትን ለመገንባትና በሂደትም የመተማመንን እና በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ የመሥራት ባህልን ለማጎልበት፣ እንዲሁም የተሸረሸሩ ለማሳለጥ የሚያስችል ሥርዓት በሕግ መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ተብሏል።

አገራዊ ምክክሮች ተቀባይነት እና ተዓማኒነት ያላቸው እንዲሆኑ ከሚያስችላቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ምክክሮቹን የሚያመቻቸውና የሚመራው አካል ብቃትና ገለልተኝነት በመሆኑ፤ ምክክሮቹን በብቃትና በገለልተኝነት ለመምራትና ለማስተባበር የሚችል ሰፊ ቅቡልነት ያለው ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

በዚህም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 55(1) መሠረት ከላይ የተያያዘው አዋጅ ታውጇል።

ይህ ኮሚሽኑ በሀገሪቱ ለዘመናት የቀጠለውን ያለመግባባት አዙሪት በማስወገድ አገራዊ አንድነት እንደሚያረጋገጥ ተስፋ እንደተጣለበት ተነግሯል።

የህ/ተ/ምክር ቤት በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ዜጎች ረቂቅ አዋጁን አንብበው ም/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ ሊያየው ይገባል የሚሉትን ሀሳብ እንዲሰጡ ጠይቋል።

(እንደ ዜጋ ከላይ የተያያዘውን ረቂቅ አዋጅ አንብበው በም/ቤቱ ገፅ https://www.facebook.com/599208023518983/posts/4270721263034289/ ገብተው ሀሳቦትን ያካፍሉ)

@tikvahethiopia
#DStv

ዙረት

ወንጀል እና ፍቅርን የሚያሳይ ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ድራማ ዘወትር ሰኞ ማታ 2፡30 በድጋሚ እሁድ ከጠዋቱ 04፡00 ሰዓት እና ማታ 02፡00 ሰዓት በአቦል ቻናል (146) ይጠብቁን !

#DStvየራሳችን
አቶ አሕመድ አሊ የኦሮሞ ብ/ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳዳር ም/ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ አቶ አሕመድ አሊን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የቀድሞው ዋና አሰተዳዳሪ አቶ አሕመድ ሐሰን እና አዲሱ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሕመድ አሊ የስልጣን ርክክብ አድርገዋል።

ም/ቤቱ የዞን ካቢኔ አባላትን ሹመት አፅድቋል (የተሿሚዎች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)

በተጨማሪም የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ አቶ ከድር አሊን የዞኑ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ፣ አቶ ጀማል ሐሰንን የዞኑ ፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ እና አቶ መሐመድ ሙሳን የዞኑ አደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ አድርጎ ሹሟል።

#AMC

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ "ታላቅ ጉዞ ወደ ሐገር ቤት " የትኬት ሽያጭ እስከ ታህሳስ 16 ቀን 2014 መራዘሙን አሳውቋል።

በሌላ በኩል ኢትዮ ቴሌኮም ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት እየተዘጋጁ ያሉ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆችን በአገልግሎቱ ላይ እስከ 51 በመቶ ቅናሽ አድርጎ ሊቀበል መሆኑ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
ፈረንሳይ በድሮን ጥቃት ስምንት ሰዎችን እንደገደለ የተጠረጠረ የIS አባል ገደለች።

የፈረንሳይ ጦር ባለፈው አመት በኒጀር 6 የፈረንሳይ ዜግነት ያላቸው የእርዳታ ሰራተኞችን እና 2 ኒጀርያውያን አስጎብኚዎቻቸውን በመግደል ከተጠረጠሩት መካከል አንዱ የሆነውን ሱማና ቡራ የተባለ ግለሰብ በድሮን ጥቃት መግደሉን አሳውቋል።

የፈረንሳይ ጦር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ትላንት ሰኞ የተገደለው ግለሰብ ሱማን ቡራ በምእራብ ኒጀር በደርዘን የሚቆጠሩ የIS ተዋጊዎችን ይመራ እንደነበር ገልጿል።

የፈረንሳይ ጦር ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል በሰጠው ቃል ቦራ የሞተር ሳይክሉን እያሽከረከረ ሲሄድ በነበረበት ወቅት በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት ተመቶ መገዱሉን ተናግሯል።

ስድስቱ ACTED የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አባላት እና አስጎብኝዎቻቸው የተገደሉት እኤአ በነሀሴ 2020 ከኒጀር ዋና ከተማ ኒያሜ 65 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን የኩሬ ብሔራዊ ፓርክን እየጎበኙ በነበረበት ወቅት ነበር።

@tikvahethiopia
#EthiopiaAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተከታታይ 4 ዓመታት የአለም አየር መንገዶች ብቃት መዛኝና ደረጃ መዳቢ በሆነው ስካይትራክስ የሚሰጠውን "የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማት" አሸነፈ።

ይህ ሽልማት በብዙዎች ዘንድ "የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ኦስካር" በመባል ይታወቃል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopia
በ2021 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ደረጃ ፦

1. Ethiopian Airlines 🇪🇹
2. South African Airways
3. Kenya Airways
4. Royal AirMaroc
5. Air Mauritius
6. Air Seychelles
7. RwandAir
8. FlySafair
9. Egyptair
10. Fastjet

#SKYTRAX #World_Airline_Award

@tikvahethiopia
#Update

አቶ አብርሃ ደስታ ከእስር ተፈቱ።

የዓረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ (ዓረና) አመራር የሆኑትና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ያገለገሉት አቶ አብርሃ ደስታ ዛሬ ከእስር ተፈተዋል።

አቶ አብርሃ ከእስር የተፈቱት በ10 ሺ ብር ዋስ መሆኑ ታውቋል።

አቶ አብርሃ ደስታ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ " ከ82 ቀናት በኋላ በፍርድ ቤት የአሰር ሺ ብር የዋስትና ብይን መሰረት ከእስር ተለቅቄያለሁ " ሲሉ ፅፈዋል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን  መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ኤስያ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከአምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጡ። 

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ?

- የፖለቲካ ፍላጎትን መሠረት አድርጎ በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ኢትዮጵያ አትቀበልም ብለዋል። የፖለቲካ ፍላጎት ባላቸው አካላት ገፋፊነት እና አስተባባሪነት የተላለፈው ውሳኔ በኢትዮጵያ ምድር ተፈፃሚ እንደማይሆን አስረግጠው ተናግረዋል።

- የህወሓት አሸባሪ ሀይል በደረሰበት ምት ይዟቸው የነበሩ አብዛኛው የአፋር እና የአማራ አካባቢዎችን በማስለቀቅ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ገልፀዋል። ይህም ቡድኑ ለሰላም ሲል በወረራ ከያዝኳቸው አካባቢዎች ለቅቂያለሁ ማለቱ ከተጨባጩ እውነታ ጋር የሚቃረን ነው ብለዋል።

- መንግስት ቡድኑ (ህወሓት) በሚሸሽባቸው እያንዳንዱ #የትግራይ_መንደሮች እግር በእግር በመከተታል የመግባት ፍላጎት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል፤ ነገር ግን ቡድኑ መቸውም ቢሆን መልሶ ጥቃት የማድረስ አቅሙ የተዳከመ መሆኑ ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

- የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትን ማስጠበቅ የመንግስት ኃላፊነት እንደመሆኑ መጠን፣ ትግራይን ጨምሮ #በማንኛውም_ሀገሪቱ_አካባቢዎች ሰራዊቱን የማስፈር መብት እንዳለው ተናግረዋል።

- በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያለመ ሁሉን አካታች ዉይይት እንዲኖር ማንኛዉም በአገሪቱ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል አካል የሚሳተፍበ የህገ መንግስት ማሻሻያን ጨምሮ በሀገሪቱ ስምምነት ያልተደረሰባቸው ጉዳዮችን የተመለከቱ ጉዳዮች ለውይይት ክፍት እንደሚደረጉ ገልጸዋል።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Minstry-of-Foreign-Affairs-of-Ethiopia-12-21

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን  መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ኤስያ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከአምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጡ።  አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ? - የፖለቲካ ፍላጎትን መሠረት አድርጎ በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ኢትዮጵያ አትቀበልም…
" መንግስት ትግራይን ጨምሮ በማንኛውም ሀገሪቱ አካባቢዎች ሰራዊቱን የማስፈር መብት አለው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

የኢትዮጵያ መንግስት ህወሓት በሚሸሽባቸው እያንዳንዱ የትግራይ መንደሮች እግር በእግር በመከታተል የመግባት ፍላጎት የሌለው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናገሩ።

አምባሳደር ሬድዋን ይህን የተናገሩት ዛሬ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ኤስያ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

አምባሳደር ሬድዋን ፥ መንግስት ህወሓት በሚሸሽባቸው እያንዳንዱ የትግራይ መንደሮች እግር በእግር በመከታተል የመግባት ፍላጎት የሌለውም፤ ነገር ግን ቡድኑ መቸውም ቢሆን መልሶ ጥቃት የማድረስ አቅሙ የተዳከመ መሆኑ ማረጋገጥ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትን ማስጠበቅ የመንግስት ኃላፊነት እንደመሆኑ መጠን፣ ትግራይን ጨምሮ በማንኛውም ሀገሪቱ አካባቢዎች ሰራዊቱን የማስፈር መብት እንዳለው አስገዝበዋል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በሀገራችን ኢትዮጵያ በቀን 2,323 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 10,016 የላብራቶሪ ምርመራ 2,323 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ የ5 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

@tikvahethiopia
" ተመጣጣኝ የአፀፋ እርምጃ እንሰጣለን " - ፑቲን

የሩሲያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ በዩክሬን ጉዳይ ይዛዋለች ላሉት የኃይል አቋም መንግስታቸው ተመጣጣኝ አፀፋዊ እርምጃ እንደሚሰጥ ዝተዋል።

ሩሲያ ጦሯን ወደ ዩክሬን ድንበር ካስጠጋች በኃላ አሜሪካ የምትመራቸው ምዕራባውያን መንግስታት ከሩሲያ ጋር የገቡት አተካራ እየተካረረ መጥቷል።

ፑቲን ዛሬ ከመከላከያ ሚኒስቴር ሹማምንት ጋር ባደረጉት ውይይት እንደተናገሩት አሜሪካ እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት (NATO) የሩሲያን ፀጥታ እንደማይጋፉ አስገዳጅ ማረጋገጫ መስጠት አለባቸው ብለዋል።

NATO ወደ ምስራቅ አውሮፓ መስፋፋቱን እንዲያቆም በተለይ ዩክሬንን አባሉ እንደማያደርግ ማረጋገጫ እንዲሰጣት ሩሲያ በተደጋጋሚ ጠይቃለች።

ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ እና NATO ማረጋገጫውን ካልሰጡ መንግስታቸው ተመጣጣኝ ወታደራዊ እና ቴክኒካዊ የአፀፋ እንደሚሰጥ አስጠንቅቀዋል።

ፕሬዜዳንቱ ምዕራባውያን መንግስታት ዩክሬን ውስጥ የሚያደርጉትንና ሊያደርጉ የሚፈልጉትን ጉዳይ በተመለከተ የምናፈገፍግበት ስፍራ እንደሌለ ሊገነዘቡት ይገባል ብለዋል።

ፑቲን " አሁን ዩክሬን ውስጥ የሚደረጉት፣ ሊደረጉ የሚሞከሩት ወይም ያቀዱት ከኛ የመንግስት ድንበር በሺህ ኪ/ሜ ርቀት ላይ አይደለም ደጃፋችን ላይ እንጂ፤ የምናፈገፍግበት ስፍራ እንደሌለ ሊገነዘቡት ይገባል " ሲሉ ነው የተናገሩት።

NATO በቅርቡ ከሩሲያ ጋር ትርጉም ያለው ድርድር እንደሚያደርግ አስታውቋል። የሩሲያ እና የNATO ምክር ቤት ስብሰባ በፈረንጆቹ 2022 አዲስ አመት መጀመሪያ እንደሚካሄድ NATO አሳውቋል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ

@tikvahethiopia
#BREAKING

የሱዳን ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ስልጣን ሊለቁ ነው።

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በሚቀጥሉት ሰዓታት ውስጥ ስልጣን ለመልቀቅ እንዳሰቡ ለፖለቲከኞች ቡድን መናገራቸውን ሮይተርስ ለሃምዶክ ቅርብ ከሆኑ ሁለት ምንጮች መስማቱን ዘግቧል።

ቡድኑ በቦታቸው ላይ እንዲቆዩ ቢጣይቃቸውም እሳቸውን ግን ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ነግረዋቸዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሀምዶክ በጥቅምት ወር በሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በሚመራው ጦር መፈንቅለ መንግስት ተደርጎባቸው ለቁም እስር መዳረጋቸው በኃላም በተደረገ ስምምነት ከሳምንታት በፊት ወደ ስልጣናቸው መመለሳቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#Update

የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ ፦

🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ 91,743 ኬዝ ተመዝግቧል። ይህ ወረርሽኙ ከተካሰተ ጊዜ አንስቶ የተመዘገበ ሁለተኛው ከፍተኛ ቁጥር ነው።

🇺🇸 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የዋይት ሀውስ የመካከለኛ ደረጃ ሰራተኞቻቸው በቫይረሱ ​​​​ከተያዙ በኋላ የኮቪድ-19 ምርመራ አድርገው ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።

🇬🇧 ለንደን የአዲስ አመት ዝግጅትን ሰርዛለች።

🇲🇦 ሞሮኮ በኮሮና ቫይረስ መባባስ ምክንያት የአዲስ ዓመት ዋዜማ ዝግጅቶችን አግዳለች። የሰዓት እላፊ ገደብም ታውጇል። ከቀናት በፊት ኦሚክሮን በሀገሪቱ መገኘቱ ተረጋግጧል።

🇳🇿 ኒውዚላንድ ኦሚክሮን እንዳይስፋፋ በመስጋት ድንበሮቿ የመክፈት እቅዷን እስከ የካቲት ወር መጨረሻ አዘግይታለች።

🇮🇷 በየመን የኢራን ልዩ መልዕክተኛ በኮቪድ-19 ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል፤ መልዕክተኛው ከሰነዓ ከወጡ በኃላ መሞታቸው ነው የተሰማው።

🏴󠁧󠁢󠁳󠁣󠁴󠁿 በስኮትላንድ ከገና በዓል ጋር ተያይዞ ገደቦች ተጥሏል፤ ከዲሴምበር 26 ጀምሮ ለሶስት ሳምንታት በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ የሚገኙ ሰዎች ላይ ገደብ እንዲኖር እና አካላዊ መራራቅ አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል።

🇩🇰 ኦሚክሮን ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ዴንማርክ ውስጥ በዋነኝነት እየተስፋፋ ከሚገኙ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች አንዱ መሆኑ ተሰምቷል።

🇮🇳 ህንድ ኦሚክሮን በእጥፍ መጨመሩን ተከትሎ ሁሉም ክልሎች ንቁ እንዲሆኑ አሳስባለች።

🇮🇱 እስራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሚክሮን ልውጥ የኮሮና ቫይረስ መሞቱ የተረጋገጠ ሰው ሪፖርት አድርጋለች።

ምንጭ፦ የየሀገራቱ የጤና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች/ የዜና ተቋማት

@tikvahethiopia