TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሰላም_እና_እርቅ !

በጅሌ ጥሙጋ እና ሃደለኤላ ወረዳ (አፋር ክልል) የሰላም እና እርቅ ኮንፍረንስ በሃደሌኤላ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በኮንፈረንሱ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች፣እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎች ተሣታፊ ይሆናሉ።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ኮንፈረንስ በሁለቱ ወረዳዎች መካከል ያለውን የሰላም እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የበለጠ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ ውይይቶች ይደረጋሉ።

መረጃው የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሱዳን ሙሉ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እያጋጠማት ነው " - የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር የሱዳን ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ሱዳን ሙሉ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እያጋጠማት ነው ብሏል። ሚኒስቴሩ ሁሉም እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱም አሳስቧል። የሱዳን ህዝብ ወታደራዊው ኃይል የሀገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ለማገድ የሚያደርገውን ጥረት ለማስቆም መሞከር አለበት ሲል ለሮይተርስ በሰጠው መግለጫ አክሏል።…
#SUDAN : አሜሪካዊው ባለስልጣን ሱዳንን ለቀው መውጣታቸው ተነግሯል።

ላለፉት 2 ቀናት ካርቱም ውስጥ የነበሩት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ከሱዳን ወጥተው ወደ ሃገራቸው ሄደዋል።

ፌልትማን ካርቱም በነበሩባቸው ቀናት ከሱዳን የሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ጋር ሲመክሩ እንደነበር አል ዓይን ዘግቧል።

ዛሬ በሱዳን ሲቪል አስተዳድሩ ላይ መፈንቅለ መንግስት መካሄዱ ጠ/ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን ጨምሮ በርካታ የሲቪል አስተዳድሩ አመራሮች መታሰራቸው ይታወቃል።

አሜሪካ በሱዳን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ እንደሚያሳስባት ፤ የሱዳን ሽግግር መንግስትን በኃይል ለመቀየር መሞከርም አሜሪካ ለሱዳን የምታደርገውን ድጋፍ ሊያሳጣ እንደሚችል በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ማስታወቋ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 19 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,703 የላብራቶሪ ምርመራ 337 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 491 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#Facebook

CNN ለአሜሪካ ህግ መምሪያ ምክር ቤት የቀረበ አንድ ሚስጥራዊ የፌስቡክ ኩባንያ ሰነድ መመልከቱን አሳውቋል።

ይኸው ሚስጥራዊ ሰነድ ፌስቡክ በኢትዮጵያ ግጭትን እያባባሰ እንደሆነ እያወቀ አንደችም ርምጃ እንዳልወሰደ የሚገልፅ ነው።

የፌስቡክ ኩባንያ ኢትዮጵያን "ለግጭት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የሆኑ ሀገራት" በሚለው ምድብ ያስቀመጣት ሀገር ናት።

የኩባንያው ሰራተኞች ፌስቡክ በኢትዮጵያ ግጭትን ለማባባስ እየዋለ መሆኑን ላቀረቧቸው ጥቆማዎች ኩባንያው ምላሽ እንዳልሰጠ ከሚስጥራዊው ሰነድ መመልከቱን CNN ዘግቧል።

ይኸው ሚስጥራዊ ነው የተባለው የፌስቡክ ሰነድ የውጭ መንግስታት እንዲሁም ድርጅቶች በኢትዮጵያ #የጥላቻ_ንግግር እና ግጭትን ለመስበክና ለማሰራጨት ፌስቡክን እንደተጠቀሙበት ያሳያል ሲል CNN ባወጣው ዘገባ ጠቅሷል።

ሙሉ የCNN ሪፖርት በዚህ ተያያዟል : https://edition.cnn.com/2021/10/25/business/ethiopia-violence-facebook-papers-cmd-intl/index.html?utm_content=2021-10-25T11%3A51%3A04&utm_term=link&utm_medium=social&utm_source=twCNN

Credit : CNN/WAZEMA

@tikvahethiopia
" ... ከግድያው ጋር በተያያዘ 10 ተጠርጣሪዎች ታስረዋል ፤ የገዳዮቹም ማንነት በምርመራ ላይ ነው " - አቶ ምስጋኑ ዋቅጋሪ

የነቀምቴ ከተማ የስራ እድል ፈጠራ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ ፈይሳ ቅዳሜ ዕለት በመንግስት ስራ ላይ ቆይተው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ከጀርባቸው በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን የነቀምቴ ፀጥታ እና አስተዳደር ፅ/ቤት ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ አስታወቀ።

የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ምስጋኑ ዋቅጋሪ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤ " ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች አቶ መልካሙ ላይ ጥይት ካዘነቡ በኃላ 03 ቀበሌ ውስጥ ወልደአራራ ቤተክርስቲያን አካባቢ ደርሰን በፍጥነት ወደነቀምቴ ሆስፒታል ብንወስደውም ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም" ብለዋል።

ከግድያው ጋር በተያያዘ 10 ተጠርጣሪዎች መታሰራቸውን እና የገዳዮቹም ማንነት በምርመራ ላይ መሆኑን አቶ ምስጋኑ ለሬድዮ ጣቢያው ገልፀዋል።

አቶ ምስጋኑ ፤ " ነቀምቴ ከተማ ውስጥ መንግስትን የሚቃወም ኃይል ታጥቆ እና ሲቪል መስሎ አልፎ አልፎ በመንግስት አመራሮች ላይ ግድያ ሲፈፅም ቆይቷል፤ አቶ መልካሙንም የገደለው ይኸው ኃይል ነው ብለን እንጠረጥራለን ነገር ግን የሚረጋገጠው በፖሊስ ምርመራ ነው " ብለዋል።

ባለፉት 4 ዓመታት በከተማይቱ ማንነታቸው አልታወቀም በተባሉ አካላት በርካታ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ንፁሃን ዜጎች የተገደሉ ሲሆን የምርመራ ሂደቱ በፖሊስ እጅ መሆኑን የነቀምቴ ፀጥታ እና አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ምስጋኑ ዋቅጋሪ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

Photo Credit : Nekemte Communication

@tikvahethiopia
የሀገራችን ልጅ ድምፃችን ያስፈልጋታል።

ጀሩሳሌም ታምሬ ኢትዮጵያን 🇪🇹 ወክላ በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው ሚስ ካልቸር ኢንተርናሽናል ውድድር ላይ ትሳተፋለች።

''በዚህ ውድድር ላይ የሀገሬን ውብ ባህል ለዓለም ለማስተዋወቅ እድሉን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ።'' ያለችው ጀሩሳሌም ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲሰጧት ጠይቃለች።

ድምጽ ሰጪዎች ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 21 ድረስ በ24 ሰዓት ልዩነት ድምፅ መስጠት ይችላሉ።

ድምጽ ለመስጠት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ https://pageantvote.net/pageants/1492/contestants/7233

@tikvahethiopia
#EthiopianPremierLeague

ዛሬ የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሁለት ተጠባቂ ጨዋታዎችን ያስተናግዳል።

በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በሚካሄደው በዛሬው ጨዋታ የሁል ጊዜ ተፎካካሪዎቹ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ሙሉ ሶስት ነጥብ ለማግኘት ይፋለማሉ።

የሁለቱ ቡድኖች ተጠባቂ ጨዋታ ምሽት 12:00 ላይ የሚካሄድ መሆኑን ከወጣው መርሀ ግብር መመልከት ተችሏል።

ከዚህ ጨዋታ በተጨማሪ ሰበታ ከተማ ከ መከላከያ የሚፈለሙ ሲሆን ይህ ጨዋታ ከቀኑ በ9 ሰዓት ላይ ነው የሚካሄደው።

#CentralHawassaHotel #Betika

Photo : File

More : @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣኗ ኢትዮጵያ ይመጣሉ። የአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ወደ ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ እና ሱዳን ይጓዛሉ። ኮሚሽነር ጁታ በሶስቱ ሀገራት ቆይታ የሚያደርጉት ከጥምቅት 14 እስከ ጥቅምት 17 ድረስ ነው። ጉዟቸው የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ ቀንድ #ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም ከአፍሪካ ጋር ያለውን ጠንካራ ግንኙነት ለመግለፅ እና ለማጠናከር ነው…
#Update

ከቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ የተገለፀው የአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ተወያዩ።

ጁታ ኡርፒላይን ትላንት ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ ከፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ እና ከምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር መነጋገራቸውን አሳውቀዋል።

ባለስልጣኗ ባይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ባወጡት ፅሁፍ ፥ " በሀገሪቱ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳዎች፣ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ግጭትና ስለሰብዓዊ ቀውስ ጉዳይ ገንቢ ውይይት አድርገናል" ብለዋል።

ኡርፒላይን ፥ ከላይ የተገለፁትን ተግዳሮቶች ለመፍታት ከኢትዮጵያውያን አጋሮቻችን ጋር አብሮ መስራታችንን ለመቀጠል ቁርጠኛ ነኝ ሲሉም ፅፈዋል።

በቅርቡ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱም አሳውቀዋል።

እንደ አውሮፓ ህብረት መረጃ ባለስልጣኗ በቀጣይ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት የሚኒስትሮች ስብሰባን ለመካፍል ኪጋሊ እንደሚገቡ ይጠበቃል።

ቀደም ብሎ በወጣው መርሃ ግብር በመጨረሻ የስራ ቆይራቸው ሱዳን ካርቱም እንደሚገቡ የታቀደ ቢሆን በሱደን አሁን ካለው ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ጋር በተያያዘ እና በተደረገው መፈንቅለ መንግስት ምክንያት ወደ ሱዳን ያቀናሉ የሚለው አልታወቀም።

ባለስልጣኗ ወደ ሱዳን ሄደው የሽግግሩን አመራሮች ሊያገኙ መርሀ ግብር ተይዞላቸው የነበረ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት እና ሱዳን የፖለቲካ ውይይትን ያስጀምራሉ ተብሎም ነበር።

@tikvahethiopia
#HappeningNow : 9ኛ ዙር የአማራ ልዩ ሀይል ፓሊስ የምረቃ ስነ ስርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በአሁን ሰዓት በደብረማርቆስ ከተማ የአማራ ክልል ፓሊስ ኮሌጅ የ9ኛ ዙር የአማራ ልዩ ሀይል ምልምል ፓሊስ ሰልጣኞችን እያስመረቀ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሱዳን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ። የሱዳን ጦር አዛዥ ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን መግለጫ ሰጥተዋል። በሀገሪቱ የአስቸኳ ጊዜ አዋጄ መታወጁን አስታውቀዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ ጀነራል አልቡርሀን አልተናገሩም። ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን በመግለጫቸው የሉአላዊ ምክር ቤት እና ሚኒስትሮች ምክር ቤት መፍረሱን ፤ የክልሎች አሰተዳዳሪዎች እና ሌሎች…
#SUDAN : የሱዳን መዲና ካርቱም ትላንት ለሊቱን በአብዛኛው ፀጥ ብላ አሳልፋለች።

የሱዳን ጦር መፈንቅለ መንግስት ማድረግን ተከትሎ የተቋረጠው የኢንተርኔት ፣ የስልክ ግንኙነት አሁንም አልተመለሰም።

የሱዳን ጦር ያደረገውን መፈንቅለ መንግስት ለመቃወም አደባባይ በወጡ እና በጦሩ መካከል በተፈጠረ ግጭት 7 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ140 በላይ መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በካርቱም በአሁን ሰዓት ሱቆች፣ የንግድ ተቋማት ፣ አገልግሎት ሰጪዎች እንደተዘጉ ሲሆን የተወሰኑ መንገዶች አሁንም በሱዳን ጦር እንደተዘጉ ናቸው።

ትላንት ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን በሰጡት መግለጫ የሉአላዊ ምክር ቤት እና ሚኒስትሮች ምክር ቤት መፍረሱን ፤ የክልሎች አሰተዳዳሪዎች እና ሌሎች አመራሮች ከስልጣን መነሳታቸውን፤ በሀገሪቱም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

ቡርሃን እ.ኤ.አ.በጁላይ 2023 ምርጫ ለማካሄድ እና ለተመረጠ የሲቪል መንግስት ስልጣን እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል።

አሁንም ድረስ በእስር ላይ ለሚገኙት ጠ/ ሚ አብደላ ሀምዶክ ታማኝ የሆነው የሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስቴር በይፋዊ ፌስቡክ ገጹ ፥ የሽግግር ህገ መንግስቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማወጅ መብት የሰጠው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቻ ነው ፤ የወታደሩ እርምጃ ወንጀል ነው " ብሎታል።

ሚኒስቴሩ አብደላ ሃምዶክ አሁንም ህጋዊ የሽግግሩ ባለስልጣን ናቸው ሲልም አክሏል።

መረጃው የአልአረቢያ ነው።

@tikvahethiopia