TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba : የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ ክልከላ ወደ ነበረበት መመለሱ ተገለፀ፡፡ በመዲናዋ የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለሱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት በከተማው ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ አየተስተዋለ…
#AddisAbaba
ከትላንት ጥቅምት 22 ጀምሮ በአዲስ አበባ የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ የሰዓት ገደብ ክልከላ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል።
የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለሱን ተከትሎ ለአፈፃፀም ይረዳ ዘንድ መመሪያ 03/2011 በመጫን አቅም ልክ መጠን ከባድና ቀላል ተሽከርካዎች በማለት የሰዓት ገደብ ክልከላውን ለይቶ አስቀምጧል፡፡
በመመሪያው መሰረት ማንኛውም የጭነት፣ የማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች ከማለዳ 12፡30 እስከ ረፋዱ 4፡00 ሰዓት እንዲሁም ከቀኑ 10፡00 እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዲሁም ጭነት መጫንና ማራገፍ አይችሉም።
በመመሪያው ክፍል ሁለት ስለሰዓት ገደብ እና ስለፈቃ በሚያትተው ጽሁፍ መሰረት ማናቸውም ቀላል የጭነት ተሽከርካሪዎች ማለትም ከ25 እስከ 35 ኩንታል (ከ2.5 እስከ 3.5 ቶን) የመጫን አቅም ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 12፡30 እስከ ረፋዱ 4፡00 እንዲሁም ከቀኑ 10፡00 እስከ ምሽቱ 2፡00 እንቅስቃሴ የሚገደቡ ይሆናል፡፡
ይህ ማለት ከሰዓት ክልከላው ውጭ ያለው ጊዜ ከረፋዱ 4፡00 እስከ ከቀኑ 10፡00 ድረስ መንቀሳቀስ የሚችሉ ይሆናል፡፡
በተጓዳኙ ከባድ ተሽከርካሪዎች ማለትም ከ35 ኩንታል (ከ3.5 ቶን) በላይ የመጫን አቅም ያላቸው ተሽከርካሪዎች ደግሞ ከማለዳው 12፡30 እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ወደ ከተማ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዲሁም ጭነት መጫንና ማራገፍ እንደማይቻሉ በመመሪያው ተቀምጧል፡፡
የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 03/2011 በሰኔ 2011 ዓ.ም ፀድቆ ተግባራዊ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡
#AATB
@tikvahethiopia

#AddisAbaba ከትላንት ጥቅምት 22 ጀምሮ በአዲስ አበባ የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ የሰዓት ገደብ ክልከላ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል። የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለሱን ተከትሎ ለአፈፃፀም ይረዳ ዘንድ መመሪያ 03/2011 በመጫን አቅም ልክ መጠን ከባድና ቀላል ተሽከርካዎች በማለት የሰዓት ገደብ ክልከላውን ለይቶ አስቀምጧል፡፡…
ቅጣትን በተመለከተ ፦
" የሰዓት ክልከላውን የሚጥሱ አካላት ከ5 መቶ እስ 6 ሺህ በገንዘብ እና ከ1 ወር እስከ 3 ወር መንጃ ፈቃድ በማገድ ያስቀጣል " - አአትቢ
የጭነት፣ ማሽነሪዎችና መሰል ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለሱን ተከትሎ ክልከላውን በሚጥሱ አካላት ላይ ከ5 መቶ እስ 6 ሺህ በገንዘብ እና ከ1 ወር እስከ 3 ወር የመንጃ ፈቃድ እገዳ ያስጥላል።
አሽከርካሪዎች በተለይ የከባድ ጭነት፣ ማሽነሪዎችና መሰል ተሽከርካሪዎችን የሚነዱ በሙሉ መረጃውን በማወቅ መመሪያውን እንዲያከንሩ ተብሏል።
የህግ አስከባሪዎችም መመሪያውን በሚጥሱ አካላት ላይ በተቀመጠው የቅጣት ወሰን መሰረት እንዲፈፀም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
* ቅጣትን በተመለከተ ከላይ በዝርዝር ይመልከቱ።
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ
@tikvahethiopi

ትምህርት ሚኒስቴር ፦
• በመቐለ፣
• በዓዲግራት፣
• በአክሱም፣
• በራያ እንዲሁም ወልድያ ዩኒቨርሲቲዎች የ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ጊዚያዊ ምደባ እንዲደረግላቸው ምዝገባ ያድርጉ ብሏል።
ምዝገባው የሚካሄደው ከዛሬ ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አርብ ጥቅምት 26/2014 ዓ.ም መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ጥሪው የሚመለከታቸው የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች በተከታዩ ሊንክ forms.gle/33My9GLyykYHg6K49 ይመዝገቡ ብሏል ሚኒስቴሩ።
@tikvahuniversity

መሳሪያ ያላስመዘገቡ የአዲስ አበባ ባለጦር መሳሪያ ግለሰቦች በ2 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግቡ የከተማ አስተዳደሩ የሰላምና ደህንነት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ አሳሰቡ።
የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ወቅታዊ ፀጥታን በተመለከተ መግለጫ ተሰጥተዋል።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመንደር እርስ በርስ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቁ ተፈቅዷል ብለዋል። አደረጃጀቱ ከፀጥታ ተቋማት ጋር እየተናበበ አካባቢውን መቆጣጠር እንዳለበት ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፀጥታ ሰላም ቢሆንም ውዥንብር የሚፈጥሩ አካላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው ብለዋል።
የፖሊስና የመከላከያ ፀጥታ አካላት ከኦሮሚያ ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ሰላምና ደህንነት ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የጦር መሳሪያን በተመለከተ ህጋዊም ሆነ ያላስመዘገቡ አካላት በሁለት ቀናት ማስገንዘብ አለባቸው ብለዋል።
የጦር መሳሪያው በመንግስት ከታወቀና ህጋዊ ከሆነ በራሱ የአካባቢውን ፀጥታ እንዲያስጠብቁ ይደረጋል ብለዋል።
መሳሪያ ያላቸው አካላት አካባቢያቸውን መጠበቅ የማይችሉ ከሆነ ለቅርብ ሰው ወይም ለመንግሥት በአደራ ሰጥተው እንዲጠበቅበት ይደረጋል ብለዋል።
የአዲስ አበባን ሰላም ለማስከበር የፍተሻ ስራዎች በየተለያዩ ቤቶችና ንግድ ቦታዎች እንደሚደረግ ጠቁመው ለዚህም ህብርተሰቡ እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

#MoE
የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጋር ምክክር አደረጉ::
በምክክር መድረኩ ላይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከትርፍ ባለፈ ማህበረሰቡን ማገልገል እንዳለባቸው ተገልጿል::
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በትምህርት ዘርፉ ላይ ካሉ የግል ተቋማት ጋር ግልፅ መናበብ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመንግስት ላይ የሚያነሱትን ቅሬታዎችን እንዲሁም ህብረተሰቡ በተቋማቱ ላይ የሚያነሳቸውን ቅሬታዎች እና ጥያቄዎች አንስተው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
ፕሮፌሰር ብርሀኑ በቀጣይ የትምህርት ዘርፉ የሚሄድበትን አቅጣጫ እና ለውጦችም ለተሳታፊዎች ገልፀዋል።
በዚህም በመንግስት እና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እኩል ቁጥጥር እንደሚደረግ እና በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የመውጫ ፈተናዎች በግል ከፍተኛ ተቋማትም እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
የግል ኮሌጆች የማስተማሪያ ፍቃድ አሰጣጥ ላይም ከፍተኛ ቁጥጥር እንደሚደረግም ገልፀዋል።
በመድረኩ የግል ከፍተኛ ተቋማት አመራሮችም ለተቋማቱ አፈፃፀም እንቅፋት ናቸው ያሏቸውን ሀሳቦች ለሚኒስትሩ አቅርበዋል።
ከዚህም ውስጥ የትምህርት አዋጁ ፣የመምህራን እጥረት፣ የመንግስት ድጋፍ አናሳ መሆን የተቋማቱ ተግዳሮቶች መሆናቸውን ነው የተናገሩት።
ምንጭ : ትምህርት ሚኒስቴር

#US : በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አሜሪካ በCOVAX በኩል ለኢትዮጵያ ያበረከተችው 1,555,590 ዶዝ የPfizer የCOVID-19 ክትባት ኢትዮጵያ መድረሱን አሳውቋል::
እኤአ ከሃምሌ 2021 ጀምሮ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የሚሰጠችው የኮቪድ-19 ክትባት መጠን ወደ አራት ሚሊዮን ገደማ መድረሱን ኤምባሲው ጠቁሟል ፤ ይህም COVID-19 ለመከላከል በአንድ ሀገር አማካኝነት ለኢትዮጵያ የተበረከተ ከፍትኛው ክትባት መሆኑን ገልጿል።

#Dessie #Kombolcha
ወሎ ህብረት የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ኃይሎች በደሴ እና በኮምቦልቻ ከተሞች በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን መጨፍጨፋቸውን የተለያዩ ምንጮች ማረጋገጣቸውን ገልጿል።
ማህበሩ ፤ እነዚህ ኃይሎች ወጣቶቹን የጨፈጨፏቸው በከተማቸው ለመቆየት ስለወሰኑ ነው ብሏል።
በተጨማሪ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ የሟቾችን አስክሬን መንገድ ላይ እንዲቀር መደረጉንና ይህም ህዝቡን በማሸበር በግዳጅ እንዲፈናቀል በማድረግ ወራሪዎቹ ኃይሎች የህዝብ እና የግል ንብረቶችን በነፃነት ለመዝረፍ እንዲያመቻቸው ነው ሲል አሳውቋል።
ወሎ ህብረት በኮምቦልቻ እና ደሴ ከተሞች ህዝብን ለማሸበር በTPLF ኃይሎች ሆን ተብሎ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው ግድያ በአለም አቀፍ ደረጃ የጦር ወንጀል የሆነ የሽብር ተግባር ነው ብሎታል።
ህብረቱ ይህን አረመኔያዊ የሽብር ድርጊት እናወግዛል ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ወንጀለኞችን በህግ እንዲጠየቅ እና ተጨማሪ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ እንዲከላከል አሳስቧል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በማያሻማ መልኩ በትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) የተፈፀመውን አሳፋሪ የሽብር ድርጊት እንዲያወግዝ ሲል አሳስቧል።
ወሎ ህብረት የልማት እና በጎ አድራጎት ማህበር በኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ የተመዘገበ ህጋዊ ሰውነት ያለው ሀገር በቀል ድርጅት ነው።

#Update የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የፊታችን ቅዳሜ አስቸኳይ ስብሰባ የሚያካሂድ ሲሆን በዚሁ ስብሰባ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝበ ውሳኔ ውጤትን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ህዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ ለ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ በሰጡት ቃል ፥ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝበ ውሳኔውን ውጤት ለፌደሬሽን ም/ቤት በደብዳቤ…
#Update
የአዲሱ ክልል የስልጣን ርክክብ ነገ ይደረጋል።
ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔውን ነገ ጥቅምት 24/2014 ዓ/ም እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አስታውቀዋል።
የተከበሩ የምክር ቤቱ ዋና አፌ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ሰርሞሎ ዛሬ እንዳሳወቁት ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሂው አስቸኳይ ጉባኤ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በፌዴረሽን ምክር ቤት 11ኛ ክልል ሆኖ ለጸደቀው ደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል የስልጣን ርክክብ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ምክር ቤቱ በሌሎች አገራዊና ክልላዊ አጀንዳዎች ዙሪያም በመወያየት ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍም የተከበሩ አፈ ጉባኤ ገልጸዋል።
Credit : SNNPP

#DAWA : በሶማሊ ክልል ዳዋ ዞን (የቦረና አጎራባች) በተከሰተ ድርቅ 25,000 ገደማ የቁም እንስሳት ማሞታቸውን የሶማሊ ክልል አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ቢሮ አስታውቋል። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሳዲቅ አብዱቃድር ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ በድርቁ የተነሳ ግመሎች እና የቀንድ ከብቶች መሞታቸውን ተናግረዋል። አስቸኳይ ድጋፍ ካልተገኘ አሁን ከሞቱት በላይ እንስሳት ሊሞቱ ይችላሉ ብለዋል። እስካሁን…
የዳዋ ዞን ነዋሪዎች ያሉበት ሁኔታ ፦
በሶማሊ ክልል ዳዋ ዞን (የቦረና አጎራባች) በተከሰተው ድርቅ የሞቱት የቁም እንስሳት 47,215 መድረሳቸውን ከአንድ ሪፖርት መመልከት ችለናል።
ሪፖርቱ የተዘጋጀው ከጥቅምት 25 እስከ 29 ቀን 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ በተካሄደ ዳሰሳ ሲሆን ይህም የተመራው በዳዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ፣ በዳዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት፣ ከዞኑ የአደጋ ስጋት አስተዳደር እና የዞን መንግስት ቢሮ እና የሰብአዊ እርዳታ አጋሮች WFP፣ Save the Childern ፣ VSF-Suisse፣ UNICEF፣ CISP፣ PC፣ PIADO፣ Racida ፣ OWDA፣ PCI እና YAADAP እንዲሁም የወረዳ መምሪያ ቢሮዎች ጋር በመሆን ነው።
በሪፖርቱ ላይ ፦
- በዚህ ወቅት ይዘንባል ተብሎ የሚጠበቀው ዝናብ በመላው ዞኑ አልጀመረም። በሙባረክ ወረዳ ብቻ በሰባት ንኡስ መንደሮች በ31 መንደሮች ትንሽ ዝናብ የዘነበ ሲሆን የቀሩት 3 ወረዳዎች ምንም ዝናብ አላገኙም።
- በዳዋ ዞን ከሁሉም ወረዳ 95% ቀበሌዎች አብዛኛው የውሃ ምንጭ በመድረቁ የውሃ ማጓጓዣ የሚያስፈልጋቸው ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ በጥቅምት ወር መጨረሻ ይደርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
- የእንስሳት ገበያ ዋጋ በእጅጉ ቀንሷል።
- በአጠቃላይ በዞኑ 47,215 የእንስሳት ሞት ተመዝግቧል።
• ግመሎች - 5,666
• ከብቶች - 4241
• ፍየሎች - 37,057
- በዞኑ በተከሰተው አስከፊ ድርቅ 10 ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል።
- 62,960 አርብቶ አደሮች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፤ ባለው ድርቅ ምክንያት እንስሳት ማርባት አልቻሉም።