TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ደሴ

የኢትዮጵያ 🇪🇹 ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ደሴ ገቡ።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ደሴ የገቡት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደሴ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ወገኖችን ለመጎብኘት ነው።

የደሴ ከንቲባ አቶ አበበ ገ/መስቀል ፥ ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀው ህወሓት በአማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ተፈናቅለው ደሴ የሚገኙ 300 ሺህ ዜጎች እንዳሉ አሳውቀዋል።

የፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጉብኝትም ተፈናቃዮች ያሉበትን ወቅታዊ ሁኔታ በትክክል ለመረዳት እንደሆነ ገልፀዋል።

ከጉብኝታቸው በኋላም ለተፈናቃዮች ድጋፍ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከንቲባው አስታውቀዋል።

Photo Credit : ENA

@tikvahethiopia
#Tigray : ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (አይሲአርሲ) በትግራይ ክልል በሆስፒታሎች እና ሌሎች የጤና ተቋማት ውስጥ ለሚገኙ 15,000 የጤና ሰራተኞች እና ሕሙማን ለ2 ወራት የሚሆን የመሠረታዊ የምግብ አቅርቦቶችን ማሰራጨት መጀመሩን ዛሬ አስታውቋል።

አይሲአርሲ ፥ "ሕሙማን የሕክምና አገልግሎት ማግኘት እንዲቀጥሉ የሕክምና ሠራተኞችን መደገፍ አስፈላጊ ነው" ብሏል።

#ICRCEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Oromia : ጨፌ ኦሮሚያ በአባ ገዳዎች ምርቃት ጉባኤውን ጀምሯል። ዛሬ አዲሱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ይመሰረታል። ነባር የጨፌው አባላት ተሸኝተው በአዲሶቹ ይተካሉ ፤ አዲሱ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ጨምሮ አዲስ የካቢኔ አባላት ይሰየማሉ። Photo Credit : ኤፍ ቢ ሲ @tikvahethiopia
#Update

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።

የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት አቶ ሽመልስ አብዲሳን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟል።

አቶ ሽመልስ የክልል ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ዛሬ ስራ በጀመረው በአዲሱ የጨፌ አባላት ነው፡፡

ፕሬዚዳንቱ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

Credit : ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ። የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት አቶ ሽመልስ አብዲሳን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟል። አቶ ሽመልስ የክልል ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ዛሬ ስራ በጀመረው በአዲሱ የጨፌ አባላት ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ Credit : ENA @tikvahethiopia
#Oromia

ጨፌ ኦሮሚያ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ያቀረቧቸውን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የክልል ካቢኔ አባላት ሹመት አጽድቋል፡፡

በዚህም :-

1.አቶ አወሉ አብዲ - የክልሉ ምክትል ፕሬዘዳንት
2. አቶ ፍቃዱ ተሰማ - በጨፌ የመንግስት ተጠሪ
3. ዶክተር ግርማ አመንቴ - በምክትል ፕሬዘዳንት ማዕረግ የክልሉ መንግስት የልማት ድርጅቶች ክላስተር አስተባባሪ
4. ወይዘሮ መስከረም ደበበ - በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ
5. አቶ አዲሱ አረጋ - በምክትል ፕሬዘዳንት ማዕረግ የከተማ ክላስተር አስተባባሪ
6. አቶ አብዱራህማን አብደላ - በምክትል ፕሬዘዳንት ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ
7. አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ - በምክትል ፕሬዘዳንት ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ
8. አቶ አበራ ወርቁ - የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ሃላፊ
9. ወይዘሮ አዱኛ አህመድ - የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዋና አቃቢ
10. አቶ ሻፊ ሁሴን - የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ
11. ኢንጂነር ሚሊዮን በቀለ - የኦሮሚያ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ
12. አቶ ቶለሳ ገደፋ - የኦሮሚያ የገንዘብና ኢኮኖሚያዊ ልማት ቢሮ ሃላፊ
13. አቶ አበራ ቡኖ - የክልሉ ሚሊሺያ ቢሮ ሃላፊ
14. ወይዘሮ ሳሚያ አብደላ - የስፖርት ኮሚሽን
15. ጉዮ ገልገሎ - የቤቶችና ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ
16. አቶ አህመድ ኢድሪስ - የስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ሃላፊ
17. ወይዘሮ ሀዋ - አህመድ የንግድ ቢሮ ሃላፊ
18. ዶክተር መንግስቱ በቀለ - የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሃላፊ
19. ወይዘሮ ሰዓዳ ዑስማን - የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝምቢሮ ሃላፊ .
20. አቶ ጉታ ላቾሬ - የመሬት ቢሮ ሃላፊ .
21. ወይዘሮ መሰረት አሰፋ - የህብረት ስራ ማስፋፊያ ኤጄንሲ ሃላፊ
22. ዶክተር ተሾመ አዱኛ - የኢንቬስመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ
23. ኢንጂነር ሄለን ታምሩ - የኦሮሚያ መንገዶችና ሎጄስቲክ ቢሮ ሃላፊ
24. ዶክተር ቶላ በሪሶ - የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ
25. ዶክተር ኢንጂነር መሳይ ዳንኤል - የኦሮሚያ መስኖና አርብቶ አደር ልማት ቢሮ ሃላፊ
26. ወይዘሮ ጀሚላ ሲንቢሩ - የኦሮሚያ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ
27. አቶ አራርሶ ቢቂላ (የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የስራ አስፈፃሚ አባል) - የኦሮሚያ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ
28. አቶ ሃይሉ አዱኛ - የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ
29. አቶ ሁሴን ፈይሶ - የፐብልክ ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ
30. ዶክተር አብዱልአዚዝ ዳውድ - የኦሮሚያ ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር
31. አቶ ጌቱ ወዬሳ - የፕሬዝዳንት ቢሮ ሃላፊ .
32. ወይዘሮ ኮኮቤ ዲዳ - የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

ሹመቱ የተሰጠው ተሿሚዎቹ ባላቸው የትምህርት ዝግጅት ፣ በአመራር ሰጪነት ፣ በፖለቲካ ቁርጠኝነትና ብቃት መሆኑ ተገልጿል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
#Somalia : ዛሬ በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሹ በፕሬዚዳንቱ መኖሪያ አቅራቢያ በሚገኝ መስቀለኛ መንገድ ላይ በአንድ የአጥፍቶ ጠፊ የመኪና ፍንዳታ 8 ሰዎች መገደላቸውን እና የተጎዱ ሰዎች ስለመኖራቸው AFP ዘግቧል።

የተጎጂዎች ቁጥር ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል ተነግሯል።

የሱማሊያ ፖሊስ ከጥቃቱ ጀርባ አል-ሸባብ እንዳለ ገልጿል።

የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት መሐመድ ኢብራሂም ሞዓሊሙ በበኩላቸው ከተገደሉት መካከል በጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሁሴን ሮቤል ጽሕፈት ቤት የሴቶችና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች አማካሪ ሂባቅ አቡካር ይገኙበታል ብለዋል።

@tikvahethiopia
#Amhara : "275 ሺህ ሄክታር መሬት አልታረሰም ፥ በዘር የተሸፈነ አንድ ሚሊዮን ሄክታር በእንክብካቤ እጦት ተበላሽቶ ቀርቷል" - ግብርና ሚኒስቴር

ግብርና ሚኒስቴር ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው ህወሓት በአማራ ክልል በፈፀመው ወረራ 275 ሺህ ሄክታር መሬት ሳይታረስ መቅረቱን እና በዘር የተሸፈነ አንድ ሚሊዮን ሄክታር በእንክብካቤ እጦት ተበላሽቶ እንደቀረ አስታወቀ።

የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሳኒ ረዲ ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፤ በሰሜን ወሎ፣ ዋግህምራ፣ ሰሜን ጎንደር ብቻ ሁለት መቶ 75 ሺህ ሄክታር መሬት ሳይታረስ መቅረቱን አመልክተዋል።

በእነዚህ አካባቢዎች አንድ (1) ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር የተሸፈነ እንክብካቤ ሳይደረግለት በእንስሳት እንዲበላ በመደረጉ የተዘራው ሰብል መበላሸቱን ገልፀዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ህወሓት በግብርናው ዘርፍ ያደረሰው የጉዳት መጠን ጠቅለል ያለ ጥናት እየተጠና ነው ብለዋል።

"ሰላም በሆኑ ሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች ሚሊሻው እና ልዩ ሃይሎች በመዝመታቸው፣ ወላጆቻቸውን በግብርና እርሻ ያግዙ የነበሩ ወጣቶች ህወሓትን ለመመከት ግንባር ላይ በመሰለፋቸው ምክንያት የሚታጣው ምርት በባለሙያዎች እየተጠና ነው" ሲሉም አቶ ሳኒ ረዲ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ሀገር መከላከያ ሰራዊት ትላንት ካማሽ ገብቷል።

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ካማሽ ከተማ ሙሉ ለሙሉ መግባቱን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ምስጋናው እንጂፈታ አሳውቀዋል።

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ካማሽ መግባቱን ተከትሎ በአካባቢው ይሰማ የነበረው የተኩስ ልውውጥ መቆሙንና በአካባቢው የነበረውን ታጣቂ ኃይልም ማፈግፈጉን ገልፀዋል።

ኢስፔክተር ምስጋናው እንጅፈታ ለ#ቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ በካማሺ ዞን የሚንቀሳቀሱ እራሳቸው የቤንሻንጉል ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ቤህነን) የሚባሉ ታጣቂዎች የዞኑን በርካታ ቦታዎች ተቆጣጥረው መቆየታቸውን አስረድተዋል።

"የቤህነን ታጣቂ ከኦነግ ሸኔ ጋር ቅንጅት አላቸው፣ ከእነሱ ጋር እየተጋገዙ ነው ይህን የሚያደርጉት፣ በዞኑ 5 ወረዳ ነው ያለው ከዞን እና የወረዳ ማዕከሎች ውጪ አንድም ቀበሌ በመንግስት እጅ ላይ የለም" ሲሉ አክለዋል።

ከመንግስት እጅ በወጡ ቦታዎች በፖለቲካው እንቅስቃሴ የለም፣ ሙሉ በሙሉ ግንኙነቶችም ተቋርጠዋል በዚህ ምክንያት በዞኑ ሰብዓዊ ቀውስ ተፈጥሯል ሲሉ ገልፀዋል።

ኢንስፔክተር ምስጋናው ፥ ባለው የፀጥታ ኃይል ውስንነት የተነሳ ችግር አለባቸው ተብሎ በጥናት የተለዩ ቦታዎች በመግባት ህግ ማስከበር እንዳልተቻለ አመልክተው ፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ ህብረተሰቡ በተጎሳቆለ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው ብለዋል።

ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ቦታዎች ያልተዘረፈ ከብት የለም፤ ያልተዘረፈ ንብረት የለም፣ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ነው ያለው ፤ ህብረተሰቡ በረሃብ እየተጎዳ ነው፣ መድሃኒት የለም ተዘርፏል፣ ጤና ኬላዎች ግብአት አይገባላቸውም ግንኙነት የለም ተቋርጧል በዚህም ህብረተሰቡ ከፍተኛ ስቃይ ላይ መሆኑን አመልክተዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Benishangul-Gumuz-09-25

@tikvahethiopia
#AddisAbaba - ማስታወሻ !

ዛሬ በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የደመራ በዓል ተጀምሮ አስከሚጠናቀቅ ከዚህ በታች የተገለፁትን መንገዶች ዝግ ይሆናሉ።

የሚዘጉት መንገዶች ፦

• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባቢ፤
• ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ፤
• ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት፤
• ከፒያሣ አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቸርችር ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ፤
• ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፤
• ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ፤
• ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኢምግሬሽን የኋላ በር መግቢያ፤
• ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፤
• ከባሻ ወልዴ ችሎት በኦርማ ጋራዥ ወደፉል ውኋ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት ፤
• ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የመወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ
• ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ
• ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ ናቸው።

ስንት ሰዓት ነው የሚዘጋው ?

ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ሁሉ ዝግ ነው።

*** ሌላው ፦
ደመራው የሚደመርበት መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ስታዲዬም እንዲሁም ከሃራምቤ ሆቴል ወደ ሴንጅ ዮሴፍ የሚያቋርጠው መስቀለኛ መንገዱ ለበዓሉ በሚደረገው ዝግጅት ምክንያት ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ከሳሪስ እና ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ከባድ ተሸከርካሪዎች መንገዱ አጎና ሲኒማ ጋር የሚዘጋ ይሆናል፡፡

#ሼር ያድርጉት !

@tikvahethiopia
* ኒውዮርክ

የኢትዮጵያ🇪🇹ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 76ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
* የጥሞና ጊዜ !

መስከረም 20 ለሚካሄደው ምርጫ የፓለቲካ ፓርቲዎች እና እጩዎች ቅስቀሳ የሚያደርጉበት ጊዜ በትላንትናው ዕለት መስከረም 15 ቀን 2014 ዓ.ም ተጠናቋል።

በዚህም አራት ቀናት ፓለቲካ ፓርቲዎች ቅስቀሳ የማያከናውንኑበት የጥሞና ጊዜ ነው።

በእነዚህ አራት ቀናት ምን ተከልክሏል ?

የፖለቲካ ፓርቲዎች ፦ ማንኛውም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይፈቀድላቸውም፡፡ (በኢንተርኔት፣ በማህበራዊ ሚዲያ፣ በግንባር፣ ቤት ለቤት፣ በአደባባይ ፣ በአዳራሽ ስብሰባ ምንም አይነት ቅስቀሳ ማከናወን በጥብቅ የተከለከለ ነው።

እንዲሁም በምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት እንዲሁም ቃለ-መጠይቆችን ማድረግ አይፈቀድላቸውም፡፡

በተጨማሪ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የሚያወጣቸውንም መመሪዎች ሊፈጽሙ ይገባል፡፡

መገናኛ ብዙሀን ደግሞ በጥሞና ወቅት ማንኛውንም ፓርቲ ምርጫ ተኮር እንቅስቃሴዎችን ማሰራጨት አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም የፓለቲካ ፓርቲ እጩዎችን አግኝተው ቃለ መጠይቆችን መስራት አይፈቀድላቸውም፡፡

የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሚወጡ መረጃዎችን እና የመራጮች ትምህርትን መረጃዎች ብቻ በማስተላለፍ ላይ ሊያተኩሩ ይገባቸዋል ፤ በነዚህ ቀናት ቦርዱ የመራጮች ትምህርቶች እና የምርጫ መረጃዎችን መስጠቱን ይቀጥላል።

@tikvahethiopia
የጎፋ 'ጋዜ ማስቃላ' እና የኦይዳ 'ዮኦ ማስቃላ' በዓል !

በጎፋ ዞን በሚገኙ በሁለቱ ብሔረሰቦች ዘንድ የሚከበረዉ የመስቀል በዓል በጎፋ ብሔረሰብ ጋዜ ማስቃላ በኦይዳ ብሔረሰብ ደግሞ ዮኦ! ማስቃላ በመባል በተለያዩ ባህላዊ ኩነቶች ታጅቦ ይከበራል።

ለአካባቢው ህብረተሰብ የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ ታላቅ ባህላዊ ክብረ በዓል ነው።

ይህ በዓል በዓመት አንድ ጊዜ ትልቅ ትኩረት ተሠጥቶበት የሚከበር ነው።

ከትንሽ እስከ ትልቅ፤ ድሃም ሆነ ሀብታም በሁሉም ማሕበረሰብ ያለዉም ይሁን የሌለዉ በመስቀል በዓል፤ አንድ የሚሆንበት ልዩ በዓል ነው።

በጎፋም ይሁን በኦይዳ ለመስቀል በዓል ካለዉ ትልቅ ከበሬታ የተነሣ በዓሉ ገና በዓመቱ እስከሚመጣ ታስቦ ቅድመ ዝግጅት ይደረግበታል፡፡

ለልጆች ልብስ፤ በዕለቱ ለሚዘጋጀዉ ምግብና መጠጥ በተለይ ለመስቀል ሥጋ ተብሎ ዓመቱን በሙሉ በመቆጠብ ፤ በዕድር ዝግጅት ከመደረጉም ባለፈ፤ ለመስቀል በዓል ተብለዉ ለሚደረጉ ነገሮች፤ ሳይሰሰት ሁሉም የሚፈፅመዉ ይሆናል፡፡

በተለይ የመስቀል በዓል በጎፋ እና በኦይዳ ብሔረሰቦች ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሠጠዉ፤ የቤተሠብ አባል ሆነዉ ተለያይተዉ የቆዩ የሚገናኙበት፤ ከአከባቢዉ በተለያዩ ምክንያቶች ርቀዉ ያሉ በእሳት ማዉጭያዉ (በደመራው) ቀን በመገናኘት ናፍቆታቸዉን የሚወጡበት፤ የተጣላ የሚታረቅበት፤ ሀዘን ዉስጥ የነበረ ሐዘኑን የሚረሳበት፤ የተነፋፈቀ የሚገናኝበት፤ የትዳር ጓደኛ የሚመረጥበት ዓይነተኛ ጊዜ መሆኑ በዓሉን በብሔረሰቦቹ ልዩ በዓል ያደርገዋል፡፡

ከጋሞ ዞን ኮሚኒኬሽን ያገኘነው ፅሁፍ፤ ለበዓሉ በሚሆን መልኩ የቀረበ።

መልካም በዓል !

@tikvahethiopia
#ጊፋታ

የወላይታ ዘመን መለወጫ በዓል ጊፋታ!

የወላይታን ብሔር ከሀገራችንና ከደቡብ ክልል ብሔሮችና ብሔረሰቦች በተለየ መልኩ የሚገለጽባቸው በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ያሉት ሲሆን ከብሔሩ የማይዳስሱ ሀብቶች መካከል የወላይታ ዘመን መለወጫ በዓል #ጊፋታ አንዱ ነው፡፡

ጊፋታ በብሄሩ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የብሔሩ ማንነት መገለጫ የሆነ የአሮጌው ዓመት ማብቅያና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ የመሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡

ጊፋታ ማለት ባይራ(ታላቅ)፣ መጀመሪያ እንደ ማለት ሲሆን በሌላ በኩል ጊፋታ ማለት መሻገር ማለት ነው፡፡ ይህም ከአሮጌ ወደ አዲስ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገር የሚለውን ይገልጻል፡፡ የወላይታ ብሔር የራሱ የሆነ የዘመን መቁጠሪያ(ካሌንደር) ያለው ሲሆን በወላይታ የዘመን አቆጣጠር ጊፋታ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ስያሜ ነው፡፡

ወላይታዎች አስራ አንድ ወራት በስራ ካሳለፉ በኋላ የመጨረሻውን አንድ ወር ለበዓሉ ያውሉታል፡፡ 15 ቀን በበዓሉ ዝግጅት፣ አስራ አምስቱን ቀን ደግሞ በመዝናናትና በመጫወት ያሳልፋሉ፡፡

መስከረም ወር በገባ ከ14-20 መካከል በሚውለው እሁድ ዕለት አዲሱን ዓመት ይቀበሉታል፡፡ በየዓመቱ ከመስከረም 14-20 ባሉት ቀናት መካከል የሚውለው እሁድ እለት የአዲስ ዓመት ቀን ይሆናል፡፡ ስሙም ሹሃ ወጋ /የእርድ እሁድ/ ይባላል፡፡

ጊፋታ የይቅርታ፤ የፍቅር እና የሰላም በዓል ነው!

ምንጭ፦ የወላይታ ዞን ባህል፣ ቱሪዝም እና መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia