#Afar
በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ እና የሰብአዊ ድጋፍ አስተባባሪ ዶ/ር ካትሪን ሶዚ የተመራ ቡድን በአፋር ክልል ጉብኝት አድርጓል።
ዶ/ር ካትሪን ሶዚ ከአፋር ክልል ፕሬዝዳንት አወል አርባ ጋር ውይይት አድርገዋል።
ውይይታቸው የነበረው በክልሉ ስላለው ሰብአዊ ሁኔታና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና አጋሮቹ ላለው የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት ምላሽ አሰጣጥ ዙሪያ ነው።
በተጨማሪ ዶ/ር ካትሪን ሶዚ የመሩት ቡድን ከአፋር ክልል ህብረተሰቡ መሪዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል።
ውይይቱ በአፋር ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሰብዓዊ እርዳታ በማስፋት ዙሪያ እና ወደ ትግራይ ክልል ቀጣይነት ያለው የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ያለመ ነው።
ዶ/ር ካትሪን ሶዚ በአፋር ጉብኝታቸው ከመሩት ቡድን ጋር በመሆን በአፋር የተፈናቀሉ ዜጎችን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና አጋሮቹ በግጭት የተጎዱ ሰዎች ሰብአዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
እንዲሁም ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ ያለውን ቅንጅትና አጋርነት ለማጠናከር በአፋር ከሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የታሪፍ ማሻሻያ በነገው እለት ይፋ አደርጋለሁ ማለቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል። ካለንበት የታህሳስ ወር ጀምሮ የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ይታወቃል። @tikvahethiopia
#Update
የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሆነ።
በአዲስ አበባ በሚኒባሶች እና ታክሲዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሆነ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በዚህ መሰረትም ፦ በሚኒባስ (ቅጥቅጥ ወይም ሃይገር ባስ) የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ በሚኒባስ በኪሎሜትር ከ40 ሳንቲም ወደ 45 ሳንቲም ከፍ የተደረገ ሲሆን÷ በታክሲ ደግሞ በኪሎሜትር ከ90 ሳንቲም ወደ 1 ብር ከፍ ብሏል፡፡
በሚኒባሶች የተደረገው ጭማሪ ዝቅተኛው 1 ብር ሲሆን÷ ከፍተኛው ደግሞ 2 ብር ሆኗል፡፡
በታክሲ ላይ የተደረገው ጭማሪ ዝቅተኛ 50 ሳንቲም ሲሆን ÷ከፍተኛው ጭማሪ 3 ብር ከ50 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡
ጭማሪው የኪሎሜትር ርቀትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
የታሪፍ ጭማሪው በብዙሃን ትራንስፖርት ላይ እንዳልተደረገ የከተማው የትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ በመግለጫው ላይ ማሳወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#Update የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሆነ። በአዲስ አበባ በሚኒባሶች እና ታክሲዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሆነ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በዚህ መሰረትም ፦ በሚኒባስ (ቅጥቅጥ ወይም ሃይገር ባስ) የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ በሚኒባስ በኪሎሜትር ከ40 ሳንቲም ወደ 45 ሳንቲም…
የታሪፍ መመሪያ 👆
የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ የታሪፍ መመሪያ ቁጥር 15/2014
Credit : ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ የታሪፍ መመሪያ ቁጥር 15/2014
Credit : ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tikvahethiopia
#Dessie
" የህክምና ቁሳቁሶቹን ባለሞያዎች መጥተው ነው የፈቷቸው " - የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
በአማራ ክልል እጅግ ከፍተኛ ውድመት ከደረሰባቸው ሆስፒታሎች መካከል የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዋነኝነት ይጠቀሳል።
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሃይማኖት አየለ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ ሆስፒታሉ 80 ዓመቱ ሲሆን የደረሰበት ጉዳት 80 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ከ0 እንዲጀምር እንደሚያደርገው ነው የምንቆጥረው ብለዋል።
ሆስፒታሉ በህወሓት ኃይሎች የመድሃኒት ቤቱ አንድም ሳይተርፍ ተዘርፏል/ወድሟል፣ የላብራቶሪ እቃዎች ተዘርፈዋል፣ በምስራቅ አማራ ብቸኛው የኦክሲጅን ማምረቻው ተዘርፎ ተወስዷል የተረፈው አገልግሎት እንዳይሰጥ ተደርጎ ወድሟል፤ በምስራቅ አማራ ብቸኛው የካንሰር ህክምና መስጫ ቁሳቁሶች ተዘርፎ ተወስዷል።
ዶ/ር ሃይማኖት አየለ ዝርፊያው በተጠና መልኩ እንደተካሄደና ባለሞያዎች መጥተው እንደፈቷቸው አሳውቀዋል።
ሆስፒታሉ አሁን ላይ በተወሰነ መልኩ ወደአገልግሎት የተመለሰ ሲሆን የወሊድ፣ ድንገተኛ አገልግሎት እና የተመላላሽ ታካሚዎችን እያስተናገደ ሲሆን ሆስፒታሉ ታካሚዎችን እያስተናገደ ያለው ቁሳቁስ ስላለው ሳይሆን ባለሞያዎች ባላቸው ሞያ ብቻ አገልግሎት መስጠት ስላለባቸው መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ ዶ/ር ሃይማኖት ገለፃ በሆስፒታሉ በወር በአማካይ 800 እናቶች በሆስፒታሉ ሲወልዱ እንደነበር አስታውሰው አገልግሎት በመቋረጡ በርካቶች ለጉዳት መዳረጋቸውን ገልፀዋል።
ደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአማራ ክልል ምስራቅ አማራ፣ አፋር ክልል እንዲሁም የትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በአጠቃላይ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይገለገሉበት እንደነበር የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ለሬድዮ ጣብያው በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

#MoH
የጤና ተቋማት ወደነበሩበት ለመመለስ ርብርብር እየተደረገ ነው።
በግጭት ምክንያት የወደሙና የተጎዱ ጤና ተቋማትን ወደነበሩበት ለመመለስ እና የጤና አገልግሎት ለማስጀመር የአዲስ አበባ ጤና ቢሮና የፌዴራል ሆስፒታሎችን ከወደሙ ሆስፒታሎች ጋር በማስተሳሰር ድጋፍ እንዲያደርጉ ሰፊ ስራ መጀመሩን ከጤና ሚኒስቴር ተሰምቷል።
በቀጣይ ሌሎች ክልሎች እና ዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎችን በማስተባበር የድጋፍ ስራው በስፋት እንዲቀጥል ይደረጋል ተብሏል።
በአሁኑ ሰዓት:-
• ቅዱስ ጳውሎስ ሚሌንየም ሜዲካል ኮሌጅ 👉 ደሴ ሆስፒታልን፤
• ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 👉 ከልዋን ሆስፒታልና ቦሩ ሜዳ ሆስፒታልን፤
• አቤት ሆስፒታል 👉 ባቲ ሆስፒታልን፤
• የካቲት 12 ሆስፒታል 👉 ወረ ኢሉ ሆስፒታን፤
• ምኒሊክ ሆስፒታል 👉 መሃል ሜዳ ሆስፒታልን፤
• ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል 👉 ከሚሴ ሆስፒታልን፤
• ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል 👉 ሀይቅ ሆስፒታልን፤
• ራስ ደስታ ሆስፒታል 👉 ደብረ ሲና ሆስፒታልን፤
• አለርት ሆስፒታል 👉 ኮምቦልቻ ሆስፒታልን፤
• ዘውዲቱ ሆስፒታል 👉 ደጎሎ ሆስፒታልን፤
• ጋንዲ ሆስፒታል 👉 ሞላሌ ሆስፒታልን፤
• አማኑኤል ሆስፒታል የአእምሮ ጤናና የስነልቦና ማህበራዊ አገልግሎት ድጋፍ 👉 ለሁሉም ሆስፒታሎች ድጋፍ ለመስጠት ትስስር በመፍጠር ወደ ስራ ገብተዋል።
ጤና ሚኒስቴር የአዲስ አበባ እና ፌዴራል ሆስፒታሎች እያደረጉ ስላሉት ርብርብ ምስጋና አቅርቧል።
ሆስፒታሎቹ በአፋጣኝ ስራ ለማስጀመር ከክልሉ እና ከጤና ሚንስቴር ጋር እየሰሩ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ ወደነበሩበት ለመመለስ አሁንም ከፍተኛ መዋለ ነዋይና ድጋፍ ስለሚያስፈልግ ሁሉም የሚመለከተው አካል ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

" ለ11 ቀናት መሳቅ አይቻልም ፤ ወደ መጠጥ ቤት መሄድ እና መጠጥ መጠጣትም አይቻልም " - ሰሜን ኮሪያ
የቀድሞውን የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኢልን 10ኛ የሙት ዓመት በማስመልከት በሀገሪቱ ለ11 ቀናት መሳቅ ተከለከለ፡፡
ኪም ጆንግ ኢል ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በአውሮፓውያኑ 2011 ሲሆን ዘንድሮ 10 ዓመት ሞልቷቸዋል፡፡
የቀድሞውን መሪ 10ኛ የሙት ዓመት አስመልክቶም በሀገሪቱ መሳቅና መጠጥ መጠጣት መከልከሉን ዴይሊ ሜል ዘግቧል፡፡
ከዛሬ ጀምሮ ሰሜን ኮሪያውያን ወደ ግሮሰሪ መሄድ እንደማይችሉ የተነገራቸውም ሲሆን በመታሰቢያ የዚህ የሀዘን ቀናቱ ውስጥ ቤተሰቡ የሞተበት ሰው ጮክ ብሎ ማልቀስ እንደማይችል ሰሜን ኮሪያ አስጠንቅቃለች፡፡
የልደት በዓላቸው በ11ዱ የሀዘን ቀናት ውስጥ የሆነባቸው ግለሰቦች ይህንን ማድረግ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል።
ዛሬ አርብ ከደቂቃዎች በፊት በፒዮንግያንግ የነበረው የቢዝነስና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ለ5 ያል ደቂቃዎች ቆሞ የኢል 10ኛ ሙት ዓመት የመታሰቢያ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።
በ69 ዓመታቸው በፈረንጆቹ ታህሳስ 17 ቀን 2011 በልብ ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የሰሜን ኮሪያ መሪ ሀገራቸውን ለ17 ዓመታት መርተዋል።
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ / ዴይሊ ሜይል

Turkey 🤝 Africa " ለጋራ እድገት እና ብልጽግና የጎለበተ ወዳጅነት " 3ኛው የቱርክ - አፍሪካ ትብብር ጉባኤ ነገ በቱርክ ኢስታንቡል ይጀመራል። ለዚሁ ጉባኤ የተለያዩ ሀገራት ባለስልጣናት ቱርክ እየገቡ ይገኛሉ። በዚህ ጉባኤ የ39 ሃገራት ሚንስትሮች እና 13 ፕሬዚዳንቶች ለመሳተፍ ከወዲሁ ማረጋገጫ ልከዋል። " ለጋራ እድገት እና ብልጽግና የጎለበተ ወዳጅነት " በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው…
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ቱርክ ገብተዋል።
ጠ/ ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በሦስተኛው የቱርክ አፍሪካ አጋርነት ጉባኤ ለመሳተፍ ቱርክ፣ ኢስታንቡል ገብተዋል።
#PMOEthiopia
@tikvahethiopia
ጠ/ ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በሦስተኛው የቱርክ አፍሪካ አጋርነት ጉባኤ ለመሳተፍ ቱርክ፣ ኢስታንቡል ገብተዋል።
#PMOEthiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ምን ይዟል ? ከትግራይ ክልል የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ጋር በተያያዘ ነገ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ይቀመጣል። ምክር ቤቱ በአውሮፓ ህብረት አማካኝነት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚመረምር ዓለም አቀፍ ባለሞያዎች ቡድን በኢትዮጵያ እንዲሰማራ የሚጠይቅ ረቀቂ የውሣኔ ሀሳብ…
#Update
የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ስብሰባውን በቀጥታ ለመከታተል ይህን ይጫኑ : https://media.un.org/en/asset/k11/k119r483hu
@tikvahethiopia
የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ስብሰባውን በቀጥታ ለመከታተል ይህን ይጫኑ : https://media.un.org/en/asset/k11/k119r483hu
@tikvahethiopia
#TechZone
ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ? 0929088890
ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!
ሙሉ ከወገብ በላይ(ቦዲ) - 899ብር
የቦርጭ ብቻ -599 ብር
ሙሉ በሙሉ ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚያጠፋ እና
ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ መዳሃንያለም
ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ? 0929088890
ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!
ሙሉ ከወገብ በላይ(ቦዲ) - 899ብር
የቦርጭ ብቻ -599 ብር
ሙሉ በሙሉ ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚያጠፋ እና
ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ መዳሃንያለም
" የሚመጡ እንግዶችን ደህንነት ለመጠበቅ ዝግጅት ተጠናቋል " - ፌዴራል ፖሊስ
በ "አንድ ሚሊዮን ዳያስፖራ ወደ ሀገር ቤት " ጥሪ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ እንግዶችንን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል አስፈላጊው ሁሉ ዝግጅት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
ፌዴራል ፖሊስ በአዲስ አበባ ከተማ ሆነ በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች የሚመጡ እንግዶችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ዝግጅት አስቀድሞ ማድረጉን ገልጿል።
የጸጥታና ደህንነት ተግባሩን የኮማንድ ፖስቱ የጸጥታ መዋቅር ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የሚያከናውን ሲሆን ጥምር የጸጥታ ሃይሎች አስቀድሞ የጸጥታ ስጋት የሆኑ ነገሮችን በመለየት እንግዶቹ በሚንቀሳቀሱበት ስፍራ ምንም አይነት ችግር እንዳይገጥማቸው በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ፖሊስ አሳውቋል።
እንግዶቹ ለሚያጋጥማቸው ማንኛውንም ነገር መረጃ ለመስጠትና አስቀድሞ መረጃ ለማግኘት የሚችሉባቸውን አድራሻዎች ከፌደራል ፖሊስና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ማህበራዊ ገጾች ማግኘት ይችላሉ።
እንግዶች በስፋት ወደ ሀገር ሲገቡ ደግሞ አድራሻዎቹን የማሳወቅ ስራ እንደሚሰራ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል።

ሀይቅ፣ ቢስቲማና ለሚ ከተሞች ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።

Turkey 🤝 Africa
የቱርኩ ፕሬዜዳንት ሪሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እና የሱማሊያው ፕሬዜዳንት ሞሀመድ አብድላሂ ፈርማጆ ወይይት አካሄዱ።
3ኛው የቱርክ-አፍሪካ ትብብር ጉባኤ በኢስታንቡል እየተካሄደ ይገኛል።
ከጉባኤው ጎን ለጎን የቱርክ እና የሱማሊያ መሪዎች ተገነኝተው ውይይት እንዳደረጉ ተሰምቷል፤ የውይይቱን ይዘት በተመለከተ የተባለ ነገር የለም።