#HappeningNow
የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የሁርሶ የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ምልምል አባላትን እያስመረቀ ይገኛል።
በሀገር መከላከያ ሚኒሰቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ዛሬ እያስመረቀ የሚገኘው ሶስተኛው ዙር በመሠረታዊ ወታደርነት ያሰለጠናቸውን ምልምል አባላትን ነው።
በምርቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ እንዲሁም ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትእ አቶ ደመቀ መኮንን እንደሚገኙ ኢብኮ ዘግቧል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD #FDREDefenseForce ሀገር መከላከያ ሰራዊት፥ ኢትዮጵያ እየገነባች ያለውን ግዙፉን የታላቁ ሕዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረውን የህወሓት ቅጥረኛ ሃይል ደመሰስኩኝ አለ። የግድቡን ግንባታ ለማደናቀፍ ተልዕኮ ውስደው የተንቀሳቀሱና ሰራዊቱ የማያዳግም እርምጃ የወሰደባቸው ኃይሎች (የተገደሉ) በቁጥር 50 ሲሆኑ ፤ ከ70 በላይ የሚሆኑት…
ሱዳን ምላሽ ሰጠች...
ሱዳን በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል በኩል የኢትዮጵያ መንግስትን እየተዋጉ ለሚገኙት የትግራይ አማፅያን ድጋፍ ታደርጋለች መባሉን አጥብቃ አስተባበለች።
ትላንት ሀገር መከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያ እየገነባች ያለውን ግዙፉን የታላቁ ሕዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረውን የህወሓት ቅጥረኛ ሃይል መደምሰሱን (50 መግደሉን፤ 70 ደግሞ ማቁሰሉን) ሪፖርት ማድረጉ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር አል-ታሂር አቡ ሀጃ "መሰረተ ቢስ ውንጀላ" ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።
አቡ ሃጃ ፥ "ሱዳን እና ሰራዊቷ በአጎራባች ኢትዮጵያ ወይም በሌሎች ሀገሮችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቀ አይገቡም" ሲሉ ተናግረዋል።
አክለው፤ "ይህ መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝብ የመብት ጥሰቶች በመቀጠላቸው ምክንያት የኢትዮጵያ አገዛዝ የገጠመውን ከባድ እውነታ ያንፀባርቃል” ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ሱዳን ለአማፅያን የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገችን እንደሆነ ሲገልፅ ነበር።
በትላንትናው ዕለት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከገለፀው በተጨማሪ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ፤ የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የታጣቂዎች እንቅስቃሴ #የሱዳን_እጅ በጣም ረጅም መሆኑን ገልጿል።
የክልሉ ም/ኮሚሽነር "በሱዳን አካባቢ የነበረው የፀረ ሰላም እንቅስቃሴ ከፍተኛ ነው፤ በመሳሪያ በሃሳብ፣ እዛ አካባቢ ያሉ ወጣቶችን መልምሎ ሱዳን አስቀምጦ የሚደግፉበትና ሽፋን የሚሰጡበት ሁኔታ አለ" ሲሉ አስረድተዋል።
ከሰሞኑን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ፤ በካማሺ ዞን ፤ በሎ ጅጋንፎይ ወረዳ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ከ50 በላይ ሴቶች በጅምላ በግፍ መገደላቸውን የክልሉ ፖሊስ ሪፖርት ማድረጉ፤ ለጥቃቱ ደግሞ "ጉህዴን"ን ተጠያቂ ማድረጉ አይዘነጋም።

ICRC በደሴ ድጋፍ እያደረገ ነው።
ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ግጭት ከቆቦ፣ ወልዲያ፣ መርሳ እና ላሊበላ ተፈናቅለው በደሴ ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ 36,000 ሰዎች መሰረታዊ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁስ ፣ የንጽህና መጠበቂያዎችን እና መጠለያን ያካተተ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
#ICRCEthiopia

#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ 108 የመገበያያ ቦታዎችን እና ከ250 ሺህ ኩንታል በላይ ተጨማሪ የግብርና ምርት መዘጋጀቱን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አሳወቁ።
ምክትል ከንቲባዋ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስራ የጀመሩት መሸጫዎቹ በከተማዋ የሚስተዋለዉን የኑሮ ዉድነት በማረጋጋት በተለይ የግብርና ውጤት የሆኑ የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን እንዲሁም እንደ እንቁላል ያሉ የእንስሳ ተዋጽኦ አቅርቦትን ይበጥል በማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።
ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ፥ በከተማዋ 56 የቁም እንሰሳት መገበያያ እንዲሁም 52 የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫዎች በሁሉም ክፍለከተሞች ስራ መጀመራቸውን ገልፀው ፤ መሸጫ ማዕከላቱ ለሸማቹ ህብረተሰብ ምርት በቀጥታ ከአርሶ አደሩ ማሳ ከማቅረባቸው በተጨማሪ ምርቶቻቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረባቸው ተመራጭ ያደርጋቸዋል ሲሉ አክለዋል።

#HijraBank ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ የሆነው ሂጅራ ባንክ ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 29 ቀን 2013 የመክፈቻ ፕሮግራሙን እንደሚያካሂድ ታውቋል። ባንኩ በዚህ የመክፈቻ ፕሮግራም የመጀመሪያውን ኦሎምፒያ-ነጃሺ ቅርንጫፍ የሚከፍት ሲሆን በተጨማሪም በዚሁ የመጀመሪያው ሳምንት በተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባና በተለያዩ የክልል ከተሞች 11 ቅርንጫፎቹን እንደሚከፍት ሪፖርት አድርጓል። በሌላ በኩል ሂጅራ ባንክ…
#HijraBank
ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ የሆነው ሂጅራ ባንክ ዛሬ የመክፈቻ ፕሮግራሙን አካሄደ።
ባንኩ በዛሬው የመክፈቻ ፕሮግራም የመጀመሪያውን ኦሎምፒያ - ነጃሺ ቅርንጫፍ የከፈተ ሲሆን በቀጣይ በተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች 11 ቅርንጫፎቹን ይከፍታል።
Photo Credit : Hijra Bank

Congratulations !
በዛሬው ዕለት የተለያዩ የመንግስት እንዲሁም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል።
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
- ሠመራ ዩኒቨርሲቲ
- ሚዛን ቴፒ (ቴፒ ካንፓስ) ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻቸውን ዛሬ ካስመረቁ ተቋማት መካከል ይጠቀሳሉ።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮችን በCARD እገዛ በሚንቀሳቀሰው የቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገፅ መከታተል ይቻላል 👉 t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h
@tikvahuniversity

ድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። “ተማር ልጄ” በሚለው ዘመን ተሻጋሪ ዘፈኑ የብዙዎችን ቀልብ የማረከው ድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ነሐሴ 27፣2013 እኩለ ሌሊት በድንገት ማረፉ ነው የታወቀው። "ተማር ልጄ ሌት ፀሀይ ነው ላልተማረ ሰው ግን ቀኑ ጨለማ ነው..." እያለ ሚሊየኖችን በዜማው መክሯል። አንጋፋዉ ሙዚቀኛ አለማየሁ እሸቴ በሚጫወታቸው የሙዚቃ ስራዎቹ 'ኤልቪስ…
የድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ሥርዓተ ቀብር መቼ ይፈፀማል ?
የድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ሥርዓተ ቀብር የፊታችን ማክሰኞ ጳጉሜን 2 ቀን 2013 በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም የአርቲስቱ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ አስታውቋል።
የአርቲስቱ የአስክሬን ሽኝት በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን መገለፁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
አርቲስት አለማየሁ እሸቴ ከትናንት በስቲያ ነሐሴ 27 ቀን 2013 ባደረበት የልብ ሕመም በ80 ዓመቱ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል፡፡

#FDREDefenseForce
የኢትዮጵያ ጦር ዛሬ በሰጠው መግለጫ በጄነራል ምግበይ ይመራል ያለውን " አርሚ 1 " የተባለ ኃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን በይፋ አሳወቀ።
የዛሬውን መግለጫ የሰጡት የመከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ ሲሆኑ የኢትዮጵያ ሰራዊትን ግዳጅ አፈጻጸምና ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው ህወሓት ህፃናትን አሰልፎ በአማራ ክልል ወረራ መፈፀሙን ያነሱት ሌ/ጄነራል ባጫ የቡድኑ ፍላጎት ኢትዮጵያ የምትባልን ሀገር መበታተን ነው ብለዋል።
ህወሓት ስልጠና ያልወሰዱ ህፃናትን ወደ ጦርነት በመማገድ ላይ ነው ሲሉም አክለዋል።
ሌ/ጄነራሉ በመግለጫቸው ፥ ህወሓት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶችን አሰልፎ በ4 አርሚ ራሱን በማደራጀት በአማራ ክልል የሚያደርገውን ወረራ እንደቀጠለ ጠቁመዋል።
በ4 አርሚዎች ካደራጃቸው ኃይሎች መካከል አንደኛው በጀነራል ምግበይ የሚመራ ሲሆን ይህ ኃይል አርሚ 1 ተብሎ የሚጠራ እንደሆነ አስረድተዋል።
ሌ/ጄነራል ባጫ ፥ ይኸው ኃይል በሁመራ አካባቢ አደርቃይ እና ማይጠብሪ አካባቢ ደባርቅንና ዳባትን በመቁረጥ ጎንደርን በመያዝ ከዚያ በኋላ ሁመራን ነፃ ለማድረግ ቢንቀሳቀስም ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል ብለዋል።
በ3 ክፍለ ጦሮች የተደራጀው ይህ የአሸባሪ ኃይል በእያንዳንዱ ክፍለ ጦር ስር ሶስት ኮሮችን ያቀፈ ሲሆን ሰሞኑን በተደረገ ውጊያ ከ5 ሺ 600 በላይ ሙት ከ2 ሺ 300 በላይ ደግሞ ቁስለኛ ሲሆኑ ፣ 2 ሺ አባላቱ ተማርከው ቀሪዎቹም ተበታትነውበታል።
በዚህም ህወሓት ወደሱዳን ለመውጣት ያቀደው ሙከራ ሳይሳካለት ቀርቷል ፥ ሙሉ በሙሉም ተዘግቶበታል ሲሉ ተናግረዋል።
More : telegra.ph/FDRE-Defense-Force-09-04