TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Audio : ዛሬ አ/አ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ታዳሚው እነ CNN፣ አልጀዚራ፣ BBC ፣ ሮይተርስ በመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ እጅግ ኃይለኛ ትችት እና ወቀሳን ሰንዝሯል። የሚዲያ ተቋማቱ እጃቸውን ከኢትዮጵያና ከህዝቧ ላይ እንዲሰበስቡ ፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ሀሰተኛ መረጃዎችን እንዲሁም ውሸቶችን ለዓለም ህዝብ ከማሰራጨት እንዲታቀቡ ሰልፈኞች አሳስበዋል። ህወሓት /TPLF/ አሸባሪ ድርጅት ነው ያሉት…
#ETHIOPIA

ከሰሞኑን የተለያዩ የውጭ ሀገራት ሚዲያዎች ተናበው ሚሰሩ በሚመስል መልኩ ኢትዮጵያን የተመለከተ በርካታ ዘገባዎችን አውጥተዋል።

የሚዲያ ተቋማቱ ድርጊት ኢትዮጵያውያንን ክፉኛ አስቆጥቷል።

ለአብነት በአራት ቀናት ብቻ CNN፣ BBC ፣ አልጀዚራ ፣ ፍራንስ 24 ፣ አሶሼትድ ፕሬስ በድምሩ 72 ዜናዎችን በኢትዮጵያ ጉዳይ አውጥተዋል (ይህን ቁጥራዊ መረጃ ያጋራው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ የሚሰራው ጋዜጠኛ ሰለሞን ካሳ ነው)

ከ72ቱ ዜናዎች 21ዱን CNN ፣ 13ቱን BBC ፣ 11ዱን አልጀዚራ ፣ 19ኙን ፍራንስ 24 እና 8ቱን አሶሼትድ ፕሬስ ነው የሰሩት።

አብዛኛዎቹ ዜናዎች ኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ለማሸበር የተሞከረበት ነው ፤ ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያን ለመበትን የሀሰት ትርክት እና የስነልቦና ጫናና አለመረጋጋት በህዝቡ ዘንድ ለመፍጠር ረጅም መንገድ የተሄደበት መሆኑ አመላካች እንደሆነ ያሳያል።

የሚዲያዎቹ ድርጊት ከሙያዊ ስነምግባር ያፈነገጠና አድሏዊ የሆነ በሀገር ውስጥ ያለው ነዋሪ ምን መአት መጣ ብሎ እንዲጨነቅ እና እንዲሸበር ፣ አካባቢውን ቄየውን ለቆ እንዲሸሽ ለማድረግ የታለመበት ይመስል ነበር።

የሚዲያዎቹ ድርጊት ያስቆጣቸው ነዋሪዎች ትላንት አዲስ አበባ ከተማ በነበረ ሰልፍ ላይ ሆን ተብሎ ህዝብ ለማሸበር እና ለማስደንገጥ የሚያደርጉትን ድርጊት እንዲያቆሙ፤ እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ እንዲሰበስቡ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Olusegun_Obasanjo ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መፍትሄ አፈላላጊው ሰው - ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ! በአፍሪካ ህብረት (AU) የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ከተሾሙ በኃላ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲፈታና ሰላም እንዲወርድ የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ። ኦባሳንጆ በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት ሲያደርጉ ነበር፤ ከኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም…
#OlusegunObasanjo

የአፍሪካ ህብረት የጸጥታው ምክር ቤት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በህብረቱ ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆ ገለጻ እንደተደረገለት አል ዐይን በድረገፁ አስነብቧል።

ህብረቱ ዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ/ም አስቸኳይ ዝግ ስብሰባ አካሂዷል፡፡ ስብሰባው በበይነ መረብ የተካሄደ እንደነበር ተገልጿል።

በስብሰባው ላይ ፦

• የህብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዲዎዬ፣

• የህብረቱ የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴገን ኦባሳንጆ፣

• በአፍሪካ ህብረት የግብጽ ቋሚ ተወካይ መሃመድ ጋድ እና በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ተወካይ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ ተሳትፈዋል፡፡

ስብሰባው የተካሄደው በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለመምክርና የአፍሪካ ህብረት የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴገን ኦባሳንጆን ገለጻ ለማድመጥ ነበር፡፡

በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ተወካይ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ በተሳተፉበት በዚህ ስብሰባ ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከመከረና የኦባሳንጆን ገለጻ ካደመጠ በኋላ ያለው ወይም ያስቀመጠው ቀጣይ አቅጣጫ እንዳለ የታወቀ ነገር የለም፡፡

ነገር ግን ም/ ቤቱ የተሰበሰበበትን ጉዳይ የተመለከተ መግለጫን እንደሚያወጣ መረጃ እንዳለው አል ዓይን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
'' ፈተናውም በማንም፤ በምንም፤ በየትም አልተሰረቀም '' - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትሩ ር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ መሰጠት የተጀመረው የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ቀንን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ መግለጫውን ተከታትሏል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ በመግለጫቸው ከሞላ ጎደል ፈተናው በሰላማዊ መንገድ መከናወኑን ገልጸዋል። ''ፈተናውም በማንም በምንም በየትም አልተሰረቀም'' ሲሉ ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለት 2 ተማሪዎች በኦሮሚያ ክልል 2 ተማሪዎች በደቡብ ክልል በስልካቸው ፎቶ አንስተው ''ኤሌክትሮኒክ ኩረጃ'' ሊፈጽሙ ሲሉ መያዛቸውን ጠቅሰዋል።

ተማሪዎቹ ፈተና ክፍል ከገቡ በኋላ ፈተናውን በፎቶ አንስተው ሲላላኩ መያዛቸው ነው የተጠቀሰው። ይህም ተማሪዎች ለፈተና ከገቡ በኋላ የተለቀቀ በመሆኑ ፈተናው ተሰርቋል ሊባል አይችልም ተብሏል።

ፈተናው በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ ከፌደራል ጀምሮ እስከታች ባሉ የኮማንድ ፖስቱ አባላት ያደረጉት አስተዋጽኦ የተሻለ መሆኑን ጠቅሰዋል። በሚቀጥሉት ሦስት ቀናትም ትብብሩ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ተማሪዎች የሞባይል፣ የስማርት ሰዓትም ሆነ ሌሎች ዲጂታል ኤሌክትሪክ መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት እንደማይፈቀድ አጽንኦት ተሰጥቶ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OlusegunObasanjo

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲቆም እና ሰላም እንዲወርድ መፍትሄ እያፈላለጉ ያሉት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ዛሬ ወደ አማራ ክልል አፋር ክልል ይጓዛሉ።

ኦባሳንጆ ከቀናት በፊት ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ተጉዘው እንደነበር አይዘነጋም።

ዛሬ ወደ ባህር ዳር እና ሰመራ በማቅናት ከክልሎቹ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እያደረጉት ስላለው የሰላም ጥረት ይወያያሉ ተብሏል፤ እስካሁን ስለጉዟቸው ዝርዝር ነገር የለም።

በሌላ በኩል ኦባሳንጆ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለመፍታት በሚያደርጉት ጥረት ተልዕኳቸውን አልቀበልም ያለ አካል እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የፌዴራል መንግስት ይሁን በትግራይ ክልል ያሉ አካላት እሳቸውን አልቀበልም ያለ እንደሌለ አሳውቀዋል።

ኦባሳንጆ ፥ "የአፍሪካ ሕብረት ሰላም ለማምጣት፣ ንግግርን ለማስጀመር እና ደኅንነትን ለማስጠበቅ ልዩ መልዕክተኛ መሰየሙን ሁሉም ወገን በበጎ ነው የተቀበሉት" ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ፥ "የጠየቅኩትን ትኩረት ሰጥተውኛል። በሚገባው ልክ አስተናግደውኛል" ሲሉ ስለተደረገላቸው መልካም አቀባበል ገልጸዋል።

ትግራይ ክልል ሲሄዱም ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ኤርፖርት ድረስ ሄደው እንደተቀበሏቸው ገልፀዋል።

ሁለቱም ወገኖች የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆን "አልተቀበሉንም የሚለው ሐሳብ ፍጹም ስህተት ነው" መሆኑን አሳውቀዋል።

አሁን ላይ የድርድሩ ሂደት ምን ላይ እንዳለና በቀጣይ የሚፈጠረውን ጉዳይ በተመለከተ ኦባሳንጆ ፤ "አሁን ገና የመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ ነኝ። ድርድሩ ወዴት እንደሚሄድ የምናገርበት ጊዜ አይደለም" ብለዋል።

አሁን ያሉበት ደረጃ በተደራዳሪ ወገኖች ዘንድ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ምን እንደሆነ የመለየት እንደሆነም ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OlusegunObasanjo በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲቆም እና ሰላም እንዲወርድ መፍትሄ እያፈላለጉ ያሉት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ዛሬ ወደ አማራ ክልል አፋር ክልል ይጓዛሉ። ኦባሳንጆ ከቀናት በፊት ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ተጉዘው እንደነበር አይዘነጋም። ዛሬ ወደ ባህር ዳር እና ሰመራ በማቅናት ከክልሎቹ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እያደረጉት ስላለው የሰላም ጥረት ይወያያሉ ተብሏል፤ እስካሁን ስለጉዟቸው…
#OlusegunObasanjo

ትናንት በወቅታዊ የአፍሪካ የጸጥታ ሁኔታዎች ላይ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ስበስባ ተቀምጦ ነበር።

በዚህ ስብሰባ ላይ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ በመደረግ ላይ ስላሉ የሰላም ጥረቶች ገለጻ አድርገዋል፡፡

በገለጻቸውም በአዲስ አበባ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ ከፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር መነጋገራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ውጥረቱን ለማርገብ እና ለቀጣይ ውይይቶች ምቹ መደላድልን ለመፍጠር የሚያስችል ፍሬያማ ንግግር ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ከተነጋገሩና ወደ ትግራይ እንዲያቀኑ ከተስማሙ በኋላ እሁድ ጥቅምት 28 ቀን 2014 ዓ/ም በመቐለ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካዔልን ጋር ተገናኝተው ውጥረቱን ለማርገብና አመርቂ መፍትሄዎችን ለመፈለግ የሚያስችል ምክክር ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ እና በሰሜን ያሉ ሁሉም መሪዎች በመካከላቸው ያለው ችግር ፖለቲካዊ እንደሆነና በውይይት ሊፈታ የሚችል ፖለቲካዊ መፍትሄን እንደሚፈልግ በግለሰብ ደረጃ መስማማታቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ችግሩ የከፋ ማህበረ ምጣኔ ሃብታዊ እና ሰብዓዊ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን በመጠቆም ዘላቂ እልባት ለመስጠት መፍጠን እንደሚያስፈልግ ኦባሳንጆ ተናግረዋል።

የጸጥታው ምክር ቤት ሁሉም አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁመው ወደ ውይይት እንዲመጡ፣ ያልተቆራረጠ የሰብዓዊ እርዳታዎች አቅርቦት እንዲኖር፣ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ እና ሁሉን አካታች ብሔራዊ ውይይት በአፋጣኝ እንዲደረግ ግፊት እንዲያደርግና ሁኔታዎችን በአንክሮ እንዲከታተል አሳስበዋል፡፡

Credit : አል ዓይን

@tikvahethiopoa
TIKVAH-ETHIOPIA
#OlusegunObasanjo ትናንት በወቅታዊ የአፍሪካ የጸጥታ ሁኔታዎች ላይ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ስበስባ ተቀምጦ ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ በመደረግ ላይ ስላሉ የሰላም ጥረቶች ገለጻ አድርገዋል፡፡ በገለጻቸውም በአዲስ አበባ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ ከፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት…
#AmbassadorTayeAtskeSelassie

ትላንት በነበረው የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ስበስባ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ንግግር አድርገው ነበር።

አምባሳደር ታዬ በህወሓት የተፈጸመው የክህደት ስራ በእጅጉ የሚያሳዝንና ኢትዮጵያ በዚህ ወንጀለኛ ቡድን ያሳለፈችውን ጊዜ ለመርሳት የአንድ ትውልድ ጊዜ የሚፈጅ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ቡድኑ ያን ሁሉ ደም መፋሰስ እንዲፈጠር ባያደርግ ኖሮ ፖለቲካዊ እጣ ፋንታውም ሆነ ሁኔታው በውይይት መፍትሄ ያገኝ እንደነበር አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡

“በአፍሪካዊ እገዛዎች ካለንበት ችግር መውጣት ጥሩ መፍትሄ ነው ብለን እናምናለን፤ ወደ ፖለቲካዊ መፍትሄ የሚወስደው መንገድ ግን አልጋ በአልጋ ነው ወይም ቀላል ነው ማለት አይቻልም” ብለዋል አምባሳደር ታዬ።

መንግስት አሁን ላይ የህወሓትን መስፋፋት ማስቆም እና በቡድኑ ጥቃት እየደረሰበት ያለውን ህዝብ መታደግ ላይ ትኩረት ማድረጉንም ለምክር ቤቱ መናገራቸውን አል አይን አስነብቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AmbassadorTayeAtskeSelassie ትላንት በነበረው የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ስበስባ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ንግግር አድርገው ነበር። አምባሳደር ታዬ በህወሓት የተፈጸመው የክህደት ስራ በእጅጉ የሚያሳዝንና ኢትዮጵያ በዚህ ወንጀለኛ ቡድን ያሳለፈችውን ጊዜ ለመርሳት የአንድ ትውልድ ጊዜ የሚፈጅ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ቡድኑ ያን ሁሉ ደም መፋሰስ እንዲፈጠር ባያደርግ…
#UNSC

በትላንትናው የፀጥታው ምክር ቤት ሰብሰባ ላይ የሀገራት ተወካዮች ምን አሉ ?

#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው አንድ (1) ዓመት ከህወሓት የተቃጣበትን ወታደራዊ አደጋ መመከቱን አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ተናግረዋል።

መንግሥት ምግብን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን በትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ለሚፈልጉ ሰዎች ከUN ጋር በመተባበር ሲያቀርብ እንደነበር ተናግረዋል።

ለሰብአዊ ድጋፍ እንዲያመች በሚል የተናጠል የተኩስ አቁም ማድረጉን ተናግረዋል። ነገር ግን የተደረገው ጥረት ሁሉ በወንጀለኛው ቡድን ምክንያት ከንቱ ሆኖ ቀርቷል ብለዋል።

"በዚህ የወንጀል ቡድን ምክንያት የትግራይ ክልል ሕዝብ ያስፈልገው የነበረውን አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እያገኘ አይደለም" ሲሉ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።

በአማራ ክልል እና በአፋር ክልል በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ሰዎችም በዚህ ቡድን በየበራቸው ላይ መገደላቸውን ገልጸዋል።

#ቻይና

ቻይናን የወከሉት ዣንግ ጁን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰተ ያለው ሁኔታ የፖለቲካ፣ የታሪክ፣ የብሔርና ሌሎች ምክንያቶች ጥምር ውጤት መሆኑን ጠቁመው መፍትሔ የሚገኘው በአገር ውስጥ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት አፍሪካዊ መፍትሄዎች ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት በድጋሚ ድጋፍ እንሰጣለን ብለዋል።

በተለይ አሜሪካና የተለያዩ አገራት የሚያደርጉትን ማዕቀብ በተመለከተም አስተያየታቸውን የሰጡት ተወካዩ፣ በንግድ ላይ ገደብ ማድረግ እና እርዳታን ማቋረጥ በፖለቲካው መፍትሄ ላይ ጣልቃ መግባት እንደሆነ አስረድተዋል።

ለፀጥታው ምክር ቤት አባላት ምክራቸውን ያስተላለፉት የቻይናው ተወካይ አባል አገራቱ የአገሪቱን ሉዓላዊነትና አመራር በማክበር ኢትዮጵያ የሰብአዊ አቅሟን እንድታሻሽል እና የሚሰጠው እርዳታም ሊጨምር ይገባል ብሏል።

#አሜሪካ

አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ 1 አመት ባስቆጠረው ግጭት ውስጥ ለተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፥ "ሁሉም ኃሃይሎች ጥፋተኞች ናቸው፤ ጥፋት የለሌለበት የለም" ሲሉ ተናግረዋል።

አምባሳደር ሊንዳ የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል እና አፋር ክልል እንዲወጡ እና ጥቃታቸውን ወደ አዲስ አበባ እንዳያሰፉ አሳስበዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ዓለም አቀፍ የጦርነት ሕጎችን እንዲሁም የሰብአዊ መብት ሕጎችን እንዲያከብር ጠይቀዋል።

ሰላምን ሊያመጡ የሚችሉት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ናቸው ሲሉም አምባሳደሯ ተናግረዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/UNSC-11-09
#DrAbiyAhmed

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባሰራጩት መልዕክት ፥ " በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መንግሥት በሚፈተን ግን በማይቀለበስ የለውጥ ጉዞ ላይ ነው " ብለዋል።

መንግሥት ጊዜያዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የልማት ግቦችን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር ገንቢ በሆነ መልኩ ለመሥራት ምንጊዜም ዝግጁ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

" መሰናክሎች ያስተምሩናል እንጂ አያስቆሙንም " ያሉት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ " በያዝነው የለውጥ ጎዳና ወደ ፊት ለመጓዝ ቁርጠኞች ነን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ጠንካራ ጥበቃ ከተጀመረ በኃላ የተለያዩ የጦር መሪያዎች በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች፣ በየጥሻው እና በየመንገድ ዳር ተጥሎ እየተገኘ ነው ብሏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ይህን ያለው ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በሰጠው ቃል ነው።

ፖሊስ የጦር መሳሪያዎች ፣ የእጅ ቦንብ፣ ጥይቶች በየጥሻው ፣ በየመንገድ ዳሩ ፣ በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ ውስጥ እየተገኙ ስለሆነ ህብረተሰቡ በእነዚህ አካባቢዎች ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና ጥቆማም እንዲሰጥ አሳስቧል።

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ፖሊስ ህብረተሰቡ በቡድን በቡድን እየሆነ በየአካባቢው ጠንካራ ጥበቃ እያደረገ ነው ያለ ሲሆን በዚህም በርካታ ውጤት መገኘቱን አሳውቋል።

ፖሊስ ለከተማው የፀጥታ ስጋት ናቸው የተባሉ ፣ ሀገርን ለማፍረስ ለተሰለፉ ኃይሎች በተለያዩ መልኩ ሲደግፉ የነበሩ፣ ስልጠና እና ስምሪት ተሰጥቷቸው በከተማው የተሰገሰጉትን እየለየን እየያዝን ነው ብሏል።

@tikvahethiopia
#ማስታወሻ

ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ትገኛለች።

በ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5 / 2014 የተከለከሉ ተግባራትና ህጉን በሚተላለፉ ሰዎች ላይ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች ከላይ ተያይዟል /ያንብቡ/ ።

ማንኛውም ሰው ከላይ የተዘረዘሩትን ክልከላዎች እና ግዴታዎች መተላለፍ የሚያስከትለውን ተጠያቂነት በመገንዘብ እንዳንዱን እንቅስቃሴውን ህጉን ያከበረ መሆኑን እያረጋገጠ በአስተውሎት ህግ አክባሪ ዜጋ በመሆን የራሱን የአካባቢውን እና የሀገሩን ሰላም እና ደህንነት መጠበቅ እና ማስጠበቅ ውስጥ ተገቢውን ሚና መጫወት አለበት ብሏል ፍትህ ሚኒስቴር።

@tikvahethiopia
" ... ድርጊቶቹ ከሞራል ወይም ከሰብዓዊነት ያፈነገጡ ናቸው " - አምነስቲ ኢንተርናሽናል

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል የነፋስ መውጫ ከተማ ላይ ጥቃት በፈጸሙበት ጊዜ የአስገድዶ መድፈር፣ ዘረፋ እና አካላዊ ጥቃቶች በነዋሪዎች ላይ መፈጸማቸውን ገለጸ።

አምነስቲ ባወጣው ሪፖርት በከተማዋ ነዋሪ የሆኑና ያናገራቸው 16 ሴቶች በህወሓት አማጺያን የአስገድዶ መደፈር ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።

ሴቶቹ እንዳሉት በህወሓት ኃይሎች መሳሪያ ተደቅኖባቸው እንደተደፈሩ፣ ዝርፊያ እንደተፈጸመባቸው እንዲሁም አካላዊ ጥቃት እና ስድብ እንደደረሰባቸው አመልክተዋል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጨምሮ ካነገራቸው አስገድዶ የመድፈር ጥቃት ከተፈጸመባቸው 16 ሴቶች መካከል 14ቱ ጥቃቱ #በቡድን እንደተፈጸመባቸው ገልጸዋል። አማጺያኑ በከተማ ባሉ የህክምና ተቋማት ላይ ዝርፊያና ውድመትን አድርሰዋል ብሏል።

በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ የምትገኘውን የነፋስ መውጫ ከተማን የህወሓት ታጣቂዎሽ ተቆጣጥረው የቆዩት ከነሐሴ 06 አስከ 15/2013 ዓ.ም ድረስ ለአስር ቀናት ነበር።

የአምነስቲ ኢንትርናሽናል ዋና ፀሐፊ አግነስ ካላማርድ፥ "የአስገድዶ መድፈር ጥቃቱ ከደረሰባቸው የሰማናቸው ምስክርነቶች የህወሓት ተዋጊዎችን አጸያፊ ተግባራት፤ ከጦር ወንጀሎች እና በሰብአዓዊነት ላይ ከተፈጸሙ ወንጀሎች ጋር የሚስተካከሉ ናቸው። ድርጊቶቹ ከሞራል ወይም ከሰብዓዊነት ያፈነገጡ ናቸው" ሲሉ ተናግረዋል።

የህወሓት ታጣቂዎች ወሲባዊ እና ፆታዊ ጥቃቶችን ጨምሮ የሰብዓዊ መብቶችን እና የዓለም አቀፍ ሕጎች ጥሰቶችን በሙሉ በማቆም በፈጻሚዎቹ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ መጠየቃቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Amnesty-International-11-10

@tikvahethiopia