TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ጅቡቲ በጎረቤት ሀገር ላይ ለሚፈጸም ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት መጠቀሚያ ሆና አታገለግልም " - ማህሙድ አሊ ዩሱፍ

የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ሀገራቸው ጅቡቲ በጎረቤቶቿ ላይ ለሚፈጸም ጣልቃ ገብነት ግዛቷ መጠቀሚያ እንደማይሆን አሳውቀዋል።

ሚኒስትሩ ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ይህንን ያለቱ ትላንት በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት ነው።

ሚኒስትሩ ሀገራቸው ጅቡቲ " በጎረቤት አገር ላይ ለሚፈጸም ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት መጠቀሚያ ሆና አታገለግልም " ብለዋል።

ይህ የሚኒስትሩ አስተያየት የመጣው አንድ ጂቡቲ ውስጥ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ከፍተኛ ወታደራዊ ጄነራል ዊሊያም ዛና ለቢቢሲ በኢትዮጵያ ቀውስ የሚከሰት ከሆነ የአሜሪካ ወታደሮች "ከእዚህ ምላሽ ይሰጣሉ" በማለት ከተናግሩ በኃላ ነው።

የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ "አንዳንዶች የጂቡቲ ግዛት በጎረቤት አገራት ላይ ለሚፈጸም ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል" በማለት የጄነራሉን ንግግር ተከትሎ የተፈጠረውን ስሜት የጠቀሱ ሲሆን ይህ ግን እንደማይሆን አስረግጠው ተናግረዋል።

ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ፥ "ጅቡቲ ከጎረቤቶቹ ጋር ትስስር ያለው የጂቡቲ መንግሥት ይህ እንዲሆን አይፈቅድም" ገልፀዋል።

ለቀይ ባሕር ስልታዊ መተላለፊያ በሆነችው ጂቡቲ ውስጥ የጦር ሰፈርና ወታደሮች ካሏቸው አገራት መካከል አንዷ የሆነችው አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ ቀውስ የሚፈጠር ከሆነ ወታደሮቿ ምላሽ እንደሚሰጡ ጅቢቲ ባሉት ጄነራሏ አማካኝነት ስንትናገር ነበር።

Credit - Mahmoud Ali Yossouf Twitter Page-BBC

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ 🇪🇹 ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ A350-900 በዱባይ ኤር ሾው 2021 ለእይታ ቀርቧል።

የዱባይ ኤር ሾው ከ1 ሺህ 200 በላይ ኤግዚቢሽን አቅራቢዎችና ከ148 በላይ ሀገራት ተወካዮች የሚሳተፉበት ትልቅ የአየር ትዕይንት ነው።

Credit : የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopia
ፎቶ : አየር ኃይል በኤር ፓሊስ ኮማንዶ ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመርቋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በመጀመሪያ ዙር በኤር ፓሊስ ኮማንዶ ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመርቋል።

ፎቶ ፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#UN

UN በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ጦርነቱ እየተባባሰ ባለበት አካባቢዎች የነብስ አድን የሰብአዊ ዕርዳታ የሚውል 40 ሚሊዮን ዶላር የእርዳታ ገንዘብ ድጋፍ መመደቡን አስታውቋል።

የUN የርዳታ ሃላፊ ማርቲን ግሪፍትስ ፥ የገንዘብ ድጋፉ ትግራይ ክልልን ጨምሮ በጦርነቱ በተጎዱ የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል እና ድርቅ ለተከሰተበት ደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል አስቀድሞ ምላሽ ለመስጠት ታስቦ የተለገሰ መሆኑን ተናግረዋል።

ነገርግን በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ ለመደገፍ የሚያስፈልገውን የ350 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ጨምሮ በመላው ኢትዮጵያ ለሚከናወኑ የሰብአዊ ድጋፍ ተግባራት የ1.3 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ክፍተት እንዳጋጠማቸው ኃላፊው በመግለጫቸው አሳስበዋል።

ግሪፊትስ ፥ " በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብአዊ ቀውሱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ሄዶ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሕይወታቸው አደገኛ ጠርዝ ላይ ይገኛሉ " ብለዋል። በመላ ሀገሪቱ መሰረታዊ ፍላጎቶች እየጨመረ መምጣቱንም ገልጸዋል።

ለአስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቱ የተመደበው ገንዘብ 25 ሚሊዮን ዶላሩ አዲስ ጥሬ ገንዘብ ከUN ማዕከላዊ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ፈንድ የተገኘ መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን የቀረው 15 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ ተቀማጭነቱን ሀገር ውስጥ ካደረገ የሰብአዊ ረድኤት ገንዘብ አቅራቢ የተገኘ መሆኑን ተናግረዋል።

ገንዘቡ በትግራይ ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች በግጭቱ ለተጎዱ ወገኖች ከለላ እና የነብስ አድን ድጋፍ ይውላል ተብሏል።

የገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ በድርቅ በተጎዱት የደቡባዊ ሶማሌና የኦሮሚያ ክልሎች የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ጨምሮ እንደ ኮሌራ ያሉ የውሃ ወለድ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም ለእንስሳት መኖ አቅርቦትና እንክብካቤ ስራዎች እንደሚውል መገለፁን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ጊዜያዊ_መታወቂያ !

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ መመሪያ ፥ የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ስርዓት መመሪያ አውጥቷል፡፡

* መመሪያው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 7 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 4,775 የላብራቶሪ ምርመራ 157 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 298 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
ከሀሰተኛ መረጃ ተጠንቀቁ - አዲስ አበባ !

ሰሞኑን አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ተክለኃይማኖት ቤ/ክርስቲያን ውስጥ በአስክሬን ሳጥን ተደርጎ የጦር መሳሪያ ተቀብሮ ተያዘ በሚል በተለየዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተናፈሰው ወሬ ትክክለኛ መረጃ እንዳልሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አረጋግጫለሁ ብሏል።

ከልደታ ክ/ከተማ በተገኘው መረጃ መሰረት ግለሰቡ ከኢትዮጲያ ውጭ በመሞቱ ምክንያት ተክለ ሐይማኖት አካባቢ ሟቹን የሚያውቁት ነዋሪዎች አስፈላጊውን ህጋዊ ሂደት ተከትለው ከውጭ እንዲመጣ በማድረግ አሰክሬኑ በተክለ ሐይማኖት ቤ/ክርስቲያን እንዲያርፍ አደርገዋል፡፡

ቀብሩ ሲፈፀም ጥቂት ሰዎች በተገኙበት መሆኑና የአስክሬን ሳጥኑ ከመደበኛውና ከሚታወቀው አይነት ውጪ መሆኑ ያጠራጠራቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ለፖሊስ መረጃ ሰጥተዋል፡፡

ፖሊስ የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ ኮሚቴ አዋቅሮና ከቤተ-ክርስቲያኗ አባቶች ጋር በመሆን ፍተሻ በማድረግ በተቀበረው የአስክሬን ሳጥን የሰው አስክሬን እንጂ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ልተገኘ መሆኑን ተረጋግጧል፡፡

ፖሊስ ባስተላለፈው መልዕክት ማነኛውንም አጠራጣሪ ነገሮች ሲታዩ መረጃውን ለፀጥታ አካላት የማድረሱ ተግባር የሚደነቅና ሊበረታታ የሚገባው ሲሆን ከዚሁ ጎን ለጎን ህብረተሰቡ ትክክለኛውን መረጃ ከትክክለኛ ቦታ የማግኘት ባህሉን ሊያጎለብት ይገባል ሲል አሳስቧል፡፡

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

ቤት የሚገዙ፣ የሚሸጡ ሁሉ ስራቸው ህገወጥ ስለሆነ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት አሳስቧል።

የቋሚ ንብረት ሽያጭ የቆመ ቢሆንም በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎቱ ሳይጀመር ሽያጭ እና ማስተላልፈ በመንደር ውል እና በውክል እየተሰራ መሆኑ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።

የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ፤ በውክልናም ሆነ በመንደር ውል የቤት ሽያጭ ማከናወን ህጉ እንደማይፈቅድ ገልፀዋል።

አገልግሎቱ የሚጀምርበትን ጊዜ እናሳውቃለን ብለዋል።

" ቤት ሽያጭ ውል ሰነድ የማረጋገጥ አገልግሎት ነው " ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ " ይህ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጧል። ተቋሙ በተለይ ከአ/አ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን ህገወጥ ይዞታዎችን የማረጋገጥ ስራ እየሰረ ስለሆነ ከዛ ጋር ተያይዞ ላልተገባ ሰዎች ያልተገባ ውል ውስጥ እንዳይገቡ ያን የማረጋገጥ ስራ እስኪጠናቀቅ በጊዜያዊነት አገልግሎቱን መስጥ ቆሟል " ሲሉ አስረድተዋል።

ይሄ ህገወጥ ይዞታዎችን የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሙሉቀን ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ላልተወሰ ጊዜ የማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም መኖሪያ ቤት ሽያጭ / በስጦታ የማስተላለፍ ውሉ አሁንም ለጊዜው እንደተቋረጠ ይቀጥላል ሲሉ አሳውቀዋል።

ተቋሙ የተቋረጠውን አገልግሎት በሚጀምርበት ሰዓት በግልፅ በተለያየ ሚዲያ መረጃውን የሚሰጥ መሆኑን አመልክተዋል።

በተለይ የተጠራቀመ አገልግሎት ካለ ተገልጋዮች በሰልፍ ብዙ ሳንይገላቱ ለመስራት አሰራር ተዘርግቶ ይኬዳል ሲሉ ጠቁመዋል።

ህብረተሰቡ ላልተገባ የመንደር ውል ሆነ ባልተገባ መረጀ ላይ ተመስርቶ ከሚደረጉ ውሎች እንዲቆጠብ የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት ለሸገር ራድዮ በሰጠው ቃል አሳስቧል።

@tikvahethiopia