TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ባድመ እና የአሜሪካ አቋም ?

በኤርትራ፣ አስመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፁ ባድመን በሚመለከት አንድ አጭር ፅሁፍ አሰራጭቷል።

" ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ብዙዎቻችሁ በባድመ ላይ የአሜሪካ ፖሊሲ ምን እንደሆነ ጠይቃችሁ ነበር " ያለው ኤምባሲው በባድመ ጉዳይ የአሜሪካንን አቋም አሳውቋል።

እኤአ በ2002 የኤርትራ - ኢትዮጵያ የድንበር ኮሚሽን ባድመ እና ተጓዳኝ አወዛጋቢ አካባቢዎችን ለኤርትራ ሰጥቷል የሚለው የአሜሪካ ኤምባሲ ፥ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ እኤአ በ2018 የሰላም ስምምነት ወቅት የኤርትራ እና ኢትዮጵያ የድንበር ኮሚሽን ውሳኔንን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸው ገልፀዋል ብሏል።

አሜሪካ ፥ ሁለቱ ሀገራት ይህን ለማድረግ ሁሉንም አስፈላጊ ቀሪ እርምጃዎች እንዲወስዱ ታሳስባለች ብሏል በአስመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር (ኢመማ) ለሁለት ኢትዮጵያውያን እውቅና ሰጠ። የኢትዮጵያ መምህርን ማህበር በ22ኛ ጠቅላላ ግባኤው ላይ ለቀድሞው ጠ/ሚ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ እና ለጋዜጠኛና መምህር ዮናስ ከበደ እውቅና ሰጥቷል ፤ ጋዜጠኛ እና መምህር ዮናስን የክብር አባሳደርም ሆነዋል። እውቅናው የተሰጣቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስተር አቶ ሀይለማሪያም ደስላኝ በሀገር አቀፍ ደረጃ መምህራን…
#Update

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ለቀጣይ አራት ዓመት ፕሬዘዳንት አድርጎ ዶክተር ዮሐንስ ባንቲን መረጠ።

ዶ/ር ዮሐንስ ባንቲ ማህበሩን ላለፉት አምስት ዓመት መርተዋል።

በዛሬው እለት በኦሮሚያ ክልል መምህራን ማህበር አቀርቢነት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ የማህበሩ ፕሬዘዳንት አድርጎ ለዶ/ር ዮሐንስ ባንቲ ሹመት ሰጥቷል።

ማህበሩ 22ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ፕሬዘዳንቱን እና የስራ አስፈፃሚወችን በመምረጥና ለሀገር ሰላም ሁሉም አካላት እንዲሰሩ በማሳሰብ የአቋም መግለጫ በማወጣት 22ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አጠናቋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን /ጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SUDAN : የሱዳን መዲና ካርቱም ትላንት ለሊቱን በአብዛኛው ፀጥ ብላ አሳልፋለች። የሱዳን ጦር መፈንቅለ መንግስት ማድረግን ተከትሎ የተቋረጠው የኢንተርኔት ፣ የስልክ ግንኙነት አሁንም አልተመለሰም። የሱዳን ጦር ያደረገውን መፈንቅለ መንግስት ለመቃወም አደባባይ በወጡ እና በጦሩ መካከል በተፈጠረ ግጭት 7 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ140 በላይ መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በካርቱም…
#SUDAN : " ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ እኔ ቤት ነው ያለው " - ሌ/ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን

የሱዳን ጦር አዛዥ ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን በመግለጫቸው በሱዳን ጦር በቁጥጥር ስር የዋሉት ጠቅላይ ሚኒስትር በአብደላ ሀምዶክ ያሉበትን አስታውቀዋል።

አልቡርሃን ፥ “ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እኔ ቤት ነው ያለው” ያሉ ሲሆን “ይህ የሆነው ለደህንነታቸው ሲባል ነው” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን ወደ ቤታቸው የወሰዷቸው የደህንነት ስጋት ስለነበረ እንደሆነ ያስታወቁት አልቡርሃን፤ “በየቀኑ እተገናኝ እየነጋገርን ነው” ሲሉ አስታውቀዋል።

"ለጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ክብር አለን" ያሉት አልቡርሃን፤ ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ የፖለቲካ ገደብ ስለተጣለባቸው ስራቸውን በነጻነት መስራት እንደማይችሉ አስታውቀዋል።

አልቡርሀን በመግለጫቸው በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎች በእስር ቤት እንደሚቆዩ ገልጸው፤ ሌሎቹ ግን ከእስር እንደሚለቀቁ አስታውቀዋል።

በትናትናው እለት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነገሮች ሲረጋጉ ይነሳል ሲሉም አስታውቀዋል።

Credit : አል ዐይን ኒውስ

@tikvahethiopia
#AddisAbaba : ዛሬ አዲስ አበባ " ቄራ በረት " አካባቢ ከቀኑ 8:00 ገደማ አካባቢ በተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የን/ስ/ላ/ክ/ከ አሳውቋል።

የን/ስ/ላ/ክ/ከ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ነፃነት ዳባ በስፍራው ተገኝተው በአደጋው የደረሰውን ጉዳት ተመልክተዋል።

የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ይፋ ባደረገው መረጃ የአደጋው መንስኤ አልተገለፀም።

በእሳት አደጋው የወደመው አጠቃላይ ንብረት መጠን አልታወቀም።

Video Credit : Elias Workneh (Tikvah-Family)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶ/ር ዐቢይ ጠ/ሚ ሆነው ተሾሙ። ዶክተር ዐቢይ አህመድ አሊ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። @tikvahethiopia
#RecepTayyipErdoğan

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ የደስታ መግለጫ ላኩ።

ዶክተር ዐቢይ አህመድ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ/ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሀገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመሩ መሾማቸው ይታወሳል።

ሹመቱን ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች የ "እንኳን ደስ አልዎት!" መግለጫ ሲልኩ እንደነበር አይዘነጋም።

ዛሬ ጥቅምት 16/2014 ዓ/ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ ፤ የቱርኩ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዴጋን ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ሆነው በመሾማቸው የደስታ መግለጫ ልከዋል።

ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን በቀጣይ ከጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና የህዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

ከዚህ በፊት ቱርክ 🇹🇷 እና ኢትዮጵያ 🇪🇹 መካከላቸው ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚያችሉ ስምምነቶችን መፈራረማቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#INVEA : በህገ-ወጥ መንገድ ፓስፖርት ሲያዘጋጁ የተገኙ 10 የኢሚግሬሽን ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በፌዴራል ፖሊስ የሙስና ወንጀሎች ዳይሬክተር ኮማንደር ታደሰ አያሌው ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፥ ተጠርጣሪዎቹ ህጋዊውን የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደት ወደ ጎን በመተው፣ የፓስፖርት ባለቤቶችን ሙሉ መረጃ በመቀየር እና በአንድ ማእከል መጠናቀቅ የነበረበትን አገልግሎት ወደ ተለያዩ ቅርንጫፎች በማዘዋወር ወንጀሉን በኔትወርክ መፈፀማቸውን ገልፀዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ከደላሎች ጋር በፈጠሩት የጥቅም ትስስር በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦች እና የውጭ ሀገር ዜጎችም ጭምር ፓስፖርት እንዲያገኙ ማመቻቸታቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም መንግስት ሊያገኝ ይችል የነበረውን ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እንዳሳጡ ነው ኮማንደር ታደሰ አያሌው ለቴሌቪዥን ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SUDAN : " ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ እኔ ቤት ነው ያለው " - ሌ/ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን የሱዳን ጦር አዛዥ ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን በመግለጫቸው በሱዳን ጦር በቁጥጥር ስር የዋሉት ጠቅላይ ሚኒስትር በአብደላ ሀምዶክ ያሉበትን አስታውቀዋል። አልቡርሃን ፥ “ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እኔ ቤት ነው…
#SUDAN : መፈንቅለ መንግስት የተካሄደባቸ እና ወዳልታወቀ ቦታ ተውስደዋል የተባሉት አብደላ ሃምዶክ ከነበሩበት ስፍራ ትላንት ምሽት ወደቤታቸው ገብተዋል።

ትላንት የሱዳን ጦር አዛዥ አብዱን ፈታህ አልቡርሃን " ጠ/ሚ አብደላ ሃምዶክ ለደህንነታቸው ሲባል እኔ ቤት ነው ያሉት" ብለው ነበር።

ሀምዶክ ትናንት ምሽት ከታሰሩበት ስፍራ ወደመኖሪያ ቤታቸው እንደተመለሱ የተዘገበ ሲሆን ወደቤታቸው ከተመለሱ በኃላ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር በስልክ አውርተዋል፡፡

ብሊንከን በትዊተር ባሰራጩህ ፅሁፍ በሀምዶክ መፈታት መደሰታቸውን ገልጸው አሁንም በእስር ላይ ያሉ ሌሎች የሲቪል አስተዳደር አመራሮች እንዲፈቱ አሳስበዋል፡፡

#አልዓይን

@tikvahethiopi
TIKVAH-ETHIOPIA
ፒተር ማውረር ኢትዮጵያ ገብተዋል። የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ፕሬዝዳንት ፒተር ማውረር በኢትዮጵያ ያለውን ሰብአዊነት ሁኔታ ለመገምገም ዛሬ አዲስ አበባ መግባታቸው ታውቋል። ማውረር በኢትዮጵያ 3 ቀናት የሚቆዩ ሲሆን ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር በአሁናዊ ሁኔታ ዙሪያ ይወያያሉ። በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ተወካዮች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ…
#Update

አቶ ደመቀ መኮንን ከፒተር ማውረር ጋር ተወያዩ።

ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ፕሬዚዳንት ፒተር ሞረርን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ድርጅታቸው በኢትዮጵያ ባለው የረጅም ጊዜ አገልግሎት በመንግስት በኩል እየተደረገለት ስላላው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ፕሬዚደንቱ ICRC በገለልተኝነት መርህ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑን አስታውሰው ፤ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በትግራይ ክልል እያደረገ ካለው እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ፦
- የአየር በረራ ፈቃድ፣
- የጥሬ ገንዘብ መጠን መጨመር
- የነዳጅ ፍላጎትን በተመለከተ መንግሰት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ICRC በአገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ሳይገባ ፤ በሰብዓዊነት መርህ ተልዕኮውን ለመወጣት እየሰጠ ስላለው አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ድርጅቱ በትግራይ ክልል እያደረገ ካለው የሰብዓዊ ድጋፍ ጋር ተያይዞ በትክክለኛ ፍላጎት ላይ በመመስረት የነዳጅ ሆነ የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት እንዲሟላ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሄ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል፡፡

አቶ ደመቀ ፤ " ህወሓት በከፈተው ወረራ ምክንያት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሰብዓዊ ዕርዳታ ለሚፈልጉ ዜጎችን ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ ነውም" ሲሉ አስረድተዋል።

በተጨማሪ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ ያሉትን የጦር እስረኞች በተመለከተ " ታሳሪዎቹ ዜጎቻችን ከመሆናቸውም ባሻገር የዓለም አቀፍ ህግን ታሳቢ በማድረግ ተገቢው አያያዝ ይደረግላቸዋል " ብለዋል።

መረጃውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
#Afar : የአፋር ክልል የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ቢሮ ለ ቢቢሲ በሰጠው ቃል በክልሉ በተለይም ከጭፍራ እና ከመጋሌ ወረዳዎች ባለፉት ጥቂት ቀናት ነዋሪዎች እየተፈናቀሉ ይገኛሉ።

ከጭፍራ ወረዳ ከ35 ሺህ በላይ ሰው ተፈናቅሏል ፤ ከመጋሌ ወረዳ ደግሞ ወደ 10 ሺህ ሕዝብ ተፈናቅሏል፤ ከዚህ ወረዳ የሁለት ቀበሌ ሕዝብ ነው የተፈናቀለው።

ከዚህ በፊት ከነበረው 150 ሺህ ተፈናቃይ ጋር ሲደመር አሁን ያለው የተፈናቃዮች ቁጥር ከ200 ሺህ በላይ ደርሷል።

ጭፍራ ወረዳ ከአማራ ክልል ጋር የሚዋሰን ሲሆን፤ መጋሌ ወረዳ ከትግራይ ክልል ጋር ይዋሰናል።

ተፈናቃዮችን ለመደገፍ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ቢሮው ገልጿል፤ ግጭት በቀጠለባቸው አካባቢዎች ሰዎች አሁንም እየተፈናቀሉ ይገኛሉ።

ቢሮው ፥ በርካታ ሰዎች በየጫካው፣ በየጥሻው ተበትነው እንደሚገኙ አሁን የጠፉ እና ከቤተሰብ የተለያዩ ሰዎችን አግኝቶ አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ ለመስጠት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክቷል።

የአፋር ክልል ማስ ሚዲያ ትላንት ባወጣው ዘገባ ህወሓት በከፈተው ጦርነት እና ወረራ ሳቢያ በተለይም ከጭፍራ ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎች ለአደጋ በመጋለጣቸው መንግስት ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ተፈናቃዮች ውሃ፣ መጠለያ፣ ምግብና የህክምና ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።

የክልሉ አደጋ መከላከል እና መቆጣጠር ተፈናቃዮች የሚያነሱት ችግር መኖሩን በመቀበል ችግሩን ለመፍታት ርብርብ እንደሚደረግ ፤ በቀጣይ ቀናቶችም ችግሩ ይቃለላል ብሎ እንደሚያስብ አሳውቋል።

የተፈናቃዮች ቁጥር መብዛት ለፈጣን ድጋፍ ፈተና ሆኗል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba : የፍትህ ሚኒስቴር የህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ብሎ ለፈረጀው ትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ድጋፍ ያደርጋሉ፤ ግንኙነትም አላቸው ተብለው የታሸጉ ፋብሪካዎች ፣ የተለያዩ ድርጅቶች አስተዳዳሪ ተሹሞላቸው በቅርቡ ስራ ይጀምራሉ ሲል አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ለሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

ከጥቂት ወራት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ የንግድ ድርጅቶች እና ሆቴሎች የንግድ ህጉን በመጣስ እና ለTPLF የሽብር ተግባር ድጋፍ ያደርጋሉ በሚል ጥርጣሬ ታሽገው ነበር።

ከተዘጉት የንግድ ድርጅቶች መካከል በርካቶቹ ተመልሰው እንደተከፈቱ ነገር ግን ቁጥራቸው በግልፅ የማይታወቅ ትልልቅ ሆቴሎች ጭምር አሁንም ድረስ ዝግ እንደሆኑ ናቸው።

ከሆቴሎቹ መካከል ፦
- ካሌብ ሆቴል
- ኔክሰስ ሆቴል
- አክሱም ሆቴል
- ንግስተ ሳባ ሆቴል
- ሀርመኒ ሆቴል እና ሌሎችም ይገኙበታል።

ቃላቸውን ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጡት የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ፀጋ ፥ " በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን የንግስ ድርጅቶች እና ሆቴሎች አስተዳዳሪ ተሹሞላቸው ስራቸውን እንደገና እንዲቀጥሉ ለማድረግ እየተሰራ ነው" ብለዋል። ነገር ግን በድርጅቶቹ ላይ የሚደረገር ምርመራ እንደሚቀጥል ለጋዜጣው አሳውቀዋል።

ፍትህ ሚኒስቴር በወንጀል የተጠረጠሩትን ተቋማትና ግለሰቦች ወደፍርድ እንደሚያቀርብ የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው የከተማ አሰተዳደሩ ድርጅቶቹን ለመክፈት ወይም ላለመክፈት አስተዳደራዊና የወንጀል ህጉን መሰረት በማድረግ ውሳኔ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

አቶ ፍቃዱ ፥ በሆቴሎችም ሆነ በንግድ ድርጅቶች ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ሰራተኞች ስራ አጥ መሆን የለባቸውም ያሉ ሲሆን ድርጅቶቹ በተቻለ መጠን ወደ ስራ እንዲመለሱ ለማድረግ እተሰራ ነው ብለዋል።

telegra.ph/ER-10-27

@tikvahethiopia
#HU : ከሰሜን ኢትዮጵያ የመጡ ተመራቂ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መቸገራቸውን ገልጸዋል።

በጦርነቱ ምክንያት ለማህበራዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር እንደተጋለጡ የሚናገሩት ተማሪዎቹ፤ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጠይቀዋል፡፡

ከአፋር ክልል የመጣው ተማሪ አሊ ሰይድ፤ ቤተሰቦቹ በሚኖሩበት አካባቢ በተቀሰቀሰ ጦርነት ምክንያት የባንክም ሆነ የኔትወርክ አገልግሎት በመቋረጡ የገንዘብ ችግር እንዳጋጠመው ተናግሯል።

ከወልዲያ አካባቢ የመጣው ተማሪ ያሬድ በሪሁን በጦርነቱ ምክንያት ቤተሰቦቹ ከቀያቸው ተፈናቅለው በወሎ ተፈናቃዮች ካምፕ እንደሚገኙ ተናግሯል።

ሌላኛው ተማሪ አንድሚሊዮን አምባው ከትግራይ ክልል የመጣ ሲሆን ቤተሰቦቹን ካገኘ ከስምንት ወር በላይ እንደሆነና ለጭንቀት በመጋለጡ በትምህርቱ ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረበት ተናግሯል።

በተለይም ከምርቃት በኋላ ያለው ጊዜ እንዳሰሰባቸው ተማሪዎቹ ይገልጻሉ፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዓለም ዐቀፍ እና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አለምሽት ተሾመ ተማሪዎቹ ያቀረቡትን የእርዳታ ጥያቄ ለመፍታት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመነጋገር የመመረቂያ ልብሶችን እና የገንዝብ ድጋፎችን በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በቀጣይ ጊዜ ስለሚኖሩ ጉዳዮች ዩኒቨርሲቲው ከትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ እየተጠባበቀ እንደሆነም ዳሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

መረጃው የሐዩ ኤፍኤም ነው።

@tikvahuniversity