TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 16 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,578 የላብራቶሪ ምርመራ 386 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 486 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
Facebook ➡️ Meta

ፌስቡክ ኩባንያ ስሙን ወደ ሜታ (Meta) እንደሚቀይር የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ማርክ ዙከርበርግ ዛሬ አሳውቀዋል።

በኩባንያው ስር የሚገኙት ፦
- ፌስቡክ፣
- ዋትስአፕ፣
- ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር የቀደመ ስማቸውን ይዘው ይቀጥላሉ።

ምንጭ፦ The Verge

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AGOA : ኢትዮጵያ በ "AGOA" በኩል ያላት ተጠቃሚነት ላይ አሜሪካ በቅርቡ ውሳኔ ላይ እንደምትደርስ ካትሪን ታይ (የንግድ ተወካይ) ተናግረዋል። ኃላፊዋ በይፋዊ መንገድ እና በግብረሰናይ ድርጅቶች በኩል የሚደርሱን መረጃዎች አበረታች አይደሉም፤ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ ነው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያ ቢልለኔ ስዩም፥ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ…
#AGOA : የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አማካሪና ዋና የንግድ ተደራዳሪ ማሞ ምህረቱ ኢትዮጵያ ከAGOA እንድትወጣ ከሚሰሩት መካከል የሕወሃት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች እንዲሁም አንዳንድ አሜሪካ መንግስት ውስጥ ያሉ ሰዎችም እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

አቶ ማሞ ይህን ያሉት ከአል ዓይን አማርኛው ክፍል ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ነው።

ኢትዮጵያ ከAGOA እንድትወጣ የሚሰሩት እንነማን እንደሆኑ ? ከዜና ወኪሉ የተጠየቁት የጠ/ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ ፦ አንደኛ የሕወሃት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች እንደሆኑ አመልክተዋል።

እነዚህ ሰዎች የሚከራከሩ ሰዎችን በመቅጠር በአሜሪካ ውስጥ ያሉ የኮንግረንስ ሰዎችን እንዲያሳምኑ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ በይፋ የሚታወቅ ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ ሰዎች (አሜሪካ መንግስት ውስጥ ያሉ ሰዎችም) እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት ትግራይን አስመከልክቶ ባለው ግጭት ውስጥ የተለያዩ የፖለቲካ ሃሳቦችን፤ የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎቶች እንዲሟሉ በማድረግ AGOAን እንደ አንድ የውጭ ፖሊሲ መሳሪያ አድርጎ የማስቀረት ጉዳይ አለ ሲሉ አቶ ማሞ ተናግረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ ፥ " በእኛ እምነት የፖለቲካ ሂደቱን በተመለከተ AGOA ትክክለኛው መሳሪያ ነው ብለን አናምንም፤ ምክንያቱም AGOA ከተነሳ የሚጎዱት በዋነኛነት በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚሰሩ ሰራተኞች ናቸው በተለይ ሴቶች ናቸው የሚጎዱት " ብለዋል።

አክለውም ፥ "አንድ ሀገር የፖለቲካ መሳሪያውን ለማሳካት ሲባል ከጦርነቱ /ከግጭቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ሰዎች መጉዳት ትክክለኛ ነው ብለን አናምንም፡፡ ይህ እንዳይሆንም የበኩላችንን ጥረት እያደረግን ነው" ሲሉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ “አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Home Grown Economic Reform) ምሰሶዎች የሆኑትን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ሥራ ዕድል ፈጠራ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ። 

በአዲስ አበባ ለ2 ቀናት በተካሄደው 18ኛው የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን መርሃግብር ላይ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከፍተኛ አመራሮች በዋና ሥራ አስፈጻሚው ሚስተር አንዋር ሱሳ መሪነት በመገኘት የኢትዮጵያን አገራዊ የዲጂታል እድገት ለውጥ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በንግግራቸው “ወደገበያ ለመግባት እየተዘጋጀንበት ባለበት በዚህ ወሳኝ ምዕራፍ የኢትዮጵያ መንግስት ላደረገልን አበረታች ድጋፍ ላመሰግን እወዳለሁ። በኢትይጵያ ድንቅ አቅም እንዳለ ተመልክተናል። ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን ማመቻቸት፣ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ የዲጂታል ክህሎት ስልጠናዎችን መስጠት እንዲሁም የኢትዮጵያን የዲጂታል 2025 ዕቅድ ከግብ ለማድረስ የሚያስችል ስነምህዳር መገንባትን እንቀጥላለን” ብለዋል። 

ያንብቡ : https://telegra.ph/Safaricom-Ethiopia-10-28
#Dessise : ከደሴ ከተማ ውጭ ካለ ስፍራ ወደ ደሴ ከተማ በተተኮሱ የመድፍ አረሮች ምክንያት 1 ሰው ሲገደል 3 ሰዎች መቁሰላቸውን የደሴ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል አስታውቁ።

አቶ አበበ ገብረ ይህን ያሳወቁት ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ነው።

ከንቲባው ጥቃቱ ትናንት ሐሙስ ጥቅምት 18/2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በግምት 9:30 የተፈፀመ መሆኑን ገልፀው ፥ "የህወሓት ኃይሎች ሰላማዊ ሰዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ላይ በመድፍ በፈጸሙት ጥቃት የሞትና የመቁሰል አደጋ ደርሷል" ብለዋል።

አቶ አበበ ህወሓት ትላንት 5 የመድፍ አረሮችን በከተማዋ ላይ መተኮሱን ፤ ሁለቱ መናፈሻ በሚባለው የከተማዋ አካባቢ፣ ሁለቱ ዳውዶ በሚባለው ስፋራ እንዲሁም ቀሪው አንድ ደግሞ እርሻ ሰብል ከሚባለው ቦታ ላይ መውደቁን ጠቁመዋል።

በሰዎች ላይ ሞትና የመቁሰል ጉዳት የደረሰው እርሻ ሰብል እና መናፈሻ በተባሉት ሁለት ስፍራዎች ላይ ሲሆን "በአንደኛው ቦታ 3 ንፁሃን ዜጎች ላይ ጉዳት ሲደርስ ከእነዚህ መካከል አንዱ ወዲያውኑ ህይወቱ ማለፉን" ከንቲባው ገልጸዋል።

የመድፍ ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው ቦታዎች መካከል አንዱ በጦርነቱ ምክንያት ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ ሰዎች የተጠለሉበትና እርዳታ የሚያገኙበት ስፍራ ይገኛል።

ባለፉት ጥቂት ቀናት በደሴ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ ስፍራዎች ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን እየተካሄደ ስላለው ውጊያ የተረጋገጠ መረጃ ማግኘት አዳጋች ሆኗል።

የደሴ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረ መስቀል በተለያዩ የወሎ ግንባሮች ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጠው፤ የከተማው ነዋሪ ግን መደበኛ ሕይወት መቀጠሉን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሱዳን ወታደራዊ ጁንታ በዚህ ሳምንት ያደረገውን የመንግስት ግልበጣ በመቃወም የተናገሩ ቢያንስ 6 አምባሳደሮችን ከሥራና ኃላፊነታቸው ማበረሩን የመንግስት ቴሊቪዥን ዛሬ ማሳወቁን የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል። ቴሌቪዥን ጣቢያው ጀኔራል አብዱፈልታ አል ቡርሃን በአሜሪካ ፣ አውሮፓ ህብረት፣ ቻይና ፣ ኳታር እና ፈረንሳይ እንዲሁም በጀኔቭ የተባበሩት መንግሥታት የሱዳን ተወካይ መልክተኛን ማባረራቸውን ገልጿል፡፡…
#SUDAN : የሱዳን ወታደራዊ ጁንታ በአስቸኳይ የሲቪል መሩን መንግስት ወደ ቦታው እንዲመልስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፀጥታው ምክር ቤት አስጠንቅቋል።

የፀጥታው ምክር ቤት ትላንት ባወጣው መግለጫ የሱዳን መፈንቅለ-መንግሥት " እጅግ የሚያሳስብ " ነው ብሎታል።

መፈንቅለ-መንግሥት የፈጸመው ወታደራዊ ጁንታ የታሰሩትን ባለሥልጣናት በአጠቃላይ ያለ አንዳች ቅድመ-ሁኔታ በፍጥነት እንዲፈታ አስጠንቅቋል።

በጠ/ሚ አብዱላህ ሀምዶክ የሚመራው የሲቪል አስተዳደር ስልጣኑን መልሶ እንዲይዝ ከተመድ በተጨማሪ የአውሮጳ ህብረት እና አሜሪካ አሳስበዋል።

@tikvahethiopua
#DAWA : በሶማሊ ክልል ዳዋ ዞን (የቦረና አጎራባች) በተከሰተ ድርቅ 25,000 ገደማ የቁም እንስሳት ማሞታቸውን የሶማሊ ክልል አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሳዲቅ አብዱቃድር ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ በድርቁ የተነሳ ግመሎች እና የቀንድ ከብቶች መሞታቸውን ተናግረዋል።

አስቸኳይ ድጋፍ ካልተገኘ አሁን ከሞቱት በላይ እንስሳት ሊሞቱ ይችላሉ ብለዋል።

እስካሁን ፦

- 1,360 ግመሎች ሞተዋል።
- 21,148 ፍየሎች ሞተዋል።
- 1098 ከብቶች ሞተዋል።

አሁንም ከዚህ በላይ ቁጥር ያላቸው የሞት አደጋ ውስጥ ናቸው።

አሁን ላይ ድጋፍ እንዲደረግ የተለያየ እንቅስቃሴ መኖሩን ያሳወቁት አቶ ሳዲቅ በወረዳ ደረጃ ውሃ እንዲዳረስ ለማድረግ እና የእስሳት መኖ ከሸበሌ እና ከጅግጅጋ እንዲመጣ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ከ83 ሺህ በላይ ነዋሪዎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አቶ ሳዲቅ አሳውቀዋል።

ድጋፍ ፈላጊዎቹ ከተለያየ ቦታ ተፈናቅለው ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች (በቁጥር ከ33 ሺ በላይ) እንዲሁም የዛው የዳዋ ዞን ነዋሪዎች (በቁጥር ከ50 ሺ በላይ) መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የምግብ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እስካሁን ድጋፍ መቅረብ እንዳልጀመረ ገልፀው ከፌዴራል መንግስት ድጋፍ እንዲደረግ ጥያቄ መቅረቡን ተናግረዋል፤ ክልሉ ከሰብዓዊ ድርጅቶችም ጋር በመነጋገር ድጋፍ እንዲደረግ ለማስደረግ እየሰራ መሆኑንም ለሬድዮ ጣቢያው ጠቁመዋል።

@tikvhahethiopia
#Bahirdar : የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ በባህር ዳር ከተማ በወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ እየመከረ ይገኛል።

መድረኩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የሚመራ ሲሆን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የሁሉም ክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል የበላይ አመራሮች ተገኝተዋል።

የግንኙነት መድረኩ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ በዝርዝር ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል።

የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኘነት መድረክ የኢፌዴሪ የመንግሥታት ግንኙነት ስርአትን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1231/2013 መሰረት የተቋቋመ ነው።

መረጃው የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
" ... ተማሪዎቹ ላይ ስለተፈጠረው ድንገተኛ ሁኔታ በባለሞያ ተረጋግጦ ይገለፃል " - ኮማንደር ሽፈራው ጉቱ

በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ በሚገኘው ሀና የመጀመሪያ ደረጃ የመንግስት ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች ባልታወቀ ምክንያት በድንገት መታመማቸውን ተሰምቷል።

በርካታ ተማሪዎች በአምቡላንስ መወሰዳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ሽፈራው ጉቱ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በሰጡት ቃል በትምህርት ቤቱ ዛሬ ማለዳ 3:30 አካባቢ ተፈጥሯል ስላሉት ሁኔታ አስረድተዋል።

ተማሪዎች ቁርሣቸውን በልተው ወደመማሪያ ክፍል ከገቡ በኃላ በመጀመሪያ ሁለት ከዛም በተከታታይ በርካታ ተማሪዎች በድንገት መውደቃቸውን ኮማንደር ሽፈራው አሳውቀዋል።

ብዛታቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎች በአምቡላንስ ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱ መደረጉን ገልፀዋል።

ተማሪዎቹ ላይ ስለተፈጠረው ሁኔታ በባለሞያ ተረጋግጦ እንደሚገለፅ ኮማንደር ሽፈራው ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

የክፍለ ከተማው የጤና ፅ/ቤት ለሬድዮ ጣቢያው በሰጠው ቃል የተማሪዎቹ የህመም መነሻ እስካሁን አልታወቀም ብሏል።

Credit : ሸገር ኤፍ ኤም 102.1
Photo : Ermo Hailu

@tikvahethiopia
#የምርመራ_ሪፖርት

ፍትህ ሚኒስቴር በአማራ ክልል በሰሜን እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እንዲሁም በአፋር ክልል በሚገኙ ወረዳዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ወንጀል ምርመራንና የመጀመሪያ ደረጃ ግኝቶችን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

ምርመራው የተካሄደው በህወሃት ተይዘው በነበሩና በኃላም ነጻ በወጡ አካባቢዎች ነው።

በዚህ መሰረት ህወሓት በሰሜን ጎንደር ዞን ለጊዜው በዝርዝር ማስረጃ የተለዩ፦
- የ96 ሰዎች ሞት
- 53 የአካል ጉዳት
- 29 አስገድዶ መደፈር
- 11 ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ
- 6 እገታ እንዲሁም የመንግስት፣ የግልና የሀይማኖት የተለያዩ ተቋማት ንብረቶች ላይ መጠነ ሰፊ ዘረፋና ውደመት ፈፅሟል ሲል ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን ባሉ አምስት ወረዳዎች በድምሩ፦
- የ129 ሰዎች ሞት
- የ54 ሰዎች የአካል ጉዳት
- በንፋስ መውጫ ከተማ ብቻ የ73 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንዲሁም በርካታ ግለሰቦች ንብረት ላይ ውድመት መድረሱ ተገልጿል።

በአፋር ክልል ነሃሴ 29/2013 ዓ.ም በጋሊኮማ ቀበሌ መጠለያ ጣቢያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት፦
- የ240 ሰዎች ሞት
- 42 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በቀሪዎቹ ሶስት ወረዳዎች ደግሞ የ17 ሰዎች ሞት እና ለ17 ሰዎች የአካል ጉዳት እንዲሁም 7 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ተፈፅሟል።

በሁለቱም ክልሎች በሰላማዊ ዜጎች ንብረት ላይ በመንግስት እና በግል ተቋማት ላይ ዘረፋና ውድመት በስፋት መድረሱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በአጠቃላይ ምርመራው በሂደት ላይ ያለ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

እስከ አሁን በተደረሰበት ግን ሁለቱም ክልሎች በተፈጸሙት የወንጀል ድርጊቶች 482 ሞት፣ 165 የአካል ጉዳት እና 109 የአስገድዶ መድፈር ኢሰብዓዊ ድርጊቶች መፈጸማቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል። #አልዓይን

@tikvahethiopia
#AddisAbaba : የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ ክልከላ ወደ ነበረበት መመለሱ ተገለፀ፡፡

በመዲናዋ የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለሱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት በከተማው ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ አየተስተዋለ በመሆኑ የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለስ እንዳስፈለገ ተገልጿል።

በመሆኑም ከጥቅምት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በመመሪያው መሰረት ማንኛውም የጭነት፣ የማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካራች ከማለዳ 12፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት እንዲሁም ከቀኑ 10፡00 እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዲሁም ጭነት መጫንና ማራገፍ እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ተማሪዎቹ ላይ ስለተፈጠረው ድንገተኛ ሁኔታ በባለሞያ ተረጋግጦ ይገለፃል " - ኮማንደር ሽፈራው ጉቱ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ በሚገኘው ሀና የመጀመሪያ ደረጃ የመንግስት ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች ባልታወቀ ምክንያት በድንገት መታመማቸውን ተሰምቷል። በርካታ ተማሪዎች በአምቡላንስ መወሰዳቸውን ለማወቅ ተችሏል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ…
" ተማሪዎች የምግብ መመረዝ አጋጠማቸው ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው " - የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች የምግብ መመረዝ አጋጥሟቸዋል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብሏል።

ክስተቱ ''ከተማሪዎቹ መካከል ሁለት ተማሪዎች አጥወለወለን ብለው ከወደቁ በኃላ ሌሎችም ተማሪዎች ልጆቹን በማየታቸው የህመም ስሜት ተሰምቷቸዋል" ሲል ከተማ አስተዳደሩ ሁኔታውን አስረድቷል።

የወደቁትንና ሌሎች ተማሪዎችን ጨምሮ ወደ ህክምና በመውሰድ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ተማሪዎቹ የምግብ መመረዝም ሆነ ሌላ ምንም አይነት ህመም ስላልተገኘባቸው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል ሲል ከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።

ከምግብ መመረዝ ጋር የተያያዘ ምንም አይነት ችግር የሌለ በመሆኑ የተማሪ ወላጆች እንዲረጋጉ እና በሀሰተኛ መረጃዎች እንዳይታለሉ ከተማ አስተዳደሩ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተማሪዎች የምግብ መመረዝ አጋጠማቸው ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው " - የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች የምግብ መመረዝ አጋጥሟቸዋል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብሏል። ክስተቱ ''ከተማሪዎቹ መካከል ሁለት ተማሪዎች አጥወለወለን ብለው ከወደቁ በኃላ ሌሎችም ተማሪዎች…
#ተጨማሪ

" ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል " ለህክምና 98 ተማሪዎች የመጡ ሲሆን ምርመራ ከተደረገላቸዉ ሴት 47 እና 51 ወንድ በአጠቃላይ 98 ተማሪዎች የመደንገጥና ከመጠነኛ ማስታወክ ስሜት ዉጭ የከፋ ኬዝ አለመኖሩን ነገር ግን ሁለት ተማሪዎች ብቻ መጠነኛ ህመም እንዳጋጠማቸው ሆስፒታሉ አሳውቋል።

ሆስፒታሉ ይህን ያሳወቀው ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ነው።

የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዶክተር ሳምሶን ጉታ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል የዛሬው ክስተት ለከፋ ጉዳት የሚዳርግ አለመሆኑን እና የሞተ ተማሪ አለመኖሩን ገልፀዋል።

ዶ/ር ሳምሶን ወደ ሆስፒታሉ የገቡ ተማሪዎች ምርመራ እየተደረገላቸዉ መሆኑን ሁሉም ተማሪዎች ጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

በምግቡ ላይ የተከሰተዉን ሁኔታ በባለሙያ ጥናት ተደርጎ ይረጋገጣል ፤ ለህብረተሰቡም ይፋ ይደረጋል ያሉ ሲሆን ወላጆች እንዲረጋጉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

በሌላ በኩል ፦

ዶ/ር ሙልጌታ እንዳለ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ፤ 714 ተማሪዎች ወደ ህክምና ማዕከላት ሄደው በተደረገላቸው ምርመራ 7 ተማሪዎች ላይ ከታየ የማስመለስ ምልክት በስተቀር በሌሎቹ ላይ ምንም አይነት ከምግብ መመረዝ ጋር የተገናኘ ችግር አላጋጠመም ብለዋል።

የሰባቱ ተማሪዎች የድምና ሰገራ ናሙና ተወስዶ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንና ውጤቱም እንደታወቀ ለህብረተሰቡ ይገለፃል ሲሉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia