TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የጦር መሳሪያ ምዝገባ እስከ ህዳር 3 ድረስ እንዲካሄድ ተወስኗል። ፈቃድ ያለው ይሁን የሌለው የጦር መሳሪያ በእጁ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ በአዲስ አበባ ደረጃ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና በስሩ በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች እየቀረበ መሳሪያውን እንዲያስመዘግብ ከዚህ ቀደም ጥሪ መተላለፉ አይዘነጋም። ምዝገባው ለሁለት ጊዜ መረዛሙ ይታወሳል። ምዝገባውን በሃገር አቀፍ ደረጃ ወጥ ለማድረግ…
#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ትላንትና ድረስ ከ23 ሺህ በላይ መሳሪያዎች የተመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 42 በመቶ የሚሆኑት ፍቃድ የሌላቸው መሆኑን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገኘው ሪፖርት ያስረዳል።
በአዲስ አበባ ፍቃድ ያለውም ይሁን የሌለው የጦር መሳሪያ በእጁ ላይ የሚገኝ ማንኛውም ግለሠብ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና በስሩ በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች በግንባር በመቅረብ እንዲያስመዘግብ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል።
የምዝገባ ጊዜው በተለያዩ ምክንያቶች ሲራዘም እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ከቀናት በፊት የተራዘመው የምዝገባ ቀን ዛሬ አርብ ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ/ም ተጠናቋል።
@tikvahethiopia

አሜሪካ በኤርትራ ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለች።
የአሜሪካ ግምጃ ቤት በድረገጹ እንዳስታወቀው በሁለት የኤርትራ ባለስለጣናት እና በ4 ተቋማት ላይ ማዕቀብ ጥሏል።
አሜሪካ ኤርትራ ላይ አዲስ ማዕቀብ የጣለችው በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ መሆኑን አሳውቃለች።
እንደ አሜሪካ ግምጃ ቤት መረጃ ማዕቀቡ የተጣለባቸው ግለሰቦች አብርሃ ካሳ ነማርያም የኤርትራ ብሄራዊ ደህንነነት ቢሮ ሀላፊ እና የኤርትራ ህዝብ ዲሞክራሲ እና ፍትህ ንቅናቄ የኢኮኖሚ አማካሪ የሆኑት ሀጎስ ገብረህይወት ናቸው።
በተጨማሪም የኤርትራ መካላከያ ሰራዊት እና የኤርትራው ገዢ ፓርቲ ህዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲና ፍትሕ (ህግደፍ) ማዕቀብ እንተጣለባቸው የአሜሪካ ግምጃ ቤት አስታውቋል።
የኤርትራ ገዢ ፓርቲ ነብረት የሆነው ህድሪ ትረስት እና የቀይ ባሕር ንግድ ኮርፖሬሽንም ማዕቀቡ የተጣለባቸው ተቋማት መሆናቸው ታውቋል።
የአሜሪካ ግምጃ ቤት ማዕቀቡ የተጣለባቸው ተቀዋማት እና ግለሰቦች በአሜሪካ ያላቸው ንብረት እንዳይንቀሳቀስ እና የጉዞ እገዳን ያካትታል።
ማዕቀቡ የተጣለባቸው ግለሰቦች እና ተቋማት በትግራይ ክልል በንጹሃን ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽማዋል በሚል መሆኑንም ግምጃ ቤቱ አስታውቋል።
አሜሪካ ከዚህ ቀደም ከትግራይ ክልለ ጋር በተያያዘ በኤርትራ ጦር ዋና አዛዥ በጀነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስ ላይ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል።
ምንጭ፦ አል አይን

የትምህርት ሚኒስትሩ በUNESCO አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ምን አሉ ?
ፓሪስ ላይ 41ኛው የዩኔስኮ አጠቃላይ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህ ጉባኤ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ንግግር አድርገዋል።
የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እና ዋና ዋና የመገናኛ ዘዴዎች መስፋፋታቸውን ተከትሎ አብዛኛው ሀገራት በተሳሳቱ መረጃዎች እና የሀሰት ዜናዎች እየተጎዱ መሆናቸውን የገለፁት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያም በዚህ ሰለባ ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ ናት ብለዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፦
" ሀገሬ ኢትዮጵያ የዚህ ክስተት ሰለባ ከሆኑ አንዷ ነች። የማህበራዊ መገናኛ አላግባብ መጠቀም እንደነዳጅ ለአሁኑ ግጭት መባባስ ብሎም ተነግሮ የማያቅል ጉዳት በማድረስ ንፁሃን ዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።
መሰረታዊ የዴሞክራሲያዊ መርሆችን ሳናናጋ የተሳሳተ የማህበራዊ መገናኛ ዜዴ አጠቃቀም እያደረሰ ያለውን ጉዳት በመቀነስ እንደ UN ቤተሰብ ጠንክረን መስራት አለብን"
ያንብቡ : https://telegra.ph/UNESCO-11-12

Telegraph
UNESCO
የትምህርት ሚኒስትሩ በUNESCO አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ምን አሉ ? ፓሪስ ላይ 41ኛው የዩኔስኮ አጠቃላይ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል። በዚህ ጉባኤ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ንግግር አድርገዋል። ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የተመድ 2030 ዘላቂ የልማት አብዛኛው ግቦችን በብሄራዊ እቅዷ ውስጥ በሚመች መልኩ አካታ እየሰራች ብትገኝም ባለፉት 2 ዓመታት በዓለማችን የተከሰተው የኮቪድ…
#ሪፖርት
ከቀናት በፊት የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር /TPLF/ ታጣቂዎች በአማራ ክልል ውስጥ የፈፀሟቸውን ግፎች በሪፖርቱ ያሳወቀው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ትላንት ሌላ ኢትዮጵያን የሚመለከት ሪፖርት ይዞ ወጥቷል።
ይኸው ሪፖርት በአዲስ አበባ ከተማ የትግራይ ተወላጆችን ትኩረት ያደረገ እስር እየተካሄደ መሆኑን የሚገልፅ ነው።
አምነስቲ በዚህ ሳምንት በኢትዮጵያ ጉዳይ ሪፖርት ሲያቀርብ ይህ 2ኛው ነው።
አምነስቲ በትላንት ሪፖርቱ በአ/አ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ እስር እየተካሄደ ነው ፤ እስሩ የተባባሰው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኃላ መሆኑን ገልጿል።
ሰዎች ከቤት ወደ ቤት በሚደረግ አሰሳ በቁጥጥር ስር ይውላሉ ፤ በአዲስ አበባ የሚገኙ የፖሊስ ጣቢያዎች በመሙላታቸው በቁጥጥር ስር የዋሉ የመንግስት ሰራተኞች፣ የኦርቶዶክስ ቄስ እና የህግ ጠበቃን ጨምሮ ሌሎች እስረኞች በወጣቶች ማእከላት እና ሌሎች መደበኛ ባልሆኑ የማቆያ ጣቢያዎች ታስረዋል ብሏል አምነስቲ ኢንተርናሽናል።
ሙሉ ሪፖርቱ : https://www.amnesty.org/en/latest/news/2021/11/ethiopia-tigrayans-targeted-in-fresh-wave-of-ethnically-motivated-detentions-in-addis-ababa/
ከቀናት በፊት #ኢሰመኮ በአ/አ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ ጀምሮ ሰዎች ከስራ ቦታቸው፣ ከመኖሪያ ቤታቸው እና ከመንገድ ላይ ጭምር በቁጥጥር ስር ውለው በተለያዩ የከተማዋ ፖሊስ ጣቢያዎች ተይዘው እንደሚገኙ አረጋግጫለሁ ሲል ሪፖርት ማድረጉ አይዘነጋም።
ኢሰመኮ እስሩ ማንነት/ብሄርን መሰረት ባደረገ መልኩ በሚመስል ሁኔታ መከናወኑን ማሳወቁ ይታወሳል ፤ (ምንም እንኳን በግልፅ እስሩ የቱን ብሄር መሰረት እንዳደረገ ባይገልፅም) ።

ማንነትን/ብሄርን መስረት አድርጎ እስር እየተፈፀመ ነው ስለሚባለው ጉዳይ መንግስት ምላሹ ምንድነው ?
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ በኃላ ማንነት /ብሄርን መሰረት ያደረገ እስር በጣም ተስፋፍቷል በሚሉ የተለያዩ ዘገባዎች የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ሆነ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ዘገባዎቹ ትክክል እንዳልሆኑ በተለያየ ጊዜ ገልፀዋል።
ለአብነት ያህል ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ ኮሚኒኬሽን ብሄር /ማንነት መሰረት ያደረገ እስር እየተፈፀመ ነው የሚባለው መሰረት የሌለው ነው ብሏል።
ወቅቱን ሀገርን ለማዳን ርብርብ ላይና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ በመሆኑ የፀጥታ አካላት የተጠናከረ የፀጥታ ስራ እያከናወኑ መሆኑንና እየተካሄደ ባለው ሀገርን የመታደግ ስራ ተጠርጣሪዎች ንፁህነታቸው ከተረጋገጠ ይቅርታ እየተጠየቁ እንደሚፈቱ አሳውቋል።
በከተማው እየተደረገ ባለው አሰሳ አሸባሪውን ድርጅት ህወሓት ሲደግፉ፣ መረጃ ሲሰጡ እና ገንዘብ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ግለሰቦች መኖራቸውንም ገልፆ ነበር።
ከአልጀዚራ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በግለሰባዊ ማንነቱ የተሰረ አንድም አካል እንደሌለ ተናግረዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፥ ፖሊስ በሚደርሰው መረጃ መሰረት ምርመራ እንደሚያካሂድ ገልፀው የትኛውም ግለሰብ በብሄሩ እና በሌሎች ግለሰባዊ ምክንያት አልታሰረም ብለዋል።
ፖሊስ በሚያካሂደው የመረጃ ማጣራት ስራ ግለሰቦች ካልተፈቀደ ድርጊት ነፃ መሆናቸው ተረጋግጦ ነፃ እንደሚለቀቁም አምባሳደሩ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ በህልውና ዘመቻ ላይ እና በህግ ማስከበር ተግባር ላይ ናት ያሉት አምባሳደር ሬድዋን እያንዳንዱ ነገር ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግበት ነው የተናገሩ።

#DrAbrahamBelay
የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ፥ ኢትዮጵያ የተደቀነባት የደህንነት ፈተና የመነጨው ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላትን አገር ለማፍረስና ለማዳከም አልመው ከሚሰሩ የውስጥና የውጭ ሃይሎች መሆኑን ገለፁ።
ዶ/ር አብርሃም ፥ " እነዚህ አጭበርባሪ ተዋናዮች ግባቸውን ይፋ አድርገው በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያን መንግስት በመጣል በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ሊኖረው የማይችል የራሳቸውን አሻንጉሊት መንግስት ለማስቀመጥ ፍላጎት አላቸው " ብለዋል።
“የዓለም ዓቀፍ አጋሮቻች ይህንን ተረድተው የህዝብ ምርጫ የሆነውን የኢትዮጵያ መንግስት መደገፍና ከፋፋይ አጀንዳ ካለው አሸባሪው ህወሃት በተቃራኒ ሊቆሙ ይገባል” ሲሉ ገልፀዋል።
የአገሪቱንና የመላ ዜጎቿን ደህንነት ለማስጠበቅ የኢትዮጵያ መንግስት ያለእረፍት እየሰራ እንደመገኝ የጠሱት ዶ/ር አብርሃም፤ “በአገራችን ውስጥ ሆነው ለአሸባሪው ህወሃት የሚሰሩ ሃይሎች አሉ” ብለዋል።
እነዚህ ሃይሎች ምናልባት ንጹሐን ትግራዋዮችን በመክሰስ የአሸባሪውን አጀንዳ አስርገው ለማስገባት ሽፋን እያደረጉት እንደሆነ ገልጸዋል።
ከነዚህ በተጨማሪ ሌሎች ተዋናዮች እንዳሉ ጠቁመው፤ የአገሪቱን ቀውስ ለማባባስ የተቻላቸውን እየሞከሩ እንደሆነ ተናግረዋል።
ይህንን ችግር ለመፍታትና እነዚህን ተዋናዮች ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል ኮሚቴ መቋቋሙን ጠቁመዋል።
ኮሚቴው በፌዴራል ፖሊስና በሌሎች አጋር ተቋማት የሚወሰደው እርምጃ ስህተት እንዳያጋጥመው የሚያስችል እንደሆነም አመልክተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ንጹሀን ትግራዋዮች ላይ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ለመጠበቅ ከትግራይ ተወላጆች ቡድን ጋር በቅርበት በመስራት ሂደቱን የመመርመርና የመገምገም ስራ እየተሰራ እንደሆነ አመልክተዋል።
Credit : ENA

Amhara Region Report AMHARIC.pdf
1.8 MB
#ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአማራ ክልል በጦርነት በተጎዱ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶችና የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶች ምርመራ ሪፖርት ይፋ አደረገ።
ኢሰመኮ በደረሱት መረጃዎች መነሻነት በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እንዲሁም በአንዳንድ የትግራይ ክልል ደቡባዊ አካባቢዎች በጦርነት አውድ ውስጥ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶችን በተመለከተ ከነሐሴ 22 እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ምርመራ አካሂዷል።
ከላይ ምርመራው ውጤት ተያይዟል።

ኢሰመኮ ከሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል በሕወሓት ኃይሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብትና የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶችን በተመለከተ ያደረገውን ምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆኗል።
ከሰኔ 21 - ነሃሴ 22 /2013 ዓ/ም ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው ይህ ሪፖርት እስከ ነሃሴ 30/ 2013 ድረስ የተካሄደ ምርመራ ውጤት ሲሆን የምርመራ ቡድኑ 128 ቃለመጠይቆችን፣ ከተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች፣ የሲቪልና የፀጥታ አካላት፣ ከሲቪክ ማኅበረሰብ አባላት፣ ከተራድዖ ድርጅቶች ጨምሮ 21 የቡድን ውይይቶችን አድርጓል።
በሪፖርቱ እንዳመላከተው ምርመራው ባተኮረባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች በተደረገው ጦርነት ቢያንስ የ184 ሲቪል ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ እንዲሁም በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት እና የሥነ ልቦና ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በተለይ የሕወሓት ታጣቂዎች በቁጥጥራቸው ስር በገቡ ከተሞች እና ገጠራማ አካባቢዎች ሲቪል ሰዎችን ተኩሰው መግደላቸውንና ማቁሰላቸውን፣ ሰፊ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት ሆን ብለው መፈፀማቸውን ኢሰመኮ አረጋግጧል።
እንዲሁም የሕወሓት ኃይሎች ወደ ከተሞች ከባድ መሳሪያዎችን መተኮሳቸውን፤ በሲቪል ሰዎች መኖሪያ ቤቶችና ቅጥር ግቢዎች ውስጥ ምሽግ በመቆፈር እና ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ሲቪል ዜጎችን በአፀፋ ለሚተኮሱ ከባድ መሳሪያዎች ጥቃት ማጋለጣቸውን፤ በዚህ የበርካታ ሲቪል ሰዎች ሞትና አካል ጉዳት እንዲከሰት እንዲሁም ንብረት እንዲወድም ምክንያት መሆናቸውን ሪፖርቱ ያሳያል።
በሌላ በኩል የመከላከያ ሰራዊት የሕወሓት ታጣቂዎች ሲቪል ሰዎች የሚኖሩባቸው መንደሮች ውስጥ ሆነው የሚፈፅሙበትን ጥቃት ለመከላከል እና ለማጥቃት ከባድ መሳሪያዎችን በመጠቀሙ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞትና አካል ጉዳት ደርሷል፤ ንብረት እንዲወድም ሆኗል።

#AddisAbaba የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ተጨማሪ አዳዲስ የደንብ ልብሶችን ስራ ላይ ማዋሉን ዛሬ አሳውቋል። ነባሩን የደንብ ልብስ መጠቀም ማቆሙን ተቋሙ ገልጿል፡፡ ከዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ አዳዲሶቹ የደንብ አልባሳትን ብቻ መጠቀም እንደሚገባ እና ነባሩ የደንብ ልብስ ሙሉ በሙሉ መቀየሩ ተገልጿል። የአዲስ አበባ ፖሊስ አሮጌውን የደንብ ልብስ ለብሶ የተገኘ አመራር እና አባል…
#ማሳሰቢያ
" የፖሊስ ደንብ አልባሳትን አስመስሎ መጠቀም ፍፁም ክልክል ነው " - የአዲስ አበባ ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ነባሩን በመተካት ሥራ ላይ ያዋላቸውን ሦስት ዓይነት የደንብ አልባሳትን አስመስሎ መጠቀም ፍፁም ክልክል መሆኑን አስታውቋል፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ የፖሊስ ተቋማትን ለማዘመን በተያዘው ስትራቴጂካዊ እቅድ የፖሊስ ሠራዊት አርማ እና የደንብ ልብስ እንዲቀየር በተወሰነው መሰረት የአዲስ አበባ ፖሊስ አዲስ አርማና የደንብ ልብስ ስራ ላይ ማዋሉ ይታወቃል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ነባሩን የደንብ ልብስ በሦስት ልዩ ልዩ ዩኒፎርሞች ተክቷል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኦሞ ሸሚዝ በጥቁር ሰማያዊ ሱሪ ከነ መለዮው፣ ካኪ ሱሪ እና ሸሚዝ በቦኔት መለዮ የደንብ ልብስን ለመደበኛ የፖሊስ ስራ እንዲሁም ቡራቡሬ ወይም ሬንጀር መልክ ያለው ለቋሚና ተወርዋሪ ኃይል የሚጠቀም መሆኑን ገልጿል።
አዲስ ስራ ላይ የዋለውን ወይም ከሌሎች የፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ዩኒፎርም መጠቀም ክልክል መሆኑ በህግ የተደነገገ ስለሆነ ከአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ዩኒፎርም የሚጠቀሙ አካላት ማስተካከያ እንዲያደርጉ ፖሊስ አሳስቧል።
የአ/አ ፖሊስ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት የነበረው ነባሩ የደንብ ልብስ አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑ ከዚህ በፊት መገለፁ ይታወሳል።

#BahirDar : በባሕር ዳር በአንድ ግለሰብ ቤት ከ3 ሺህ በላይ ጥይትና ሌሎች የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ።
በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ፥ በግሸ አባይ ክፍለ ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ3 ሺህ በላይ ጥይትና ሌሎች የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
ፖሊስ ጥቆማው የደረሰው ከማኅበረሰቡ መሆኑን
አመልክቷል።
በጥቆማው መሰረት ተጠርጣሪው ቤት ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ፍተሻ በማካሄድ በግለሰቡ መኖሪያ ውስጥ 2 ክላሽ ፣ ከ3 ሺህ በላይ የክላሽ እና የብሬን ጥይት፣ አንድ ኤፍዋን ቦንብ እና አንድ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ ተገልጿጻ።
የቤት አከራዮች የተከራዮቻቸውን ማንነት በአግባቡ በማጣራት አድራሻቸውን ለፖሊስ እንዲያሳውቁም ጥሪ ቀርቧል።
Credit : AMC

አሜሪካ በኤርትራ ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለች። የአሜሪካ ግምጃ ቤት በድረገጹ እንዳስታወቀው በሁለት የኤርትራ ባለስለጣናት እና በ4 ተቋማት ላይ ማዕቀብ ጥሏል። አሜሪካ ኤርትራ ላይ አዲስ ማዕቀብ የጣለችው በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ መሆኑን አሳውቃለች። እንደ አሜሪካ ግምጃ ቤት መረጃ ማዕቀቡ የተጣለባቸው ግለሰቦች አብርሃ ካሳ ነማርያም የኤርትራ ብሄራዊ ደህንነነት ቢሮ ሀላፊ እና የኤርትራ…
ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አወገዘች።
አሜሪካ በትናንትናው ዕለት በኤርትራ መንግስት ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ኢትዮጵያ አውግዛለች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ውሳኔ በግልጽ የሚታወቁ እውነታዎችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነበር ብሏል።
የአሜሪካ መንግስት የሚከተሉትን እውነታዎች ከግምት ውስጥ እንዲያስገባ መንግስት ጠይቋል፦
1. ህወሓት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ያደረሰውን ያልተጠበቀ ጥቃት ተከትሎ ሉዓላዊት ሀገር በሆነችው ኤርትራ ላይ ሮኬቶችን ተኩሷል።
2. የኤርትራ መንግስት በግዛቱ አንድነት እና ደህንነት ላይ ለተቋጣው ጥቃት ምላሽ የመስጠት ሉዓላዊ መብት አለው።
3. የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ጦር ግዛቱን አልፎ መገኘቱን አስመልክቶ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቅሬታ አለማቅረቡንም መግለጫው አስታውሷል።
እንዲህ ዓይነት ቅሬታ የማቅረብ መብት ያለው ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ እንጂ ሌላ አካል አይደለም።
4. የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት ያወጀውን የተናጥል የሰብአዊ መብት ተኩስ አቁም ተከትሎ ወታደራዊ ሀይሉን ከኢትዮጵያ ማስወጣቱም ይታወቃል።
5. የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዳይሰፍን የኤርትራ መንግስት እንቅፋት ነው ብሎ አያምንም። በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለው የሰላም ስጋት የህወሓት ጠብ አጫሪነት እና ወረራ ነው።
የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህወሓትን የማተራመስ ሚና አጥብቆ ለማውገዝ አለመፈለጉም የሽብር ቡድኑን አበረታቶታል ብሎ መንግስት ያምናል።
ያንብቡ : telegra.ph/ETHIOPIA-11-13 #ኢብኮ

ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አወገዘች። አሜሪካ በትናንትናው ዕለት በኤርትራ መንግስት ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ኢትዮጵያ አውግዛለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ውሳኔ በግልጽ የሚታወቁ እውነታዎችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነበር ብሏል። የአሜሪካ መንግስት የሚከተሉትን እውነታዎች ከግምት ውስጥ እንዲያስገባ መንግስት ጠይቋል፦ 1. ህወሓት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት…
" አሜሪካ ማዕቀብ ስትጥል ይህ አዲስ አይደለም ፤ ማዕቀቡ ከዓለም አቀፍ ህግ እና ከሉዓላዊነት አንጻር ትክክል ያልሆነ እና ህገወጥ ነው " - ኤርትራ
ኤርትራ በትናንትናው ዕለት በአሜሪካ በተጣለባት አዲስ ማዕቀብ ዙሪያ በሀገሪቱ የማስታወዊያ ሚኒስቴር በኩል መግለጫ አውጥታለች።
ኤርትራ የተጣለባት አዲስ ማዕቀብ አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ እና በኤርትራ ላይ የምትከተለው የተሳሳተ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ውጤት መሆኑን ገልጻለች።
አሜሪካ ማዕቀብ ስትጥል ይህ አዲስ አይደለም ያለቸው ኤርትራ፤ ማዕቀቡ ከዓለም አቀፍ ህግ እና ከሉዓላዊነት አንጻር ትክክል ያልሆነ እና ህገወጥ ነው ብላለች።
በተጨማሪ ማዕቀቡ አሜሪካ እንዳለችው በምስራቅ አፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ከማምጣት ይልቅ አፍሪካ በተለይም ምስራቅ አፍሪካ ሁሌም ወደ አለመረጋጋት እንዲመጣ ያደርጋል ብላለች።
አሜሪካ ይሄንን ህገወጥ ማዕቀብ በኤርትራ ላይ ለመጣል ስትልም በማይታመኑት ብዙሃን መገናኛ ጣቢያዎች የተሳሳቱ ዘገባዎችን እና ተከፋይ የአይን ምስክሮችን መጠቀሟንም ኤርትራ ገልፃለች።
የአሜሪካ ማዕቀብ ዋና አላማ ኤርትራዊያንን ለማስራብ እና በአካባቢው የፖለቲካ አለመረጋጋት በመፍጠር የራሷን ጥቅም ለማግኘት ስትል የተደረገ እንደሆነ ኤርትራ በመግለጫዋ አሳውቃለች።
Credit : Al Ain News / Shabiat