#DAWA : በሶማሊ ክልል ዳዋ ዞን (የቦረና አጎራባች) በተከሰተ ድርቅ 25,000 ገደማ የቁም እንስሳት ማሞታቸውን የሶማሊ ክልል አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ቢሮ አስታውቋል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሳዲቅ አብዱቃድር ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ በድርቁ የተነሳ ግመሎች እና የቀንድ ከብቶች መሞታቸውን ተናግረዋል።
አስቸኳይ ድጋፍ ካልተገኘ አሁን ከሞቱት በላይ እንስሳት ሊሞቱ ይችላሉ ብለዋል።
እስካሁን ፦
- 1,360 ግመሎች ሞተዋል።
- 21,148 ፍየሎች ሞተዋል።
- 1098 ከብቶች ሞተዋል።
አሁንም ከዚህ በላይ ቁጥር ያላቸው የሞት አደጋ ውስጥ ናቸው።
አሁን ላይ ድጋፍ እንዲደረግ የተለያየ እንቅስቃሴ መኖሩን ያሳወቁት አቶ ሳዲቅ በወረዳ ደረጃ ውሃ እንዲዳረስ ለማድረግ እና የእስሳት መኖ ከሸበሌ እና ከጅግጅጋ እንዲመጣ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል ከ83 ሺህ በላይ ነዋሪዎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አቶ ሳዲቅ አሳውቀዋል።
ድጋፍ ፈላጊዎቹ ከተለያየ ቦታ ተፈናቅለው ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች (በቁጥር ከ33 ሺ በላይ) እንዲሁም የዛው የዳዋ ዞን ነዋሪዎች (በቁጥር ከ50 ሺ በላይ) መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የምግብ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እስካሁን ድጋፍ መቅረብ እንዳልጀመረ ገልፀው ከፌዴራል መንግስት ድጋፍ እንዲደረግ ጥያቄ መቅረቡን ተናግረዋል፤ ክልሉ ከሰብዓዊ ድርጅቶችም ጋር በመነጋገር ድጋፍ እንዲደረግ ለማስደረግ እየሰራ መሆኑንም ለሬድዮ ጣቢያው ጠቁመዋል።
@tikvhahethiopia

#Bahirdar : የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ በባህር ዳር ከተማ በወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ እየመከረ ይገኛል።
መድረኩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የሚመራ ሲሆን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የሁሉም ክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል የበላይ አመራሮች ተገኝተዋል።
የግንኙነት መድረኩ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ በዝርዝር ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል።
የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኘነት መድረክ የኢፌዴሪ የመንግሥታት ግንኙነት ስርአትን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1231/2013 መሰረት የተቋቋመ ነው።
መረጃው የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።
@tikvahethiopia

" ... ተማሪዎቹ ላይ ስለተፈጠረው ድንገተኛ ሁኔታ በባለሞያ ተረጋግጦ ይገለፃል " - ኮማንደር ሽፈራው ጉቱ
በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ በሚገኘው ሀና የመጀመሪያ ደረጃ የመንግስት ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች ባልታወቀ ምክንያት በድንገት መታመማቸውን ተሰምቷል።
በርካታ ተማሪዎች በአምቡላንስ መወሰዳቸውን ለማወቅ ተችሏል።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ሽፈራው ጉቱ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በሰጡት ቃል በትምህርት ቤቱ ዛሬ ማለዳ 3:30 አካባቢ ተፈጥሯል ስላሉት ሁኔታ አስረድተዋል።
ተማሪዎች ቁርሣቸውን በልተው ወደመማሪያ ክፍል ከገቡ በኃላ በመጀመሪያ ሁለት ከዛም በተከታታይ በርካታ ተማሪዎች በድንገት መውደቃቸውን ኮማንደር ሽፈራው አሳውቀዋል።
ብዛታቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎች በአምቡላንስ ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱ መደረጉን ገልፀዋል።
ተማሪዎቹ ላይ ስለተፈጠረው ሁኔታ በባለሞያ ተረጋግጦ እንደሚገለፅ ኮማንደር ሽፈራው ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።
የክፍለ ከተማው የጤና ፅ/ቤት ለሬድዮ ጣቢያው በሰጠው ቃል የተማሪዎቹ የህመም መነሻ እስካሁን አልታወቀም ብሏል።
Credit : ሸገር ኤፍ ኤም 102.1
Photo : Ermo Hailu

#የምርመራ_ሪፖርት
ፍትህ ሚኒስቴር በአማራ ክልል በሰሜን እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እንዲሁም በአፋር ክልል በሚገኙ ወረዳዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ወንጀል ምርመራንና የመጀመሪያ ደረጃ ግኝቶችን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
ምርመራው የተካሄደው በህወሃት ተይዘው በነበሩና በኃላም ነጻ በወጡ አካባቢዎች ነው።
በዚህ መሰረት ህወሓት በሰሜን ጎንደር ዞን ለጊዜው በዝርዝር ማስረጃ የተለዩ፦
- የ96 ሰዎች ሞት
- 53 የአካል ጉዳት
- 29 አስገድዶ መደፈር
- 11 ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ
- 6 እገታ እንዲሁም የመንግስት፣ የግልና የሀይማኖት የተለያዩ ተቋማት ንብረቶች ላይ መጠነ ሰፊ ዘረፋና ውደመት ፈፅሟል ሲል ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
በደቡብ ጎንደር ዞን ባሉ አምስት ወረዳዎች በድምሩ፦
- የ129 ሰዎች ሞት
- የ54 ሰዎች የአካል ጉዳት
- በንፋስ መውጫ ከተማ ብቻ የ73 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንዲሁም በርካታ ግለሰቦች ንብረት ላይ ውድመት መድረሱ ተገልጿል።
በአፋር ክልል ነሃሴ 29/2013 ዓ.ም በጋሊኮማ ቀበሌ መጠለያ ጣቢያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት፦
- የ240 ሰዎች ሞት
- 42 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በቀሪዎቹ ሶስት ወረዳዎች ደግሞ የ17 ሰዎች ሞት እና ለ17 ሰዎች የአካል ጉዳት እንዲሁም 7 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ተፈፅሟል።
በሁለቱም ክልሎች በሰላማዊ ዜጎች ንብረት ላይ በመንግስት እና በግል ተቋማት ላይ ዘረፋና ውድመት በስፋት መድረሱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በአጠቃላይ ምርመራው በሂደት ላይ ያለ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
እስከ አሁን በተደረሰበት ግን ሁለቱም ክልሎች በተፈጸሙት የወንጀል ድርጊቶች 482 ሞት፣ 165 የአካል ጉዳት እና 109 የአስገድዶ መድፈር ኢሰብዓዊ ድርጊቶች መፈጸማቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል። #አልዓይን

#AddisAbaba : የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ ክልከላ ወደ ነበረበት መመለሱ ተገለፀ፡፡
በመዲናዋ የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለሱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት በከተማው ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ አየተስተዋለ በመሆኑ የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለስ እንዳስፈለገ ተገልጿል።
በመሆኑም ከጥቅምት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በመመሪያው መሰረት ማንኛውም የጭነት፣ የማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካራች ከማለዳ 12፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት እንዲሁም ከቀኑ 10፡00 እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዲሁም ጭነት መጫንና ማራገፍ እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።
@tikvahethmagazine

TIKVAH-ETHIOPIA
* ወቅታዊ ጉዳዮች ! (ለቲክቫህ አባላት የተላከ - #1) - በደቡብ ጎንደር ዞን የተፈፀመው ጥቃት ፣ ዝርፊያ እና ውድመት በተጎኚዎች አንደበት ሲገለፅ ፤ የህወሓት ኃይል በቆየባቸው አጭር ቀናት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰ የተገለፀ ሲሆን ከክልል እስከወረዳ ድረስ የጉዳት መጠን የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሟል። - በትግራይ ክልል ፣ የግጭት ቀጠና በሆኑ የአማራ ክልል አካባቢዎች የኔትዎርክ አለመኖር የንፁሃ ዜጎች…
#WHO : ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገብረእየሱስ ለዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዋና ዳሬክተርነት ብቸኛ እጩ ሆነው መቅረባቸውን የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ሲጂቲኤን አፍሪካ በሰበር ዜናው ዘግቧል።
@tikvahethiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ተማሪዎቹ ላይ ስለተፈጠረው ድንገተኛ ሁኔታ በባለሞያ ተረጋግጦ ይገለፃል " - ኮማንደር ሽፈራው ጉቱ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ በሚገኘው ሀና የመጀመሪያ ደረጃ የመንግስት ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች ባልታወቀ ምክንያት በድንገት መታመማቸውን ተሰምቷል። በርካታ ተማሪዎች በአምቡላንስ መወሰዳቸውን ለማወቅ ተችሏል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ…
" ተማሪዎች የምግብ መመረዝ አጋጠማቸው ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው " - የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች የምግብ መመረዝ አጋጥሟቸዋል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብሏል።
ክስተቱ ''ከተማሪዎቹ መካከል ሁለት ተማሪዎች አጥወለወለን ብለው ከወደቁ በኃላ ሌሎችም ተማሪዎች ልጆቹን በማየታቸው የህመም ስሜት ተሰምቷቸዋል" ሲል ከተማ አስተዳደሩ ሁኔታውን አስረድቷል።
የወደቁትንና ሌሎች ተማሪዎችን ጨምሮ ወደ ህክምና በመውሰድ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ተማሪዎቹ የምግብ መመረዝም ሆነ ሌላ ምንም አይነት ህመም ስላልተገኘባቸው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል ሲል ከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።
ከምግብ መመረዝ ጋር የተያያዘ ምንም አይነት ችግር የሌለ በመሆኑ የተማሪ ወላጆች እንዲረጋጉ እና በሀሰተኛ መረጃዎች እንዳይታለሉ ከተማ አስተዳደሩ መልዕክት አስተላልፏል።

" ተማሪዎች የምግብ መመረዝ አጋጠማቸው ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው " - የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች የምግብ መመረዝ አጋጥሟቸዋል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብሏል። ክስተቱ ''ከተማሪዎቹ መካከል ሁለት ተማሪዎች አጥወለወለን ብለው ከወደቁ በኃላ ሌሎችም ተማሪዎች…
#ተጨማሪ
" ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል " ለህክምና 98 ተማሪዎች የመጡ ሲሆን ምርመራ ከተደረገላቸዉ ሴት 47 እና 51 ወንድ በአጠቃላይ 98 ተማሪዎች የመደንገጥና ከመጠነኛ ማስታወክ ስሜት ዉጭ የከፋ ኬዝ አለመኖሩን ነገር ግን ሁለት ተማሪዎች ብቻ መጠነኛ ህመም እንዳጋጠማቸው ሆስፒታሉ አሳውቋል።
ሆስፒታሉ ይህን ያሳወቀው ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ነው።
የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዶክተር ሳምሶን ጉታ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል የዛሬው ክስተት ለከፋ ጉዳት የሚዳርግ አለመሆኑን እና የሞተ ተማሪ አለመኖሩን ገልፀዋል።
ዶ/ር ሳምሶን ወደ ሆስፒታሉ የገቡ ተማሪዎች ምርመራ እየተደረገላቸዉ መሆኑን ሁሉም ተማሪዎች ጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
በምግቡ ላይ የተከሰተዉን ሁኔታ በባለሙያ ጥናት ተደርጎ ይረጋገጣል ፤ ለህብረተሰቡም ይፋ ይደረጋል ያሉ ሲሆን ወላጆች እንዲረጋጉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
በሌላ በኩል ፦
ዶ/ር ሙልጌታ እንዳለ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ፤ 714 ተማሪዎች ወደ ህክምና ማዕከላት ሄደው በተደረገላቸው ምርመራ 7 ተማሪዎች ላይ ከታየ የማስመለስ ምልክት በስተቀር በሌሎቹ ላይ ምንም አይነት ከምግብ መመረዝ ጋር የተገናኘ ችግር አላጋጠመም ብለዋል።
የሰባቱ ተማሪዎች የድምና ሰገራ ናሙና ተወስዶ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንና ውጤቱም እንደታወቀ ለህብረተሰቡ ይገለፃል ሲሉ አሳውቀዋል።

#EthiopianAirlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የወደብ-አየር የጭነት አገልግሎት ጀምሯል።
የጅቡቲ ዓለም አቀፍ ነጻ የንግድ ቀጠና አካል በሆነው የጅቡቲ ወደብ የሚተላለፍና የኤሌክትሮኒክስና የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎችን የያዘው 17 ቶን የሚመዝን የመጀመሪያ የወደብ-አየር ጭነት አገልግሎት ጥቅምት 18 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮጵያና ጅቡቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።
ጭነቱ ከሸንዘን ቻይና በመነሳት በጅቡቲ ወደብ አልፎ ሌጎስና ካኑ ይራገፋል ተብሎ ይጠበቃል።
የወደብ-አየር የጭነት አገልግሎቱን ስራ ያስጀመሩት የጅቡቲ ወደቦችና ነጻ የንግድ ቀጠና ሊቀመንበር፣ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ዲፕሎማት አቶ አቦበክር ኡመር፣ አቶ ቢኒያም ኤፍሬም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጅቡቲ ቅርንጫፍ ቢሮ ሀላፊ፣ እንዲሁም በአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ናቸው።
በአፍሪካ ግዙፍ የሆነው የጭነት አገልግሎት አቅራቢ የኢትዮጵያ አየር መንገድና ጅቡቲ በጋራ የሚተገብሩት ይህ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት ሲጀምር የአየር መንገዱን የጭነት አገልግሎት አቅም በሁለት እጥፍ የሚያሳድግ ሲሆን፣ ጅቡቲን የወደብ-አየር ጭነት አገልግሎት ሎጂስቲክስ ማእከል ያደርጋታል ተብሎ ይጠበቃል።
መረጃው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው።

#WHO : ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገብረእየሱስ ለዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዋና ዳሬክተርነት ብቸኛ እጩ ሆነው መቅረባቸውን የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ሲጂቲኤን አፍሪካ በሰበር ዜናው ዘግቧል። @tikvahethiopia
#Update
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊነት ዶ/ር ቴድሮስ ብቸኛ እጩ መሆናቸውን አረጋገጠ።
ከሰዓታት በፊት CGTN Africa ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ብቸኛ እጩ ሆነው መቅረባቸውን ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ መዘገቡ ይታወሳል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፥ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊው ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ለቀጣይ ዙር ብቸኛ ተወዳዳሪ መሆናቸውን አረጋግጧል።
ዶ/ር ቴድሮስ በማመልከቻ ጽሑፋቸው ላይ ኮቪድ-19 ወረርሺኝ ዓለምን ማንኮታኮቱን ገልፀው በሁለተኛ ዙር የሥልጣን ዘመናቸው ዓለማችንን ለመሰል ወረርሺኝ "የምር ዝግጁ" መሆኗን ማረጋገጥ ፍላጎታቸው መሆኑን ገልፀዋል።

ፎቶ : ዛሬ የአዲስ አበባ ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ የሰብአዊ አገልግሎት ተቋርጣል።
ንጋት 12:00 ሰዓት ጀምሮ ምንም ግልፅ ባልሆነ መልኩ አፍራሽ ግብረሀይል ግቢው ውስጥ በመገኘት በማፍረሳቸው ፣ መብራት እና ስልክ ተቋርጣል ፤ አሁን ላይም አገልግሎት በማይሰጥበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በጎ-ፈቃደኞች የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት እንዲያውቁት በሚል መልዕክት ልከዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቃላቸውን ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ የሰጡ ጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች የፈረሰዉ የሪል ስቴት ገንቢ ለሆነዉ አልሳም ግሩፕ ለማስተላለፍ መሆኑን መስማታቸዉን ገልፀዋል።
ቀይ መስቀል ቅጥር ግቢ ዉስጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መግባት የተከለከለ ሲሆን፣ ጽህፈት ቤቱን በሚፈርስበት ሰዓት ፖሊሶች በጉልበት መሳሪያ ይዘዉ ገብተዋል ሲሉም ለጋዜጣው አሳውቀዋል።
Photo Credit : Tikvah Family

ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 9 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,753 የላብራቶሪ ምርመራ 478 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 435 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily