TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#WHO : ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገብረእየሱስ ለዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዋና ዳሬክተርነት ብቸኛ እጩ ሆነው መቅረባቸውን የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ሲጂቲኤን አፍሪካ በሰበር ዜናው ዘግቧል። @tikvahethiopia
#Update

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊነት ዶ/ር ቴድሮስ ብቸኛ እጩ መሆናቸውን አረጋገጠ።

ከሰዓታት በፊት CGTN Africa ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ብቸኛ እጩ ሆነው መቅረባቸውን ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ መዘገቡ ይታወሳል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፥ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊው ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ለቀጣይ ዙር ብቸኛ ተወዳዳሪ መሆናቸውን አረጋግጧል።

ዶ/ር ቴድሮስ በማመልከቻ ጽሑፋቸው ላይ ኮቪድ-19 ወረርሺኝ ዓለምን ማንኮታኮቱን ገልፀው በሁለተኛ ዙር የሥልጣን ዘመናቸው ዓለማችንን ለመሰል ወረርሺኝ "የምር ዝግጁ" መሆኗን ማረጋገጥ ፍላጎታቸው መሆኑን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
ፎቶ : ዛሬ የአዲስ አበባ ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ የሰብአዊ አገልግሎት ተቋርጣል።

ንጋት 12:00 ሰዓት ጀምሮ ምንም ግልፅ ባልሆነ መልኩ አፍራሽ ግብረሀይል ግቢው ውስጥ በመገኘት በማፍረሳቸው ፣ መብራት እና ስልክ ተቋርጣል ፤ አሁን ላይም አገልግሎት በማይሰጥበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በጎ-ፈቃደኞች የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት እንዲያውቁት በሚል መልዕክት ልከዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቃላቸውን ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ የሰጡ ጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች የፈረሰዉ የሪል ስቴት ገንቢ ለሆነዉ አልሳም ግሩፕ ለማስተላለፍ መሆኑን መስማታቸዉን ገልፀዋል።

ቀይ መስቀል ቅጥር ግቢ ዉስጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መግባት የተከለከለ ሲሆን፣ ጽህፈት ቤቱን በሚፈርስበት ሰዓት ፖሊሶች በጉልበት መሳሪያ ይዘዉ ገብተዋል ሲሉም ለጋዜጣው አሳውቀዋል።

Photo Credit : Tikvah Family

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 9 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,753 የላብራቶሪ ምርመራ 478 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 435 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#EMA

ከዛሬ ጀምሮ በአገር ውስጥ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የውጭ አገር ፕሮግራሞችን ሊንክ አድርጎ ማስተላለፍ ከዛሬ ጀምሮ መከልከሉን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ እድሪስ አሳውቀዋል።

አቶ መሃመድ ይህ ያሳወቁት ለኢዜአ በሰጡት ቃል ነው።

አቶ መሃመድ ፥ በውጭ አገራት የሚሰሩ የሬዲዮ ጣቢያዎች የሚተላለፉ ፕሮግራሞች የአገር ውስጥ ህግና ስርዓትን ተከትለው አይካሄዱም ብለዋል።

በተጨማሪ የአገሪቷን ፖለቲካዊ ነበራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያላስገቡ ፕሮግራሞችም ሲተላላፉ እንደነበርም አስታውሰዋል።

እነዚህ አካላት በአገር ውስጥ ፈቃድ ያላገኙ በመሆናቸው የሚተላለፉ መርሃ ግብሮችን በመከታተል ግብረ መልስና የማስተካከያ ሃሳብ ለመስጠት የሚቻልበት ሁኔታ አለመኖሩን ገልጸዋል፡፡

በአገር ውስጥ የሚያስተላልፉ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ፕሮግራሞቹ ላይ የሚያደርጉት ቁጥጥር አነስተኛ መሆኑን አቶ መሃመድ ተናግረዋል።

"በፕሮግራሞቹ የአንዳንድ አገራት አቋም መግለጫ ሲተለለፍ የሚታይበት እና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ግምት ውስጥ ያላስገ ሲሆን ተስተውሏል" ሲሉም አስረድተዋል።

የተጠቀሱትን ሃሳቦች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ባለስልጣኑ ከዛሬ ጀምሮ ከውጭ ሚዲያዎች ወደ አገር ውስጥ የኤፍ ኤም ጣቢያዎች ሊንክ አድርጎ ማስተላለፍን ከልክሏል ሲሉ አሳውቀዋል።

በአገር ውስጥ ፈቃድ ያልተሰጣቸው የውጭ አገር የሬዲዮ ጣቢያዎች ፈቃድ ባላቸው የአገር ውስጥ የኤፍ ኤም ማሰራጫ ጣቢያዎች አማካኝነት ፕሮግራሞቻቸውን ሲያስተላልፉ ቆይተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Dessise : ከደሴ ከተማ ውጭ ካለ ስፍራ ወደ ደሴ ከተማ በተተኮሱ የመድፍ አረሮች ምክንያት 1 ሰው ሲገደል 3 ሰዎች መቁሰላቸውን የደሴ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል አስታውቁ። አቶ አበበ ገብረ ይህን ያሳወቁት ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ነው። ከንቲባው ጥቃቱ ትናንት ሐሙስ ጥቅምት 18/2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በግምት 9:30 የተፈፀመ መሆኑን ገልፀው ፥ "የህወሓት ኃይሎች ሰላማዊ ሰዎች በሚገኙባቸው…
#Dessie

ደሴ ትላንት ከሰዓት መጠነኛ አለመረጋጋት ተከስቶ ነበር፤ አስተዳደሩ ክስተቱ የተፈጠረው " የህወሓት ተላላኪዎች በፈጠሩት ሀሰተኛ ውዥንብር ነው " ብሏል ፤ አለመረጋጋቱ ተስተካክሎ ማህበረሰቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው እየተመለሰ መሆኑም ለኢዜአ ገልጿል።

ለከተማው አለመረጋጋት ምክንያት የነበሩትንም ከማህበረሰቡ ውስጥ ተለይተው በማውጣት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል ተብሏል።

በሌላ በኩል ትላንት ወደ ደሴ በተወረወረ ከባድ መሳሪያ አንድ ሰው መገደሉን ከከተማው አስተዳደር ተሰምቷል፤እስካሁን ወደከተማው በተወረወረ ከባድ መሳሪያ የተገደሉ ሰዎች 3 ደርሰዋል።

የደሴ ም/ከንቲባ ሰይድ የሱፍ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል፥ በትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) በሚወረወረው ከባድ መሳሪያ እስካሁን 3 ሰዎች መሞታቸውና 10 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ላይ ናቸው ብለዋል።

ህወሓት ከደሴ ከተማ ውጭ ሆኖ የሚተኩሳቸው የከባድ መሳሪያ አረሮች የሚያርፉት በጦርነት ምክንያት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ዜጎች የተጠለሉባቸው ቦታዎች መሆኑን፤ ትላንት ይኸው የከባድ መሳሪያ አረር የወደቀው ተፈናቃዮች መጠለያ አካባቢ ነው ብለዋል አቶ ሰይድ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Dessie ደሴ ትላንት ከሰዓት መጠነኛ አለመረጋጋት ተከስቶ ነበር፤ አስተዳደሩ ክስተቱ የተፈጠረው " የህወሓት ተላላኪዎች በፈጠሩት ሀሰተኛ ውዥንብር ነው " ብሏል ፤ አለመረጋጋቱ ተስተካክሎ ማህበረሰቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው እየተመለሰ መሆኑም ለኢዜአ ገልጿል። ለከተማው አለመረጋጋት ምክንያት የነበሩትንም ከማህበረሰቡ ውስጥ ተለይተው በማውጣት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል ተብሏል። በሌላ በኩል…
ማህበራዊ ሚዲያው ?

ደሴ ከተማ ምትገኝበት ቀጠና ግጭት በመኖሩ ሳቢያ ከተማይቱ የማህበራዊ እና ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የአይን ማረፊ ሆናለች።

መልዕክታቸውን የላኩልን የደሴ አባላት በበኩላቸው በየዕለቱ የከተማውን ህዝብ ለመረበሽ ከፍተኛ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በሚነዛበት በዚህ ወቅት አንዳንዶች አውቀውና ሆን ብለው ሌሎች ባለማወቅ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያው በህዝቡ ላይ ከፍተኛ የስነልቦና ጫና እሳደሩ ነው ብለዋል።

ከሰሞኑን በተደጋጋሚ ደሴና ኮምቦልቻ ላይ የሚነዙት የሀሰት ወሬዎች ህዝቡን ለማስደንገጥና ለመረበሽ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የሀገር ጉዳይ ያሳስበኛል የሚል ሁሉ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀሙን እንዲያስተካክል ፤ አንዳንዴ የሚሰጡት መረጃዎችም ትክክለኛ መሬት ላይ ያለውን እውነት መሰረት ያደረጉ መሆን አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል።

በሌላ ሀገር እና ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች ሆነው ምንም ተጨባጭ መረጃ በሌላቸው እና አንዳንዴ ደግሞ ሆን ብለው የህዝብን ችግር እያባባሱ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው ቢታረሙ መልካም ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሱዳን ወታደራዊ ጁንታ በዚህ ሳምንት ያደረገውን የመንግስት ግልበጣ በመቃወም የተናገሩ ቢያንስ 6 አምባሳደሮችን ከሥራና ኃላፊነታቸው ማበረሩን የመንግስት ቴሊቪዥን ዛሬ ማሳወቁን የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል። ቴሌቪዥን ጣቢያው ጀኔራል አብዱፈልታ አል ቡርሃን በአሜሪካ ፣ አውሮፓ ህብረት፣ ቻይና ፣ ኳታር እና ፈረንሳይ እንዲሁም በጀኔቭ የተባበሩት መንግሥታት የሱዳን ተወካይ መልክተኛን ማባረራቸውን ገልጿል፡፡…
#SUDAN : የሱዳን የፀጥታ ሀይሎች ተቃውሞዋቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት አደባባይ በሚወጡ ዜጎች ላይ የሀይል እርምጃ እንዳይወስዱ አሜሪካና ብሪታኒያ አስጠነቀቁ።

በዛሬው እለት የሱዳን ጦር በሲቪል አስተዳደሩ ላይ የወሰደውን እርምጃ በመቃወም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሲዳናውያን አደባባይ ወጥተው ተቃውሞዋችን እንደሚያሰሙ ይጠበቃል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፤ የሱዳን የፀጥታ ሐይሎች ዛሬ ቅዳሜ ሱዳናውያን ለማድረግ ባሰቡት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ሰብአዊ መብት ሊያከብሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

እንዲሁም የፀጥታ ሀይሎች ተቃውሞዋቸውን በሰላማዊ መንገድ በሚያሰሙ ሰዎች ላይ የሀይል እመርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል።

የሱዳን ህዝቦች ዴሞክራሲን ለማስፈን በሚያደርጉት ሰላማዊ ትግል አሜሪካ ከጎናቸው መሆኗንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ እና ልማት ቢሮም በትዊተር ገጹ ፥ የሱዳን የፀጥታ ሀይሎች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞዋቸውን የሚያሰሙ ዜጎችን መብት ሊያከብሩ ይገባል ብሏል።

“በርካታ ሱዳናውያን ዛሬ ለተቃውሞ አደባባይ ይወጣሉ” ያለው ቢሮው፤ “የፀጥታ ሀይሎች በዚሁ ወቅት የዜጎችን ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ሊያከብሩ ይገባል” ሲል አሳስቧል።

ምንጭ፦ አል ዓይን

@tikvahethiopia
#AddisAbaba : በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሳለሚያ እህል በረንዳ አካባቢ አማኑኤል ጸጋ አብ ህንጻ ላይ የእሳት አደጋ ደርሷል።

የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር እና ወደ ሌሎች እንዳይዛመት በእሳትና ድንገተኛ አገልግሎት ባለሙያዎች ፣ፖሊስ አባላት እና የአካባቢው ወጣቶች እየተረባረቡ ይገኛሉ ብሏል።

የእሳት አደጋውን መንስኤ በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት እና ተያያዥ ጉዳዮች በቀጣይ ይገለፃል ተብሏል።

Credit : AAPS
Photo ፦ Amaye

@tikvahethiopia
#DireDawa : " ሙሉ እና ጎዶሎ በሚል የተጀመረ የትራንስፖርት አገልግሎት የለም " - የት/ባለስልጣን

በት/ባለስልጣን የድ/ዳ/ቅ/ጽ/ቤት ፥ በድሬደዋ የታክሲ አገልግሎት ሙሉ ጎዶሎ በሚል
መሰጠት ስለመጀመሩ እየተሰራጨ ያለው መረጃ
#ሀሰት ነው ሲል አሳውቋል።

ቅ/መስሪያ ቤቱ የታክሲ አሽከርካሪዎች ከመሰል የሀሰት ማደናገሪያዎችበመጠበቅ አገልግሎት መስጠታቸውን እንዲቀጥሉም አሳስቧል፡፡

የሚቀየሩ የአገልግሎት አሰጣጦች ሲኖሩ ከትራፊክ ፖሊስ ዳይሬክቶሬት ጋር በመቀናጀት እንደሚወጡና ይህንንም በተቋሙ ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅና በሌሎች ሚዲያዎች ይፋ እንደሚደረግ አሁን ላይ ግን ምንም አይነት የሙሉ ጎዶሎ አገልግሎት እንዳልተጀመረ እና እንደማይጀመር ገልጿል።

ከሰሞኑ በከተማው የታክሲ አገልግሎት ጎዶሎና ሙሉ በሚል እየተሰጠ አንደሚገኝ ተደርጎ ምንጩ ያልታወቀ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የስራ ጊዜ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ያካሂዳል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልልና ህዝበ ውሳኔ ውጤትን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ @tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች የክልልነት ሕዝበ ውሳኔ ውጤት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በደብዳቤ ባሳወቀውና በአካል ቀርቦ ማብራሪያ በስጠው መሰረት ምክር ቤቱም ውይይት በማድረግና በተቀመጠው ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችና አግባብነት ባላቸው ሕጎች አንጻር መርምሮ እንዲያጸድቅ አፈ ጉባዔው በጠየቁት መሰረት ሕዝበ ውሳኔው በምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡

Via House of Federation of Ethiopia

@tikvahethiopia