#ALERT🚨
ሶስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ተደሰ ገለጹ።
ዶክተር ሊያ በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 5 ሺህ 547 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡
በአንድ ቀን ውስጥ ከ1ሺህ በላይ ሰዎች መያዛቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ÷ የወረርሽኙ መጠን ከዚህ በፊት ካለው በእጅጉ መጨመሩን ተናግረዋል።
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአሁኑ ሰአት ቫይረሱ የሚገኝበት ሰው ቁጥር ምጣኔ በእጅጉ መጨመሩ የሚያሳየው ሶስተኛው የኮቪድ 19 መረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
ማህበረሰቡም ከዚህ በፊት የሚያደርገውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሚኒስትሯ አሳስበዋል። #ኤፍቢሲ
@tikvahethiopia

#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ፥ "የዳቦ ዋጋን ተመን ለማውጣት የሚፈቅድ አሰራር የለንም" አለ።
ቢሮ ይህን ያለው ለአሀዱ ኤፍ ኤም 94.3 ሬድዮ ጣቢያ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ሚኤሳ በሰጡት ቃል ፥ በመዲናዋ በርካታ ነዋሪዎች የዳቦ ዋጋ በእጅጉ መጨመሩን እንዲሁም የዳቦው መጠንና ዋጋው እንደማይመጣጠን ተደጋጋሚ ቅሬታ ያቀርባሉ ብለዋል።
በመዲናዋ ያሉ ከ 2 ሺህ በላይ ዳቦ ቤቶች ካለፈው 1 አመት ወዲህ ከንግድ ቢሮው ጋር የነበራቸውን ትስስር ያቋረጡ በመሆኑ አሁን ላይ ቢሮው የዋጋ ተመንን ለማውጣት የሚፈቅድ አሰራር እንደሌለው ተናግረዋል፡፡
መንግስት የስንዴ ድጎማውን ማቋረጡን ተከትሎም በመዲናዋ ያሉ ከ 2ሺ በላይ ዳቦ ቤቶች ትስስራቸውን ማቋረጣቸውንም አስረድተዋል፡፡
አቶ ዳንኤል ፥ "ምንም እንኳን በርካታ የመዲናዋ ነዋሪዎች ቅሬታ ቢያቀርቡም አሁን ባለው የቢሮው አሰራር ዳቦ ቤቶቹ ባስቀመጡት የዳቦ ግራም እና ዋጋ በትክክል እየሸጡ መሆን አለመሆኑን ቁጥጥር ይደረጋል እንጂ ዋጋ በመተመን በገበያው ጣልቃ መግባት አይቻልም" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አክለው በተያዘው አመት ባስቀመጡት የዳቦ ግራም መጠን ዋጋ ሲሸጡ ያልተገኙ ወደ 24 የሚጠጉ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡
መረጃው የአሀዱ ኤፍ ኤም 94.3 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

#አደይ
ልብ አንጠልጣዩ የቤተሰብ ድራማ ምዕራፍ 2
ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ላይ በመታየት ላይ ይገኛል:
የሳምንቱን 5 ተከታታይ ክፍሎች እሁድ ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በአቦል ቻናል (146) ይመልከቱ!
#DStvየራሳችን
የዲኤስቲቪን ቤተሰብ ይቀላቀሉ!
https://bit.ly/3D2O1t4

TIKVAH-ETHIOPIA
"...ጦሩ በፍጥነት አብዬን ለቆ እንዲወጣ እንፈልጋለን" - መሬም አልሳዲግ አልመሀዲ ዛሬ ሱዳን በአብዬ ግዛት የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስካባሪ ኃይል ከቦታው ለቆ እንዲወጣ ተመድን መጠየቋን በይፋ አስታውቃለች፡፡ ሱዳን ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰቸው በኪንሻሳ የተካሄደው የግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በተመድ ስር በመሆን በሱዳን እና…
#SUDAN
በአብዬ ግዛት የተሰማራው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣ ያቀረበችውን ጥያቄ ተመድ እንደተቀበላት ሱዳን አስታወቀች፡፡
የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት መርያም አል ሳዲቅ አል መህዲ ከተመድ ዋና ጸሃፊ የምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ ፓርፊት አንያንጋ ጋር ትናንት ሰኞ ምሽት የበይነ መረብ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ የድርጅቱ የሰላም አስከባሪ ዋና ኃላፊ ዦን ፔሬ ላክሮይ እንዲሁም የኦፕሬሽን ዋና ኃላፊ አቱል ካሪ ተካፍለዋል፡፡
ውይይቱ በዋናነት በአብዬ ግዛት ስለተሰማራው የተመድ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡
የጸጥታ ኃይሉ አካል ሆኖ በስፍራው ሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር በሱዳን ጥያቄ በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ውስጥ ለቆ እንዲወጣ ስምምነት ስለተደረሰባቸው ሁኔታዎች በውይይቱ መነሳቱንም ነው የሃገሪቱ ዜና አገልግሎት (ሱና) የዘገበው፡፡
ተመድ የሱዳንን ሁኔታ ተረድቶ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር ወጥቶ በሌላ ይተካ የሚለውን ጥያቄ በመቀበሉ ያመሰገኑት መርያም አል ሳዲቅ ሃገራቸው ከደቡብ ሱዳን ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደምትሰራ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር በቶሎ ሊወጣ የሚችልበትን የተቀላጠፈ ሁኔታ ለማመቻቸትም እና ለተተኪው አቀባበል ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡
ሱዳን በጋራ የድንበር ጉዳዮች ላይ ያሉ ጋሬጣዎችን በማጽዳት የራሷን ሚና እንደምትጫወትም ነው ሚኒስትሯ የገለጹት፡፡
በአሀኑ ወቅት ከ3 ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሀይል በአብዬ ግዛት እንዳለ የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት ያስረዳል።
ደቡብ ሱዳን ከሱዳን በህዝበ ውሳኔ ነጻ አገር ለመመስረት መወሰኗን ተከትሎ ነበር የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሀይል ወደ አብዬ ግዛት የተሰማራው።
(አል-ዓይን ኒውስ)

ችሎት !
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በዕግድ ላይ የሚገኘው የዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ አስተዳዳሪ እንዲሾም ውሳኔ ሰጠ፡፡
ዓቃቢ ህግ በአ/አ ከተማ የሚገኘው የዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ የማይቀሳቀስ ንብረት ኪራይ ለህውሐት ቡድን ለሽብር ተግባር እየዋለነው ብሎ ንብረቱን ማሳገዱ ይታወሳል፡፡
ይህ የታገደው የዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ የማይቀሳቀስ ንብረትን የሚያስተዳድር አካል ሊሾም ይገባል ሲል ዓቃቤ ህግ መከራከሪያ ነጥብ አንስቶ ተከራክሮ የነበረ ሲሆን በዶ/ር አዲስ አሌም ባሌማ በኩል ደግሞ የታገደው ንብረቴ ቤተሰቦቼ የሚተዳደሩበት በመሆኑ መተዳደር ያለበት በቤተሰቦቼ ነው ሲሉ መከራከሪያ ነጥብ አንስተው ተከራክረው ነበር፡፡
ክርክሩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱ ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ ንብረቴን ቤተሰቦቼ ናቸው ማስተዳደር ያለባቸው ሲሉ ያቀረቡትን መከራከሪያ ነጥብን ውድቅ አድርጎታል፡፡
ንብረቱን የሚያስተዳድር ሌላ አስተዳዳሪ አካል እንዲሾም ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
የመረጃ ባለቤት ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

#MinistryofPeace
የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ ዶክተር አኔቴ ዌበር ጋር ተወያይተዋል።
በውይይየታቸው ወ/ሮ ሙፈሪያት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ልማት በተለያዩ መስኮች እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍ አመስግነዋል።
ዶ/ር አኔቴ ዌበር በበኩላቸው፥የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለረጅም ዘመናት የቆየውን መልካም የዲፕሎማሲያዊ እና የልማት ትብብር ለመቀጠል ያለውን ጠንካራ ፍላጎት መግለጻቸውን የሰላም ሚኒስቴር አሳውቋል።

ከባህር ዳር ተነስቶ አዲስ አበባ ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ።
ከባህር ዳር ተነስቶ አዲስ አበባ ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ።
ሱሉልታ ከተማ በቁጥጥር ስር የዋለው መሳሪያ 83 ትንሿ ሽጉጥ፣ 199 ኤም ፎርቲን ጥይት እና 10 ሺህ 865 የሽጉጥ ጥይት መሆኑ ታውቋል።
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና አዲስ አበባ ፖሊስ በጋራ ባደረጉት የተቀናጀ ክትትል ተጠርጣሪ የሆኑት ሹፌሩና ረዳቱ ተይዘዋል።
#ኢፕድ

''ቱኒዚያ በድጋሜ ለተባበሩት የፀጥታው ምክር ቤት ለግብጽ ተገቢ ያልሆነ ድጋፍ ለማድረግ እየተዘጋጀች ነው'' - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
ቱኒዚያ ድጋሚ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የግብፅን ሀሳብ ብቻ የሚደግፍ የውሳኔ ሀሳብ ለማቅረብ እየተዘጋጀች በመሆኑ አፍራሽ አካሔዷን ለመቀልበስ የላይኛው የናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት በጋር መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ይህን ያሉት ከላይኛው የናይል ተፋሰስ አባል ሐገራት አምባሳደሮች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።
የላይኛው ተፋሰስ አገራት አምባሳደሮችም በበኩላቸው በቀረቡት ሃሳብ ላይ በመንተራስ ድንበር ተሻጋሪ ሃብቶችን ለጋራ ልማት ለማዋል የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግ እንዲሁም የአፍሪካን ጉዳይ በአፍሪካዊያን መፍታት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
ቱኒዚያ ለተባበሩት የፀጥታው ምክር ቤት ለግብጽ ተገቢ ያልሆነ ድጋፍ ለማድረግ ያቀረበችው የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ ቢደረግባትም በድጋሚ ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጓን አንስተው፣ ይህ ውሳኔ ቢወሰን የሁሉም የላኛው ተፋሰስ አገራት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሊያስገባ እንደሚችልና ይህን ሃሳብ ለመቀልበስ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል፡፡
አምባሳደር ሬድዋን የቱኒዚያ አካሄድ በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን የሶስትዮሽ ድርድር ጥረት የሚያደናቅፍ መሆኑን ገልጸው፣ አገራቱ ኒውዮርክ ለሚገኙት ሚሲዮኖቻቸው ይህንኑ እንዲገልጹላቸው ጠይቀዋል።
መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ነው።

#iCog
የኮምፒዩተር ዝንባሌ ያላቸው ልጆች የክረምቱን ጊዜ ይበልጥ እንዲጠቀሙት ይመከራል።
መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀት በዛሬው የዲጂታል ዘመን መሰረት መጣል ያለበት ገና ከልጅነት እንደሆነ ይታመናል። ለዚህ ደግሞ በዘርፉ ሞያዊ ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት ሚናቸው ቀላል አይደለም።
ወደፊት የተሻለ የሥራ ዘርፍ የትኛው እንደሆነ ባይታወቅም ነገሮችን በፍጥነት የመረዳት፤ ችግር ፈቺነት፣ በጥልቀት ማሰብና ማገናዘብ ፣ የፈጠራ ክህሎት ተወዳዳሪ እንደሚሆኑ የአይኮግ ላብ መስራች ቤቴልሔም ደሴ ትገልጻለች።
እነዚህን ክህሎቶች በቀላሉ ለመማር የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ (Coding) ትክክለኛው ዘርፍ እንደሆነም ታስረዳለች። ይህንን ትምህርትም ህጻናት በጊዜ መማር ቢጀምሩ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንደሚኖረውም ታነሳለች።
ይህንን በመረዳት ልጆች የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎችን፣ የተለያዩ የኮምፒውተር ችሎታዎችን እየተማሩ እግረ መንገዳቸውን እንደ ችግር ፈቺነት፣ በጥልቀት ማሰብና ማገናዘብ፣ የፈጠራ ክህሎት እና ሌሎችም አስፈላጊ ክህሎቶችን በሥልጠና በክረምቱ ወራት iCog Anyone Can Code ይሰጣል።
ይህ የክረምት ሥልጠና ዓለም አቀፍ ጭምር ሲሆን በክፍያ የሚሰጥ ነው። ይህንን ሥልጠና አምስት ህጻናት በአካል በመገኘት እንዲሰለጥኑ 10 ህጻናት ደግሞ በonline መማር እንዲችሉ ለቲክቫህ ቤተሰቦች ነጻ የትምህርት እድል ቀርቧል።
እዚ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ወላጆች ልጆቻቸው ለምን መማር እንደሚፈልጉ ቪዲዮ ቀርጻችሁ @iCogACC_bot ላይ መላክ ትችላላችሁ። ስለ ሥልጠናው ሙሉ መረጃ https://icogacc.com/register ላይ መመልከት ይችላሉ።

#Tigray
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ያስተምሩ የነበሩ መምህራን ችግር ላይ መሆናቸውን ገለጸዋል።
በጸጥታ ችግር ምክንያት ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው አዲስ አበባ የሚገኙ የመቐለ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ከ2 እስከ 3 ወር ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው ይገልፃሉ።
በአራቱ ዩኒቨርሲቲዎች ያስተምሩ የነበሩት መምህራን፤ የደሞዝ ክፍያው የተዛባው ከጥቅምት 2013 ጀምሮ ቢሆንም በመሀል በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ተወካዮች በኩል ክፍያ ተፈጽሞላቸው እንደነበር ገልፀዋል።
ይሁን እንጂ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ከግንቦት ወር ጀምሮ የ3 ወር ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው እና በባንክ ያላቸውን ገንዘብ እንዳይጠቀሙ የባንክ አካውንታቸው መታገዱን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ይገልጻሉ።
በመቶዎች የሚቆጠሩት መምህራኑ፤ የሚሰሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በሚገኙበት አካባቢ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ዝውውር ቢጠይቁም ጥያቄያቸው ተቀባይነት አለማግኘቱን ተናግረዋል።
የተለያዩ መምህራን ተደራጅተው ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት የደሞዝ ጥያቄ በደብዳቤ ያቀረቡ ሲሆን ሚኒስቴሩም ጉዳያቸውን ለማስፈጸም ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ ባንክ እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር እየሠራ እንደሚገኝ ገልጾላቸው ነበር።
ይሁን እንጂ እስካሁን ደሞዛቸው እንዳልተከፈላቸውና የአብዛኞቹ መምህራን የባንክ አካውንት አለመለቀቁን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ገልፀዋል። #አዲስማለዳ
@tikvahuniversity

በጋይንት ነፋስ መውጫ የኢትዮጵያ ንግድ ባንድ ተዘረፈ፤ ወደመ።
በህ/ተ/ም/ቤት አሻባሪ ተብሎ የተፈረጀው "ህወሓት" በጋይንት ነፋስ መውጫ ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገብርዬ ቅርንጫፍ ሙሉ ለሙሉ ዘርፎ ማውደሙን የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ አለምነው ስዩም አሳወቁ።
ስራ አስኪያጁ ይህን ያሳወቁት ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ቃል ነው።
ከዝርፊያ እና ውድመት ባለፈ የባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ እንደተገደለ ተገልጿል።
የባንኩ ስራ አስኪያጅ አቶ አለምነው ፥ ህወሓት ባንኩን በመሳሪያ በመደብድብ የኤቲ ኤም (ATM) ማሽኑን ጨምሮ የባንኩን ቋሚ ሀብቶች ሙሉ ለሙሉ አውድሞታል ብለዋል።
የህወሓት ታጣቂዎች የዘረፉትን ገንዘብ ሳይጨምር ከአንድ ነጥብ ስምንት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የሀብት ኪሳራ ማድረሳቸውን አክለዋል።
አቶ አለምነው እንዳሉት፤ ህወሓት የተቋሙንና የግለሰቦችን መረጃ የያዙ ፋይሎችን፣ ኮምፒዩተሮችን፣ የዳታ ሰርቨሩን፣ ጠረጴዘና ወንበሮችን ጨምሮ አጠቃላይ የባንኩ ንብረት ላይ ኪሳራ አድርሷል ሲሉ አስረድተዋል።
ቋሚ ንብረቶችን ከማውደሙ በተጨማሪ ካዝና ውስጥ ከነበረው ገንዘብ ውጭ በኤቴም ማሽን ውስጥ ያለውንም ሰብሮ ዘርፏል ብለዋል።
የህወሓት ታጣቂዎች የባንኩን ጥበቃ ሠራተኛ አንደገደሉት ገልጸዋል፡፡
ወደ 4 ሺ የሚሆኑ የደንበኛ ፋይሎች ከጠቅም ውጭ እንደሆኑ ገልፀው ፤ ወጭና ገቢ የተደረጉ የመረጃ ዶክመንቶች አገልገሎት በማይሰጡበት ደረጃ ተበታትነው እንደጠፉ ተናግረዋል፡፡
ያንብቡ : telegra.ph/EPA-08-25
ፎቶ፦ ኢፕድ