TIKVAH-ETHIOPIA pinned «#ETHIOPIA ፕሮፌሰር አን ፊትዝዠራልድ የአፍሪካ ቀንድ የፀጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች አጥኚ እና ተመራማሪ ናቸው። በተጨማሪ ለበርካታ አመታት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ በኢትዮጵያ የሚገኙ የፀጥታ ተቋማትን በፀጥታ አመራር ተጠያቂነት እና በብሄራዊ ደህንነት ዙሪያ የተለያዩ ስልጠናዎችን የሰጡ ባለሞያ ናቸው። በአፍሪካ ቀንድ ከሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ጋር በመሆን በደቡብ ሱዳን፣ ዩጋንዳ፣ ሱማሊያ…»
TIKVAH-ETHIOPIA
#Balderas : አቶ እስክንድር ነጋ ማረሚያ ቤት ውስጥ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ገለፀ። አቶ እስክንድር በተፈፀማባቸው ድብደባ ምክንያት ጉልበታቸው መቁሰሉን ዋና ሳጅን መስፍን ይልማ (የቂሊንጦ ወህኒ ቤት የፈረቃ ሓላፊ) ለፍርድ ቤት መናገራቸውን ፓርቲው ገልጿል። አቶ እስክንድር ዛሬ ችሎት መቅረብ እንዳልቻሉ ተገልጿል። በዚህም ምክንያት በተከታታይ ምስክር የመስማት…
#Balderas
ባልደራስ ፓርቲ በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ ስለተፈጸመው ድብደባ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠየቀ።
ፓርቲው ይህን የጠየቀው በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ባሰራጨው መልዕክት ነው።
ባልደራስ ፥ አቶ እስክንድር ነጋ በሚኖሩበት ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ውስጥ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም. ንጋት 12፡20 ደቂቃ ላይ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ገልጿል።
አቶ እስክንድር ነገ ወህኒ ቤት ውስጥ በተደራጀ የውንብድና ቡድን መደብደባቸውን ከአቶ እስክንድር ጋር በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ስንታየሁ ለፍርድ ቤት መናገራቸው ተመላክቷል።
አቶ እስክንድር በተፈጸመባቸው ድብደባ ግንባራቸው፣ ዓይናቸው አካባቢ እና ጉልበታቸው ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ፓርቲው ማረጋገጡን ገልጿል።
ለደረሰባቸው ጉዳት የተደረገላቸው ህክምና አለመኖሩም ተመላክቷል።
ባልደራስ ፓርቲ አቶ እስክንድር በአስቸኳይ ቤተሰቦቻቸው ወደ መረጡት ሆስፒታል ተወስደው እንዲታከሙ የጠየቀ ሲሆን ስለተፈጸመው ከባድ ድብደባ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በቀጥታ ለሕዝብ መግለጫ እንዲሰጥ ጠይቋል።
የአቶ እስክንድር ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ አቶ እስክንድር ድብደባ የተፈጸመባቸው ከዚህ ቀደምም ያሰጓቸው ስለነበር ወደ ሌላ ማረሚያ ቤት ከተወሰዱ በኋላ በድጋሚ ወደ ቂሊንጦ በተመለሱ 2 ግለሰቦች ነው ብለዋል።
በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት የመንግሥት የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፥ ክስተቱ በግለሰቦች መካከል የተፈጠረ አለመግባባት እንጂ ሆነ ተብሎ አቶ እስክንድርን ለማጥቃት ታስቦ የተደረገ አይደለም ብለዋል፡፡
@tikvahethiopia

#Balderas ባልደራስ ፓርቲ በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ ስለተፈጸመው ድብደባ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠየቀ። ፓርቲው ይህን የጠየቀው በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ባሰራጨው መልዕክት ነው። ባልደራስ ፥ አቶ እስክንድር ነጋ በሚኖሩበት ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ውስጥ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም. ንጋት 12፡20 ደቂቃ ላይ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ገልጿል። አቶ እስክንድር…
#Balderas
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በነአቶ እስክንድር ነጋ የፍርድ ሂደት ችሎት ታድመው የነበሩ 42 የፓርቲው አባላት ታፍሰው ልደታ ክፍለ ከተማ የፖሊስ መምሪያ ከቆዩ በኋላ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው እንዲታሠሩ እንደተደረጉ ገልጿል።
ከታሠሩት ውስጥ አስራ ሁለቱ (12) ሴቶች መሆናቸውን ፓርቲው አረጋግጫለሁ ብሏል።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደረስ) ፥ የታሠሩት አባሎቹ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ ሲል ጠይቋል።

#JigjigaUniversity
የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ/ም " የነዳጅ ምህንድስና/ ፔትሮሊየም ኢንጅነሪንግ " የአዲስ የትምህርት ፕሮግራም ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።
የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር በሽር አብዱላሂ ለኢፕድ በሰጡት ቃል፥ በሶማሌ ክልል ካሉት የተፈጥሮ ሀብቶች መካከል አንዱ የነጭና የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ነው ብለዋል።
ይህን የተፈጥሮ ሀብት አልምቶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚደረገው እንቅስቃሴም በእውቀትና በምርምር የታገዘ ለማድረግም ዩኒቨርሲቲው በዚህ ዓመት የፔትሮሊየም ኢንጅነሪንግ የትምህርት ፕሮግራም መስጠት ይጀምራል ሲሉ አሳውቀዋል።
Credit : ኢፕድ

#AddisAbaba : የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ለማስፈጸም በከተማ አስተዳደሩ ከተዋቀረው የኮማንድ ፖስት አባላት ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
ከጥቅምት 29 - ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠዉ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
ብሄራዊ ፈተናው በከተማ ደረጃ በስኬት እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተከናውነዋል ያሉት የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ አንዳንድ የግል ትምርት ቤቶች ግን እስከ አሁን አድሚሽን ካርድ ለተማሪዎች አለማድረሳቸውን ጠቁመዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በ62 የፈተና ጣቢያዎች 36,415 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ፈተና እንደሚወስዱ እና ይህንንም የሚመሩና የሚያስተባብሩ 2ሺ 600 የፈተና አስፈጻሚዎች ምልመላ መካሄዱን ቢራ ገልፆል፡፡
መረጃው የአ/አ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ነው።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥቅምት 12/2014 ዓ/ም ይጀምራል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጥቅምት 2014 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ አርብ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሚጀምር ተገልጿል። ይህንን ተከትሎ ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በምልአተ ጉባኤው እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል። ፎቶ ፦ ፋይል @tikvahethiopia
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ !
በሰላም እጦትና አለመረጋጋት ሳቢያ በንፁሃንና በሀገር ደህንነት ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት እንዲያበቃ ህዝበ ምዕመኑ ፀሎትና ተማፅኖውን እንዲያበረታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አቅርባለች።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የቅዱስ ሲኖዶስ ዓመታዊ ምልዓተ ጉባዔን አስጀምረዋል።
ምዕመናንና ሀገርን መጠበቅ ሰላምን መሻት የቅድስት ቤተክርስቲያን ግብርና ተልዕኮ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ለወገን ሰላም የሃይማኖት አባቶችና አብያተ ክርስቲያናት ተግተው እንዲፀልዩ አሳስበዋል።
ሰላም ለመንፈሳዊም ለዓለማዊ እንቅስቃሴ እጅጉን አስፈላጊ ነው ያሉት ፓትሪያርኩ በተወሰኑ አካባቢዎች ባለው የሰላም እጦት ሳቢያ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት እንዲያበቃ ምዕመኑ ፀሎትና ልመናውን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።
በየዓመቱ ጥቅምት 12 የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ መካሄድ ጀምሯል።
Credit : AMN

#Mekelle : በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል መዲና መቐለ የአየር ጥቃት መፈፀሙን ሮይተርስ ዘግቧል። የዛሬው ጥቃት በአራት ቀናት ውስጥ ለ3ኛ ጊዜ የተፈፀመ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ ሐሙስ የአየር ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጠዋል። የዛሬው የአየር ድብደባ ኢላማ ያደረገው የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት ይዞታ የነበረ (ሰሜን ዕዝ)ና በአሁኑ ጊዜ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር…
#ENDF: የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ ተጨማሪ የአየር ጥቃት ፈፅሟል።
ጥቃቱ በዚህ ሳምንት ብቻ 4ኛው ነው።
የዛሬው የአየር ድብደባ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) የማሰልጠኛ ማዕከል መሆኑን በፌዴራል መንግስት ስር ያለው የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገፅ አሳውቋል።
ገፁ የአየር ድብደባው የት እንደተፈፀመ በግልፅ ባይጠቅስም " ሌላው የአሸባሪው ቡድን የህወሓት ማሰልጠኛ ማዕከል ዛሬ የአየር ጥቃት ዒላማ ሆኗል" ሲል ገልጿል።
አክሎም ፥ " ይህ ማዕከል ለአሸባሪው ቡድን ወታደራዊ ሥልጠና ከመዋሉ በፊት የኢፌዴሪ መከላከያ ማሠልጠኛ ማዕከል ነበር በአሁኑ ወቅት አሸባሪው ቡድን በዚህ ተቋም ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና የሚሠጥበት፤ የዉጊያ ግንኙነት ኔት ወርክ ያለበት ነው" ብሏል።
ሮይተርስ፣ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪሎች እንዲሁም የሀገር ውስጡ ኢዜአ የዛሬው የአየር ድብደባ በመቐለ የተፈፀመ መሆኑን ዘግበዋል።

ሩሲያ በኢትዮጵያ ተኩስ እንዲቆም ጠየቀች።
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ “በመንግስት ወታደሮች እና በትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር /TPLF/ መካከል ያለው ግጭት መጠናከሩን ተከትሎ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተልን ነው” ብለዋል፡፡
አክለውም ፥ “የግጭቱ ተዋናዮች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁመው ሁኔታውን እንዲያረግቡ እናሳስባለን” ሲሉ ተናግረዋል።
Credit : MFA RUSSIA

#Harari : በሀረሪ ክልል የአዲስ መንግስት ምስረታ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ማካሄድ በጀመረው የመንግስት ምስረታ ጉባኤው የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር , የምክር ቤቱን አፈጉባኤ እና ምክትል አፈጉባኤ እንደሚሾም ይጠበቃል።
በተጨማሪም ጉባኤው በቆይታው በርዕሰ መስተዳድሩ የሚቀርቡ የምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የካቢኔ አባላትንም እጩዎችን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡
በክልሉ የአዲሱን መንግስት ምስረታ ለመታደም ከፌዴራል መንግሥት እና የሀረሪ ክልልን ከሚያዋስኑ አጎራባች ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

" ነፃ የጡት ካንሰር ምርመራ "
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ከጥቅምት 15 እስከ ጥቅምት 22 ደረድ ነፃ የጡት ካንሰር ምርመራ እንደሚያካሂድ አሳውቆናል።
ምርመራው ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ከጥዋቱ 3 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ድረስ 5ኛ በር አካባቢ ነው የሚካሄደው።

#ENDF: የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ ተጨማሪ የአየር ጥቃት ፈፅሟል። ጥቃቱ በዚህ ሳምንት ብቻ 4ኛው ነው። የዛሬው የአየር ድብደባ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) የማሰልጠኛ ማዕከል መሆኑን በፌዴራል መንግስት ስር ያለው የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገፅ አሳውቋል። ገፁ የአየር ድብደባው የት እንደተፈፀመ በግልፅ ባይጠቅስም " ሌላው የአሸባሪው ቡድን የህወሓት ማሰልጠኛ ማዕከል ዛሬ…
" ... በራሳቸው ምክንያት ካልሆነ በስተቀር የአየር ድብደባውና የሰብአዊ እርዳታ ጫኝ አውሮፕላን እንቅስቃሴ አይገናኝም " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ
ዛሬ ሮይተርስ 2 የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የተመድን የሰብአዊ እርዳታ የጫነ አውሮፕላን መንግስት በትግራይ ክልል ባካሄደው የአየር ድብድባ ምክንያት መቐለ ማረፍ አልቻለም ብሏል።
ሮይተርስ በዚህ ጉዳይ ሁለት ሰማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰዎችን ማናገሩን ጠቅሷል።
ይህንን ጉዳዩን በተመለከተ ለአል ዐይን ቃላቸውን የሰጡት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ፥ " በራሳቸው ምክንያት ካልሆነ በስተቀር የአየር ድብደባው እና የሰብአዊ እርዳታ ጫኝ አውሮፕላን እንቅስቃሴ አይገናኝም" ብለዋል።
“አንደኛ ሰዓቱ የተለያየ ነው” ያሉት ዶ/ር ለገሰ፤ “መዳረሻዎችም የተለያዩ ናቸው” ሲሉም ተናግረዋል።
ምንጭ፦ አል ዓይን
Photo : FILE

#ኢህአፓ : የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ አገራዊ ምክር ቤት አዲስ አበባ በሚገኘው ፅ/ቤቱ ለሶስት ቀናት ስብሰባ አድርጎ ነበር። ም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴው ባቀረበለት አጀንዳ ውይይት ካካሄደ በኃላ ከላይ የተያያዘውን መግለጫ አውጥቷል።
@tikvahethiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Harari : በሀረሪ ክልል የአዲስ መንግስት ምስረታ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ማካሄድ በጀመረው የመንግስት ምስረታ ጉባኤው የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር , የምክር ቤቱን አፈጉባኤ እና ምክትል አፈጉባኤ እንደሚሾም ይጠበቃል። በተጨማሪም ጉባኤው በቆይታው በርዕሰ መስተዳድሩ የሚቀርቡ የምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የካቢኔ አባላትንም እጩዎችን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡ በክልሉ…
#UPDATE
አዲሱ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው የመጀመሪያ ጉባኤ አቶ ኦርዲን በድሪ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሹሟል።
አቶ ኦርዲን በድሪ ላለፉት ሶስት አመታት የሀረሪ ክልልን በርዕሰ መስተዳድርነት መርተዋል።
በተጨማሪ መረጃ ፦ አቶ ሱልጣን አብዱሰላምን የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤ ፤ አቶ አሪፍ መሀመድ አዱስ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ በመሆን ተሹመዋል፡፡
ምንጭ፦ የሀረሪ ክልል ኮሚኒኬሽን