TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ መንግስት / የጥምር የፀጥታ ኃይሉ / ከህወሓት ነፃ በማድረግ መቆጣጡሩን የገለፃቸው አካባቢዎች ዝርዝር ፦

- ጋሸና
- ላሊበላ
- አርቢት
- አቀት
- ዳቦ
- ጃማ ደጎሎ
- ወረኢሉ
- ገነቴ
- ፍንጮፍቱ
- አቀስታ
- መዘዞ
- ሞላሌ
- ሸዋሮቢት
- ራሳና
- ለምለም አምባ
- ጀውሐ
- ሰንበቴ
- አጣየ
- ካራ ቆሬ
- ኮን
- ዳውንት
- ልጓማ
- መሐል ሜዳ
- ጨፋ ሮቢት
- ሐርቡ
- መኮይ
- ቀውዝባ
- ጭላ
- አጅባር
- ተንታ
- ዶባ
- ማጀቴ
- ጭረቲ
- ከሚሴ
- ርቄ
- ወለዲ
- አልቡኮ
- የቃሉ ወረዳ አብዛኛውን ክፍል መቆጣጠሩን አሳውቋል።

የኢትዮጵያ መንግስት /ጥምር የፀጥታ ኃይሉ / ተቆጣጥሮ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች የመለሰባቸው፦
- ካሳጊታ
- ቡርቃ
- ዋኢማ
- ጭፍራ
- ጪፍቱ
- ድሬሮቃ
- አለሌ ሱሉላ ናቸው።

@tikvahethiopia
#Update

ከህወሓት ነፃ በሆኑ የሰሜን ሸዋ ዞን አካባቢዎች መደበኛ የመንግስት ስራ ከነገ ጀምሮ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል ላሊበላ፣ ጋሸና ፣ ዋድላ ፣ ላስታ ፣ ዳውንት እና ሌሎች በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ ወረዳዎች የህብረተሰቡን ህይወት ወደ ቀደመው ለመመለስ ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች መደበኛ ስራቸውን ጀምረዋል።

ፎቶ : ፎቶግራፈር አቤል ጋሻው

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ትምህርት ሚኒስቴር ፦ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት ይዘጋሉ። ዝግ የሚሆኑት ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ ነው። #ምክንያት ፦ መምህራን ፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች ለሀገራዊ ትግል እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ነው። ት/ቤቶች ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ቀናት ያልተሰበሰቡ የዘመች ሰብል መሰብሰብ እና ቤተሰብን የመርዳት…
#ትምህርት_ሚኒስቴር

በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከነገ ህዳር 27 ጀምሮ እስከ ታህሳስ 3 ድረስ ለአንድ ሳምንት ይዘጋሉ።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ መምህራን ፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች ለሀገራዊ ትግል እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አስተዋጽኦ ያድረጋሉ።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ቀናት ያልተሰበሰቡ የዘመች ሰብል መሰብሰብ እና ቤተሰብን የመርዳት ዘመቻዎች በስፋት ይካሄዳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በማይናማር ወታደሩ ስልጣን ተቆጣጠረ። በቀድሞ በርማ በአሁኗ ማያንማር ወታደሩ ሥልጣን መቆጣጠሩ ተሰምቷል። ወታደሮች ሥልጣን መቆጣጠራቸውን ይፋ ያደረጉት የሲቪል መንግሥት አባላትን በቁጥጥር ሥር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። የኖቤል ተሸላሚዋ ኦንግ ሳን ሱ ቺ እና ሌሎች የፖለቲካ መሪዎች ተለቅመው ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደዋል። በሚየንማር በወታደሩ እና በሲቪሊያን አስተዳደሩ መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ውጥረት…
#Update

ኦንግ ሳን ሱ ኪ የ4 ዓመት እስር ተፈረደባቸው።

ከስልጣናቸው በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የተነሱት የማይናማር መሪ ኦንግ ሳን ሱ ኪ የ4 ዓመት እስር ተፈረደባቸው።

የማይንማር ፍርድ ቤት ከስልጣን የተነሱት የሲቪል መሪ አውንግ ሳን ሱ ኪ በወታደራዊ ኃይሉ ላይ ተቃውሞ በማነሳሳት/ግጭት በመቀስቀስ እና የኮቪድ ህጎችን በመጣስ የ4 አመታት እስር ፈርዶባቸዋል።

የማይናማር ጁንታ ቃል አቀባይ ለኤኤፍፒ በሰጡት ቃል የቀድሞ የሀገሪቱ መሪ የኖቤል ሰላም ሽልማት ተሸላሚ ኦንግ ሳን ሱ ቺ በሁለቱ ክሶች የሁለት ሁለት አመት እስር ይቀጣሉ ብለዋል።

ኦንግ ሳን ሱ ኪ 11 ክሶች የቀረቡባቸው ሲሆን በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም ብለው ተከራክረዋል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዊን ሚይንትም በተመሳሳይ ክስ የ4 ዓመታት እስር እንደተፈረደባቸው የማይናማር ጁንታ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
ገቢዎች ሚኒስቴር ፦

ህገ-ወጥ ድርጅቶች ሲጠቀሙባቸው ከነበሩ ካሽሬጂስተር ማሽኖች ከ32 ቢሊዮን ብር በላይ ሀሰተኛ ግብይት መፈፀሙ በምርመራ ተረጋገጠ።

የገቢዎች ሚኒስቴር ሰሞኑ 63 ህገ-ጥ ድርጅቶች እና ለህገ-ወጥ ዓላማ ሲውሉ የነበሩ 20 የሽያጭ መመዘገቢያ መሳሪያዎች /የካሽሬጂስተር ማሽኖች/ መያዙን ሰሞኑን ይፋ አድርጎ ነበር።

በሽያጭ መመዝገቢያ ማሽኖች 32,527,510,503.5 ብር ዋጋ ያላቸው ሀሰተኛ ደረሰኞች ወይም ሀሰተኛ ግብይቶች እንደተሳራባቸው በማሽኖቹ ላይ በተደረገው ምርመራ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በተያያዘ ደረሰኝ የማይቆርጡ ድርጅቶች ላይ በተደረገ ክትትል 199 ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

በታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 አንቀፅ 108 ድንጋጌ መሠረት ብር 8,150,000 አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጣልባቸው ተወስኗል፡፡

ህብረተሰቡ ሀሰተኛ ደረሰኝ የሚያሰራጩና በግብይት ወቅት አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥመው በአቅራቢያው ወደ ሚገኝ የታክስ ማዕከልና የፀጥታ አካላት በማሳወቅ ትብብር እንዲያደርግ የገቢዎች ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
" መምህራን እና ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በማህበራዊ አገልግሎት ይሰማራሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር

በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት ዝግ ሆነው መምህራንና ተማሪዎች በተለያዩ ስራዎች ህዝባቸውን እንዲያግዙ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ ይታወሳል።

ይህንን ውሳኔ ተከትሎ መምህራን እና ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራ ይሰማራሉ።

ሰብል መሰብስብ፣ በግንባር ላሉ ለኢትዮጵያ ኃይሎች ድጋፍ ማሰባሰብ፣ የዘማች ቤተሰቦችን ማገዝ እና ደም መለገስ የዘመቻው አካል ነው።

ተማሪዎችና መምህራን አቅማቸው በሚፈቀድውና በሚችሉት መልኩ ህዝባቸውን ለአንድ ሳምንት ያገለግላሉ።

የበጎ ፍቃድ የዘመቻ ስራው በሁሉም ክልሎች የሚደረግ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ መምህራንና ተማሪዎች ይሳተፋሉ።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵየ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ፥ " በሁሉም ግንባሮች ከፍተኛ ሽንፈትን እያስተናገደ የሚገኘው አሸባሪው ቡድን ተሸንፎ በሚወጣባቸው አካባቢዎች ለመስማት የሚዘገንኑ ወንጀሎችን በንጹሃን ላይ ፈጽሟል " ብለዋል።

" ለአብነት በጋሸናና በሰሜን ሸዋዋ አንጾኪያ ከሰሞኑ እንኳን በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎችን በጅምላ መጨፍጨፉን የሚያረጋግጡ መረጃዎች ወጥተዋል " ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት " እነዚህ ድርጊቶች የአሸባሪ ቡድኑን ትክክለኛ ማንነት በግልጽ ያወጡ ናቸው " ብለዋል።

ወ/ሮ ሰላማዊት ፥ " በአማራና በአፋር ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት እየፈጸመ ያለው ይህ የሽብር ቡድን ሆኖ ሳለ ትክክለኛውን ሐቅ ማየት የማይፈልጉ አካላት ግን ዛሬም በእነዚህ ክልሎች ውስጥ የሽብር ቡድኑ ስለሚፈጽማቸው ወንጀሎች ማንሳት አይፈልጉም " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው ፥ " የአሸባሪው የህወሃት ቡድን የአንጾኪያና የጋሸናን ጨምሮ ከዚህ ቀደም በጭና፣ ጋሊኮማ፣ አጋምሳ፣ ቆቦ፣ ዉርጌሳ፣ ውጫሌ፣ ኮምቦልቻና ሌሎችም አካባቢዎች ላይ የተፈፀሙት ጅምላ ግድያዎችና ዘግናኝ ወንጀሎችን በገለልተኛ ቡድን በማጣራት አለም እውነቱን እንዲገነዘብ ማድረግ ይገባል " ብለዋል።

" ለሰብአዊ መብት ቆመናል የሚሉት አለም አቀፍ ተቋማትም ይህንን የሽብር ቡድኑን ወንጀሎች እንደ እስከዛሬው ሁሉ እንዳላየ እንደማያልፉትም እምነታችን ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የደንበኞች ትምህርት ቡድን አባል አቶ ምትኩ አበባዉ ለኢትዮጵያ ቼክ ከተናገሩት ፦

- ደብዳቤዎቹ ከኛ ነዉ የወጡት፤ ትክክለኛ ናቸዉ።

- የክልከላው ምክንያት ለንግድ ማይዉሉ የግል መገልገያ ዕቃዎችን ዝርዝር ለመወሰን የወጣዉን መመሪያ 51/2010ን በመጠቀም በተመላላሽ መንገደኞች ከቀረጥ ነጻ የሚገቡ ነገር ግን ለንግድ አላማ እየዋሉ የሚገኙ ዕቃዎች በህጋዊ ነጋዴዎች ላይ ጫና በመፍጠራቸዉ ነው።

- አንድ መንገደኛ ሁሌ የሚመላለስ ከሆነ ያለቀረጥ ሁሌም እየተመላለሰ የሚያመጣ ከሆነ በህጋዊ መልኩ በኮንቴነር የሚያስጭኑና ግብር የሚከፍሉ ነጋዴዎችን ኪሳራ ዉስጥ የሚያስገባና ተጽዕኖ የሚያሳድር በመሆኑ ይህ ደብዳቤ ወጥቷል።

- ማንኛዉም መንገደኛ ማንኛዉንም አልባሳት ሆነ የንግድ ባህሪ ያለዉ ዕቃ ይዞ ከመጣ ቀረጥና ታክስ መክፈሉ እንደተጠበቀ ሆኖ በወንጀል ምርመራ ህግም እስከ ማስጠየቅ ድረስ የሚደርስ ነዉ።

- ከአንድ ወር በላይ የቆዩና ተመላላሽ ያልሆኑ የመጀመሪያ መንገደኞች፤ ቱሪስቶች እና ዲፕሎማቶች ፓስፖርታቸዉና ማህደራቸዉ ታይቶ የንግድ ባህሪ የሌለዉ ዕቃ የያዙ ከሆነ ለጊዜዉ በመመሪያ 51/2010 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል።

- ጠቅልለዉ ወደ ሀገር የሚመለሱ መንገደኞች ጓዞቻቸዉን ይዘዉ ቢመጡም ሆነ በካርጎ ቢልኩ በመመሪያ 51/2010 የተፈቀደና ሲገለገሉበት የቆየ ዕቃ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ ማስገባት ይችላሉ። ይሁን እንጂ በመመሪያዉ ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ የተፈቀዱ ቢሆኑም ዕቃዎቹ አዳዲስ እስከሆኑ ድረስ ቀረጥና ታክስ ይከፈልባቸዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/ETHIOPIA-12-06

@tikvahethiopia
#Oromia

ከቀናት በፊት በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት እና ፈንታሌ ወረዳዎችን በሚያዋስን እና ካራ ወይም ሞቶማ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ 14 ሰዎች ተገድለዋል።

ከሟቾቹ መካከል የከረዩ አባ ገዳ ከድር ሃዋስ ቦሩ ይገኙበታል።

የክልሉ መንግሥት አባ ገዳ ከድር ሃዋስን የገደለው "ሸኔ" ነው በማለት በሽብርተኛ ቡድንነት የተሰየመውን ታጣቂ ቡድንን ከሷል።

የሟች ቤተሰብ እና የአካባቢው ነዋሪ በበኩላቸው አባ ገዳውን ጨምሮ ረቡዕ ዕለት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 14 መሆናቸውንና የተገደሉትም በፀጥታ አስከባሪ ኃይሎች ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ወርቄ ሀዋስ የአባገዳ ከድር ሀዋስ እህት መሆናቸው የተናገሩ ሲሆን ወንድማቸው ከጊዳራ ቀበሌ ማህበር ተውስደው መገደላቸው ተናግረዋል።

" ባለፈው እሮብ እነሱ ለገዳ ስነስርዓት በተሰበሰቡበት መጡ፤ በስብሰባው ላይ የነበሩት በርካቶች ነበሩ አርብቶ አደር የሆኑ ሰላማዊ ነዋሪዎች ናቸው ቤት የነበሩትን እና ወንዶች የሆኑትን ሁሉ ይዘዋቸው ሄዱ ከተያዙት ውስጥ 2 ሰው ብቻ ነው በህይወት የተመለሰው " ብለዋል።

ይዘዋቸው የሄዱት የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እንደሆኑ የተናገሩት ወ/ሮ ወርቄ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና የፖሊስ ዩኒፎርም አድርገው ነው የመጡት ፤ እኛ የገዳ ስርዓት ሰዎች ነን በማለት ሊያስረዷቸውም ቢሞክሩም አልሰሟቸውም።

የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳደር ግድያውን ሸኔ እንደፈፀመው ገልጿል።

" ባለፈው ሳምንት ለጠ/ሚኒስትሩና ለህግ ማስከበር ዘመቻው ድጋፍ ተደርጎ ነበር በሰልፉ ላይ በርካታ ነዋሪ ተገኝቶ ነበር በዚህ ምክንያት አባገዳዎችን ማስፈራራት ነበር። ህዝቡን ከኛ አስመለጣችሁ በሚል ነው ግድያድን የፈፀሙት እንጂ የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች ግድያውን ፈፀመ ሚባለው ሀሰት ነው " ብሏል የዞኑ አስተዳደር ለቪኦኤ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" መምህራን እና ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በማህበራዊ አገልግሎት ይሰማራሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት ዝግ ሆነው መምህራንና ተማሪዎች በተለያዩ ስራዎች ህዝባቸውን እንዲያግዙ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ ይታወሳል። ይህንን ውሳኔ ተከትሎ መምህራን እና ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራ ይሰማራሉ። ሰብል መሰብስብ፣ በግንባር…
ፎቶ : ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎችና መምህራን በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ ሲሳተፉ መዋላቸውን አሳውቋል።

ለ1 ሳምንት መደበኛ ትምህርት መቋረጡን ተከትሎ በተለያዩ አከባቢዎች የ ሚገኙ ተማሪዎች እና መምህራን በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በዛሬው እለት በተለያዩ የ ሀገራችን ክፍል የሚገኙ ተማሪዎች እና መምህራን ሰብል በመሰብሰብ፣ ደም በመለገስ እና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶችን ሲያከናውኑ መዋላቸው ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

መርሃ ግብሩ እስከ አርብ ድረስ በተለያዩ አገልግሎቶች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡

@tikvahethiopia
" ከፍተኛ የገንዘብ ጉድለት አጋጥሞኛል " - WFP

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በሚቀጥሉት ስድስት ወራት በኢትዮጵያ ለሚያቀርበው ድጋፍ ከፍተኛ የገንዘብ ጉድለት እንዳጋጠመው መግለፁን ቢቢሲ አስነብቧል።

ይህ የገንዘብ ችግር ድርጅቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዜጎችና ስደተኞች የምግብ ድጋፍ እንዲሁም አልሚ ምግቦች ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በሚያቀርበው ድጋፍ ላይ ተጽዕኖ እንደሚኖረው አመልክቷል።

በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በጦርነት እና በዝናብ እጥረት ምክንያት ሰብአዊ ድጋፍ የሚፈልጉ ሲሆን፤ በተጨማሪ ደግሞ ከተለያዩ አገራት የመጡ ስደተኞችም እርዳታን ይሻሉ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሚቀጥሉት ስድስት ወራት የተለያዩ ድጋፎች ለሚያስፈልጋቸው 12 ሚሊዮን ሰዎች ከሚያስፈልገው ገንዘብ የ579 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ጉድለት አጋጥሞታል። ይህም በሰሜን ኢትዮጵያ ለ3.7 ሚሊዮን ሰዎች በሚቀጥሉት ስድስት ወራት በአስቸኳይ ለሚያቀርባቸው የምግብና የአልሚ ምግቦች የሚውለውን 316 ሚሊዮን ዶላር ይጨምራል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተወካይና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ስቴቨን ዌሬ ኦማሞ "በአገሪቱ ውስጥ የምግብ አቅርቦት አለ። ነገር ግን በሚቀጥሉት ሳምንታት የገንዘብ ድጋፍ ካልተነኘ፣ ያለውን ምግብ በመግዛት ወደሚፈለግበት ቦታ ማቀረብ ካልተቻለ ከጥቂት ወራት በኋላ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለከባድ ረሃብና ችግር ሊጋለጡ ይችላሉ" ብለዋል።

ዳይሬክተሩ ጨምረውም በበርካታ ክልሎች ውስጥ በግጭት ምክንያት ለችግር ከተጋለጡት በተጨማሪ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለምግብ ዋስትና ችግር የተጋለጡት የቆላማ አካባቢዎች ነዋሪዎች ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል።

More : telegra.ph/WFP-12-06

@tikvahethiopia
#SouthAfrica

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

ፕሬዜዳንቱ በመግለጫቸው በኦሚክሮን ቫይረስ ሳቢያ ለ4ኛ ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተመታቸው ደቡብ አፍሪካ ቁጥራቸው የበዛ ህሙማንን ለመቀበል ሆስፒታሎችዋን እያዘጋጀች መሆኑን አስታውቀዋል።

በደቡብ አፍሪካ ወደ 2 ሺህ 300 የነበረው እለታዊው የኮቪድ-19 ተጋላጮች ቁጥር እየጨመረ መጥቶ ባለፈው ዓርብ ከ16 ሺህ በላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡

ፕሬዚዳንት ራሞፎሳ ኮቪድ-19ን አስመልክቶ በየሳምንቱ በሚወጣው የዜና መጽሄት “በሃገሪቱ የኦሚክሮን ቫይረስ በአብዛኛው የሃገሪቱ ክፍል መነጋገሪያ የሆነ ይመስላል” ካሉ በኋላ ሰዎች እንዲከተቡ አሳስበዋል፡፡

በቂ ክትባት መኖሩን ጠቅሰው ብዙ ሰዎች እየተከተቡ በሄዱ ቁጥር ብዙ የንግድ አገልግሎቶች እየተከፈቱ ይመጣሉ ማለታቸውን ቪኦኤ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
የ5G ኔትዎርክ በኢትዮጵያ ፦

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) ኔትወርክን በሃገር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙከራ አገልግሎት ለማስጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ካፒታል ጋዜጣ በድረገፁ አስነብቧል።

የሙከራ አገልግሎቱ በመጪው ሳምንት ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባው ያስረዳል።

ኩባንያው ፕሮጀክቱን ከቻይናው የሁዋዌ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በተገኘ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ነው ተግባራዊ እንደሚያደርግ የተነገረው።

ኢትዮ ቴሌኮም በዝግጅት ላይ ላለፉት ሁለት ወራት ሲሰራ መቆየቱ ተገልጿል።

5G ኔትዎርክ በኢትዮ ቴሌኮም ዋና መ/ቤት እና ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ጨምሮ በአዲስ አበባ በሚገኙ አንዳንድ ቦታዎች የሚተገበር እንደሆነ የካፒታል ዘገባ ያስረዳል።

@tikvahethiopia
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከ780 በላይ ተማሪዎችን ተቀበለ።

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርታቸዉን አቋርጠው የነበሩ ከ780 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሏል።

ተማሪዎቹ በአክሱም፣ መቐለና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው።

የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች እና ሀዳ ሲንቄዎች ተማሪዎቹን በእንኩዋን ደህና መጣችሁ ምርቃት ተቀብለዋቸዋል።

የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ታደሰ ሀብታሙና የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ፥ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ፎረም አባላት በጋራ በመሆን ተማሪዎቹ በሚያስፈልጋቸው ድጋፍ ከጎናቸው በመሆን እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹም ከነበሩበት ዩኒቨርሲቲ አሁናዊ ሁኔታ በመነሳት የሠላም አምባሳደርነት ሚና እንዲጫወቱና ከነባር ተማሪዎች ጋር በአብሮነት ስሜት እንዲተባበሩ አመራሮቹ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ለተማሪዎቹ አስፈላጊውን ምክር በመስጠት የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት እንዲወስዱ ተደርጓል።

ምንጭ፦ ጅማ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahyniversity