#WFP
በትላንትናው ዕለት የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በትላንትናው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው ላይ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በደሴ እና በኮምቦልቻ ከተሞች የነበሩት መጋዘኖቹ በህወሓት ኃይሎች በመዘረፋቸው የምግብ እርዳታ ማቋረጡን አስታውቋል።
ቃል አቀባዩ ፥ የእርዳታ ምግብ ተከማችተውባቸው የነበሩት መጋዘኖቹ በህወሓት ኃይል በተዘረፉበት ወቅት በስፍራው በነበሩ ሠራተኞቹ መሳሪያ ተደግኖባቸው እንደነበረ አመልክተዋል።
በመጋዘኖቹ ላይ በህወሓት በተፈጸመው ዝርፊያ በምግብ እጥረት ለተጎዱ ህጻናት የሚቀርቡ አልሚ ምግቦችን ጨምሮ ከፍተኛ መጠን ያለው የምግብ አቅርቦት ክምችት ከሁለቱ ከተሞች ተወስደውበታል።
በስፍራዎቹ የነበሩ ሠራተኞቹም በጦር መሳሪያ ጭምር ጫናና ማስፈራሪያ ስለተደረሰባቸው ይህንን ዝርፊያ ለመከላከል ሳይችሉ መቅረታቸው ተገልጿል።
ይህ ዝርፊያ በአሁኑ ወቅት ከ9 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በምግብ እርዳታ ላይ ጥገኛ በሆነበት በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የምግብ ዋስትና ችግርና የተመጣጠነ ምግብ እጦትን የበለጠ እንደሚያባብሰው ድርጅቱ ተናግሯል።
በሌላ በኩል በአማራ ክልል ለሰብአዊ አገልግሎት የሚውሉ ሶስት የWFP መኪኖች በዚህ ሳምንት በወታደሮች ታዝዘው ለራሳቸው ዓላማ መዋላቸውን ዱጃሪች ተናግረው ድርጊቱን አውግዘዋል ሁሉም አካላት የሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎችን እንዲያከብሩና እንዲጠብቁ ጠይቀዋል።
ለአንድ ወር ያህል በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር የቆዩት የደሴና የኮምቦልቻ ከተሞች በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተመራው የኢትዮጵያ ጥምር የፀጥታ ኃይሎች በዚህ ሳምንት ነፃ መውጣታቸው ይታወቃል።
@tikvahethiopia

December 9, 2021
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በዛሬው ዕለት ለተሰወኑ ጊዜያት ከጦር ግንባር ወደ ቢሮ መመለሳቸውን ያሳወቁት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከጎረቤት ሀገራት መሪዎች ጋር የስልክ ውይይት አደርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፥ " ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ቅድሚያ ሰጥታ እየሠራች ነው። "ሲሉ ገልፀዋል። ዶ/ር ዐቢይ ፥ " ዛሬ ከጅቡቲ ፣ ከኬንያ ፣…
#Update
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከተመድ ዋና ፀሀፊ ፣ ከአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር እና ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዜዳንት ጋር ተወያዩ።
ዶ/ር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ " ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ሆነ የአፍሪካ ህብረት መስራች አባል እንደ መሆኗ መጠን፣ የሀገራዊ ሉዓላዊነት ክብርን መሰረት ያደረገ የባለብዙ ወገን ግንኙነት አራማጅ ነች " ብለዋል።
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይም ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ ከአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት እና የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚሼል ጋር ውጤታማ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከተመድ ዋና ፀሀፊ ፣ ከአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር እና ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዜዳንት ጋር ተወያዩ።
ዶ/ር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ " ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ሆነ የአፍሪካ ህብረት መስራች አባል እንደ መሆኗ መጠን፣ የሀገራዊ ሉዓላዊነት ክብርን መሰረት ያደረገ የባለብዙ ወገን ግንኙነት አራማጅ ነች " ብለዋል።
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይም ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ ከአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት እና የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚሼል ጋር ውጤታማ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።
@tikvahethiopia
December 9, 2021
TIKVAH-ETHIOPIA
ፌልትማን ምን አሉ ? " የአሜሪካ ፍላጎት ለ27 ዓመት በስልጣን ላይ የነበረውን ህወሓት መራሽ ኢህአዴግን ወደ ስልጣን መመለስ አይደለም " - አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ከትናንት በስቲያ ከአ/አ ወደ ሀገራቸው አሜሪካ የሄዱት በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ስለቆይታቸው ከብዙሃን መገናኛዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል። አምባሳደሩ በዚህ ጊዜ እንዳሉት…
የፌልትማን የግብፅ፣ ቱርክ እና የUAE ጉዞ ፦
የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ፣ ቱርክ እና ግብፅ እንደሚያማሩ ተሰምቷል።
የጉዟቸው ዓላማ ደግሞ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመምከር ነው።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤህ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራስ በሰጡት መግለጫ ፌልትማን ወደ ሦስቱ አገራት ጉዟቸውን የሚያደርጉት ከዛሬ ሐሙስ ህዳር 30/2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደሆነ አሳውቀዋል።
ፕራይስ ፥ " በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደህንነት ስጋት እንደሆነ እናውቃለን፤ አምባሳደር ፌልትማን ወደ አገራቱ ተጉዘው ከአጋሮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ " ብለዋል።
ቃል አቀባዩ ፥ የአሜሪካ መንግሥት ለዚህ ግጭት ወታደራዊ እርምጃ መፍትሄው አይሆንም ብሎ እንደሚያምን አስታውሰው " የፌልትማን ተልዕኮ ግጭቱን ለማስቆም ዲፕሎማሲን የመጀመሪያው፤ የመጨረሻው እና ብቸኛው አማራጭ በማድረግ ተዋጊ ኃይሎች ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁመው ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ ማስቻል ነው " ማለታቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።
ፌልትማን ለሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት መፍትሄ ለማፈላለግ ከሳምንታት በፊት ኢትዮጵያ መጥተው እንደነበር ይታወሳል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Video : የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ትላንት ለስራ ጉብኝት በሄዱበት ካንሳስ ከተማ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የቀድሞ ፕሬዜዳንት ትራምፕ ደጋፊዎች ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።
የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የሚያካሂደውን እንቅስቃሴ አጥብቀው ተቃውመዋል።
ተቃዋሚዎቹ ፥ " የጆ ባይድን አስተዳደር ሽብርተኛውን የህወሃት ቡድን የመደገፍ እንቅስቃሴውን ሊያቆም ይገባል፣ የኢትዮጵያን ዴሞክራሲ ለማጥፋት የሚያካሄደው ጣልቃ ገብነትም ሊቆም ይገባል #NoMore” ብለዋል።
በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ፣ ገለልተኛና ነጻ መንግስት አለን ጣልቃ ገብነቱ እንዲቆም እናሳስባለን ሲሉም የሰልፉ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
የትራምፕ ባንዲራ የያዙ ወደ ደርዘን የሚጠጉ ሰዎችም ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን ፤ በፕሬዚዳንት ባይደን በደቡብ ድንበር አያያዝ፣ አሜሪካ ከአፍጋኒስታን መውጣት እና በ COVID-19 የደህንነት ጥንቃቄዎች ጉዳይ ተቃውሞ አሰምተዋል።
Video Credit : KMBC

#Update የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከተመድ ዋና ፀሀፊ ፣ ከአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር እና ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዜዳንት ጋር ተወያዩ። ዶ/ር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ " ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ሆነ የአፍሪካ ህብረት መስራች አባል እንደ መሆኗ መጠን፣ የሀገራዊ ሉዓላዊነት ክብርን መሰረት ያደረገ የባለብዙ ወገን ግንኙነት አራማጅ ነች " ብለዋል።…
#Update
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከሴኔጋል ፣ ደ/አፍሪካ እና ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ መሪዎች ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ።
ዶ/ር ዐቢይ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ከሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል፣ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ እና ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሼኬዲ ጋር ገንቢ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አሳውቀዋል።
የሁለትዮሽና አህጉራዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እንሰራለን ሲሉም ገልፀዋል።

#WeCare
በተለያዩ የህክምና ዘርፍ ስፔሻሊስት የሆኑ ዶክተሮችን ኦንላይን በቪድዮ፣ በድምጽ አልያም በ አጭር መልእክት ማግኘት የሚያስችል አዲስ አገልግሎት ተጀመረ።
ለራስዎ ፣ ለልጅዎ ወይም ለቤተሰቦ የሚሰማዎትን ህመም ወይም አጠራጣሪ ነገር በ WeCare መተግበሪያ በሙያው የተካኑ ሐኪሞችን በፍጥነት በማማከር እፎይታ ያግኙ።
መተግበሪያውን ለማውረድ👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient
አጠቃቀሙን ለመረዳት ቻናሉን @wecareet ይቀላቀሉ
ለበለጠ መረጃ : 9394 በመደወል ማብራሪያ ይጠይቁ!

#OCHA
በተመድ የሠብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኦቻ) ፥ በደቡብ ኦሮሚያ ቦረና ዞን የተከሰተው ድርቅና የደህንነት ችግር በአስፈላጊ የጤና አገልግሎት ቀጣይነት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን ገልጿል።
የትምህርት ማቋረጥ እየጨመረ ፣ የሰብል ምርት ኪሳራ እየታየ ፣ የዋጋ ጭማሪ እና የውሃ እጦት ችግር መቀጠሉ ሪፖርት እየተደረገ ነው ብሏል።
ኦቻ ለቦረና ድርቅ ምላሽ ለመስጠት የሰብአዊ ድጋፍ ቅንጅት እና ግብአት የማሰባሰብ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲል አስገንዝቧል።
የሰብዓዊ ድጋፍ አጋሮች ውስን የሆነ ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ ፤ ነገር ግን የፋይናንስ እና የሰው ኃይል አቅም እጦት ፈተና መሆኑን ኦቻ ገልጿል።

የዳዋ ዞን ነዋሪዎች ያሉበት ሁኔታ ፦ በሶማሊ ክልል ዳዋ ዞን (የቦረና አጎራባች) በተከሰተው ድርቅ የሞቱት የቁም እንስሳት 47,215 መድረሳቸውን ከአንድ ሪፖርት መመልከት ችለናል። ሪፖርቱ የተዘጋጀው ከጥቅምት 25 እስከ 29 ቀን 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ በተካሄደ ዳሰሳ ሲሆን ይህም የተመራው በዳዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ፣ በዳዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት፣ ከዞኑ የአደጋ ስጋት አስተዳደር እና…
#SomaliRegion
በሶማሊ ክልል በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች እገዛ እንዲደረግ ተጠየቀ።
የሶማሊ ክልል የሰላም እና አንድነት ምክር ቤት በክልሉ የተከሰተውን ድርቅ አሰመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫው ፦
1. የክልሉ ህዝብ በተፈጥሮ ድርቅ አደጋ ምክንያት ከቀያቸዉ የተፈናቀሉ ወንድሞቻቸዉን ባላቸዉ ነገር በማገዝና ከጎናቸዉ በመቆም።
2. የክልሉ ማህበረሰብ ባላቸዉ ነገር በድርቅ የተጎዱና አቅመ ደካማ የሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎችን በመረዳት።
3. ዲያስፖራው ማህበረሰብ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው የተፈጥሮ ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ የበኩላቸዉን ድርሻ እንዲወጡ።
4. ግብረሰናይ ድርጅቶች በድርቅ የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚደረገው ድጋፍ የበኩላቸዉን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
#SomaliRegionCommunication

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የደንበኞች ትምህርት ቡድን አባል አቶ ምትኩ አበባዉ ለኢትዮጵያ ቼክ ከተናገሩት ፦ - ደብዳቤዎቹ ከኛ ነዉ የወጡት፤ ትክክለኛ ናቸዉ። - የክልከላው ምክንያት ለንግድ ማይዉሉ የግል መገልገያ ዕቃዎችን ዝርዝር ለመወሰን የወጣዉን መመሪያ 51/2010ን በመጠቀም በተመላላሽ መንገደኞች ከቀረጥ ነጻ የሚገቡ ነገር ግን ለንግድ አላማ እየዋሉ የሚገኙ ዕቃዎች…
" የሰሞኑ የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ መመሪያ ለዳያስፖራው ከቀረበው ጥሪ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።
ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፥ " ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ያወጣውን መመሪያ በተመለከተ ከዳያስፖራው የሚቀርቡ ጥያቄዎች አሉ ፤ብዥታው የተፈጠረው መመሪያው የወጣበት ጊዜና ለዳያስፖራው የቀረበው ጥሪ በመገጣጠሙ ነው " ብለዋል።
ሚኒስትሩ መመሪያው ለዳያስፖራው ከቀረበው ጥሪ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም ሲሉ አሳውቀዋል።
መመሪያው የሚመለከተው ተመላላሽ ነጋዴዎችን ብቻ መሆኑን ሁሉም የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ሊገነዘብ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
በቀረበው ጥሪ መሠረት ለሀገሩ አጋርነቱን ለመግለጽ ዳያስፖራው ሲመጣ አሠራሩን ቀላል አድርጎ ለመጠበቅ ከተዘጋጁት ተቋማት አንዱ የጉምሩክ መሥሪያ ቤት መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ለገሰ ፥ " የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክም በቅርቡ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ይሰጥበታል " ብለዋል።
በዛሬው መግለጫ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦችን በዚህ ያንብቡ : https://telegra.ph/FDRE-Government-Communication-12-09

እስከ ከሜሴ ያለው መስመር ጥገና ተጠናቋል።
ከካራቆሬ - ከሜሴ ያለው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮቹንና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ከሥርጭት ኔትወርክ መስመሮች ጋር እንዲገናኙ ለማድረግ በርብርብ ሲሰራ ቆይቶ ዛሬ እስከ ከሚሴ ድረስ ያሉት ከተሞች ኃይል ማግኘት ችለዋል፡፡
ከደብረብርሃን ኮምቦልቻ ድረስ ያሉት ከተሞች በ132 እና በ230 ኪሎ ቮልት መስመሮች ኃይል ያገኙ የነበረ ቢሆንም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ይሁንና የኃይል ተጠቃሚው ህብረተሰብ በፍጥነት ኃይል እንዲያገኝ ለማድረግ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመር ለጊዜው በማቆየትና ባለ 132 ኪሎ ቮልት መስመሩን በአስቸኳይ በመጠገን ዛሬ እስከ ከሚሴ ድረስ ያሉት ከተሞች ኃይል አግኝተዋል።
የጥገና ሥራው ወደ ደሴ ከተማ ቀጥሎ እስከ ሀርቡ ባለው አካባቢ መስመሮችን የመጠገን ሥራም እየተካሄደ ነው።
አሁን አስቸኳይ ጥገና እየተደረገለት ያለው 132 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የከሚሴ፣ ኮምቦልቻ እና ደሴ እንዲሁም ዓለም ከተማና በምዕራብ አፋር የሚገኙ ከተሞችን ኃይል እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው፡፡
በተያያዘ ዜና በሚሌ ባቲ ያለው መስመር ላይ 2 ኃይል ተሸካሚ ምሶሶዎች በከባድ መሳሪያ በመመታቸውና ጉዳቱ ከባድ በመሆኑ ምሶሶዎቹን እንደገና የመትከል ስራ ተጀምሯል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

#BREAKING ብሔራዊ ባንክ የብድር ክልከላውን ሙሉ በሙሉ አነሳ። ለባለፉት አራት ወራት ተግባራዊ የነበረው የብድር ክልከላ ሙሉ በሙሉ መነሳቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ አስታወቀ። ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ብድር አገልግሎት ለሁሉም ደንበኞቻቸው እንዲሰጡ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ክልከላው የተጣለው "የኢኮኖሚ አሻጥርን" ለመከላከል እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ተግባራዊ ተድርጎ…
" ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር እሰጣለሁ " - ንግድ ባንክ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተያዘው በጀት ዓመት ለግሉ ዘርፍ፣ ለግብርና ግብዓትና ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለመስጠት መዘጋጀቱን አሳውቋል።
ከዚሁ ገንዘብ ውስጥ 25 ቢሊዮን ብር ለግሉ ዘርፍ፣ 30 ቢሊዮን ብር ለግብርና ግብዓት ሲሆን ቀሪው ለመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚውል ነው።
ገንዘቡ ኢኮኖሚውን በከፍተኛ ሁኔታ ያነቃቃል፤ ለስራ ፈጠራ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል።
መንግስት አስቀምጦት የነበረው የብድር ክልከላ መነሳት የአገሪቷን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው ተነግሯል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በደብረ ብርሃን ከተማ ተቋርጦ የነበረው የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ እና ታክሲ የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ከነገ ታህሳስ 01/2014 ዓ.ም እንዲጀምር ኮማንድ ፖስቱ ወስኗል።
ምንጭ፦ የሰሜን ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን

ከታህሳስ 2 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አፋር ክልል መዲና ሰመራ እለታዊ የበረራ አገልግሎት እንደሚኖረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

ወደሀገር ቤት ለምትመጡ፦
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንግዶቹን ለመቀበል የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል አሳውቀዋል።
በዚሁ መሰረት፦
• የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ የታደሰ ሆነ የአገልግሎት ግዜው ያለፈበት፣በልዩ ሁኔታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ያለ ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ መግባት ትችላላችሁ፤ የታደሰም ሆነ ግዜው ያለፈበትን መታወቂያ ኤርፖርት በኢሚግሬሽን ካውንተር ላይ ስለምትጠየቁ በእጅዎ መያዞትን አይዘንጉ።
• የሌላ አገር ፓስፖርት የያዛችሁና የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ አገልግሎት ለማግኘት የምትፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና በውጭ አገር የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን የፓስፖርት እድሳት አገልግሎት ከፈለጋችሁ አስፈላጊ ሰነዶችን በማዘጋጀት www.digitalinvea.com/ ድህረ ገጽ ላይ ማመልከት የምትችሉ ሲሆን ተቋሙ በተለየ መልኩ ከ15 ቀን ባልበለጠ ግዜ ውስጥ እናንተ በሞላችሁት አድራሻ ድረስ በመላክ አገልግሎት ይሰጣል።
• ከዚህ በፊት የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ያሌላችሁ ደንበኞች የቪዛ አገልግሎት ለማግኘት በ www.evisa.gov.et ድህረ ገጽ ላይ ማመልከት የምትችሉ ሲሆን፣በሂደቱ ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግሮች support@evisa.gov.et በሚል የኢሜል አድራሻችን ላይ ጥያቄ ማቅረብ ትችላላችሁ።
• ጥሪ በተደረገበት የጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ ሀገር ቤት ለምትገቡ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የመዳረሻ ቪዛ/on arrival visa/ አገልግሎት የምንሰጥ ሲሆን፣ ኤርፖርት ላይ የሚቆዩትን ግዜና ድካም ለመቀነስ በኦንላይን ላይ ቀድሞ ቢያመለክቱ ይበረታታል።