የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር ኩዌት ናቸው።
የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከኩዌት ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሳባህ ካሊድ አልሃምድ አልሳባህ ጋር በሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር ላይ ተወያይተዋል።
አቶ አህመድ ዛሬ ህዳር 22 በኩዌት በሚገኘው ባያን ቤተመንግስት ተገናኝተው ነው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በኢትዮጵያና በኩዌት የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር ላይ ውይይት ያካሄዱት።
ውይይቱ ፍሪያማ እንደነበር የገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።
በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ በኩል ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን በኩዌት በኩል ፦
• የነዳጅና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ሞሀመድ አልፋሬስ፣
• የገንዘብ ሚኒስትር እና የኢኮኖሚና የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ካሊፋ ሃማዳ
• የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና አማካሪ አብዱል አዚዝ አልዳኬል በውይይቱ ላይ ተገኝተው እንደነበር ከኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
" ዛሬ ጠዋት በADF ካምፖች ላይ ከኮንጎ አጋሮቻችን ጋር በጋራ የአየርና የመድፍ ጥቃቶችን ፈፅመናል " - የኡጋንዳ ጦር ቃል አቀባይ የኡጋንዳ ጦር ከጎረቤት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) ሃይሎች ጋር በመሆን በAllied Democratic Force (ADF) ታጣቂ ቡድን ላይ በጋራ የአየር ድብደባ እና የመድፍ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ። የኡጋንዳ መከላከያ ሃይል ቃል አቀባይ በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪድዮ
የኡጋንዳ ጦር ከጎረቤቱ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) ሃይሎች ጋር በመሆን በ Allied Democratic Force (ADF) ታጣቂ ቡድን ላይ በጋራ የአየር ድብደባ እና የመድፍ ጥቃት መፈፀሙን ትላንት አሳውቋል።
ዛሬ ደግሞ ኡጋንዳ ይህን የታጠቀ ቡድን ለማደን እና ለመቅጣት ጦሯን ድንበር አሻግራ ወደ ኮንጎ መላኳ ተሰምቷል።
የኡጋንዳ ባለስልጣናት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በካምፓላ ለደረሰው የአጥፍቶ ጠፊ የቦንብ ጥቃት ADFን ተጠያቂ አድርገዋል።
ይሄ የታጠቀ ቡድን በምስራቃዊ ኮንጎ ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ጥቃቶችን ፈጽሟል በሚል ይከሰሳል።
ሁለቱም ሀገራት ADF የተባለው የታጠቀ ቡድን በርካታ ሲቪል ሰዎችን መጨፍጨፉን ይገልፃሉ።

#Qatar
ዛሬ ጥዋት የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ በዶሃ ከኳታር አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒን ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ ግንኙነት እና #በአፍሪካ_ቀንድ ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ጋሮዌ ዘግቧል።
ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ በኳታር 2021 የፊፋ የአረብ ዋንጫ መክፈቻ ላይ የተሳተፉ ሲሆን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ቆያታቸውን በማጠናቀቅ ከዶሃ መውጣታቸውን ከኳታር ዜና አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

#Update
ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ በቁጥጥር ስር መዋሏን የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፥ " የጋሸናን ግንባር ምሽጎችን በመሰባበር የአሸባሪውን አከርካሪ የሰበሩት የመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል ፣ የአማራ ሚሊሻና ፋኖ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማንና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ተቆጣጥረዋል " ብሏል።
በአሁን ሰዓት የመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ፣ ሚሊሻ እና ፋኖ የላስታ ላሊበላን አካባቢ በማጽዳት የሰቆጣ ከተማን ለመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሡ ነው ሲልም አሳውቋል።
ዛሬ ጥዋት የመንግስት ኮሚኒኬሽን በሰጠው መግለጫ ፦
• በጋሸና ግንባር : ጋሸና ፣አርቢት፣ አቀት እና ዳቦ፤
• በወረኢሉ ግንባር : ጃማ ደጎሎ ፣ ወረኢሉ፣ ገነቴ፣ ፍንጮፍቱ እና አቀስታ፤
• በሸዋ ግንባር : መዘዞ ፣ ሞላሌ ፣ሸዋሮቢትና አካባቢው፣ ራሳና አካባቢው የኢትዮጵያ ጦር መቆጣጠሩን ማሳወቁ ይታወሳል።
እንዲሁም በምስራቅ ግንባር በኩል ነፃ በሆኑ አካባቢዎች የአካባቢው አስተዳደር ወደ ቦታው መመለሱ መገለፁ አይዘነጋም።
የአካባቢው አስተዳዳሪዎች የተመለሱባቸው ፦
- ካሳጊታ
- ቡርቃ
- ዋኢማ
- ጭፍራ
- ጪፍቱ
- ድሬሮቃ
- አለሌ ሱሉላ ናቸው።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ዛሬ ማምሻዉን ባደረገው ስብሰባ የዐዋጁን አፈጻጸም የገመገመ ሲሆን አዋጁን በመፈፀም ረገድ የህዝቡ ተነሳሽነት እና ቆራጥነት የሚደነቅ ነው ብሏል። የተገኙትን ድሎች ለማስቀጠል 4 ትእዛዝትን አስተላልፏል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ፥ " ከአሸባሪው የሕወሐት እጅ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ሰላምንና ጸጥታን ለማስፈን እንዲሁም የሕዝብንና የንብረትን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲባል ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የሰዓት እላፊ ታውጇል " ሲል አሳውቋል።
ዕዙ ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በወጡ አካባቢዎች የታወጀውን የሰዓት እላፊ በተመለከተ ወደ አካባቢው የገቡ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲፈጥሩ፤ እንዲሁም የሰዓት እላፊውን እንዲያስፈጽሙ ትእዛዝ መሰጠቱንም ገልጿል።
በተጨማሪ ፥ " ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በወጡ አካባቢዎች ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ መንግሥት ከሚመደብ ሲቪል አስተዳደር ጥምር ኮሚቴ በአስቸኳይ እንዲቋቋም። በዚህ ኮሚቴ አማካኝነት በአሸባሪው ወራሪ ኃይል በመንግሥት ተቋማት፣ በግለሰብ ንብረቶች፣ በማኅበራዊ ተቋማትና በመሠረተ ልማቶች ላይ የደረሰውን ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመትን የሚያሳዩ ማስረጃዎች እንዳይጠፉ እንዲጠበቁ፣ በተገቢው መንገድ እንዲመዘገቡ፣ ማስረጃዎች እንዲሰነዱ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዙ ትእዛዝ ሰጥቷል " ብሏል።
በመጨረሻም ፥ የፍትሕ አካላት በየቦታው ከተቋቋሙ ጥምር ኮሚቴዎች ማስረጃዎችን ተቀብለው በማደራጀት ለሚመለከተው አካል እንዲያስረክቡ መታዘዙን ገልጿል።

ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 16 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,616 የላብራቶሪ ምርመራ 136 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 234 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

" እርዳታ የጫኑ ከ150 በላይ ተሽከርካሪዎች መቐለ ደርሰዋል " - ስቴፋን ዱጃሪች
እርዳታ የጫኑ ከ150 በላይ የጭነት ተሽከርካሪዎች መቐለ መድረሳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።
የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ትናንት በሰጡት መግለጫቸው ፥ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ከ5 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የትግራይ ህዝብ የሚፈልገውን መጠነ ሰፊ እርዳታ በየእለቱ እየላከ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በአካባቢው ባለ ግጭት ወደ አንድ ወር ለተጠጋ ጊዜ ወደ ትግራይ የሚያስገባው መንገድ ተዘግቶ የቆየ መሆኑን ያስታወሱት ቃል አቀባዩ ወደ በአማራ ክልልም በደሴ እና በኮምቦልቻ ለሚገኙ 100 ሺህ ተፈናቆዮች ባላፈው ሳምንት የምግብ እርዳታ መከፋፈሉን ተናግረዋል፡፡
በእነዚህ ከተሞችም እርዳታ ሲሰጥ በ1 ወር በተቃረበ ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያው ነው ብለዋል፡፡
በሚቀጥሉት ሳምንታት የWFP እና አጋሮቹ ወደ 450 ሺ ለሚደርሱ ሰዎች የምግብ እርዳታ የሚያቀርቡ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
በአካባቢው ላይ ባለ አለመረጋጋት የተነሳ በኢትዮጵያ ሰአብአዊ ምላሽ ለመስጠት አሁንም ችግር እንደሆነ መቀለጡን ዋና ጸሀፊው አመልክተዋል፡፡
WFP በ1,700 ተሽካርካሪዎችን ሊጫን የሚችል ከ67 ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆን እህል በሰሜን ኢትዮጵያ ያከማቸ መሆኑን ስቴፋን ዱጃሪች አስታውቀዋል፡፡
ይህ ወደ 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብን ለሁለት ወራት መመገብ የሚችል መሆኑን ገልጸው፣ ይሁን እንጂ ከፍተኛ የገንዘብና የነዳጅ እጥረት መኖሩን ማሳወቃቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።
#WFP #UN

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር ኩዌት ናቸው። የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከኩዌት ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሳባህ ካሊድ አልሃምድ አልሳባህ ጋር በሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር ላይ ተወያይተዋል። አቶ አህመድ ዛሬ ህዳር 22 በኩዌት በሚገኘው ባያን ቤተመንግስት ተገናኝተው ነው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በኢትዮጵያና በኩዌት የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር ላይ ውይይት ያካሄዱት። ውይይቱ ፍሪያማ እንደነበር…
#Update
የኢትዮጵያና የኩዌት ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት በሁለቱ ሀገራት የገንዘብ ሚንስትሮች መካከል ተደረገ፡፡
የኢፌዲሪ የገንዘብ ሚንስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና የኩዌት አቻቸው ከሊፋ ሙሳዱ ሀማዳ ሁለቱ ሀገራት በቀጣይ በንግድና መዋዕለ ነዋይ ፍሰት ላይ በጋራ መሰራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ኩዌት ካላቸው ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ባለፈ ብዛት ያላችው በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ልማት ላይ ጠንካራ ተሳትፎ እያደረጉ እንዳሉ ይታወቃል ብሏል የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር።
@tikvahethiopoa

#Ethiopia
ሩሲያ እና ቻይና በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ያለው ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑን ሲገልፁ አሜሪካ በአንፃሩ ዜጎቿ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ እየወተወተች ነው።
አሜሪካ ዜጎቿ እንዲወጡ መወትወት ከጀመረች ቀናት ያለፉ ሲሆን አሁንም ዜጎቿ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ እዚህ አዲስ አበባ ባለው ኤምባሲ አማካኝነት ጥሪ እያቀረበች ነው።
ከሰሞኑን " በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እየተባባሰ ነው " በሚል አሜሪካውያን ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ ሲያሳብ የነበረው የአሜሪካ ኤምባሲ ትላንትና ምሽት ደግሞ ከኢትዮጵያ የመውጣት ፍላጎት ያላቸው አሜሪካውያን የተለያዩ አማራጮች እንዳላቸው ገልጿል።
ከዚህ በተቃራኒ የተለያዩ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ አትሂዱ እዛም ያላችሁ ዜጎቻችን ውጡ ሲሉ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ እና ባልደረቦቻቸው ትላንት ኢትዮጵያ ገብተዋል።
ዋንግ ዪ ፥ ቻይና በኢትዮጵያ ላይ እምነት እንዳላት፣ የሀገሪቱ መንግስትም መላው ኢትዮጵያውያንን እና በኢትዮጵያ ያሉ ቻይናውያንን የመጠበቅ ብቃት እንዳለው ገልፀው "አስጠንቃቂ" ባሏቸው አካላት ዜጎችን ከአዲስ አበባ አስወጡ የሚለውን ጥሪ በጭፍን እንደማትቀበል አሳውቀዋል።
በሌላ በኩል ፥ ሩሲያ አንዳንድ የውጭ ሚዲያዎች አዲስ አበባ በታጣቂ ኃይሎች ከበባና ስጋት ውስጥ እንደሆነች የሚነዙት መረጃዎች ከእውነት የራቁ ናቸው ስትል በድጋሚ አስታውቃለች።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ሩሲያ የኢትዮጵያን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለች መሆኑን አሳውቀዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት የሩሲያ ኤምባሲ አዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ መሆኗን ቢያሳውቅም አንዳንድ ሚዲያዎች ዛሬም በውሸት ዘገባቸው መቀጠላቸውን ማሪያ ዛካሮቫ ገልፀው የአዲስ አበባ ሁኔታ ግን ዛሬም የተረጋጋ እና ሰላማዊ መሆኑን አሳውቀዋል።

#ETHIOPIA
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው በመግለጫቸው አሁንም አንዳንድ ኤምባሲዎች እና ተቋማት በኢትዮጵያ በተላይ በአዲስ አበባ ከተማ ያለው የሠላምና ፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ ነው በሚል የሚያቀርቡት ጥሪ በሀገሪቱ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የሚቃረንና ከትላልቅ ሀገራት ተቋማትና ኤምባሲዎች የማይጠበቅ ነው ብለዋል።
አቶ ከበደ ዴሲሳ ፥ " አሁንም አንዳንድ ኤምባሲዎች የኢትዮጵያ ሰላም እና ፀጥታ ሁኔታ ላይ በተለይም የአዲስ አበባ የሰላም እና ፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ያለ በማስመሰል ጥሪያቸውን በየቀኑ ሲያቀርቡ ነው የሚውሉት ፤ ማስጠንቀቂያዎችን እና ማሳሰቢያዎችንም በማውጣት ላይ ናቸው " ብለዋል።
ድርጊታቸው ግን አሁን ኢትዮጵያ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ የሚቃረን መሆኑን አስረድተዋል።
አዲስ አበባ አሁን ላይ የምትገኝበት የፀጥታ ሁኔታ እጅግ የተረጋጋ፣ ከማንኛውም ጊዜ በላይ ፀጥታዋ የተጠበቀበት ጊዜ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አንስተዋል።
የሚደረጉት ጥሪዎችም ከትላልቅ ሀገራት ተቋማት እና ኤምባሲዎች የማይጠበቅ መሆኑን ገልፀዋል።
አዲስ አበባ ከሌሎች ሀገራት ከተሞች በተሻለ ደረጃ የፀጥታ ሁኔታዋ ተረጋግጦ ነው የሚገኘው ያሉት አቶ ከበደ የማንኛውም ሀገር ዜጋ ኢትዮጵያ መጥቶ፣ ቆይቶ፣ ጎብኝቶ፣ ሰርቶ መውጣት የሚችልበት ሁኔታ ላይ ነው የምትገኘው ብለዋል።
በውጭ ያሉ ዜጎችም ያለምንን ስጋት ኢትዮጵያን መጎብኘት እንደሚችሉ፤ የኢትዮጵያ ሰላምና ደህንነትም የተረጋገጠ መሆኑን አስገዝበዋል።
በቀጣይ በሚከበሩ የተለያዩ በዓላት ላይ የኢትዮጵያ ዜጎችና ወዳጆች በሙሉ መተማመን ኢትዮጵያን መጥተው እንዲጎበኙ ፣ ኢትዮጵያን እንዲያስተዋውቁ፣ ሰላም እና ደህንነቷንም ለዓለም እንዲያሳውቁ ጥሪ አቅርበዋል።

#ETHIOPIA የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። ሚኒስትር ዴኤታው በመግለጫቸው አሁንም አንዳንድ ኤምባሲዎች እና ተቋማት በኢትዮጵያ በተላይ በአዲስ አበባ ከተማ ያለው የሠላምና ፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ ነው በሚል የሚያቀርቡት ጥሪ በሀገሪቱ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የሚቃረንና ከትላልቅ ሀገራት ተቋማትና ኤምባሲዎች የማይጠበቅ ነው ብለዋል። አቶ ከበደ ዴሲሳ…
#ETHIOPIA | #AddisAbaba
" አዲስ አበባ ከሌሎችም ሀገራት ከተሞች በተሻለ ደረጃ የፀጥታ ሁኔታዋ የተረጋገጠ ነው።
የማንኛውም ሀገር ዜጋ ኢትዮጵያ መጥቶ፣ ቆይቶ፣ ጎብኝቶ፣ ሰርቶ መውጣት የሚችልበት ሁኔታ ላይ ነው የምትገኘው።
በውጭ ያሉ ዜጎች ያለምንን ስጋት ኢትዮጵያን 🇪🇹 መጎብኘት ይችላሉ፤ የኢትዮጵያ ሰላም እና ደህንነት የተረጋገጠ ነው።
በቀጣይ በሚከበሩ የተለያዩ በዓላት ላይ የኢትዮጵያ ዜጎችና ወዳጆች በሙሉ መተማመን ኢትዮጵያን መጥታቸው ጎብኙ ፣ ኢትዮጵያን አስተዋውቁ ፣ ሰላም እና ደህንነቷንም ለዓለም አሳውቁ "
(አቶ ከበደ ዴሲሳ)

#Wenchi : ወንጪ ሐይቅ ምርጥ የቱሪዝም መንደር ሆኖ ተመረጠ።
በስፔን ማድሪድ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በ24 ኛው የአለም የቱሪዝም ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ወንጪ ሐይቅ የ2021 ምርጥ የቱሪዝም መንደር ሆኖ ተመረጠ።
በኦሮሚያ ክልል በደቡብ ምዕራብ ሸዋ የሚገኘው ወንጪ ሐይቅ ከ170 የቱሪዝም መንደሮች መካከል ቀዳሚ ሆኖ መመረጡ በጉባኤው ላይ ይፋ ተደርጓል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር ያለው የአለም የቱሪዝም ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በመድረኩ ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል።
Photo Credit : Hilena Tafesse