TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
* እንዳትደናገጡ !

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ነገ መስከረም 1/ 2014 ዓ/ም የሚከበረውን የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ ምክንያት በማድረግ በዕለቱ ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ ለ21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ አስታውቋል።

ህብረተሰቡ ይህን አውቆ እንዳይደናገጥና የጸጥታ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
እንቁጣጣሽ ሎተሪ ወጣ !

እንቁጣጣሽ ሎተሪ ዛሬ አርብ ጷጉሜን 5 ቀን 2013 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፡፡

1ኛ. 20,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 0580856

2ኛ. 10,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 0470508

3ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 1973063

4ኛ. 3,000,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 0612715

5ኛ. 1,500,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 0816001

6ኛ. 750,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር 1963913

7ኛ. 300,000 ብር የሚያስገኘው የ7ኛ ዕጣ ቁጥር 0716025

8ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 20,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 37510

9ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 10,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 79593

10ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 5,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 27663

11ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 2,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 8326

12ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 2843

13ኛ. 2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 022

14ኛ. 20,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 300 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 42

15ኛ. 200,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 100 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር (የማስተዛዘኛ ዕጣ) ደግሞ 2 ቁጥር በመሆን ወጥቷል፡፡

Credit : National Lottery Administration

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

በኮቪድ-19 ሳቢያ በአንድ ቀን የ27 ዜጎች ህይወት አለፈ። በየዕለቱ በሽታው የሚገድላቸው ሰዎች ቁጥር እይሻቀበ ነው።

ዛሬ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 27 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,177 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,334 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 753 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ በመሆኑ መላው የቲክቫህ አባላት ጥንቃቄያችሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ እንድታጠነክሩ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ባይደን "እንኳን ለአዲሱ ዓመት / እንቁጣጣሽ/ አደረሳችሁ" አሉ !

(ቢቢሲ)

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ባለቤታቸው ጂል ባይደን ኢትዮጵያውያንን እና ኤርትራውያንን እንኳን ለአዲስ ዓመት አደረሳችሁ ሲሉ የመልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም ባልተለመደ ሁኔታ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በራሳቸውና በባለቤታቸው ስም ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን እንዲሁም ከእነዚሁ አገራት የዘር ሐረጋቸው ለሚመዘዝ በመቶሺህዎች ለሚቆጠሩ አሜሪካውያን የአዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በዚሁ መልዕክታቸው ላይ ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ስለሚፈጸሙ ጥቃቶች ሪፖርቶች በእጅጉ እንዳሳሳባቸው ገልጸው፤ አስተዳደራቸው በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ከአጋሮቻችን ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ፕሬዝዳንቱ ጨምረውም ሰላምን ማምጣት ቀላል እንዳልሆነ ነገር ግን በውይይት ሊጀመር እንደሚችል በመግለጽ “ታላቋና ባለብዝሃነቷ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የገጠማትን መከፋፈል እንደምትወጣውና በድርድር ላይ በተመሰረተ የተኩስ አቁም በማድረግ እየተካሄደ ያለውን ግጭት እንደምትፈታው እንምናለን” ብለዋል።

በመልዕክታቸው ላይ በአማርኛ “መልካም አዲስ ዓመት” በማለት በዓሉን ለሚያከብሩ በሙሉ የተመኙት ፕሬዝዳንት ባይደን “አዲሱ ዓመት በኢትዮጵያ፣ በኤርትራና በዓለም ዙሪያ ላሉ ቤተሰቦችና ማኅበረሰቦች ሰላም፣ እርቅ እና ፈውስ የሚመጣበት እንዲሆን እጸልያለሁ” ብለዋል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት !

አዲሱ ዓመት ለ30 ዓመታት ኢትዮጵያን የተጣባትን ፈተና” ተገላግለን “አዲስ መንግሥት የምንመሠርትበት እንደሚሆን እምነቴ ነው” ብለዋል።

አዲሱ ዓመት በወሳኝ ሀገራዊ ፈተና እና ተስፋ መካከል ሆኖ የሚከበር መሆኑን ገልጸው፤ ይህ ሲሆን የመጀመሪያም የመጨረሻም እንዳይደለ ጠቁመዌ።

ጠ/ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የገጠሟትን ፈተናዎች እንደየ አመጣጣቸው “አሸንፋ” ሺ ዘመናትን በነጻነት መኖሯንም አስታውሰዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ፥"ይህ አዲሱ ዓመት ለ30 ዓመታት ኢትዮጵያን የተጣባትን ፈተና የምንገላገልበት፣ አዲስ መንግሥት የምንመሠርትበት፣ ከደረሰብን ፈተና የምናገግምበትና ፊታችንን ወደ ኢትዮጵያ ብልጽግና የምናዞርበት እንደሚሆን እምነቴ ነው” ያሉ ሲሆን “አዲሱ ዓመት ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን የሚጸናበት፣ ዴሞክራሲያዊ ዕሴቶቻችን የሚጎለብቱበት፣ የጀመርነው ሪፎርም መልክ የሚይዝበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።

* የዶ/ር ዐቢይ ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
መልካም አዲስ ዓመት!

ውድ በዚህ ቤት #ሰውነትን አስቀድማችሁ የተሰባሰባችሁ የሀገራችን ልጆች እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

ሁላችን እንደምናስታውሰው 2013 በገባ በጥቂት ወራት በሀገራችን ጦርነት ተቀስቅሶ ደስታ የተሞላ፣ ሰላም የሰፈነበት፣ ብዙ እቅዶቻችን የምናሳካበት ብለን ያሰብነው ዓመት በጦርነት፣ ሰቆቃ፣ በዜጎች ሞት፣ በረሃብ፣ በጭንቀት፣በደህንነት ስጋት ተሞልቶ ተሰናብተነዋል።

በ2013 በጦርነት ምክንያት ቁጥራቸውን የማናውቃቸው ነገር ግን እጅግ በርካታ ዜጎቻችን ረግፈዋል፣ አንዳዶች እንደወጡ ቀርተዋል፣ ባላሰቡበት ተጨፍጭፈዋል፣ ሺዎች አካላቸው ጎድሏል፤ሴት እህቶቻችን ተደፍረዋል ተጠቅተዋል ሚሊዮኖች ተርበዋል ተጠምተዋል፣ሚሊዮኖች ከገዛ ቀያቸው ተፈናቅለው ተሰደዋል።

በትግራይ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያ (ወለጋ)፣ ቤ/ጉሙዝ...ምንም ከጦርነት ጋር ንክኪ የሌላቸው፣ ስለሚሆነው ነገር ፍፅሞ የማያውቁ ንፁሃን ዜጎቻችን፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ህፃናት ከነተስፋቸው አሸልበዋል፤በወጡበት ቀርተዋል፤እናቶች ልጆቻቸውን አንጠልጥለው ተሰደዋል፣አባቶች አልቅሰዋል፣አንብተዋል።

በዓመቱ ወንድም እህቶቻችሁን ያጣችሁ፣ የምትወዱትን የተነጠቃችሁ፣ እናት አባቶች ፅናቱን ብርታቱን ይስጣችሁ። አሁንም በችግር ላይ ላሉ ወገኖቻችን ፈጣሪ ይድረስላቸው።

እንደአንድ ሀገር ዜጋ ይህን አዲስ አመት የምንቀበለው በፍፁም የስሜት መረበሽ ውስጥ ቢሆንም ፈጣሪ ሁሉን እንዲያቀናው እንማፀናለን።

ዓመቱ የሰላም፣ግጭትና ሰቆቃ የማንሰማትበት፣ ከጎናችን ማንም የማይጎድልበት እንዲሆን እንመኛለን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤታችን፤ መሰብሰቢያችን ነው፤ በአዲሱ ዓመት ቤተሰባዊ ቅርርባችን ሚጠናከርባቸውን ሀሳቦች ለእናተ እንደምናቀርብ ከወዲሁ ቃል እንገባለን።

❤️ኢትዮጵያ እናታችን ተከብራ ትኑርልን❤️

@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ሀገራችን 🇪🇹 አዲሱን 2014 ዓ/ም አንድ ብላ ጀምራለች።

እንሆ 2013ትን ተሰናብተነው አዲሱን ዓመት ጀምረናል። የአዲስ ዓመት በዓልም በሀገሪቱ እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉን ስናከብር ከተቸገሩት፣ ካጡት ወገኖቻችን ጋር ማዕድ በማጋራት ሊሆን ይገባል።

የጦርነት ቀጠና በሆኑ አካባቢዎች አቅራቢያ የምትገኙ ምናልባትንም ይህንን መልዕክት ኔትዎርክ አግኝታችሁ የምታነቡ የቲክቫህ አባላት ከቀያቸው ተሰደው፣ የሚወዱትን ተነጥቀው በሀዘን ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን በመደገፍ፣ አብሮ በመብላት፣ በማፅናናት፣ ተስፋን በመስጠት እንድታከብሩ እንማፀናለን።

በሌሎች የሀገራችን ከተሞች የምትገኙ አባላት ደግሞ በጦርነት ምክንያት በችግር ላይ የወደቁ ወገኖችን በማሰብ፣ ስለሀገራችን ፍቅር እና ሰላም በመፀለይ ፣ በአካባቢያችሁ ከተቸገሩት ጋር ማዕድን በማጋራት ይህንን በዓል እንድታከብሩት በትህትና ዝቅ ብለን እንጠይቃለን።

የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ ፣ የስኬት ዓመት ይሁንልን!

Photo Credit : Social Media

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

በኮቪድ-19 ሳቢያ በአንድ ቀን የ23 ዜጎች ህይወት አልፏል።

ዛሬ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 23 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,169 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 845 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 733 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ በመሆኑ መላው የቲክቫህ አባላት ጥንቃቄያችሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ እንድታጠነክሩ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እጅግ ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግበት እስር ቤት ያመለጡት ፍልስጥኤማውያን … 6 ፍልስጤማውያን እስረኞች ጠንካራ ጥበቃ ከሚደረግለት እስር ቤት ካመለጡ በኋላ እስረኞቹን አድኖ ለመያዝ እስራኤል ኦፕሬሽን ጀመረች። ከ6ቱ 5ቱ የእድሜ ልክ እስር የተፈረደባቸው ናቸው:: ከእስር ቤቱ ያመለጡት እስረኞች ለወራት ያህል የእስር ቤት ክፍላቸውን ውጪ ካለ መንገድ ጋር የሚያገናኝ ዋሻ ለመሥራት ሲቆፍሩ ቆይተዋል ተብሏል።…
ፎቶ : ከጊልቦዋ እስር ቤት ካመለጡት ፍልስጥኤማውያን 4ቱ ተይዘዋል።

የእስራኤል የፀጥታ ኃይሎች በከፍተኛ ሁኔታ ጥበቃ ከሚደረግለት የእስራኤል እስር ቤት ጊልቦዋ ካመለጡት 6 ፍልስጤማውያን መካከል 4ቱን መልሰው ይዘዋቸዋል።

ከተያዙት ፍልስጤማውያን መካከል ሁለቱ የተገኙት የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ነው። ሌሎች ሁለቱ ደግሞ ናዝሬት ከተማ አካባቢ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ስድስቱ ፍልስጤማውያን ባለፈው ሰኞ ከእስር ቤት ካመለጡ በኋላ በፖሊሶች ሲፈለጉ ነበር።

ፍልስጥኤማውያኑ በሰሜን እስራኤል ከሚገኘው ጊልቦዋ እስር ቤት ያመለጡት በማንኪያ መሬት ሰርስረው ነበር። እስረኞቹ ካመለጡ በኃላ በርካቶች በትንግርት ጉዳዩን ሲቀባበሉት፤ በጋዛ ምድርም ደስታ ሆኖ ነበር።

እስራኤል የእስረኞቹ ማምለጥ ቢያስደነግጣትም ፤ የፍልስጤም ታጣቂዎች ግን በተፈጠረው ነገር ኩራት ተሰምቷቸዋል።

እንደ ቢቢሲ መረጃ ፥ ፍልስጤማውያን ከእሰራኤል ከእስር ቤት በዚህ መንገድ ካመለጡ 20 ዓመታት ተቆጥረዋል።

@tikvahethiopia
#Tigray : ኢሰመኮ በትግራይ ክልል የተነሳው ግጭት ወደ አጎራባች ክልሎች መስፋፋት የፈጠረው የፀጥታ ችግር በሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳደረ መሆኑ እንደሚገነዘብ ገልጾ በክልሉ ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል ብሏል።

በአንዳንድ የክልሉ ቦታዎች የተወሰነ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት የተመለሰና፤አንዳንድ የባንክ ቅርጫፎች የኔትዎርክ ግንኙነት ባይኖርም በአካባቢ አስተዳዳሪዎች ትዕዛዝ መሰረት መጠነኛ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን መረዳት እንደቻለ ኢሰመኮ ገልጿል።

ነገር ግን በክልሉ ከፍተኛ የምግብ እና የጥሬ ገንዘብ እጥረት መከሰቱ፣የምግብና ሌሎች መሰረታዊ አቅርቦቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን እንዲሁም የነዳጅ አቅርቦት እና የትራንስፖርት አገልግሎት ውስን ስለሆነ ሰዎች ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ መቸገራቸውን ለማወቅ እንደቻለ አስታውቋል።

ስለሆነም ጉዳዮ የሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ ለሲቪል ነዋሪዎች የሚቀርበው ሰብዓዊ እርዳታ እንዳይሰናቀፍ እና እንዲሻሻል ተገቢውን ሁሉ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኢሰመኮ ጠይቋል።

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ ባለፉት 2 ወራት በአዲስ አበባ በፀጥታ ኃይሎች በወንጀል ጉዳይ ተጠርጥረዋል በሚል ከተያዙ የትግራይ ተወላጆች እና የንግድ ቤቶች መዘጋት ጋር በተያያዘ በሚደርሰው በርካታ አቤቱታ ተመስርቶ በተለይ በ2 ክ/ከተሞች ትኩረት በማድረክ ክትትል ማድረጉን አሳውቋል።

ድርጅቶቹ የተዘጉት በደንብ መተላለፍና በወንጀል በመጠርጠር በሚል አዲስ በተቋመውና የህገወጥ ንግድ እና ኮንትሮባንድ ክትትል እና ቁጥጥር ግብረኃይል ውሳኔ ቢሆንም በርካታ የድርጅት ባለቤቶች በተጠረጠሩበት ወንጀል ወይም ደንብ መተላለፍ ጉዳይ ውሳኔ ስላልተሰጣቸው ድርጅቶቹ ለረጅም ጊዜ ተዘግተው እንዲቆዩ ተደርጓል።

ያንብቡ : telegra.ph/EHRC-09-11

@tikvahethiopia
ታላቁ አሊምና ፈቂህ ሐጅ ሙሐመድ አልሳፊ አረፉ።

ሸይኽ ሙሐመድ አልሳፊ ከሐጅ ሙሐመድ ሳኒ ሀቢብ ጋር በመሆን መጅሊስን ከመሰረቱት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሊቀመንበር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ለኢስላም ሲባል በደርግ መንግስት ታስረው ከፍተኛ የሆነ ግርፋትና ድብደባ የተፈፀመባቸውና በዚህም ምክንያት የመናገር ልሳናቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ሸይኽ ሙሐመድ አልሳፊ የቀብር ስነ ስርአት ትላልቅ መሻኢኾች በተገኙበት ዛሬ መስከረም 2 ኮልፌ በሚገኘው መቃብር ከዙሁር በኋላ ይፈፀማል።

Credit : Ethiopia Islamic Affairs Supreme Council

@tikvahethiopia