TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WFP

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ያቋረጠውን ድጋፍ ከቀናት በኃላ እንደሚጀመር አሳውቋል።

ድርጅቱ በአማራ ክልል የነፍስ አድን ምግብ እርዳታ ማድረግ መቀጠሉን ገልጿል።

በሰ/ጎንደር 470,000 ሰዎች በደሴ/ኮምቦልቻ 172,000 ሰዎች በJEOP በኩል መድረሱን አሳውቋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፤ በዘረፋ እና በደህንነት ማጣት ምክንያት ባለፈው ሳምንት አቋርጦት የነበረውን ድጋፍ በሚቀጥሉት ቀናት ለመቀጠል ተስፋ እንደሚያድረግ ገልጿል።

@tikvahethiopia
" ከደቡብ ሱዳን በኩል የሚመጣ ኢትዮጵያን ለመጉዳት ያለመ እንቅስቃሴ አሁንም ሆነ ወደፊት አይኖርም " - ዶ/ር ሪያክ ማቻር

በደቡብ ሱዳን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደር ነቢል መህዲ ከደቡብ የሱዳንን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሪያክ ማቻር ጋር በሁለቱ ሀገራት በጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ዶ/ር ሪያክ ማቻር በኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን እና መካከል ያለውን ዘመን ተሻጋሪ ታሪካዊ ግንኙነት አውስተው የደ/ሱዳን ህዝብ በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ የኢትዮጵያ መንግስታት ለሰጡት ያልተቋረጠ ድጋፍ ምስጋናው ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለው ለኢትዮጵያ ሰላም መስፈን ሀገራቸው ቁርጠኛ አቋም እንዳላት ጠቁመው፣ ከደቡብ ሱዳን በኩል የሚመጣ ኢትዮጵያን ለመጉዳት ያለመ እንቅስቃሴ አሁንም ሆነ ወደፊት እንደማኖር ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።

አምባሳደር ነቢል መህዲ በበኩላቸው ፥ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ በተለይ የህወሃት ወራሪ ሀይል በደረሰበት ምት ከያዛቸው ቦታዎች እየወጣ እንደሆነ ፤ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ለማድረስ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲሁም የህወሃት ወራሪ ሀይል ይዟቸው በነበሩ ቦታዎች የፈጸማቸውን አሰቃቂ ጭፍጨፋን በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል።

አንዳንድ የምዕራባውያን የመገናኛ ብዙሃን ሀሰተኛ ዘገባዎች በማሰራጨት የአገሪቱ እና የአመራሩን ገጽታ ለማጠልሸት የጀመሩትን ስራ እየገፉበት እንደሆነ አምባሳደር ነቢል ማብራራታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#Update

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በኮቪድ-19 ሳቢያ የሰው ሞት አልተመዘገበም።

ከተደረገው 3,452 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 115 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow " አዲስ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ትውልድ " ሴንተር ፎር አድቫንስመንት ኦፍ ራይትስ ኤንድ ዴሞክራሲ (ካርድ) “የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አዲስ ትውልድ’’ በሚል ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል። ዛሬ የሚመረቁት 364 የሚሆኑ የመንግሥትና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መሠረታዊ የሰብዓዊ መብት ፅንሰ ሐሳቦችን፣ የሥርዓተ ፆታ እኩልነት፣ ሐሳብን በነጻነት…
ፎቶ : ዛሬ ሴንተር ፎር አድቫንስመንት ኦፍ ራይትስ ኤንድ ዴሞክራሲ (ካርድ) “የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አዲስ ትውልድ’’ በሚል ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱኳን ሚዴቅሳ እንዲሁም የህግ አማካሪ እና ጠበቃ አመሃ መኮንን ተገኝተው ለተመራቂዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
የ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የብሄራዊ ህክምና ስፔሻሊቲ መግቢያ ፈተና ነገ ይሰጣል።

ነገ ሰኞ ታህሳስ 4/2014 ዓ/ም የህክምና ስፔሻሊቲ መግቢያ ፈተና የሚሰጥ ሲሆን ፈተናው በአማራ ክልልም የሚሰጥ ይሆናል።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ለኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ፅፎ በነበረው ደብዳቤ አሸባሪው ህወሓት ወረራ በፈፀመት ወቅት በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ ፈተናውን ለመፈተን ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ጠቅላላ ሀኪሞች ላይ ጫና በመፈጠሩ መግቢያ ፈተናው ለመፈተን ስለሚቸገሩ እንዲራዘም ወይም ሌላ የተለየ አማራጭ እንዲፈለግላቸው ጠይቆ ነበር።

ጤና ሚኒስቴር በደብዳቤ በሰጠው ምላሽ የመግቢያ ፈተናው ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀው የፈተና አስተባባሪዎች በአስራ ስምንቱ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተሰማርተው ፈተናውን ለመስጠት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን በመገለፅ ፈተናውን ለማራዘም እንደሚቸገር አሳውቋል።

በዚህም የነገው ፈተና በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ በአማራ ክልል ጨምሮ የሚሰጥ ይሆናል።

ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እና ለፀጥታ ኃይል አባላት በክልሉ ውስጥ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ምክንያት በወጣው መርሃግብር የመግቢያ ፈተናውን መፈተን የማይችሉ ሀኪሞች ካሉ ጤና ሚኒስቴር በሚደርሰው ማረጋገጫ አማካኝነት ሌላ ፈተና አዘጋጅቶ እንደሚያስፈትን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
የአሜሪካ መግለጫ ...

ትላንት ለሊት ላይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ በቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ አማካኝነት አንድ መግለጫ አውጥቶ ነበር።

ይኸው መግለጫ በአማራ እና አፋር ክልሎች በትግራይ ኃይሎች ተፈጽመዋል የተባሉ " ያልተረጋገጡ " የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና የንብረት ውድመቶች እጅግ አሳሳቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ነው።

አሜሪካ በአማራ እና አፋር ክልሎች በትግራይ ኃይሎች ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን፣ አስደንጋጭ የጭካኔ ድርጊቶችንና በሕዝብ መሠረተ ልማቶች ላይ የተፈጸሙ ውድመቶችን በተመለከተ እየወጡ ያሉ " ያልተረጋገጡ " ሪፖርቶች ያሳስበኛል ብላለች።

በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በሙሉ በንጹሃን ዜጎች ላይ የኃይል እርምጃዎችን ከመወሰድ መቆጠብ አለባቸውም ይላል መግለጫው።

ቃል አቀባዩ ፕራይስ ፥ " የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት እነዚህን ሪፖርቶችን በመመርመር ትክክለኛነታቸውን እንዲያጣሩ እና ጥፋተኛ የሆኑትን ተጠያቂ ለማድረግ ሁሉን አካታች እና ግልጽ ሥርዓት እንዲከተሉ እንጠይቃለን" ብለዋል።

አሜሪካ ፥ ይህ ጦርነት እንዲቋጭ የመጀመሪያው፣ የመጨረሻው እና ብቸኛው አማራጭ የዲሎማሲያዊ መንገድ ብቻ ነው ለዚህ ደግሞ በድጋሚ ድጋፋችንን እንገልፃለን ብላለች።

ከዚህ በተጨማሪ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ እንዲያበቃ ፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ድርድር እንዲጀመር፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት እንዲኖር እና ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት እንዲጀመር ጥሪ አቅርባለች።

* መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#AmharaRegion

እስካሁን ከህወሓት ነፃ ስለሆኑ አካባቢዎች በኢትዮጵያ ፌዴራሉ መንግስት ፣ በአማራ ክልል መንግስት እና በየአካባቢው አስተዳደሮች እንዲሁም በተቋማት ደረጃ ሪፖርት የተደረጉ፦

- በተለያዩ አካባቢዎች የጅምላ ግድያዎች ተፈፅመዋል ለአብነት ሰሜን ሸዋ አንፆቂያ ፣ ጋሸና፣ ኮምቦልቻ፣ ውጫሌ አካባቢዎች በዋናነት ይጠቀሳሉ።

- ከፍተኛ የሆነ ሲቪሎች ላይ ያነጣጠረ የንብረት ዘረፋ ተፈፅሟል። ለአብነት ሆቴሎች ፣ የንግድ ቦታዎች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።

- የላሊበላ ኤርፖርት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።

- የደሴ ሆስፒታልን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የጤና ተቋማት ተዘርፈዋል፤ ወድመትም ደርሶባቸዋል። ለአብነት ዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ ውድመት ደርሶበታል። ሌላ በደ/ወሎ ብቻ 103 ጤና ጣቢያዎች እና 9 ሆስፒታሎች ዝርፊያ እና ውድመት ደርሶባቸዋል።

- ከ4 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እና በከፊል ወድመዋል፤ የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም 11 ቢሊዮን ብር እንደሚጠይቅ ተገልጿል።

- የኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ዘረፋ እንዲሁም ውድመት ደርሶበታል። ለአብነት ከ251 በላይ የደንበኛ ንብረት የያዙ ኮንቴነሮች ተዘርፈዋል።

- የሚዲያ ተቋማት የጥቃት ሰለባ ከሆኑት መካከል ናቸው ለአብነት የአማራ ኤፍ ኤም ደሴ 87.9 ውድመት ደርሶበታል።

- በርካታ የመንግስት የሆኑ ተቋማት ፣ ተሽከርካሪዎች ፣ የተከማቹ የህብረተሰቡ መረጃዎች ላይ ውድመት ደርሷል። በተጨማሪ ባንኮች ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ለአብነት ዳሸን፣ አቢሲኒያ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ አማራ ብድርና ቁጠባ ውድመት ከደረሰባቸው መካከል ይጠቀሳሉ።

NB : ከላይ የቀረቡት ሪፖርት ከተደረጉት ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው።

@tikvahethiopia
#Update

ተንታ፣ ማሻና ወግዲ ከተሞች ትላንትና እና ዛሬ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት መካነሰላምና ከላላ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዳገኙ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#ATTENTION

" ዝናብ ሊዘንብ ባለመቻሉ ድርቁ ለ4 ወራት ሊራዘም ይችላል " - አቶ ቦሩ ጃርሶ

ቦረና ዞን ውስጥ የተከሰተው ድርቅ ለ4 ወራት ሊራዘም ስለሚችል ለእንስሳት ሀብቱ የማይቋረጥ ድጋፍና ክትትል እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

በዞኑ እስካሁን ድረስ ዝናብ እንዳልዘነበ ተነግሯል።

የቦረና ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቦሩ ጃርሶ የድርቁን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ በዞኑ የተከሰተው ድርቅ እስካሁን ድረስ በአካባቢው ዝናብ ሊዘንብ ባለመቻሉ ድርቁ ለአራት ወራት ሊራዘም ይችላል ብለዋል።

መንግሥትና ዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች እያደረጉት ባለው ድጋፍ የሰው ሕይወት ማዳን ቢቻልም ድርቁ በተለይ የእንስሳት መኖና ውሃ እጥረት በማስከተሉ በእንስሳት ላይ አደጋ ጋርጧል ሲሉ ተናግረዋል።

ድርቁ በዞኑ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ 84 ሺ እንስሳት መሞታቸውን፣ 100 ሺ የሚሆኑ እንስሳት በአሳሳቢ ደረጃ እንደሚገኙ አሳውቀዋል።

በቦረና ዞን ውስጥ የሚገኙት የእንስሳት ዝርያዎች የአገር ሀብት እንደመሆናቸው መጠን የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥታት አሁንም ትልቅ ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

አቶ ቦሩ ጃርሶ ማኅበረሰቡ በአካባቢው ያለውን የዝናብ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ዝናብ ሳይዘንብ ለ4 ወራት ሊቆይ እንደሚችል እየተናገሩ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የቦረና እንስሳት ዝርያ በድርቁ ምክንያት የከፋ ጉዳት እንዳይደርስባቸው በአንድ ማዕከል ተለይተው ድርቁን የሚሻገሩበት ሁኔታ የሚፈጠርበት ሁኔታ እንዲመቻች መጠየቃቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

@tikvahethiopia