TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ብፁዕ አቡነ በርናባስ የዋግህምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽህፈት ቤት በዛሬው ዕለት አስታወቀ።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፥ የሲዳማ ጌዲዮ አማሮና ቡርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለኢኦተቤ ቴሌቭዥን እንደገለጹት ብፁዕ አቡነ ባርናባስ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና ቀደም ሲል በማኅበራዊ ሚዲያ ሲባል እንደነበረው ክፉ እንዳልገጠማቸው አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ EOTC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Uganda: ዛሬ በኡጋንዳ በደረሱ 2 የሽብር አደጋዎች 3 ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ቆሰሉ፡፡ ካምፓላ ሁለት ቦታዎች በደረሱ የአጥፍቶ ጠፊዎች የሽብር ጥቃት ይ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የከተማይቱ ፖሊስ አስታቋል፡፡ በአደጋው ከቆሰሉት 33 ሰዎች ውስጥ አምስቱ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተገልጿል፡፡ የተጎጂዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ ይችላል፡፡…
#UGANDA

የኢትዮጵያ መንግስት በዩጋንዳ መዲና ካማፓላ ከተማ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አወገዘ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ በትናንትናው ዕለት በካምፓላ ሁለት ቦታዎች ላይ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት በንጹሃን ዜጎችና ፖሊስ ባልደረቦች ላይ በደረሰው የሞትና የአካል ጉዳት ማዘኑን ገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት በጥብቅ እንደምታወግዝም ነው በመግለጫው የተመላከተው።

ኢትዮጵያና ዩጋንዳ በጋራ ሽብርተኝነትን የመዋጋት ልምድ እንዳላቸው በመጥቀስ ጥቃቱ ዩጋንዳም ሆነ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ሽብርተኝነትን የበለጠ በቁርጠኝነት ከመዋጋት እንደማያግዳቸው የኢትዮጵያ መንግስት ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለኡጋንዳ ህዝብና መንግስት እንዲሁም ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ/ የውጭ ጉዳዩ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Uganda: ዛሬ በኡጋንዳ በደረሱ 2 የሽብር አደጋዎች 3 ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ቆሰሉ፡፡ ካምፓላ ሁለት ቦታዎች በደረሱ የአጥፍቶ ጠፊዎች የሽብር ጥቃት ይ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የከተማይቱ ፖሊስ አስታቋል፡፡ በአደጋው ከቆሰሉት 33 ሰዎች ውስጥ አምስቱ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተገልጿል፡፡ የተጎጂዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ ይችላል፡፡…
ኬንያ በተጠንቀቅ ላይ ናት።

ኬንያ፣ ትናንት በኡጋንዳ ሽብርተኞች ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ዜጎቿ ሁኔታዎችን በንቃት እንዲከታተሉ አሳስባለች።

ናይሮቢ የትኛውንም ዐይነት የሽብር ጥቃት ለመከላከል በሚያስችል ተጠንቀቅ ላይ መሆኗን አስታውቃለች፡፡

በትናንቱ የካምፓላ ፍንዳታ አጥፍቶ ጠፊዎቹን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆስለዋል፡፡

ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ዝርዝር ማብራሪያን የሰጡት የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ ጥቃቱ በሽብርተኝነት በተፈረጀው አሊያንስ ፎር ዴሞክራሲ (ADF) ሶስት አጥፍቶ ጠፊዎች መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡

የኬንያ መንግስት ቃል አቀባይ የሃገራቸው የጸጥታ አካላት በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውንና አጎራባች በሆኑ የድንበር አካባቢዎች ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኬንያውያን ነቅተው አካባቢቺውን እንዲጠብቅና አዳዲስ ነገሮችን ሲመለከቱ ለፖሊስ እንዲያስታውቁም ኮሎኔል ሳይረስ ኦጉና በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
Ethiopian Human Rights Commission - 1.pdf
265.7 KB
ኢሰመኮ፦

የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ ከአዋጁ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችን አያያዝ የእስር ሁኔታና የታሳሪዎችን ሁኔታ ለመከታተል በሚያስችለው መልኩ መረጃ ማሰባበሰብ አለመቻሉን አሳውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ እና በየካ ክ/ ከተሞች የሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎችንና ማቆያዎችን ጎብኝቷል፤ ታሳሪዎችንና ቤተሰቦቻቸውን አነጋግሯል፤ በክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ ካሉ ከፖሊስ አባላት እና አመራሮች ጋር ውይይት በማድረግ መረጃዎችን አሰባስቧል፡፡

በአንጻሩ የአዲስ ከተማ፣ የልደታ፣ የጉለሌ፣ የቦሌ እና የአራዳ ክፍለ ከተማ ኃላፊዎች ከበላይ ትእዛዝ ካልመጣልን መረጃ አንሰጥም፣ እስረኛም መጎብኘት አትችሉም በማለታቸው ኮሚሽኑ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባር እና ኃላፊነት እንዳይወጣ ምክንያት ሆነዋል፡፡

በኮሚሽኑ ክትትል የታሰሩ ሰዎችን ብዛት በሚመለከት የተሟላ መረጃ ለማግኘት እንዳልቻለ አሳውቋል።

ኮሚሽኑ በአንጻራዊነት የተሟላ መረጃ ያገኘው ከቂርቆስ ክ/ከተማ ሲሆን መረጃው በተሰጠበት ኅዳር 2/2014 ዓ.ም በክፍለ ከተማው ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ 714 ሰዎች መታሰራቸውንና ከነዚህ ውስጥ 124ቱ ሴቶች እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።

በሌሎች ክ/ከተሞች በተመሳሳይ ሁኔታ እስሮች ሲከናወኑ ስለነበርና በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሂደት አሁንም የቀጠለ በመሆኑ በአዲስ አበባ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መታሰራቸው ይገመታል።

በድሬዳዋ ደግሞ እስከ 300 የሚሆኑ ሰዎች ታስረዋል።

የተወሰኑ ሰዎች በሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት መረጃ መሰረት የሚታሰሩ ሲሆን አብዛኛዎቹ ግን ከህብረተሰቡ ተገኘ በተባለ ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር እንደሚውሉና ከመካከላቸው የትግራይ ተወላጆች የሆኑ ሰዎች ብዛት ከፍተኛ ነው።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል (PDF)

@tikvahethiopia
#Somalia #Ethiopia #Sudan #SouthSudan

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እና የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ባሉ አሁናዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ላይ ተወያይተዋል።

ውይይቱን በተመለከተ አንቶኒ ብሊንከን በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ላይ ፥ ውጤታማ ውይይት መደረጉን ገልፀዋል ።

ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው ቀጠናዊ ሰላም እና ደህንነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ በኢኮኖሚ እንዲሁም በሌሎችም ቀጠናዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ከአንቶኒ ብሊንከን ጋር መወያየታቸውን በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።

ዶ/ር ወርቅነህ ፥ " በቀጣይም ከአሜሪካ ጋር በበርካታ ዘርፎች አብረን እንሰራለን " ያሉ ሲሆን " አሜሪካ የኢጋድ ወሳኝ አጋር ናት "ብለዋል።

Photo : Secretary Antony Blinken

@tikvahethiopia
የልዩ ዕድል ሎተሪ የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች ፦

1ኛ. 20,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 1535477

2ኛ. 10,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 0165840

3ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 0411256

4ኛ. 3,000,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 1543809

5ኛ. 1,500,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 0503560

6ኛ. 750,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር 0837825

7ኛ. 300,000 ብር የሚያስገኘው የ7ኛ ዕጣ ቁጥር 1907437

8ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 20,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 30688

9ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 10,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 02294

10ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 5,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 96608

11ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 2,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 3696

12ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 5789

13ኛ. 2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 846

14ኛ. 20,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 300 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 67

15ኛ. 200,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 100 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር (የማስተዛዘኛ ዕጣ) ደግሞ 4 ቁጥር በመሆን ወጥቷል፡፡

ምንጭ፦ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

4 ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ በንብረት ግምጃ ቤት ውስጥ የተቀመጡ ከ 1 ሺህ 800 በላይ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ህዳር 8 ቀን 2014 ዓ/ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ብርበራ ከ1 ሺህ 800 በላይ ጥይቶች በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በቤተ ክህነቱ ግቢ በሚገኝ የንብረት ግምጃ ቤት በሚገኝ የፅህፈት እና የፅዳት እቃዎች ማስቀመጫ ውስጥ በተደረገው ብርበራ የተገኙት 1ሺህ 363 የብሬን እና 493 የሽጉጥ ጥይቶች ናቸው፡፡

በተጨማሪም 2 የጥይት ማስቀመጫ ሳጥኖች እና 1 የክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ ካዝና ተይዟል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 1 ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ ሲሆን ህብረተሰቡ በስልክ፣ በአካል እና ሌሎች የመገናኛ አማራጮችን በመጠቀም እየሰጠ የሚገኘው ጥቆማ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፥ " አሸባሪው የህወሃት ቡድን ለሽብር ተግባሩ የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በተለያዩ የኃይማኖት ተቋማት ውስጥ ሲያከማች እና በኃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ግለሰቦችን በተላላኪነት እያሰማራ በበርካታ ንፁሃን ላይ አሰቃቂ እልቂት ሲፈፅም እንደቆየ ይታወሳል " ብሏል።

@tikavhethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sidama ከነገ ጀምሮ በሲዳማ ክልል የሰአት እላፊ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ክልከላዎች ተላለፉ። የሲዳማ ክልል ኮማንድ ፖስት ከነገ ጀምሮ ገደብ የተጣለባቸውን የሰአት እላፊ፣ የእንቅስቃሴዎች ገደብ እና ክልከላዎችን ይፋ አድርጓል። በዚህ መሰረት ፦ - ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል (ታርጋ ያለው ብቻ) አንድ ሰው ጭኖ ከጠዋት 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ…
#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚኖረውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማስቀጠል ሲባል በክልሉ የሰዎችና ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ መነሳቱ ተገልጿል።

የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሰዎችም ሆኑ ተሸከርካሪዎች ሕግና ስርዓትን አክብረው በማንኛውም ሰዓት መንቀሳቀስ እንደሚችሉ አሳውቋል።

በተለያዩ ቦታዎች ላይ ፍተሻዎች ስለሚኖሩ ማንኛውም በክልሉ የሚዘዋወር ሰው መታወቂያ መያዝ እንዳለበት ማሳሰቢያ ተላልፏል።

#ኢብኮ

@tikvahethiopia
" የትምህርት ስራ ከብሔርና ከፖለቲካ ነፃ ማድረግ ይገባል " ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ማህብርሰብ ጋር እየተወያዩ ነው ።

ሚኒስተሩ ከዩንቨርስቲው ማህበረሰብ ጋር የሚደርጉት ውይይት የአዲስአበባ ዮንቨርስቲን ችግሩች ለመፍታትና በቀጠይ የዩንቨርስቲውን አቅም ለማሳደግ ስራ ለመስራት እንደሆነ ተገልጿል።

ፕ/ር ብርሃኑ ፤ የትምህርት ስራ ከብሔርና ከፖለቲካ ነፃ ማድረግ እንደሚገባ በመድረኩ ላይ ተናግረዋል።

በውይይት መድረኩ ከዩንቨርስቲው የተለያዩ የትምህርት ክፍል የመጡ ተወካዩች ለትምህርት ሚኒስተሩ በቀጣይ መደርግ ያለባቸውን እና የነበሩ ከፍተቶች ተነስቷል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን(ጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው)

@tikvahethiopia
ችሎት !

አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ እንዲገደል የግድያ ቦታ አመቻችታለች ተብላ የተከሰሰችው ላምሮት ከማል በተሻሻለው አንቀጽ በ5 ሺህ ብር ዋስትና እንድትወጣ ታዘዘ።

የዋስትና ትዛዙን የሰጠው የከፍተኛው ፍርድ ቤት 2ኛ የፀረሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ፍርድ ቤቱ በወንጀለኛ መቅጫ ስነስርአት ህግ 113 ንዑስ ቁጥር 2 መሰረት የጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት የተከሰሰችበት የሽብር ወንጀል አንቀጽን በማሻሻል በቸልተኝነት የሚፈጸም የወንጀል ህግ አንቀጽ 575 መሰረት እንድትከላከል በተሰጠ ውሳኔ መነሻ አንቀጹ ዋስትና አያስከለክም ሲል ነው ዋስትና የተፈቀደላት።

ፍርድ ቤት በዚህ አንቀጽ የመከላከያ ማስረጃዋን ለመመልከት ለህዳር 23 እና 24 ቀን 2014ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

የመረጃ ባለቤት ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia