#AddisAbaba
4 ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ በንብረት ግምጃ ቤት ውስጥ የተቀመጡ ከ 1 ሺህ 800 በላይ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ህዳር 8 ቀን 2014 ዓ/ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ብርበራ ከ1 ሺህ 800 በላይ ጥይቶች በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
በቤተ ክህነቱ ግቢ በሚገኝ የንብረት ግምጃ ቤት በሚገኝ የፅህፈት እና የፅዳት እቃዎች ማስቀመጫ ውስጥ በተደረገው ብርበራ የተገኙት 1ሺህ 363 የብሬን እና 493 የሽጉጥ ጥይቶች ናቸው፡፡
በተጨማሪም 2 የጥይት ማስቀመጫ ሳጥኖች እና 1 የክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ ካዝና ተይዟል፡፡
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 1 ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ ሲሆን ህብረተሰቡ በስልክ፣ በአካል እና ሌሎች የመገናኛ አማራጮችን በመጠቀም እየሰጠ የሚገኘው ጥቆማ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ፥ " አሸባሪው የህወሃት ቡድን ለሽብር ተግባሩ የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በተለያዩ የኃይማኖት ተቋማት ውስጥ ሲያከማች እና በኃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ግለሰቦችን በተላላኪነት እያሰማራ በበርካታ ንፁሃን ላይ አሰቃቂ እልቂት ሲፈፅም እንደቆየ ይታወሳል " ብሏል።
@tikavhethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Sidama ከነገ ጀምሮ በሲዳማ ክልል የሰአት እላፊ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ክልከላዎች ተላለፉ። የሲዳማ ክልል ኮማንድ ፖስት ከነገ ጀምሮ ገደብ የተጣለባቸውን የሰአት እላፊ፣ የእንቅስቃሴዎች ገደብ እና ክልከላዎችን ይፋ አድርጓል። በዚህ መሰረት ፦ - ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል (ታርጋ ያለው ብቻ) አንድ ሰው ጭኖ ከጠዋት 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ…
#Oromia
በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚኖረውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማስቀጠል ሲባል በክልሉ የሰዎችና ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ መነሳቱ ተገልጿል።
የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሰዎችም ሆኑ ተሸከርካሪዎች ሕግና ስርዓትን አክብረው በማንኛውም ሰዓት መንቀሳቀስ እንደሚችሉ አሳውቋል።
በተለያዩ ቦታዎች ላይ ፍተሻዎች ስለሚኖሩ ማንኛውም በክልሉ የሚዘዋወር ሰው መታወቂያ መያዝ እንዳለበት ማሳሰቢያ ተላልፏል።
#ኢብኮ
@tikvahethiopia

" የትምህርት ስራ ከብሔርና ከፖለቲካ ነፃ ማድረግ ይገባል " ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ማህብርሰብ ጋር እየተወያዩ ነው ።
ሚኒስተሩ ከዩንቨርስቲው ማህበረሰብ ጋር የሚደርጉት ውይይት የአዲስአበባ ዮንቨርስቲን ችግሩች ለመፍታትና በቀጠይ የዩንቨርስቲውን አቅም ለማሳደግ ስራ ለመስራት እንደሆነ ተገልጿል።
ፕ/ር ብርሃኑ ፤ የትምህርት ስራ ከብሔርና ከፖለቲካ ነፃ ማድረግ እንደሚገባ በመድረኩ ላይ ተናግረዋል።
በውይይት መድረኩ ከዩንቨርስቲው የተለያዩ የትምህርት ክፍል የመጡ ተወካዩች ለትምህርት ሚኒስተሩ በቀጣይ መደርግ ያለባቸውን እና የነበሩ ከፍተቶች ተነስቷል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን(ጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው)

ችሎት !
አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ እንዲገደል የግድያ ቦታ አመቻችታለች ተብላ የተከሰሰችው ላምሮት ከማል በተሻሻለው አንቀጽ በ5 ሺህ ብር ዋስትና እንድትወጣ ታዘዘ።
የዋስትና ትዛዙን የሰጠው የከፍተኛው ፍርድ ቤት 2ኛ የፀረሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ፍርድ ቤቱ በወንጀለኛ መቅጫ ስነስርአት ህግ 113 ንዑስ ቁጥር 2 መሰረት የጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት የተከሰሰችበት የሽብር ወንጀል አንቀጽን በማሻሻል በቸልተኝነት የሚፈጸም የወንጀል ህግ አንቀጽ 575 መሰረት እንድትከላከል በተሰጠ ውሳኔ መነሻ አንቀጹ ዋስትና አያስከለክም ሲል ነው ዋስትና የተፈቀደላት።
ፍርድ ቤት በዚህ አንቀጽ የመከላከያ ማስረጃዋን ለመመልከት ለህዳር 23 እና 24 ቀን 2014ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።
የመረጃ ባለቤት ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

#Ethiopia
የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ ልኡክ ጄፈሪ ፊልትማን ጋር መወያየታቸውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ይፋ ባደረገው መረጃ ፤ በውይይቱ ወቅት ከአሸባሪው ሕወሐት ጋር የሚደረገው ጦርነት ስለሚቆምበት መንገድ የአሜሪካ ሐሳብ ምን እንደሆነ በልዩ ልኡኩ በኩል የተነሣ ሲሆን፣ አቶ ደመቀ የኢትዮጵያን አቋም አስረድተዋል።
አቶ ደመቀ መኮንን #በኮምቦልቻ እና #በላሊበላ ለሰብአዊ ርዳታ የሚውሉ በረራዎች መፈቀዳቸውን የገለፁ ሲሆን ወደ ትግራይም 369 ርዳታ የጫኑ መኪናዎች እንዲገቡ መፈቀዱን ገልፀዋል።
በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎችን ሁኔታ በተመለከተም ውይይት አድርገዋል።
አቶ ደመቀ ፥ " አሸባሪው ሕወሐት አሁንም ቢሆን በአፋርና በአማራ ክልሎች ጥቃት እየፈጸመና ከፍተኛ ሰብአዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውድመት እንዲሁም ሥነ ልቡናዊ ጉዳት እያደረሰ ነው " ያሉ ሲሆን ህወሓት ከሁለቱ ክልሎች ለቅቆ እንዲወጣ ግፊት ሊደረግበት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ፎቶ ፦ ፋይል

#Adama
ሀሰተኛ መታወቂያ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት እና በገንዘብ ተቀጡ።
በአዲስ አበባ እና በአዳማ ከተማ በተለያዩ ቀበሌዎች ስም በተዘጋጁ ሀሰተኛ መታወቂያ ሲንቀሳቀሱ የተያዙ 13 ሰዎች በእስራት እና በገንዘብ ተቀጡ።
የአዳማ ከተማ ፖሊስ የመረጃ ባለሞያ ረ/ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በሰጡት ቃል በእስራት እና በገንዘብ የተቀጡት በአዲስ አበባ ቀበሌዎች ስም ሀሰተኛ መታወቂያ ያሰሩት 10 ግለሰቦች በአዳማ ከተማ ቀበሌዎች ስም ሀሰተኛ መታወቂያ ያሰሩ 3 ግለሰቦች ናቸው።
ረ/ኢኒስፔክተር ወርቅነሽ አሁን ላይ ባለው ጥብቅ ቁጥጥር እና ፍተሻ ግለሰቦቹ ሊያዙ መቻላቸውን ገልፀዋል።
በአዳማ ቦኩ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው " ባቡር ጣቢያ " አካባቢአንደኛ ተከሳሽ (ወንድ)፣ ሁለተኛ ተከሳሽ (ወንድ) እና ሶስተኛ ተከሳሽ (ሴት) በህገወጥ መንገድ በተዘጋጀ መታወቂያ ወደ ድሬዳዋ ሊንቀሳቀሱ ሲሉ ተይዘዋል።
ሀሰተኛ መታወቂያው በቦሌ ክ/ከተማ ጠገቻ አራራ ቀበሌ ስም የተዘጋጀ እና ግለሰቦቹ በገንዘብ ያወጡት መሆኑና ቀበሌውን ሆነ አካባቢውን እንደማያውቁት ረ/ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ተናግረዋል።
አዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት ሶስቱ ግለሰቦች ፍርድ ቤት በሰነድ እና በሰው ማስረጃ ተረጋገጦ የቀረበለትን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ ትላንት እያንዳንዳቸው በ3 ዓመት እስራት እና በ1500 ብር የገንዘብ ቅጣት ተቀጥተዋል።
በተጨማሪ በህገወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች መታወቂያ በማውጣት ወደ ሀረር ነው የምንጓዘው በሚል 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው መዝገባቸው ሲጣራ ቆይቶ እያንዳዳቸው በ4 ዓመት እስራት እና በ5 ሺህ ገንዘብ ተቀጥተዋል።

ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 8 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,480 የላብራቶሪ ምርመራ 230 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 264 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አዲስ አበባ ገቡ።
የአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ኦባሳንጆ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመገናኘት፣ የሰላም መፍትሔ በማፈላለግ ሂደታቸው የደረሱበትን ሐሳብ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያብራሩ ይሆናል።
ከዚህ በተጨማሪም በሰብአዊ ርዳታ ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
ኦባሳንጆ በዚሁ ቆይታቸው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአፍሪካ ኅብረት አምባሳደሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ እስካሁን በደረሱባቸው ነጥቦች ዙሪያ ማብራሪያ ይሰጣሉ።
መረጃው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ነው።

#Mota : በሞጣ ከተማ በተካሄደ ድንገተኛ ፍተሻ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።
የከተማው ፖሊስ ህዳር 9 / 2014 ዓ/ም በተጠርጣሪ ስማቸው ባለው በሞጣ 03 ቀበሌ የአነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ማዕከል በተገነባው ሼድ የቤትና የቢሮ እቃ ስራዎች ድርጅትበተካሄደ ድንገተኛ ፍተሻ የተለያዩ መሳሪያዎች መገኘታቸው ተገልጿል።
ፖሊስ ፍተሻውን ያካሄደው ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ ነው።
በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ በድርጅቱ ውስጥ ፦
• 16 የተለያዩ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች፣
• 3 ክላሽንኮፕ ጠመንጃ፣
• 4 የቃታ መሳሪያዎች ፣
• 6 የተለያዪ ካዝናዎች፣
• 1 ገጀራ፣
• 54 የክላሽ ጥይት፣
• 16 የሽጉጥ ጥይቶችና የተለያዩ የመሳሪያ ወለዋወጫዎች መገኘቱን ፖሊስ አመልክቷል።
ፖሊስ ህብረተሰቡ ላደረገው ጥቆማ ምስጋና ያቀረበ ሲሆን ተጠርጣሪው ለጊዜው በመሰወሩ ተጠርጣሪውን ለመያዝ በሚደረገው ጥረት የህብረተሰቡ ጥቆማ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል።

#ETHIOPIA
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልክተኞች ኮሚቴ ቢሮ አባላት፣ ከ5ቱ ቀጣናዊ የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲኖች፣ ከአጠቃላይ የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲን እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበርን ካካተተ የልዑካን ቡድን ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ፦
• የሴኔጋል አምባሳደር የኢትዮጵያ ሉዑላዊነት እና የግዛት አንድነት በተመለከተ የአፍሪካ አምባሳደሮች የማይናወጥ አቋም አላቸው ብለዋል። በህዝብ ከተመረጠው እና ቅቡልነት ካገኘው የኢትዮጵያ መንግስት ጎን እንደሚቆሙኑ እና አጋርነታቸው የጸና መሆኑን አሳውቀዋል፡፡
• አምባሳደሮቹ ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ችግር ለመፍታት አቅሙ እንዳላት እንደማይጠራጠሩና የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ሰላማዊ መፍትሄ ለማፈላለግ ለሚያደርጉት ጥረት የአፍሪካ አምባሳደሮች ሙሉ ድጋፍ እንደማይለያቸው ገልጸዋል፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን ምን አሉ ?
• ኢትዮጵያ አሁን በገጠማት አስቸጋሪ ሁኔታ በፓን አፍሪካዊነት መርህ አፍሪካውን ወንድሞች እና እህቶች ላሳዩት አጋርነት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ልዩ አክብሮት ያላቸው መሆኑን ገልፀው አመስግነዋል።
• አሉ ሚባሉ የአገራችንን መሠረታዊ ችግሮችን ለመፍታት መንግስት በአገር ደረጃ ሁሉን አቀፍ ውይይት ለመጀመር ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
• በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያውያን ያጋጠማቸውን ፈተና በጋራ ለመሻገር በአንድነት እየተረባረቡ መሆኑንም በዝርዝር አብራርተዋል፡፡
ያንብቡ : https://telegra.ph/ETHIOPIA-11-18-2

Telegraph
ETHIOPIA
#ETHIOPIA ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልክተኞች ኮሚቴ ቢሮ አባላት፣ከአምስቱ ቀጣናዊ የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲኖች፣ ከአጠቃላይ የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲን እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበርን ካካተተ የልዑካን ቡድን ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ በወቅቱም ቡድኑን በመወከል በኢትዮጵያ የሴኔጋል አምባሳደር ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ…
#ETHIOPIA
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከእንግሊዝ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጋር በስልክ ተወያዩ።
ውይይቱ በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ነበር።
በውይይቱ ቪኪ ፎርድ ምን አሉ ?
- ከህወሓት ሃይሎች ጋር ያለውን ግጭት ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲያገኝ እንዲሁም ሁሉም ወገኖች ግጭት አባባሽ ከሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ አስተያየቶችን እንዲያቆሙ አሳስበዋል።
- ህወሓት ግጭቱን የማስፋፋት ድርጊት እንዲያቆም ፤ መንግስት በኩልም ለትግራይ፣ አማራ እና አፋር ህዝቦች ሰብአዊ ርዳታ እንዲደርስ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ጠይቀዋል።
- በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴን ኦባሳንጆ ሰላም ለመፍጠር እያደረጉ ያለውን ጥረት በደስታ እንደሚቀበሉ ፤ ለዚህ የሰላም ጥረት እንግሊዝ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልፀዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ?
- በህወሃት ጠብ አጫሪነት ምክንያት በመንግስት የተደረጉ በርካታ የሰላም ጥረቶች እንዳልተሳኩ አስረድተዋል።
- ህወሓት በአማራና አፋር ክልል ወረራ በመፈፀሙ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ገልፀዋል።
- የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦትን በተመለከተ ፥ ወደ መቐለ፣ ኮምቦልቻ እና ሰመራ የሚደረጉ ሰብዓዊ በረራዎችን ለማስቀጠል ከሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር እየሰራ እንደሚገኝና ሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽ ለማድረግ የመንግስትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
- ለሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት የሚመለከታቸው አካላት በአባላ በኩል የየብስ ትራንስፖርት በማመቻቸት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።
- ህወሓት ለወታደራዊ አገልግሎት ያዋላቸው ከ860 በላይ የእርዳታ ተሽከርካሪዎች መመለስ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር