TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ቀይ መስቀል (አ/አ ቅርንጫፍ) ተለዋጭ ቦታ ተሰጠው።

በአዲስ አበባ ከተማ ከ1973 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተለዋጭ ቦታ ማግኘቱንና ከኅዳር 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ አዲሱ ሕንፃ ተዘዋውሮ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰብዓዊ፣ የዲፕሎማሲና የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሰለሞን ዓሊ (ዶ/ር) ፥ የአዲስ አበባ ከተማ የቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ይገለገልበት የነበረውን ቦታ ለልማት በመፈለጉ ምክንያት የቦታ ይዞታውን እንዲለቅ ተደርጓል ብለዋል።

በዚህ መሠረት የከተማ አስተዳደሩ በምትኩ ሰእሊተ ምሕረት አካባቢ ከሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ፊት ለፊት የሚገኘውን የቀድሞ የማምረቻዎች ልማት ኤጀንሲ ጽሕፈት ቤት የነበረውን ጂ+4 ሕንፃ ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አገልግሎት እንዲውል በስጦታ መልክ ማበርከቱን ኃላፊው ገልፀዋል።

አዲሱ ጽሕፈት ቤት ከ15 በላይ አምቡላንሶችን የመያዝ አቅም እንዳለው የሚናገሩት ዶ/ር ሰለሞን፣ " ከዚህ ቀደም አገልግሎት ይሰጡበት ከነበረው ሕንፃ የተሻለ፣ እንዲሁም እጅግ ዘመናዊ የሆነ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ቀይ መስቀል አ/አ ቅርንጫፍ ከዚህ ቀደም የነበረበት ሕንፃ መፍረሱን ተከት ቅሬታ ማስነሳቱ፤ በተለይም ደግሞ ለተቋሙ የሚሆን ተለዋጭ ቦታ አለመሰጠቱ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም።

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SUDAN የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ወደ ቀደመው ኃላፊነታቸው ለመመለስ የሱዳን የፖለቲካ እና ወታደራዊ ኃይሎች ከስምምነት መድረሳቸው ተሰምቷል። የሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ሀገሪቱን ከቀውስ ለማውጣት እያካሄዱት ባለው ድርድር ላይ በወታደራዊ ኃይሎች ከስልጣናቸው ተነስተው የነበሩትን አብደላ ሀምዶክ ወደ ቀድሞ ኃላፊነታቸው ለመመለስ ተስማምተዋል። የሱዳን…
#SUDAN

አብደላ ሀምዶክ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ተመለሱ።

ሃምዶክ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው የተመለሱት በሀገሪቱ የተፈረመውን አዲስ ፖለቲካዊ ስምምነት ተከትሎ ነው።

የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በሀገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግስት ከተፈፀመ 3 ሳምንታት በኋላ ስልጣን ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመመለስ የሚያስችል ስምምነት ዛሬ ፈርመዋል።

ዛሬ በካርቱም በሚገኘው ቤተ መንግስት ውስጥ የተካሄደውን የፖለቲካ ስምምነትም ሌተናል ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ መፈረማቸው ተነገሯል።

ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሀን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላህ ሃምዶክ በ14 ጉዳዮችን ዙሪያ መፈራረማቸውም ነው የተገረው።

ከተስማሙባቸው ጉዳዮች መካከልም ፦
- ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እና አንድ ወጥ የሆነ የሱዳን ጦር መመስረት፣
- የሱዳንን ግዛታዊ አንድነት ማስጠበቅ፣
- የሽግግር ጊዜውን የሚመራውን ሕገ መንግሥታዊ፣ ህጋዊ እና ፖለቲካዊ አስራሮች መወሰን የሚሉት ይገኙበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ ከስምምነቱ በኋላ ባደረጉት ንግግር፤ " አንድነት ለሱዳን አስፈላጊ ነው " ያሉ ሲሆን " የሱዳን ጥቅም ማስጠበቅ ቀዳሚ ጉዳይ ነው " ሲሉ አሳስበዋል።

“ዛሬ የተፈረመው ስምምነት ለሳምንታት የተሰራ የጠንካራ ስራ ውጤት ነው” ያሉት ሀምዶክ፤ “ሱዳን ምንም መመለስ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ብትደርስም መመለስ እንደምትችል ያረጋገጠ ነው” ብለዋል።

ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሀን በበኩላቸው “ዛሬ የተፈረመው ስምምነት የሱዳናውያን የስራ ውጤት ነው፤ ይህ የእውነተኛ ሽግግር ጅማሮ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
" በቦረና ዞን የሞቱ እንስሳት ቁጥር 70 ሺህ ተሻግሯል "

በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሞቱ እንስሳት ቁጥር ከ70 ሺ ማለፉን የዞኑ አርብቶ አደር ልማት ኃላፊ ዶ/ር ቃሲም ጉዮ አስታወቁ።

ድርቁ ከእንስሳት ሞት ባሻገር በሰዎች ህይወት ላይ ማህበራዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም አመልክተዋል።

ዶ/ር ቃሲም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ " 70,185 ከብቶች ሞተዋል ፤ 117,462 እራሳቸው መነሳት የማይችሉ በሰው ድጋፍ የሚነሱ ናቸው" ብለዋል።

ጉዳት ከፍተኛ ነው ያሉት ዶ/ር ቃሲም ጉዮ ፥ " 50,552 አባወራዎች ናቸው ከብቶቻቸውን በጉልበታቸው እያነሱ የሚገኙት ፤ ከብቶች የሞቱባቸው 28,238 አባወራዎች ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

ድርቁ እንስሳት ላይ እያደረሰ ካለው ጉዳት በተጨማሪ በማህበራዊ ህይወት ላይ ተፅእኖ እያሳረፈ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል።

ለድርቅ ተጎጂዎች የእንስሳት መኖ ድጋፍ ይዞ ወደ ቦረና ዞን ሄዶ የነበረው የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ልዑካን ቡድን በስፍራው ያለድ ጉዳት በመገናኛ ብዙሃን ከሚነገረው በላይ ነው ብሏል።

የሶማሊ ክልል ደግሞ ባለፈው ሳምንት ከ50 ሺህ በላይ እንስሳት እንደሞቱበት ያሳወቀ ሲሆን ድርቁን ለመከላከል መንግስት ከሚያደርገው ጥረት በተጨማሪ በውጭ ያሉ የሶማሊ ክልል ተወላጆች ድርጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/BORANA-11-21-2

Credit : Addis Checkol - VOA
Photo : Haramya University
TIKVAH-ETHIOPIA
" በቦረና ዞን የሞቱ እንስሳት ቁጥር 70 ሺህ ተሻግሯል " በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሞቱ እንስሳት ቁጥር ከ70 ሺ ማለፉን የዞኑ አርብቶ አደር ልማት ኃላፊ ዶ/ር ቃሲም ጉዮ አስታወቁ። ድርቁ ከእንስሳት ሞት ባሻገር በሰዎች ህይወት ላይ ማህበራዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም አመልክተዋል። ዶ/ር ቃሲም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ " 70,185 ከብቶች ሞተዋል ፤ 117,462 እራሳቸው መነሳት…
#BORANA

• " ነፍሴን ካወቅኩ ጀምሮ ግን እንደዚህ አይነት ድርቅ አይቼ አላዉቅም " - የ88 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋው አቶ አብጃሀታኒ ሞሉ

• " ምን እንደሚገጥመንም ፈጣሪ (ዋቃ) ብቻ ነዉ የሚያወቀው " - ወ/ሮ ደቦ ዋቅቶላ

ወይዘሮ ደቦ ዋቅቶላ አካባቢቸውን ለቀው ወደ ሌላ ስፍራ ለስደት ከሄዱ አርብቶ አደሮችን መካከል ሲሆኑ ቀበሌያቸው በድርቅ በመጎዳቱ ለእንስሳቱ ዉሃና ሳር ለሰዉም የሚሆን ምግብ በመጥፋቱ እንስሳቶቹን እየነዱ ወደ ድሬ ወረዳ መሰደዳቸውን ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ኤፍ ኤም 91.5 ተናግረዋል።

ወ/ሮ ደቦ፥ " ምን እንደሚገጥመንም ፈጣሪ (ዋቃ) ብቻ ነዉ የሚያወቀው " ብለዋል፡፡

የ88 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋው አቶ አብጃሀታኒ ሞሉ በበኩላቸው፥ ከዚህ በፊትም አልፎ አለፎ ድርቅ ይመጣል፣ ነፍሴን ካወቅኩ ጀምሮ ግን እንደዚህ አይነት ድርቅ አይቼ አላዉቅም ብለዋል።

" ከእኔ ብቻ 132 ከብቶች አልቀውብኛል " የሚሉት እኚህ አባታችን " አሁን ደግሞ እኔና በአካባቢዬ ያሉ ሰዎች እየተራብን ነዉ፣ በቦረና ሰማይ ላይ ደመናም አይታይም ስለዚህ ፈጣሪ፣ ህዝብና መንግስት ተረባርበዉ ካልደረሱልን እንኳን እንስሳት እኛም በረሀብ ልናልቅ ስለሆነ መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲረዳን ጥሪዬን አቀርባለሁ " ብለዋል፡፡

በቦረና ዞን በድርቅ በተመቱት 5 ወረዳዎች ከሌሎች እንስሳት በተለየ መልኩ አህያዎች በራሳቸዉ ያሉበትን አካባቢ በመልቀቅ ደመና ወዳለበት እየጠፉ ሲሆን ይህም የተለመደ የአህያ ልዩ ባህሪይ በመሆኑ በርካታ አርብቶ አደሮች አህያዎቻቸውን ፍለጋ ተሰማርተዋል።

በቦረና ዞን በድርቅ በተመቱ አካባቢዎች በየቦታው የሞቱ እንስሳቶች ቅሪት ፣ በህይወት ያሉትም በጣም ተዳክመው አጥንታቸው ከቆዳቸው ጋር ተጣብቆ ይታያል።

ከሀዩ ኤፍ ኤም የተወሰደ።

@tikvahethiopia
የተቃውሞ ሰልፎች ፦

በ27 የተለያዩ ዓለም አቀፍ ከተሞች በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገ ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ ተደረገ።

በዓለማ አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያውያን በ27 ከተሞች የአሜሪካ መንግስት እና አንዳንድ የምእራባዊያንን መንግስታት በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉ ያሉትን ጣልቃ ገብነትና ጫና የሚቃወም ሰልፍ አድርገዋል።

በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ " ኋይት ሃውስ ቤተ መንግስት " በርካቶች የተሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍም ተካሂዷል። በዚሁ ሰልፍ ሽብረተኛ ተብሎ የተፈረጀውን ህወሓት መደገፍ የአፍሪካ ቀንድን እና መላ አህጉሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል አካሄድ መሆኑን የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር እንዲገነዘብ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።

በእስራኤልና እንግሊዝ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ብዛት ያለው ህዝብ በመሳተፍ የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን የሀሰት ዘገባ እና መንግስታት በምርጫ ወደ ስልጣን የመጣ መንግስትን ለመጣል የሚያደርጉትን ጥረት ክፉኛ ኮንነዋል።

ሰልፈኞቹ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ በተለይም የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦችን በመከፋፈል ላይ የተመሰረተ ፖሊሲዋን እንድታርም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያን እጅ ለመጠመዘዝ የሚደረግ ሙከራ የአፍሪካን ነጻነት መግፈፊያ ዳግም የቅኝ አገዛዝ ፖሊሲ አካል በመሆኑ “#NoMore” በሚለው መሪ መፈክራቸው ተቀባይነት እንደሌለው ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ሶሻል ሚዲያ

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል ዛሬ እና ነገ ይመሰረታል።

5 ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ ሆነው የሚያቋቁሙት የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ዛሬና ነገ በሚካሄዱ መርሀ ግብሮች 11ኛው ክልል ሆኖ በይፋ ይመሰረታል፡፡

ለክልሉ ምስረታ ከአምስቱ ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ የተውጣጡ የሥራ ሃላፊዎች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

ከትላንት ምሽት ጀምራ የክልል እና የፌደራል እንግዶች ለክልሉ ምስረታ ቦንጋ ከተማ እየገቡ ይገኛሉ።

በነገው እለት የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ህገ መንግስት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዕለቱ የአዲሱ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይመረጣል፡፡

በተያያዘ ልዩ ልዩ አዋጆች እና ህጎች ይፀድቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የከፋ ዞን መንግስት ኮምዩኒኬሽን ሀላፊ አቶ መስፍን ተስፋዬ አሳውቀዋል።

Credit : ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ወታደሮች ትልካለች ?

" ከዚህ ክፉ ሀሳብ ቢታቀቡ ይሻላቸዋል " - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ከሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የጆ ባይደን አድተዳደር በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ሁኔታ ጋር በተያየ ወደ ኢትዮጵያ ወታደሮችን ሊልክ ነው ፤ ወታደሮችን ሊያስገባ ነው የሚሉ የተለያዩ መረጃ ሲናፈሱ ነበር።

በዚህ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን አስተያየት የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፥ አሜሪካ ወታደር ታስገባለች ለሚባለው ጉዳይ ለምን ? የሚለው ጥያቄ ምላሽ የለውም ብለዋል።

አምባሳደሩ ፥ " በዚህ ሰዓት ኢትዮጵያ ላይ ወታደራዊ ጫና ለማሳረፍ ፣ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያሳስባቸው ምንም ነገር የለም፤ የአሜሪካን ጥቅም ህዝብም የሀገርን ጥቅም የሚጠብቅ አይደለም። ሁለቱንም ሀገሮች ግንኙነት ቁመናን የሚለካም አይደለም። እብደት ካልሆነ በስተቀር " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው " ህዝባችን እያለ ያለው የኛ ጉዳይ ፣ የኛ ህልውና ፣ የኛ ነፃነት ሁሉ ነገር በእጃችን ነው ያለው እንጂ በእነሱ እጅ አይደለም ያለው ፣ በሌሎች እጅ አይደለም ያለው፤ በማንም እጅ ሊሆን አይችልም። ይህንን ህዝቡ በአንድ ትልቅ ድምፅ እየተናገረ ነው " ብለዋል።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የሰላሙን ጉዳይ በተመለከተም ፥ "ይሄ ሀገር ተጭኖበት ካልሆነ በስተቀር ለሰላም ሁል ጊዜ የቆመ ህዝብ እና መንግስት ነው ፤ መንግስት ለሰላም ከአንዴም ሁለቴ እርምጃዎችን የወሰደበት ሁኔታ ነው ያለው። መጥተው እዚህ ስለ ሰላም የሚያወሩትም ሰዎች ስለሰላም ምንም አዲስ ነገር እየነገሩን አይደለም ይሄ የህዝባችን ፍላጎት ነው እሱ። ህዝባችን ለምንድነው የሚጭኑብን እያለ ነው፤ ግን ከህልውናችን በላይ ምንም ነገር የለም የሚል ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

አምባሳደር ዲና ፤ [ አሜሪካኖቹ ወደ ኢትዮጵያ ወታደር የማስገባት ] እርምጃ ባይገቡበት ይሻላል ያሉ ሲሆን እነሱ ገብተው ሰላም የፈጠሩበት ሀገር ብዙም የለም ብለዋል።

" እዚህ በአካባቢያችን ሊቢያን፣ የመንን ፣ ሶሪያን ፣ ኢራቅን ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና ራቅ ያሉ የኤዥያ ሌሎች ሀገራትን አይተናልና የሚፈጥሩት ነገር የለም። ይልቁን የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነትና የቆየ ግንኙነት ማበላሸት ነው የሚሆነው ይሄን መላልሰው ቢያስቡበት እና ከዚህ ክፉ ሀሳብ ቢታቀቡ ይሻላል " ብለዋል አምባሳደር ዲና።

@tikvahethiopia
ኤጀንሲው የሰነድ ማረጋገጫ ማህተም አሰራርን ቀየረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ እየተበራከተ የመጣውን ሰነድ አስመስሎ የመስራት ወንጀል ለመቀነስ ኤጀንሲው በሚሰጣቸው የልደት፣ የጋብቻ ፣ የፍቺ ፣ የያላገባ እንዲሁም ሌሎች ማስረጃዎች አገልግሎት ሲሰጥበት የነበረውን የማረጋገጫ አሰራር በዘመናዊ አሰራር በመተካት ፎርጀሪ እያደረሰ ያለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳት ለመቀነስ የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ተቋሙ በዋና መስሪያ ቤት የሚሰጠውን ለፖስፖርት አገልግሎት፣ ለውጭ ሃገራት የቪሳ ጥያቄ ፣ ለተለያዩ የውጭ እና የሃገር ውስጥ ጉዳዮች የሚውሉ ማስረጃዎች የሚረጋገጥበትን የቀድሞ የማህተም አሰራር በማስቀረት በውጭ ሃገር አሰርቶ ባስገባው ዘመናዊ የሆሎግራም ማረጋገጫ አሰራር ከዛሬ ህዳር 13 2014 ዓ.ም ጀምሮ በመተካት ተግባራዊ ያደርጋል።

ይህ አሰራር ከፖስፖርት እና ከውጭ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በየቦታው ተመሳስሎ በመስራት ለማለፍ የሚሞከሩ ሌብነቶች ኤጀንሲውን እንዳያልፉ እገዛ የሚያደርግ እንደሚሆን ታምኖበታል።

በተያዘው በጀት ተቋሙ የሚሰጣቸውን ሰርተፍኬቶች የደህንነት ደረጃ ከፍ ለማድረግ አዲስ የPersonalization ቴክኖሎጂ ባላቸው ፕሪንተሮች ለመተካት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

ምንጭ፦ ወ/ኩ/ም/መ/ኤጀንሲ

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ዴንማርክ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ርዳታ ተጨማሪ 4.5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች።

አዲሱ አስተዋፅኦ የኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ ፈንድ በኢትዮጵያ በጣም ለተቸገሩ ሰዎች ህይወት አድን ሰብአዊ ርዳታ ለመስጠት የሚረዳ ነው።

በሌላ በኩል የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርገውን የ 1.3 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚቀጥል ዛሬ ገልጿል።

USAID በአፋር፣ በአማራ፣ በትግራይ ክልሎችና በሌሎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች የህይወት አድን ሰብአዊ ድጋፉን እንደሚቀጥል አሳውቋል።

አሜሪካ በጤናና በትምህርት በኢትዮጵያ የምታደርገው ኢንቨስትመንት እንደሚቀጥል አሳውቃለች።

ከኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ጋር እየተሰጠ ላለው ምላሽ የምናደርገው ድጋፍና የኮቪድ ክትባት ልገሳውም ይቀጥላል ብላለች። ከግጭቱ በኋላ ሀገሪቷ እንድታገግም የያዝነው ዕቅድ ሁሉ አይቆምም ፣ ይቀጥላል ስትልም ገልጻለች።

የአሜሪካ ኤምባሲ ክፍት ነው ፣ የአሜሪካ ህዝብም የኢትየጵያን ህዝብ በሚያስፈልገው ሁሉ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቃለች።

ምንጭ፦ Embassy of Denmark in Ethiopia & US EMBASSY AA

@tikvahethiopia