#AddisAbaba
በቂርቆስ እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ህገ- ወጥ የጦር መሳሪያ በተሸከርካሪ ጭነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 3 ግለሰቦች ተይዘዉ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ የተያዘው በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ለገሀር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም ነው፡፡
በኮድ 3 " A.21299 አ/አ " አይሱዙ ከሸዋ ሮቢት ተነስቶ መዳረሻውን አዲስ አበባ መሳለሚያ ሊያደርግ የነበረው ተሽከርካሪ የተሽከርካሪዎች መፍቻ ማስቀመጫ የብረት ሳጥን በኩል ሻግ በማሳራት 3 መትረየሥጠብ-መንጃ ከመሰል አንድ ጥይትና ባዶ የጥይት ማስቀመጫ ዝናር ጋር ተይዟል።
ህገ- ወጥ የጦር መሳሪያው ፣ተሽከርካሪው እንዲሁም 2 ተጠርጣሪዎችን ተይዘው አስፈላጊውን ምርመራ እያጣራ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡
በተመሳሳይ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው መሳለሚያ እህል በረንዳ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ኮድ 1. 34301 አ/አ ላዳ ታክሲ ውስጥ በመዳበሪያ ተፈታቶ የተቀመጠ 1 ኤስ ኬኤስ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ ሲያሽከረክር የነበረው አሽከርካሪ ተይዞ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አሳውቋል።
ህገወጥ የጦር መሳሪዎቹ የተያዙት የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ባደረጉት ክትትል ነው።
@tikvahethiopia

#ETHIOPIA
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ለህዝቡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
" ይኼ ጊዜ ችግሮች ተደራርበው የመጡበት የፈተና ጊዜ ነው" ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፈተናው እስኪያልፍ ሁሉም ሰው መፈተኑ አይቀርም ብለዋል።
" ችግሮቻችን አፋጣኝ መፍትሄ አግኝተው ወደ መደበኛ ኑሮ እስክንመለስ ሁላችንም አኗኗራችንን ለፈተና ጊዜ እንዲስማማ አድርገን መቆየት አለብን፤ እንደ ሰላሙ ጊዜ ነገሮች አልጋ በአልጋ እንዲሆኑ መጠበቅ የሰላሙን ጊዜ ያርቀዋል እንጂ ፈጽሞ አያቀርበውም " ሲሉ ገልፀዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀውም የመከራውን ጊዜ ለማሳጠርና የመፍትሔውን ጊዜ ለማቅረብ መሆኑን አሳውቀዋል።
ዜጎች ወቅቱ እንደሚጠይቀው በመሆን፣ አዋጁ የሚያዝዛቸውን መመሪያዎች በማክበር፣ የሕግ አስከባሪ አካላት ሥራቸውን በቅልጥፍና እንዲያከናውኑ በመተባበር እና አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#ሰበር_ዜና ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በetv እየሰጡ በሚገኙት መግለጫ ዛሬ ምሽት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከመቐለ ጀምሮ በበርካታ ስፍራዎች ጥቃት እንደተፈፀመበት አስታውቀዋል። ጥቃቱን የፈፅሙት "ካሃዲ ኃይሎች እና ያደራጁት ኃይል" ነው ሲሉ ገልፀዋል። ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ፥ "ጥቃቱ በሀገራችን እስካሁን ከደረሱ ጥቃቶች እጅግ አስነዋሪ ነው፤ ሰላም ለማስከበር በተለያየ ሀገር የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት…
ሰሜን እዝ ላይ የተፈፀመው ጥቃት 1ኛ ዓመት እየታሰበ ነው።
የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ የተፈፀመበት ጥቃት አንደኛ አመት እየታሰበ ይገኛል።
በመርሃ ግብሩ በመከላከያ ሚኒስቴር ግቢ ውስጥ እየተካሄደ ሲሆ በመርሃ ግብሩ ላይ ፦
- ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፣
- ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣
- የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ፣
- የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የዛሬው ዕለት ‹‹አልረሳውም እኔም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነኝ›› በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት መርሃ ግብር ላይም የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት እና በጧፍ ማብራት ስነ ስርዓት ተካሂዷል።
በተጨማሪም ዛሬ ጥዋት የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ባይፋዊ የማህባራዊ ትስስር ገፃቸው ዕለቱን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል (ከላይ ተያይዟል)።
የኢትዮጵያ መንግስት ልክ የዛሬ ዓመት ህወሓት ሰሜን ዕዝን ከጀርባ መውጋቱን መግለፁ አይዘነጋም።
ምንም እንኳን በተለያዩ የፖለቲካ ጉዳዮች ውጥረት ውስጥ የነበረው የፌዴራል መንግስቱ እና የህወሓት ግኝኑነት ጥቅምት 24 ቀን 2014 ህወሓት ሰሜን እዝን በመውጋቱና በማጥቃቱ ዛሬም ድረስ ለዘለቀው ጦርነት መነሻ ዋነኛው ምክንያት ሆኗል።

#Update የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ ግጭት ዙሪያ በጋራ ያካሄዱት ምርመራ ሪፖርት ጥቅምት 24/2014 ዓ/ም ይፋ ይሆናል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ እንዲሁም የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት የጋራ ሪፖርቱን ግኝቶች፣ መደምደሚያዎች…
#ETHIOPIA
ዛሬ ጥቅምት 24/2014 ዓ/ም የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ ግጭት ዙሪያ በጋራ ያካሄዱት ምርመራ ሪፖርት ይፋ ይደረጋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ እና የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት የጋራ ሪፖርቱን ግኝቶች ፣ መደምደሚያዎች እና ምክረ ሃሳቦችን ለማቅረብ በአዲስ አበባ እና ጄኔቫ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ።

* ዝርዝር መረጃ ! ከዛሬ ጀምሮ በመላ አገሪቱ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተከለከሉ ተግባራትና ግዴታዎች ከላይ በዝርዝር ተቀምጠዋል ያንብቡ። @tikvahethiopia
#የወንጀል_ተጠያቂነት
መላው ሀገሪቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ትገኛለች፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ድንጋጌዎች እንዲሁም አዋጁን መሰረት አድርጎ የወጡትን መመሪያዎች መተላለፍ የወንጀል ተጠያቂነትን ያመጣል ፤ ቅጣትን ያስከትላል።
ይህም የወንጀል ተጠያቂነት ፦
- የአዋጁን ድንጋጌዎች እና በአዋጁ መሰረት የወጡ መመሪያዎችን ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም ሰው እስከ 3 አመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም እንደጥፋቱ ክብደት እስከ 10 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ይቀጣል።
- የአዋጁን ድንጋጌዎች እና በአዋጁ መሰረት የወጡ መመሪያዎችን በመተላለፍ የተፈፀመው ወንጀል በሌሎች ሕጎች ከዚህ ከፍ ያለ ቅጣት የሚያስከትል ከሆነ የከበደው ቅጣት ተፈጻሚ ይሆናል።
- በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የተፈፀሙ የአዋጁ እና በአውጁ ማዕቀፍ የወጡ መመሪያዎች ጥሰቶች የአዋጁ ተፈጻሚነት ጊዜ ቢያበቃም፣ የሚያስከትሉት የወንጀል ተጠያቂነት በመደበኛው የወንጀል ሥነ ስርዐት ሕግ መሰረት ይቀጥላል።
#StateofEmergencyEthiopia

#AddisAbaba መሳሪያ ያላስመዘገቡ የአዲስ አበባ ባለጦር መሳሪያ ግለሰቦች በ2 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግቡ የከተማ አስተዳደሩ የሰላምና ደህንነት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ አሳሰቡ። የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ወቅታዊ ፀጥታን በተመለከተ መግለጫ ተሰጥተዋል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመንደር እርስ በርስ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቁ ተፈቅዷል ብለዋል። አደረጃጀቱ ከፀጥታ…
#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ማንኛውም አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ወይም የፖሊስ አገልግሎትን ማግኘት ስትፈልጉ በ 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 ፣ 997 መጠቀም እንደምትችሉ አዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።
በሌላ በኩል ማንኛውም ግለሰብ በእጁ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ትላንት በተቀመጠው የሁለት ቀን ጊዜ ውስጥ በ11ዱ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎችና በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በስራ ሰዓት በግንባር ቀርቦ ማስመዝገብ አለበት።
በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማንኛውም ግለሰብ በእጁ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ በማስመዝገብ ህጋዊነቱን ተላብሶ የጦር መሳሪያውን ተጠቅሞ እራሱንና አካከበቢው እንዲጠብቅበት ሲል ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

#Update የአዲሱ ክልል የስልጣን ርክክብ ነገ ይደረጋል። ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔውን ነገ ጥቅምት 24/2014 ዓ/ም እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አስታውቀዋል። የተከበሩ የምክር ቤቱ ዋና አፌ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ሰርሞሎ ዛሬ እንዳሳወቁት ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሂው አስቸኳይ ጉባኤ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ…
#Update
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ አስቸኳይ ጉባዔውን በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ማከሄድ ጀምሯል።
በዚህ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በፌዴረሽን ምክር ቤት 11ኛ ክልል ሆኖ ለጸደቀው ደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል የስልጣን ርክክብ ያደርጋል።

#ENDF
በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ የአየር ኃይል አዲሀገራይ በተባለ አካባቢ በሚገኝ አዲቡክራይ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ማሠልጠኛ ማዕከል ላይ የአየር ድብደባ መፈፀሙን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል።
በዚህ ማሠልጠኛው በአሁኑ ወቅት የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ለሽብር ተልዕኮው የመለመላቸው በርካታ ታጣቂዎች እያሠለጠነበት የሚገኝበት ቦታ ነው ሲል የመንግስት ኮሚኒኬሽን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል።

#ETHIOPIA ዛሬ ጥቅምት 24/2014 ዓ/ም የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ ግጭት ዙሪያ በጋራ ያካሄዱት ምርመራ ሪፖርት ይፋ ይደረጋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ እና የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት የጋራ ሪፖርቱን ግኝቶች ፣ መደምደሚያዎች እና ምክረ ሃሳቦችን…
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
3.8 MB
#የምርመራ_ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (EHRC) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (OHCHR) በትግራይ ግጭት ዙሪያ በጋራ ያካሄዱት ምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆኗል።
የEHRC እና OHCHR የጋራ ሪፖርት በትግራይ ግጭት ላይ የተሳተፉ ሁሉም አካላት የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን ያሳያል።
* ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (EHRC) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (OHCHR) በትግራይ ግጭት ዙሪያ በጋራ ያካሄዱት ምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆኗል።
የEHRC እና OHCHR የጋራ ሪፖርት በትግራይ ግጭት ላይ የተሳተፉ ሁሉም አካላት የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን ያሳያል።
* ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING በመላ ሀገሪቱ ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ያሳለፈው ውሳኔ ከዛሬ ጀምሮ ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን በ48 ሰዓታት ውስጥ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፀድቃል። @tikvahethiopia
#Update
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ነገ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ይፀድቃል።
በሃገር ህልውናና ሉአላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነገ ለም/ቤቱ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኃላ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በኢፌደሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 93/1 ፦
• የውጪ ወረራ ሲያጋጥም ወይም ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የህግ ማስከበር ስርዓት ለመቋቁም የማይቻል ሲሆን፣
• ማንኛውም የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ወይም የህዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት፣ የፌዴራሉ መንግስት የሚኒስትሮች ም/ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማውጣት ሥልጣን እንዳለው ይደነግጋል፡፡
በዚሁ አንቀጽ 2(ሀ) የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሥራ ላይ ባለ ጊዜ የታወጀ ከሆነ በታወጀ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መቅረብ አለበት በሚል ተደንግጓል ፡፡
በዚህም በሚኒስትሮች ም/ቤት የተዘጋጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነገ ለም/ቤቱ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኃላ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
@tikvahethiopia
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ነገ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ይፀድቃል።
በሃገር ህልውናና ሉአላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነገ ለም/ቤቱ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኃላ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በኢፌደሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 93/1 ፦
• የውጪ ወረራ ሲያጋጥም ወይም ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የህግ ማስከበር ስርዓት ለመቋቁም የማይቻል ሲሆን፣
• ማንኛውም የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ወይም የህዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት፣ የፌዴራሉ መንግስት የሚኒስትሮች ም/ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማውጣት ሥልጣን እንዳለው ይደነግጋል፡፡
በዚሁ አንቀጽ 2(ሀ) የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሥራ ላይ ባለ ጊዜ የታወጀ ከሆነ በታወጀ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መቅረብ አለበት በሚል ተደንግጓል ፡፡
በዚህም በሚኒስትሮች ም/ቤት የተዘጋጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነገ ለም/ቤቱ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኃላ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
" Genocide ተካሂዷል ለማለት መረጃ የለም" - ሚሼል ባሽሌት
ጄኔቫ ላይ መግለጫ የሰጡት የተመድ (UN ) የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት በተለያየ ደረጃ በሁሉም አካላት የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን መኖራቸውን ገልፀዋል።
ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት እጅግ በተደጋጋሚ ምርመራው ጭብጦች (Facts) ላይ ተመስርቶ ለማድረግ ጥረት መደረጉን ገልፀዋል።
የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በሁሉም አካላት ቢፈፀሙም #Genocide ዘር ላይ ያተኮረ የጅምላ ፍጅት (የዘር ማጥፋት ወንጀል) ተካሂዷል ለማለት በቂ መረጃ የለም ብለዋል።

#ሪፖርት
በትግራይ ግጭት ሁሉም አካላት ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ፈፅመው መገኘታቸውን የጋራ ሪፖርቱ አመላክቷል።
ተፈፅመዋል የተባሉ ጥሰቶች ፦
• ከሕግ ውጪ ግድያና ርሸና፣
• ማሰቃየት፣
• ወሲባዊና ጾታዊ ጥቃቶች፣
• በስደተኞች ላይ የተፈጸሙ ግፎች እንዲሁም ሰላማዊ ሰዎችን በኃይል ማፈናቀል ይገኙበታል።
በጋራ የምርመራ ሪፖርቱ ከቀረቡት ክስተቶች መካካል በጥቂቱ ፦
በማይካድራ "ሳምረ" በተባለ ቡድን የተፈጸመ ጥቃት ይገኝበታል ፤ ምንም እንኳን ቁጥሩን እርግጠኛ ለመሆን ባይቻልም ከ200 በላይ ሰዎች በዚህ ጥቃት ተገድለው በጅምላ መቃብሮች መቀበራቸውን ተመላክቷል።
የመከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ልዩ ኃይል ከተማውን በተቆጣጠሩባቸው ቀጣይ ቀናት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የማይካድራ ከተማ ነዋሪዎች ላይ የበቀል ግድያዎች መፈጸማቸውን እና የፋኖ ሚሊሺያዎችም በግድያው መሳተፋቸውን ሪፖርቱ ያስረዳል።
በአክሱም ከተማ የኤርትራ ሠራዊት አባላት ከ100 በላይ ሲቪሎችን መግደላቸውን፤ በወቅቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ግድያዎቹ ሲፈጸሙ ጣልቃ ሳይገቡ መቅረታቸውን ሪፖርቱ ገልጿል።
በቦራ አምደውሃ ፣ በቦራ ጫማላ እና ማኢ ሊሃም ከተሞች ከ70 በላይ ሲቪሎች በመከላከያ ሠራዊት መገደላቸውን የጋራ ሪፖርቱ ገልጿል።
እነዚህን እና ሌሎች የግድያ ማስረጃዎችን በመያዝ የሕግ ትንታኔ የሰጠው የምርመራ ቡድኑ በዚህ ጦርነት ውስጥ "የጦር ወንጀሎች" ተፈጽመው ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል።
#EHRC #OHCHR

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ !
ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ የወጣውን የጋራ ሪፖርት በተመለከተ ምላሽ ሰጥተዋል።
TPLF በትግራይ ክልል በቀሰቀሰው ግጭት ወቅት የዘር ማጥፋት ተፈጽሟል በሚል ያናፈሰው የሐሰት ውንጀላ ተጨባጭ መሠረት እንደሌለው በቡድኑ የጋራ ምርመራ በግልፅ ተረጋግጧል ብለዋል።
ቡድኑ ባወጣው ሪፖርት መሰረትም መንግስት ረሃብን 'የጦርነት መሳሪያ' አድርጎ ይጠቀምበታል የሚለውን ተደጋጋሚ ክስ በአሳማኝ ማስረጃ ላይ ያልተመሰረተ ሲል መደምደሙ ይፋ ባደረገው መግለጫ ተመላክቷል ሲሉ ገልፀዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በትግራይ ውስጥ ሆን ተብሎ መንግስት ለህዝቡ የሰብአዊ እርዳታ እንዳይደርስ ከልክሏል በሚል የቀረበውን ክስ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዳላገኘ በሪፖርቱ እንደማለከተ አንስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ''እነዚህ ውንጀላዎች ውሸት መሆናቸውን እናውቃለን፣ ነገር ግን ጠላቶቻችን አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሰርተዋል'' ብለዋል።
በሪፖርቱ ላይ አንዳንድ ጥርጣሬዎች ቢኖሩንም ሪፖርቱን እንደ ጠቃሚ ሰነድ ተቀብለነዋል፤ ለተጎጂዎች መፍትሄ ለመስጠት፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።
አክለውም የሁለቱ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው ሙያዊና ተዓማኒ የሆነ የሰብአዊ መብት ምርመራ ለማካሄድ ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።
* ሙሉ ምላሻቸው ከላይ ተያይዟል።
#ENA