TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Debre_Birhan ማሳሰቢያ !

" ... በሌሊት አካባቢያቸውን የሚጠብቁ ሁሉ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ማክበር አለባቸው "- የደብረብርሃን ሰላምና ህዝብ ደህንነት ጽ/ ቤት

የደብረብርሃን ሰላምና ህዝብ ደህንነት ጽ/ ቤት በሌሊት አካባቢያቸውን የሚጠብቁ ሁሉ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ማክበር እንዳለባቸው አሳስቧል።

ጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ ፥ በወቅታዊ ሀገራዊ ችግር ምክንያት ነዋሪዎች ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ተቀናጅተው አካባቢያቸውን እየጠበቁ እንደሚገኙ አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ ህብረተሰቡ አካባቢውን በተራ በመጠበቅ ሰላሙን ማረጋገጥ መቻሉ መልካም እና በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር ቢሆንም አንዳንድ የሌሊት የጥበቃ ተረኞች የዜጎችን ሰብኣዊ መብት የጣሱ መኖራቸው መልካሙን ስራ አጉድፎታል ብለዋል፡፡

መስከረም 12 ቀን 2014 ዓ/ም በቀበሌ 07 ሌሊት አካባቢያቸውን ሲጠብቁ ከነበሩት ውስጥ አንድ ሰው በጥይት መምታቱን ጠቅሰው ድርጊቱን የፈጸመው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተደረገ መሆኑን አሳውቀዋል።

በቀጣይም ከህግ ጋር የሚጻረር ተግባር ሲፈጽሙ የሚገኙ ሲያጋጥሙ ለሚመለከተው አካል ማስረከብ ይገባል ያሉት ኃላፊው ህብረተሰቡ ለወጣው ህግ ተገዢ በመሆን ከምሽቱ 4 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ እንዲያቆም አሳስበዋል፡፡

#ANRSDebrbrihanCommunication

@tikvahethiopia
" በደቡብ ሱዳን ከ10 ክፍለ ግዛቶች፣ 9ኙ አስጊ በሆነ ከፍተኛ ግጭት ውስጥ ተውጠዋል" - ተመድ

በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የሰአብዊ መብት ኮሚሽን “አገሪቱ ለረጅም ጊዜ በከፍተኛ የሰብአዊ መብት ቀውስ እየተሰቃየች፣ ህዝቧም በድህነት፣ በአመጽና በደል ኡዙሪት ውስጥ ነው” ሲል አስጠነቀቀ።

ይህን አስመልከቶ የተጠናቀረው ሪፖርት ለመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንደሚለው በደቡብ ሱዳን ከሚገኙ 10 ክፍለ ግዛቶች፣ 9ኙ አስጊ በሆነ ከፍተኛ ግጭት ውስጥ ተውጠዋል፡፡

ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን ከተቀዳጀች 10 ዓመታት በኋላ፣ እኤአ 2013 ላይ የተጀመረው የእርስ በርስ ግጭት እንዲቆም፣ በርካታ የሰላም ስምምነቶች ቢደረጉም ፣ወደ ከፍተኛ ደረጃ የደረሱትን ግጭቶች ሊያቆሙ አልቻሉም፡፡

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የሆኑት ያስሚን ሱካበተለይ በዋረን እና ሌክስ ስቴትስ በሚባሉት ግዛቶች ያሉት ግጭቶች ልዩ ትኩረት የሚሹ ናቸው ብለዋል።

“በመጋቢትና ሀምሌ ወራት ውስጥ በዋረን እና ሌክስ ስቴትስ ውስጥ ህጻናትን ጨምሮ ከ56 ሰዎች በላይ ተረሽነዋል፡፡ እንዲህ ያሉት ህገወጥ ግድያዎች በገዢው ፓርቲ አባል በሆኑ አስተዳዳሪዎች የሚፈጸም ሲሆን በሌሎች ዘንድ በስፋት የተስፋፋ ሲሆን ብዙዎቹ በሰአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ናቸው፡፡”

ሪፖርቱ በግዴታ እንዲሰወሩ የተደረጉ፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከግጭት ጋርየተያያዙ ወሲባዊ ጥቃቶችና እንዲሁም ለውትድርና በግዴታ የሚመለመሉ ህጻናት በመላው አገሪቱ የሚታዩ ናቸው ብሏል፡፡

በስፋት የተሰራጨው ህገወጥትነትና ጥቃት የተባባሰ ሲሆን ለብዙዎች ሞትና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት ሆኗል፡፡

ያንብቡ : telegra.ph/UN-09-24

Credit : VOA

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 40 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 40 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 9,468 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,352 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 813 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#OROMIA : የኦሮሚያ ክልል አዲስ መንግስት ነገ ይመሰረታል።

ነገ መስከረም 15 ቀን 2014 ዓ.ም የጨፌ ኦሮሚያ ጉባኤውን የሚያካሄድ ሲሆን አዲሱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ይመሰረታል።

በነገው ጉባኤ ነባር የጨፌው አባላት ይሸኛሉ፤ አዲሶቹ ደግሞ ይተካሉ ፤ አዲሱ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ጨምሮ አዲስ የካቢኔ አባላት ይሰየማሉ።

@tikvahethiopia
የብቃት ምዘና ፈተና ውጤት ዛሬ አርብ ይፋ ሆኗል።

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ከነሀሴ 10 - 14/2013 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች ከዛሬ መስከረም 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ አሳውቋል።

በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ፦
- በስልክ ቁጥር 0118275936/37 በመደወል ወይም
- በኢሜይል [email protected] ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር እና የተማሩበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄያቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በሌላ በኩል ጤና ሚኒስቴር የቀጣዩ ፈተና ምዝገባ በቅርብ ቀናት የሚካሄድ መሆኑን አሳውቋል።

ምዝገባው ለአዲስም ሆነ ነባር ተመዛኞች ሙሉ ለሙሉ በonline የሚካሄድ ሲሆን ተመዛኞች ይህንን አውቀው ዝግጅት እንዲያደርጉም አሳስቧል።

የግል የትምህርት ተቋማት ተመዛኞች ለፈተናው ለመመዝገብ የትምህርት ማስረጃዎቻቸው ህጋዊነቱን ማረጋገጥ (Authenticate) ማስደረግ ይጠበቅባቸዋል የተባለ ሲሆን ከምዝገባው በፊት በዚህ መልክ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OROMIA : የኦሮሚያ ክልል አዲስ መንግስት ነገ ይመሰረታል። ነገ መስከረም 15 ቀን 2014 ዓ.ም የጨፌ ኦሮሚያ ጉባኤውን የሚያካሄድ ሲሆን አዲሱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ይመሰረታል። በነገው ጉባኤ ነባር የጨፌው አባላት ይሸኛሉ፤ አዲሶቹ ደግሞ ይተካሉ ፤ አዲሱ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ጨምሮ አዲስ የካቢኔ አባላት ይሰየማሉ። @tikvahethiopia
#Oromia : ጨፌ ኦሮሚያ በአባ ገዳዎች ምርቃት ጉባኤውን ጀምሯል።

ዛሬ አዲሱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ይመሰረታል።

ነባር የጨፌው አባላት ተሸኝተው በአዲሶቹ ይተካሉ ፤ አዲሱ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ጨምሮ አዲስ የካቢኔ አባላት ይሰየማሉ።

Photo Credit : ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
#Tigray #Afar #Amhara

UN OCHA በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ሁኔታው አሁንም መሻሻል እንዳላሳየ እና በአስከፊ ሁኔታ እንደቀጠለ ሪፖርት አድርጓል።

ጦርነቱ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች መስፋፋቱን ተከትሎ በሁለቱ ክልሎች ሰብዓዊ ችግሩ እየተባባሰ ነው ብሏል።

ወደ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ማስገቢያ መንገድ በሰመራ - አብአላ - መቐለ መስመር ብቻ በመሆኑ እርዳታ የማድረሱ እንቅስቃሴ በከባዱ የተገደበ መሆኑን ገልጾ የመንገዱ ፀጥታ የተረጋጋ ቢሆንም በቀጣይነት የሚፈጠረውን መተንበይ አይቻልም ብሏል።

ውጊው ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች መስፋፋቱ በሲቪሎች ላይ ያስከተለው የምግብ ችግር እና መፈናቀል እየተባባሰ መሆኑን አሳውቋል።

ሙሉ ሪፖርት : reports.unocha.org/en/country/ethiopia/

@tikvahethiopia
#ኢሬቻ #መስቀል #የመንግስት_ምስረታ !

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከመስቀል፣ ከኢሬቻ በዓላት እና ከመንግስት ምስረታ ስነ-ስርዓት በፊትና በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ የፀጥታ ችግሮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ፤ ችግር ቢከሰት እንኳን ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ጠንካራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን ይፋ አድርጓል።

ኮሚቴው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮምሽነር ጀኔራል የሚመራ ሲሆን ፦
- ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ፣
- ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፣
- ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣
-ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
- ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከተውጣጡ አመራሮች የተዋቀረ ነው።

@tikvahethiopia
* Hawassa

የሲዳማ ክልል መዲና ሀዋሳ ከተማ በዓለም ለ42ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ የሚከበረውን የቱሪዝም ቀን እያስተናገደች ትገኛለች።

በሲዳማ ክልል እየተካሄደ ባለው የቱሩዝም ቀን ላይ የፌዴራሉ እና የክልል ከፍተኛ ባለልስጣናት ፣ ባለድርሻ አካላት ተካፋይ እየሆኑ ነው ፤ ዛሬ መስከረም 15 ይጠናቀቃል።

በሌላ በኩል ፥ የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሴንትራል ሆቴልን መሥራች እና ባለቤት ለወይዘሮ አማረች ዘለቀ ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ልማት ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽዎ የዕውቅና ሰርተፍኬት ሰጥቷቸዋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba : ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

መሰከረም 16/2014 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የደመራ በዓል ተጀምሮ አስከሚጠናቀቅ ከዚህ በታች የተገለፁትን መንገዶች ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ ከአ/አ ፖሊስ ማሳሰቢያ ተላፍሏል።

የሚዘጉት መንገዶች ፦

• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባቢ፤
• ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ፤
• ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት፤
• ከፒያሣ አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቸርችር ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ፤
• ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፤
• ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ፤
• ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኢምግሬሽን የኋላ በር መግቢያ፤
• ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፤
• ከባሻ ወልዴ ችሎት በኦርማ ጋራዥ ወደፉል ውኋ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት ፤
• ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የመወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ
• ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ
• ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ ናቸው።

ስንት ሰዓት ነው የሚዘጋው ?

ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ሁሉ ዝግ ነው።

*** ሌላው ፦
ደመራው የሚደመርበት መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ስታዲዬም እንዲሁም ከሃራምቤ ሆቴል ወደ ሴንጅ ዮሴፍ የሚያቋርጠው መስቀለኛ መንገዱ ለበዓሉ በሚደረገው ዝግጅት ምክንያት ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ከሳሪስ እና ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ከባድ ተሸከርካሪዎች መንገዱ አጎና ሲኒማ ጋር የሚዘጋ ይሆናል፡፡

#ሼር ያድርጉት !

@tikvahethiopia
* ኒውዮርክ

የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ መከሩ።

በኒውዮርክ የተመድ ስብሰባ እየተካፈሉ የሚገኙት አቶ ደመቀ፥ ከሀገራት ባለስልጣናት እና ከተቋማት አመራሮች ጋር የሚያደርጉት የጎንዮሽ ምክክር የቀጠለ ሲሆን ትላንት ከአንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር መክረዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ ባደረገው መረጃ ዋና ፀሐፊው እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ውስጣዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

ዋና ፀሐፊው ወደ ሰላም የሚወስዱ እርምጃዎች እንዲኖሩ በድጋሚ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን የሰብአዊ ተደራሽነትን ይበልጥ ማመቻቸት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተመለከተ ዋና ፀሐፊው ውይይቱን እንደገና ማስጀመርን አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለአፍሪካ ህብረት የማሸማገል ጥረቶች ድጋፉን እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
#ደሴ

የኢትዮጵያ 🇪🇹 ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ደሴ ገቡ።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ደሴ የገቡት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደሴ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ወገኖችን ለመጎብኘት ነው።

የደሴ ከንቲባ አቶ አበበ ገ/መስቀል ፥ ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀው ህወሓት በአማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ተፈናቅለው ደሴ የሚገኙ 300 ሺህ ዜጎች እንዳሉ አሳውቀዋል።

የፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጉብኝትም ተፈናቃዮች ያሉበትን ወቅታዊ ሁኔታ በትክክል ለመረዳት እንደሆነ ገልፀዋል።

ከጉብኝታቸው በኋላም ለተፈናቃዮች ድጋፍ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከንቲባው አስታውቀዋል።

Photo Credit : ENA

@tikvahethiopia
#Tigray : ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (አይሲአርሲ) በትግራይ ክልል በሆስፒታሎች እና ሌሎች የጤና ተቋማት ውስጥ ለሚገኙ 15,000 የጤና ሰራተኞች እና ሕሙማን ለ2 ወራት የሚሆን የመሠረታዊ የምግብ አቅርቦቶችን ማሰራጨት መጀመሩን ዛሬ አስታውቋል።

አይሲአርሲ ፥ "ሕሙማን የሕክምና አገልግሎት ማግኘት እንዲቀጥሉ የሕክምና ሠራተኞችን መደገፍ አስፈላጊ ነው" ብሏል።

#ICRCEthiopia

@tikvahethiopia