TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba መሳሪያ ያላስመዘገቡ የአዲስ አበባ ባለጦር መሳሪያ ግለሰቦች በ2 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግቡ የከተማ አስተዳደሩ የሰላምና ደህንነት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ አሳሰቡ። የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ወቅታዊ ፀጥታን በተመለከተ መግለጫ ተሰጥተዋል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመንደር እርስ በርስ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቁ ተፈቅዷል ብለዋል። አደረጃጀቱ ከፀጥታ…
" የጦር መሳሪያ ምዝገባ እስከ ነገ ድረስ ተራዝሟል " - ዶ/ር ቀነዓ ያደታ
በአዲስ አበባ የጦር መሳሪያ እንዲመዘገብ ትናንት በተላለፈው ጥሪ መሰረት ነዋሪዎች በከተማዋ በሚገኙ ፓሊስ ጣቢያዎች በመቅረብ እያስመዘገቡ ይገኛሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፤ የከተማዋን ሰላም የበለጠ ለማረጋገጥ ማንኛውም ግለሰብ በእጁ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ከዚህ ቀደም ቢመዘገብም ባይመዘገብም እንደ አዲስ እንዲያስመዘግብ ቢሮው ጥሪ ማቅረቡ አስታውሰዋል።
ይህንን ጥሪ ተከትሎ መሳሪያ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በእጃቸው የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ወደየፖሊስ ጣቢያዎች በመቅረብ እያስመዘገቡ ይገኛሉ ሲሉ አሳውቀዋል።
አስቀድሞ በተላለፈው ጥሪ መሰረት ምዝገባው ትናንት እና ዛሬ ብቻ የሚከናወን ቢሆንም ምዝገባው የተጀመረው ትናንት ከሰአት በኋላ በመሆኑ የጦር መሳሪያ ምዝገባው እስከ ነገ ተራዝሟል ብለዋል ዶ/ር ቀነዓ።
Credit : ኢፕድ
@tikvahethiopia

አዲስ አበባ !
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ማንኛውም አጠራጣሪ ጉዳዮችን ሲመለከቱ የሚያመለክቱበት ነፃ የስልክ መስመር ይፋ ሆነ።
ነዋሪዎች አጠራጣሪ ጉዳዮችን ሲመለከቱ የሚያሳውቁበት ነፃ የስልክ መስመር " 9977 " ነው።
#ሼር #SHARE

ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 8 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,730 የላብራቶሪ ምርመራ 321 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 423 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily
@tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 8 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,730 የላብራቶሪ ምርመራ 321 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 423 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጄፍሪ ፌልትማን ኢትዮጵያ ይገኛሉ። የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ዳግም ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ከዚህ ቀደም ተገልጾ ነበር። ፌልትማን በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ የሚገኙ ሢሆን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ውይይት አድርገዋል። አቶ ደመቀ መኮንን ህወሃት በሰሜን ዕዝ ላይ ስላደረሰው ጥቃት እንዲሁም ቡድኑ እየፈጸማቸው ያለው አስከፊ ድርጊቶች…
ፌልትማን ዳግም ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው።
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ነገ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አሳውቋል።
የጉዞአቸው ዓለማ ሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄድ ያለው ግጭት አሳሳቢነቱ እየጨመረ በመምጣቱ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
ፌልትማን ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሲመጡ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው የሚሆነው ከዚህ ቀደም ሁሉት ጊዜ ኢትዮጵያ መጥተው ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ምክክር አድርገው እንደነበር አይዘነጋም።
ለመጨረሻ ጊዜ በኢትዮጵያ ያደረጉት ቆይታ በነሃሴ 11 ቀን 2013 ዓ/ም ሲሆን በወቅቱ የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተቀብለዋቸው በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገው ነበር።
ፎቶ ፦ ፋይል

* ዝርዝር መረጃ ! ከዛሬ ጀምሮ በመላ አገሪቱ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተከለከሉ ተግባራትና ግዴታዎች ከላይ በዝርዝር ተቀምጠዋል ያንብቡ። @tikvahethiopia
#ETHIOPIA
ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ትገኛለች።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 ተመጣጣኝ ኃይልን ስለመጠቀም እና ስለማይታገዱ መብቶች ምን ይላል ?
- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተመለከቱ የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን ለማስፈጸም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ሕግ አስከባሪ አካላት ተመጣጣኝ ኃይል እንዲጠቀሙ መመሪያ ለመስጠት ይችላል።
- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በሚያወጣቸው መመሪያዎች በሚወስናቸው ውሳኔዎች እና በሚወስዳቸው እርምጃዎች በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 93 (4)(ሐ) መሰረት ሊታገዱ የማይችሉ የሕገ መንግስት ድንጋጌዎችን እና
መብቶችን ማክበር ይኖርበታል።
NB : በኢትዮጵያ ከትላንት ጀምሮ ተፈፃሚ እየሆነ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሃገር ህልውና እና ሉዐላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል የታወጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነው።
#StateofEmergencyEthiopia

#Update የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ነገ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ይፀድቃል። በሃገር ህልውናና ሉአላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነገ ለም/ቤቱ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኃላ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በኢፌደሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 93/1 ፦ • የውጪ ወረራ ሲያጋጥም ወይም ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና…
በዛሬው ዕለት 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል።
ምክር ቤቱ በስብሰባው ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ያፀድቃል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት ለመሰየም የሚቀርበውን የውሳኔ ሃሳብ በመመርመር ያፀድቃል።

" ... ከ5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስገልገዋል " - የአማራ ክልል መንግስት
የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስታና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ፥ በክልሉ ህወሓት ወረራ በፈፀመባቸው ዞኖች ማለትም ፦
- ሰሜን ወሎ
- ደቡብ ወሎ
- ከፊል ደቡብ ጎንደር
- ዋግኽምራ ውስጥ የሚኖሩ እና ተፈናቅለው ያሉትን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል አሳውቋል።
ህወሓት በከፈተው ጦርነት ከ991 ሺ በላይ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን በወረራ በተያዙ አካባቢዎች ደግሞ ከ5 ሚሊዮን ህዝብ በላይ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፤ እነዚህ ነዋሪዎች ለምግብ እጦት ፣ የመጠጥ ውሃ እና የመድሃኒት እጦት ችግር ተጋልጠዋል።
በሰሜን ወሎ ሜቄት አካባቢ ብቻ በህክምና እጦት 90 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ በተመሳሳይ የወለሊድ አገልግሎት ባለመኖሩ ምክንያት 13 እናቶች ሞተዋል።
በጋዝጊብላና በዝቋላ አካባቢ በመድሃኒት እጥረት ፣ በምግብ እጦት 13 ሰዎች ሞተዋል።
በአጠቃላይ በወረራ ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች ቤታቸውን እንደዘጉ በምግብ እና በመድሃኒት እጦት ሞተው የሚገኙበት ሁኔታ ነው እየተፈጠረ ያለው።
ከላይ የተገለፀው ቁጥር ሙሉ አይደለም ፤ ከዚህ በጣም ሊጨምር ይችላል፤ በየአካባቢው የመንግስት መዋቅር በመፍረሱ በምግብ እና በህክምና እጦት የሞቱ አጠቃላይ ሰዎችን ቁጥር ማወቅ አልተቻለም።

" ... ከ5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስገልገዋል " - የአማራ ክልል መንግስት የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስታና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ፥ በክልሉ ህወሓት ወረራ በፈፀመባቸው ዞኖች ማለትም ፦ - ሰሜን ወሎ - ደቡብ ወሎ - ከፊል ደቡብ ጎንደር - ዋግኽምራ ውስጥ የሚኖሩ እና ተፈናቅለው ያሉትን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል…
አድሎ ፈፃሚዎቹ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች !
አማራ ክልል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ችግር ላይ በወደቁበት በዚህ ወቅት አንዳንዱ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ሲያልፍ አንዳንዶቹ ደግሞ ቃል ከመግባት የዘለለ መሬት የወረደ ስራ ሲሰሩ አይታይም።
5 ሚሊዮን ህዝብ ችግር ላይ ይገኛል፤ የዓለም አቀፍ ረጂ ተቋማት ሆኑ የውጭ ሚዲያዎች ይህን ጉዳይ አላስጨነቃቸውም ፤ ምክንያቱን ጊዜ ይፈታዋል።
የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስታና እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ ኮሚሽን ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት የተቋቋሙበት ዓለም አቀፋዋ ህግጋትን ወደጎን ትተው አድሎ ሲፈፅሙ መመልከቱ እንዳሳዘነው ገልጿል።
በተደጋጋሚ የዩኒሴፍ ፣ የWFP ፣ የUNOCHA ካንትሪ ዳይሬክተሮች ወደ አማራ ክልል ሄደው ውይይት አድርገዋል፤ ክልሉ ያለውን ችግር እና ስፋት በአግባቡ እንዲያዩት ተደርገዋል።
እስካሁን ግን አንድም ምላሽ አልተደረገም።
የክልሉ መንግስት መሰረታዊ የገለልተኝነት ችግር አለ ብሎ ያምናል።
ሰብዓዊነት ዘርን፣ ቀለምን፣ ሃይማኖትን፣ የፖለቲካ ልዩነትን የሚጠይቅ ጉዳይ አይደለም፤ ተቋማቱም ሲቋቋሙ ዘርን ሃይማኖትን ፣ ብሄርን፣ የፖለቲካ አመለካከትን ማዕከል አድርገው ድጋፍ ለማድረግ አይደለም የተቋቋሙት፤ ሰብዓዊነት ሁሉም ሰው በመሆኑ ብቻ የሚደረግ ድጋፍ ነው።
ተቋማቱ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ አይደለም።
የሰብዓዊ ድርጅቶቹ በዓለም አቀፍ ድንጋጌ መሰረት ችግር ላይ ያሉ 5 ሚሊዮን ዜጎችን የመታደግ ኃላፊነት አለባቸው።
የአማራ ክልል አሁንም ተቋማቱ ከተቋቋሙበት ዓላማ አንፃር ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ እንዲወጡና ህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ እንዲታደጉ ጥሪ አቅርቧል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ : በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት የጤና መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡
በአማራ ክልል የደብረ ዘቢጥ ጤና ጣቢያ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቁሟል፡፡ በዚህም ህሙማን በህክምና እና መድኃኒት እጥረት #እየሞቱ ይገኛሉ፡፡
የህክምና መሰረተ ልማቶች እና ባለሞያዎች የጦርነት ኢላማ መሆን የለባቸውም፡፡
#ICRCEthiopia
@tikvahethiopia
በአማራ ክልል የደብረ ዘቢጥ ጤና ጣቢያ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቁሟል፡፡ በዚህም ህሙማን በህክምና እና መድኃኒት እጥረት #እየሞቱ ይገኛሉ፡፡
የህክምና መሰረተ ልማቶች እና ባለሞያዎች የጦርነት ኢላማ መሆን የለባቸውም፡፡
#ICRCEthiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በዛሬው ዕለት 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል። ምክር ቤቱ በስብሰባው ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ያፀድቃል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት ለመሰየም የሚቀርበውን የውሳኔ ሃሳብ በመመርመር ያፀድቃል። @tikvahethiopia
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በህ/ተ/ም/ቤት ፀደቀ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ6 ወራት ተፈጻሚ የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርምሮ አፅድቋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአንድ ድምጽ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።
#ተጨማሪ_መረጃ ፦ ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላት ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አፅድቋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድን ፤ አቶ ለማ ተሰማ - በሰብሳቢነት ፤ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ- በም/ሰብሳቢነት ይመሩታል።
መርማሪ ቦርዱ ሌሎች አምስት አባላት አሉት።

ፌልትማን ዳግም ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው። የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ነገ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አሳውቋል። የጉዞአቸው ዓለማ ሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄድ ያለው ግጭት አሳሳቢነቱ እየጨመረ በመምጣቱ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል። ፌልትማን ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሲመጡ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው የሚሆነው ከዚህ ቀደም…
ፎቶ ፦ ፌልትማን ኢትዮጵያ ገብተዋል።
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ጄፍሪ ፌልትማን ዛሬ ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) ገብተዋል፤ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በኃላም ከሙሳ ፋኪ ማሃመት ጋር ተገናኝተው መክረዋል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ፌልትማንን በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ጄፍሪ ፌልትማንን በቢሯቸው ተቀብለው በ #ኢትዮጵያ እና #ሱዳን ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን አሳውቀዋል።
Credit : Moussa Faki Mahamat (Twitter)

#ማስጠንቀቂያ
በሀረሪ ክልል የህክምና ቁሳቁሶችን ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የሚሸጡ መድሃኒት መደብሮችን ከእኩይ ተግባራቸድ እንዲቆጠቡ የክልሉ ጤና ቢሮ አሥጠንቅቋል።
ቢሮው ፥ በጤና ባለሞያዎች የታዘዙ የመድሃኒት ምርቱ እያለ የለም በማለት እና ለህብረተሰቡ በተጋነነ ዋጋ በማቅረብ የግል ጥቅማቸውን የሚያሯሩጡ መድሀኒት መደብሮች ከዚህ እኩይ ተግባር ሊቆጠቡ ይገባል ብሏል።
በተያያዘ በጤና ባለሞያዎች ያልታዘዙ መድሃኒቶችን በግድ የለሽነት የሚሸጡ የግል መድሃኒት መደብሮች ህጋዊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ቢሮው አሳውቋል።
መድሀኒት ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የሚሸጡ መድሃኒት መደብሮችን ህብረተሰቡ በማጋለጥ የበኩሉን እንዲወጣ ሲል የክልሉ ጤና ቢሮ መልዕክት አስተላልፏል።

#HappeningNow
ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ማብራሪያ እየተሰጠ ነው።
በአሁን ሰዓት መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላይ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እየተሰጠ ይገኛል።
ማብራሪያው በኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና በፍትህ ሚንስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ነው እየተሰጠ የሚገኘው።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ማብራሪያው የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ብዥታውን ለማጥራት ይረዳል ብለዋል። በሃገሪቱ ላይ የተጋረጠውን ፈተና ለመከላከል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ እንዳስፈለገም ተናግረዋል።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ የፍትህ ሚንስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።
Credit : ኤፍቢሲ

#Update በትግራይ ክልል እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ፡፡ በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወልዲያ የኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች…
የተማሪዎች ምደባ ይፋ ሆኗል።
በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጊዚያዊ ምደባ ይፋ ሆኗል።
ተማሪዎች ተከታዩን ሊንክ በመከተል የዩኒቨርሲቲ መለያ ቁጥር እና ሙሉ ስም በማስገባት ጊዚያዊ ምደባቸውን መመልከት ይችላሉ፦ https://Placement.ethernet.edu.et
@tikvahuniversity

የተማሪዎች ምደባ ይፋ ሆኗል። በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጊዚያዊ ምደባ ይፋ ሆኗል። ተማሪዎች ተከታዩን ሊንክ በመከተል የዩኒቨርሲቲ መለያ ቁጥር እና ሙሉ ስም በማስገባት ጊዚያዊ ምደባቸውን መመልከት ይችላሉ፦ https://Placement.ethernet.edu.et @tikvahuniversity
የዩኒቨርሲቲ ምደባ !
በመቐለ ፣ አክሱም ፣ ዓዲግራት ፤ ራያ እንዲሁም ወልዲያ ዩኒቨርስቲ ሲማሩ የነበሩና በፀጥታ ችግር ትምህርታቸውን መቀጠል ላልቻሉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ጊዜያዊ ምደባ ዛሬ ይፋ ሆኗል።
ምደባውን በዚህ https://Placement.ethernet.edu.et መመልከት ይቻላል።
• ምደባዉ እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም. የነበረዉን የትምህርት ጊዜ ሰሌዳን ጨርሰው የወጡት ተማሪዎችን ብቻ ይመለከታል፡፡
• ምደባዉ የተካሄደዉ መረጃዎችን በትክክል ላሰገቡ ተማሪዎች ሲሆን፣ በተጠየቀዉ መሰረት መረጃዎችን በትክክል ያላስገቡ ተማሪዎችና የኦን ላይን ፎርሙን በተለያየ ምክንያት በወቅቱ መሙላት ያልቻሉ ተማሪዎች ስማቸውን ኦንላይን ምደባ በሚረጋገጥበት ሶፍትዌር ላያገኙ ስለሚችሉ፣ በነበሩበት የትምህርት ክፍልና ዩኒቨርሲቲን መነሻ በማድረግ በዲፓርትመንት ስለተመደቡ፤ የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል።
• ተመዝግበው ሳይመደቡ የቀሩ ተማሪዎች በቂና ግልፅ መረጃ ያላቀረቡ መሆኑን በመገንዘብ ትምህርት ክፍላቸው የተመደበበትን ዩነቨርስቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል።
• ያልተመዘገቡ እንዲሁም ቅሬታ ወይም አቤቱታ ያላቸው ተማሪዎች በቴሌግራም ቦት (@moeplacementbot) አቤቱታቸውን ማቅረብ ይችላሉ። ትምህርት ሚኒስቴር አቤቱታዎችን በአካል እንደማያስተናግድ በጥብቅ አሳስቧል።
• በዩኒቨርስቲዎች ተፈቅዶላቸው እረፍት (Withdrawal) ላይ የነበሩ ተማሪዎች የትምህርት ክፍላቸው ለተመደበበት ዩኒቨርስቲ ማስረጃቸውን አቅርበው የሚታይላቸዉ ይሆናል ተብሏል።
NB : ተማሪዎች የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ጥሪ ሲያደርግ ብቻ ነው በአካል ቀርበው ሪፖርት የሚያደርጉት።
#MoE