" ባንክ ኦፍ አዲስ / Bank of Addis "
በ10 ቢሊዮን ብር በተመዘገበ ካፒታል አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ወደ ባንክ ማደጉ ተገለፀ።
አዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም በ3.7 ቢሊዮን የተከፈለ እና በ10 ቢሊዮን ብር በተመዘገበ ካፒታል " ባንክ ኦፍ አዲስ " በሚል ወደ ባንክ ማደጉን የተቋሙ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ዳምጠው አለማየሁ አስታውቀዋል።
የተቋሙ አመራሮችና ባለአክሲዮኖች ትላንት ጉባኤ ያካሄዱ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት በማድረግ ወደ ባንክ እንዲሸጋገር መወሰናቸው ተገልጿል።
ወደ ባንክ የተሸጋገረው ተቋሙ ከሌሎች ባንኮች በተለየ ሁኔታ ጣምራ አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ለመስጠት ያስችላል ተብሏል።
የአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ከመደበኛ ባንኮች የፋይናንስ አገልግሎት ማግኘት ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች አዲስ አበባ ከተማ የስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ተብሎ በ1988 ዓ.ም በ5 አክሲዮኖች በ517 ሺህ ብር የተከፈለ ካፒታል እና ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ በተመዘገበ ካፒታል ነበር የተመሰረተው።
Credit : AAPS
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የስራ ርክክብ አደረጉ፡፡ በአዲሱ የመንግስት ምስረታ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከቀድሞ የትምህርት ሚኒስትር ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡ ለአዲሱ ሚኒስትር የቀድሞ የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በርክክቡ ወቅትም…
የትምህርት ሚኒስትሩ ከሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄዱ።
በዛሬው ዕለት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከሚኒስቴሩ አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።
ውይይቱ በቀጣይ በትኩረት ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል።
ሰራተኞቹ በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ አሉ ያለቱን የአሰራር ፣ የመልካም አስተዳደር እና የአደረጃጀት ችግሮች ለሚኒስትሩ አሳውቀዋል።
በቀጣይም ሚኒስትሩ በተቋም ውስጥ ያሉትን ችግሮች በመፈተሽ መፍትሄ የመስጠት እና የትምህርት ሴክተሩን ከፓለቲካ እና ከንግድ ነፃ ለማድረግ ሊሰሩ እንደሚገባ ሰራተኞቹ ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ፥ በሰራተኞች የተነሱትን ሀሳቦች እንደ ግብዓት በመውሰድ እና መፍትሄ በመስጠት በቅንጅት የተሻለ ስራዎችን ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ፥ " የትምህርት ሴክተሩ የፓለቲካ መስሪያ ቤት ሳይሆን ህዝብን ለማገልገል የተቋቋመ ሴክተር በመሆኑ የፓሊቲካ አመለካከታችንን ትተን ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል " ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም፥ "ሚኒስቴሩ የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር ከፍተኛ ሀላፊነት ያለበት ተቋም በመሆኑ የተሻለ ስራ መስራት ይጠበቅበታል " ብለዋል።
መረጃው ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

ሹመት !
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት አቶ አብርሃም አለኸኝን በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዘርፍ አስተባባሪ አድርገው ሾመዋቸዋል።
#PMOEthiopia

የጥቅምት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ በመስከረም ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲቀጥል ንግድና ኢዱስትሪ ሚኒስቴር አሳውቋል።
@tikvahethiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የ "እንኳን ደስ አለዎት! " መልዕክት አስተላለፉ። ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቱን ዶ/ር አቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሰየማቸውን ተከትሎ የ "እንኳን ደስ አለዎት" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው ፥ የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት በመልካም የወዳጅነት እና እርስ በርስ መከባበር ላይ የተመሠረተ…
#DrAbiyAhmed
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀጣይ 5 ዓመታት ኢትዮጵያን እንዲመሩ ከተሾሙ በኃላ የተለያዩ ሀገራት የደስታ መግለጫ እያስተላለፉ ይገኛሉ።
ኬንያ፣ ሱማሊያ ፣ ዩጋንዳ፣ ደ/ሱዳን፣ ጁቡቲ ፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ አልጄሪያ መሪዎቻቸው እና ከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው እዚህ ኢትዮጵያ ተገኝተው መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
የኤርትራ በፕሬዘዳንቷ ፣ የዩኤኢ መሪዎች ፣ ቬትናምም በጠቅለይ ሚኒስትሯ የመልካም ምኞት መግለጫቸውን የላኩ ሲሆን ዛሬም ሩሲያ በፕሬዜዳንቷ ለ5 ዓመታት የኢትዮጵያ መሪ እንዲሆኑ ለተሾሙት ዶ/ር ዐቢይ "እንኳን ደስ አልዎት" መልዕክት ልካለች።
ማምሻውን ደግሞ የኳታር አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ ቀጀላ መርዳሳ የሥራ ርክክብ አደረጉ፡፡ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት አቶ ቀጀላ መርዳሳ ከቀድሞው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ጋር የሥራ ርክክብ አድርገዋል፡፡ ለአዲሱ ሚኒስትርም የቀድሞዋ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር የነበሩት ዶ.ር ኂሩት ካሳው እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በርክክቡ ወቅትም ለሚኒስትሩ ስለ የባህልና…
አዲስ የተሾሙ ሚኒስትሮች እንዲያገለግሉ በተሾሙባቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በመገኘት ከቀድሞ ሚኒስትሮች የስራ ርክክብ እያደረጉ ይገኛሉ።
ዛሬ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከቀድሞ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ፊልሰን አብዱላሂ ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡
በተጨማሪ ለኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተሾሙት አቶ መላኩ አለበል እና አቶ ገብረመስቀል ጫላ ዛሬ የስራ ርክከብ አድረዋል፡፡

#ETHIOPIA😷
ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 33 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 33 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 8,415 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 921 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 745 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

#EU #AU
የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚሼል ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ከሆኑት ከቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ጋር ተገናኝተው መከሩ።
ቻርልስ ሚሼል እንደገለፁት ከሆነ ምክክሩ በትግራይ ግጭት ዙሪያ ሲሆን ፤ ዘላቂ እና ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት በሚደረግ አስቸኳይ ጥረት ላይ ነው ትኩረቱን አድርጎ የነበረው።
የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ፤ " የቀጠናውን መረጋጋት ለማረጋገጥ የአውሮፓ ህብረት ከአፍሪካ ህብረት ጋር በቅርበት ለመስራት ዝግጁ ነው " ብለዋል።

#AAU
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት ነገ ያከናውናል።
ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮችና መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 6 ሺህ 163 ተማሪዎች ነገ መስከረም 29/2014 ዓ.ም ያስመርቃል።
ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 3 ሺ 604ቱ በመጀመሪያ ዲግሪ የሚመረቁ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 2 ሺህ 559 ተማሪዎች የድህረ ምረቃ ተመራቂዎች ናቸው።
155 ተማሪዎች በሦሥተኛ ዲግሪ (PhD) የሚመረቁ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ዳይሬክተር ጥላሁን ተስፋዬ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።
የምረቃ ስነ ስርዓቱ በሸገር ፓርክ የወዳጅነት አደባባይ እንደሚከናወን ታውቋል።
ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦች የትምህርት ተቋማትን ብቻ ትኩረት አድርጎ መረጃ የሚልክላችሁን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገፅ መቀላቀል ትችላላችሁ : https://t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h
@tikvahuniversity @tikvahethiopia

#Amhara
የትግራይ ክልል ጦርነት ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች ከሰፋ በኃላ ህወሓት የተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎችን ፣ በርካታ ህዝብ የሚኖርባቸውን ከተሞች እንደተቆጣጠረ ይገኛል።
መንግስት አካባቢዎቹን ከቡድኑ ለማስለቀቅ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀ መሆኑንም ከዚህ ቀደም ሲገልፅ ነበር።
ከሰሞኑ የህወሓት ቡድን ታጣቂዎች ይዘዋቸዋል በተባሉ ቦታዎች ላይ የአየር ድብደባ እየተፈፀመ መሆኑን ተነግሯል።
ሮይተርስ ትላንት በድረገፁ ባሰራጨው መረጃ ከሀሙስ ዕለት ጀምሮ ጠንከር ያሉ እርምጃዎች በኢትዮጵያ ጦር እየተወሰዱ መሆኑን ይገልፃል።
የህወሓት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ፥ የሰሞኑን ጠንካራ ጥቃት በኢትዮጵያ ሠራዊት የምድር ጥቃት ሊጀመር መሆኑ ምልክት ሊሆን የሚችል ነው ብለዋል።
አክለውም፥ "በሁሉም ግንባሮች በኩል ግዙፍ ኃይል እየተንቀሳቀሰ ነው. . . በየትኛው ግንባር ጥቃት ሊከፍቱ እንደሚችሉ እርግጠኛ አይደለንም" ለሮይተርስ ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ አዲስ ተከፈተ ባሉት የተጠናከረ ጥቃት በኢትዮጵያ ሠራዊት በኩል "መድፎችና ሰው አልባ አውሮፕላኖች [ደሮን] ጥቅም ላይ ውለዋል" ሲሉም ተደምጠዋል።
ሀሙስ የጀመረው ተከታታይ የአየር ጥቃት አርብም የቀጠለ ሲሆን፣ ትኩረቱን ያደረገውም በ3 አካባቢዎች ላይ ነው።
እነዚህም፦
- ከውርጌሳ አቅራቢያ ባለ ቦታ
- በወገል ጤና እና
- በምሥራቅ በኩል የአማራ ክልልን ከአፋር ጋር በሚያገናኘው መንገድ ላይ ነው ብሏል ሮይተርስ።
የዜና ወኪሉ ውርጌሳ የተባለው አቅራቢያ የአየር ጥቃት እንደነበር አንድ ዲፕሎማቲክ ምንጭ እንዳረጋገጡለት የጠቀሰ ሲሆን በሌሎቹ አካባቢዎች ተፈጸመ ስለተባለው የአየር ጥቃት ከገለልለተኛ ወገን ለማረጋገጥ እንዳልቻለ ገልጿል።
telegra.ph/Reuters-10-09

#AAU አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት ነገ ያከናውናል። ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮችና መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 6 ሺህ 163 ተማሪዎች ነገ መስከረም 29/2014 ዓ.ም ያስመርቃል። ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 3 ሺ 604ቱ በመጀመሪያ ዲግሪ የሚመረቁ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 2 ሺህ 559 ተማሪዎች የድህረ ምረቃ ተመራቂዎች ናቸው። 155 ተማሪዎች…
አዲስ አበባ እና አርባምንጭ ዩኒቨርሲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በማታ እንዲሁም በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር ያስተማራቸውን 6 ሺህ 163 የቅድመ ምረቃና ድሕረ ምረቃ ተማሪዎችን በወዳጅነት አደባባይ እያስመረቀ ይገኛል።
የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ5 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል፡፡
አርባምጭ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ እያስመረቀ የሚገኘው ለ34ኛ ዙር ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን : https://t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h
Photo Credit : ENA & FBC

#TheWeeknd
ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቀንቃኝ አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ) የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) የበጎ አድራጎት አምባሳደር ሆኖ በድርጅቱ መመረጡን ቢቢሲ ዘግቧል።
አቀንቃኙ ፥ በመላው ዓለም ረሃብን ለማስወገድ ከሚታገሉ በጎ ፈቃደኛ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) አምባሳደሮች ጋር በጋራ የሚሠራ ይሆናል።
ዘ ዊኬንድ ከወራት በፊት በትግራይ ክልል በተነሳው ጦርነት ለተጎዱ ሰዎች የሚውል አንድ ሚሊዮን ዶላር ለWFP መለገሱ ይታወሳል።
ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ፥ ዘ ዊኬንድ ይህንን አንድ ሚሊዮን ዶላር ጨምሮ ባለፈው ዓመት ለተለያዩ የረድዔት ድርጅቶች ከ3 ሚሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ ለግሷል።
Photo Credit : David Beasley (WFP)

አዲስ አበባ እና አርባምንጭ ዩኒቨርሲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በማታ እንዲሁም በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር ያስተማራቸውን 6 ሺህ 163 የቅድመ ምረቃና ድሕረ ምረቃ ተማሪዎችን በወዳጅነት አደባባይ እያስመረቀ ይገኛል። የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ5 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል፡፡ አርባምጭ ዩኒቨርሲቲ…
ፎቶ : የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ በ " ወዳጅነት አደባባይ " እየተካሄደ ነው።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ፦
- የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣
- የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እና የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣
- የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ፣
- የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣ እንግዶች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
የዛሬው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ለ72ኛ ጊዜ የሚካሄድ ነው።
Photo Credit : AAPS