TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ባለሃብቱ በሹ ቱሉ አረፉ።

የሲዳማ ክልል ካፈራቸው እውቅ የሀገራችን ባለሃብቶች መካከል በዋነኝነት ሚጠቀሱት ባለሃብቱ በሹ ቱሉ በህመም ምክንያት ማረፋቸው ተሰምቷል።

ባለሃብቱ በሹ ቱሉ በሆቴል ዘርፍ ጨምሮ በሌሎችም የስራ መስኮች ተሰማርተው ለበርካቶች የስራ እድል በማመቻቸት እራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ ሀገራቸውን ያገለገሉ ዜጋ ነበሩ።

በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርተው ሀገራቸውን ከማገልገላቸው ባለፈ በሲዳማ ክልል ነዋሪዎች ዘንድ እንደ ነፃነት ታጋይም ይወደሳሉ።

@tikvahethiopia
#ItsMyDam

ከአሜሪካ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ወገኖች ከተሰባሰበው ገንዘብ ውስጥ ለ3ኛ ግዜ ወደ ኢትዮጵያ 🇪🇹 መላኩን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ አሳወቁ።

አሁን ከአሜሪካ የተላከው $757,294.78 ሲሆን በድምሩ $1,757,304.78 የአሜሪካን ዶላር በኢትዮጵያ የግድቡ የባንክ ሂሳብ ገቢ መደረጉን ገልፀዋል።

ለግድቡ ድጋፍ ማሰባሰቡ ስራ መቀጠሉንም አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
#Alert🚨

በሀገራችን በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እያሻቀበ ነው።

ዛሬ ምሽት ዘግይቶ በወጣው የጤና ሚኒስቴር እና የአትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት መሰረት በ24 ሰዓት 1,282 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

እነዚህ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተለዩት ከተደረገው 9,017 የላብራቶሪ ምርመራ ነው።

በሌላ በኩል በበሽታው ተይዘው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓት 14 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

የፅኑ ታማሚዎች ቁጥርም 478 ደርሷል።

@tikvahethiopia
* ATTENTION

ከዛሬ ነሃሴ 15/2013 ጀምሮ በሰ/ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሎ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል።

የሰአት እላፊ ገደቡን የወሰነው የወረዳዉ ፀጥታ ምክር ቤት ነው።

የሚዳ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት አሁን ያለዉ የሃገሪቱ የሰላም ሁኔታ ከወረዳዉ መልክአ ምድር አቀማመጥ ጋር ሲነፃፀር አሳሳቢ ሆኖ በመገኘቱ የወረዳዉ ፀጥታ መዋቅር ዉይይት አካሄዶ ለፀጥታ ስጋት ነዉ በማለት የዉሳኔ አቅጣጫ አስቀምጧል ብሏል።

በዚህ መሰረትም ከዛሬ ነሃሴ 15/2013 ዓ.ም ጀምሮ ፦

1ኛ. መጠጥ ቤቶች ከንጋቱ 12 ሰአት እስከ ምሽቱ 2 ሰአት ድረስ #ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል።

2ኛ. የግል አሽከርካሪዎች ሞተር ሳይክልን ጨምሮ ከምሽቱ 1 ሰአት በኋላ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ውሳኔ ተላልፏል።

3ኛ. ማንኛዉም የመንግስት ተሸከርካሪ ለስራ የወጡ ካልሆነ በስተቀር ከሁለት ሰአት በኋላ የትም ቦታ ከመንግስት ተቋም ዉጪ መቆም የለባቸውም ፤
- የጤና ባለሙያዎች፣
- የሃይማኖት አባቶች
- ለፀጥታ ስራ ከሚንቀሳቀሱ ሰዎች በስተቀር ከምሽቱ 3 ሰአት በኋላ እንቅስቃሴ የተገደበ ነው።

ህብረተሰቡ ማንኛውም አይነት #የተለየ_ነገር ከተመለከተ ጥቆማ ለመስጠት እነዚህን ስልክ ቁጥሮች ፦
• 096602287 ፣
• 0913146121
• 0901064105 መጠቀም ይችላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ ዜጎቿን ከካቡል ማስወጣቷን ቀጥላለች። የአሜሪካ ፕሬዜዳንይ ጆ ባይደን በሰጡት መግለጫ አሜሪካ እስካሁን ድረስ 13,000 ሰዎችን ከአፍጋኒስታን ማስወጣቷን፤ ይህ በታሪክ ትልቁ እንዲሁም አስቸጋሪው እንደሆነ ተናግረዋል። ፕሬዜዳንቱ አሜሪካ እያካሄደችው ያለው ዜጎቿን በአየር የማስወጣት ዘመቻ በታሊባን እንቅፋት እየገጠመው አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል። ይህም ከመከላከያ ኃላፊያቸው ጋር የተቃረነ ንግግር…
ካቡል ኤርፖር ት አካባቢ ውጥረት ነግሷል።

#ISIS የአፍጋኒስታን ቅርጫፉ ከአፍጋኒስታን የሚወጡ የአሜሪካ ዜጎች እና ሌሎችም ላይ ጥቃት ሊፈፅም ነው የሚል መረጃ በመገኘቱ በካቡል ኤርፖርት አካባቢ ውጥረት ነግሷል።

ቀደም ብሎ ካቡል ኤርፖርት መግቢያ ባለው የደህንነት ስጋት ከአፍጋኒስታን ሊወጡ ወደካቡል ኤርፖርት የሚሄዱ ሰዎች አዲስ መመሪያ እስኪደርሳቸው ወደኤርፖርት እንይሄዱ መልዕክት ከአሜሪካ ኤምባሲ ደርሷቸዋል፤ ነገር ግን የደህንነት ስጋቱ ምን እንደሆነ አልገለፀም ነበር።

አሁን ላይ አሜሪካ ዜጎቿን ጨምሮ ከአፍጋኒስታን ሚወጡ ሰዎች ወደኤርፖርት የሚገቡበትን አማራጭ መንገዶች እየፈለገች ነው ተብሏል፤ ይህም ከሀገሪቱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተሰምቷል።

እኤአ ከነሃሴ 14 ጀምሮ 17 ሺህ ሰዎች የአፍጋኒስታንን ምድር ለቀው የወጡ ሲሆን 2,500 የሚሆኑት አሜሪካውያን ናቸው። አሁን ላይ ወደ 5 ሺህ 800 የአሜሪካ ወታደሮች በካቡል ኤፖርት ጥበቃ እያደረጉ ነው።

@tikvahethiopia
ጄሲ ጃክሰን ሆስፒታል ገቡ።

በዓባይ ውኃና በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያን በመደገፍ የሚታወቁት እውቁ ጥቁር አሜሪካዊ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ጄሲ ጃክሰንና ባለቤታቸው በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ሆስፒታል ናቸው፡፡

የ79 ዓመቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ጃክሰን ባሳለፍነው ጥር ብዙዎች በተሳተፉበትና ብዙዎች እንዲከተቡ ባሳሰቡበት ይፋዊ ስነ ስርዓት የቫይረሱን ክትባት ወስደው ነበረ፡፡ ሆኖም አሁን በቫይረሱ ተይዘው ከ77 ዓመቷ ባለቤታቸው ዣኩሊዬን ጋር ህክምና ላይ ናቸው፡፡

ጃክሰን ምንም እንኳን የፓርኪንሰን ህመም ተጠቂ ቢሆኑም ጥቁሮች የኮሮና ክትባቶችን እንዲያገኙ ሲቀሰቅሱ እና ሲያስተምሩ ነበር፡፡

የድምጽ አሳጣጥ መብቶችን በተመለከተ የአሜሪካ ኮንግረስ የያዘውን አቋም እንዲተው ለማሳሰብ በያዝነው ወር መባቻ በካፒቶል ሂል ሲደረጉ ከነበሩ ሰልፎች ጋር ተያይዞ ለእስር ተዳርገውም ነበረ፡፡

ከወጣትነት ዕድሜአቸው አንስቶ ከዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጋር ስለ ሲቪል መብቶች በመሟገት የሚታወቁት ጃክሰን በዓባይን ውኃ እና በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያን በመደገፍ ይታወቃሉ፡፡

ግብፅ በናይል ውሃ ላይ አለኝ የምትለውን “ታሪካዊ መብት” የቅኝ ግዛት ዘመን መብት እንዲሁም የዐረብ ሊግን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ይታወቃሉ፡፡

የግድቡን ጉዳይ በተመለከተ በግብጽ እና ዐረብ ሊግ ተጽፈው ለተመድ ጸጥታው ም/ቤት የገቡ ደብዳቤዎችን ጉዳይ ጥቁር የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ኮሚቴ /Congressional Black Caucus እንዲቃወም ከአሁን ቀደም ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡

ከፍ ያለ ተደማጭነት ያላቸው ቄስ (ሪቨረንድ) ጄሲ ጃክሰን ለሁለት (2) ያህል ጊዜ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ተወዳድረው እንደነበር የህይወት ታሪካቸውን የተመለከቱ ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ለተሽከርካሪዎች ዋስትና የሚያስከፍሉት የዓረቦን መጠን ጨመረ።

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከወቅታዊ #የዋጋ_ንረት ጋር በተያያዘ የዋስትና ሽፋን ለሚሰጧቸው ንብረቶች የሚያስከፍሉትን የዓረቦን መጠን እየጨመሩ መሆኑን ሪፖርተር አስነብቧል።

ኩባንያዎቹ በተለይ በሞተር ኢንሹራንስ ዘርፍ ለተሽከርካሪዎች የመድን ሽፋን ይጠይቁ የነበረውን የዓረቦን መጠን ከመቼውም ጊዜ በላይ መጨመራቸው ታውቋል ብሏል ጋዜጣው።

ኩባንያዎቹ ለሚሰጡት የመድን ሽፋን ይጠይቁ ከነበረው ዋጋ እስከ እጥፍ ጭማሪ እየጠየቁ መሆኑን የኩባንያዎቹ ደንበኞች እየገለጹም ነው፡፡

ደንበኞቹ የተሽከርካሪ የመድን ሽፋን ሲያሳድሱ በወቅቱ የተሽከርካሪዎች ዋጋ መሠረት ዓመታዊ የዓረቦን ክፍያቸውን እንዲፈጽሙ እየተደረገ ነው፡፡

የኩባንያዎቹ ደንበኞች እንደሚገልጹት ከሆነ ፣ የተሽከርካሪዎቻቸውን የኢንሹራንስ ሽፋን ለማሳደስ ሲቀርቡ ከዚህ ቀደም ሲከፍሉ ከነበረው የዓረቦን ዋጋ በላይ እየተጠየቁ ነው፡፡ ከኩባንያዎቹ የተገኘው መረጃም ፣ ጭማሪ ሳይሆን ወቅቱን ያገናዘበ ማስተካከያ እየተገረገ ነው፡፡

ይህ የተለመደ አሠራር ሲሆን፣ የአሁኑን የሚለየው ከሌላው ጊዜ በተለየ የተሽከርካሪዎች ዓረቦን ዋጋ ጭማሪ ከፍተኛ መሆኑ ነው፡፡ 

አንዳንድ ደንበኞችም አደጋ ደርሶባቸው የጉዳት ካሳ በሚጠይቁበት ወቅት የኢንሹራንስ ሽፋናቸው በወቅታዊው ተሽከርካሪዎች ዋጋ መሠረት ገቢ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውንም እያመለከቱ ነው፡፡

የሪፖርተርን ዘገባ ያንብቡ : telegra.ph/Reporter-08-22

@tikvahethiopia
ሐጂ የሱፍ አደም አረፉ።

በደሴ ከተማ ከ50 አመት በላይ የአረበኛ እውቀትን ሲያስተምሩ የኖሩት ሐጂ ዩሱፍ አደም ማረፋቸው ተሰምቷል።

ሐጂ ዩሱፍ አደም ለደሴ ህዝበ ሙስሊም የአረብኛ እውቀት አባት ነበሩ።

ወጣቱ የአረብኛ እውቀትን ሲማር ከእሳቸው እውቀት ያልተቋደሰ እንደሌለ ይነገራል።

ለደሴ ከተማ ወጣቶች ትልቅ የእውቀት ባለውለታ ፣ የእድሜ ባለፀጋ ፣ መካሪ እና አቃፊ አባት ነበሩ።

መረጃው ከኡስታዝ አቡበክር አህመድ ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA🇪🇹

ጦርነት ያቀዘቀዛቸው የሻደይ፤ አሸንድየ እና አሸንዳ በዓላት...

በሰሜን የሀገራችን ክፍል ከሚከበሩ በዓላት መካከል የሻደይ ፤ አሸንድየ እና አሸንዳ በዓላት ይጠቀሳሉ።

እነዚህ በዓላት ባለፈው ዓመት በዓለም አቀፉ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ በነበረው ከፍተኛ የሆነ ስጋት በአደባባይ ሳይከበሩ ቀርተዋል ፤ ዘንድሮ ደግሞ በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ጦርነት ሳቢያ ተቀዛቅዘዋል።

ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ በተለይ ሴቶች ዘንድ የሚከበሩት የአሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል በዓላት ከጊዜ ወደ ጊዜ ትኩረት እየሳቡ እና እየደመቁ መጥተው ነበር ፤ አምና የኮቪድ-19 ወረሽኝ ፤ ዘንድሮ ደግሞ ጦርነት ያቀዘቀዛቸው።

ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ገጽታ ያላቸው እነዚህ በዓላት ከማህበራዊ እሴታቸው በተጨማሪ በየዓመቱ የሚፈጥሩት የኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እያየለ መጥቶ ነበር።

በተለይ በዓላቱ ሚከበሩባቸው አካባቢዎች ያለው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እጅግ ከፍተኛ ነበር።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው ሁሉም አካባቢዎች ዘላቂ ሰላም ወርዶ በዓላቱ ዳግም በድምቀት የሚከበሩበት ጊዜ ይመጣ ዘንድ ምኞታችን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia

የሻዳይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል ባህል ዓመታዊ ክብረ በዓል በአማራ ክልል የሚከበር በዓል ነው።

በዋግ ሹሞች መዲና ሰቆጣና አካባቢዋ ሻደይ፣ በቆቦ አካባቢ ሶለል እና በላስታ እና በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች አሸንድዬ በሚል የሚከበረ የልጅ አገረዶች ጨዋታ በዓል ነው።

በዓላቱ አማራ ክልል ባለብዙ ዘርፍ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ሀብት ባለቤት መሆኑን ፣ የተለያዩ ቋንቋዎች እና ባሕላዊ ትውፊቶች ያሉት፣ ሕዝቦች በመተሳሰብ በመፈቃቀር እና በአንድነት የሚኖሩበት መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው።

የሻደይ፣ አሸንድዬ፣ሶለል በዓል የአዲስ አመት መምጣቱን ተከትሎ የሚከበር ብስራት ነው።

ልጃገረዶች ከክረምት መግባት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ውጣ ውረዶችን አልፈው ብሩህ ዘመን እየመጣ መሆኑን የሚያበስሩበት፣ እጮኛ የሚያጩበት፣ ከአቻዎቻቸው ጋር የሚጨፍሩበት እና የሚጫወቱበት ባሕላዊ ጨዋታ ነው።

በተጨማሪ እናቶች እና ህጻናት ያለ ልዩነት ሚሳተፉበትም ነው።

በዓላቱ በህዝባዊ አንድነት የሚያከብሩ፣ የመተሳሰብ፣ የፍቅር እና አብሮ የመኖር እሴትን ለትውልድ ማስተላለፊያ ጠንካራ ገመድ ናቸው።

ለውጭ ሀገራት ብርቅ በመሆኑም የገቢ ምንጭም ነው።

(ከአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ያገኘነው)
ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia

በአሸንዳ በዓል ዙሪያ የተደረገ ጥናት...

#መብራህተን_ገብረማሪያም

በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች የሚከበረው የአሸንዳ በዓል ፍቅር፣ ይቅር ባይነት እና መልካም ተግባቦት በተግባር የሚንጸባረቅበት በዓል ነው።

በዓሉ በልጃገረዶች ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶት ይከበረል፤ ልጃገረዶች አደባባይ ወጥተው የሚያከብሩት ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓል ነው።

የበዓሉ ይዘት በዋናነት ህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ መልካም ተግባቦቶች፣ ፍቅርንና ይቅር ባይነት ላይ ያነጣጠረ ነው።

በዓሉ የሌሎች ሃሳቦች፣ጭፈራዎችና ትእይንቶችም እንዲታዩ የሚጋብዝ ከመሆኑ ባለፈ የሃይማኖትና የብሔር ልዩነት አይንፀባረቅበትም።

በአሸንዳ በዓል ላይ የሚነገሩ ስነ ቃሎች ይዘት በአብዛኛው ህብረትን የሚሰብኩ፣ መድልዎን የሚጠየፉና ለሰው ክብርን የሚያጎናጽፉ ናቸው።

ልጃገረዶች በዓሉን በህብረሰቡ ውስጥ ያለውን እርስ በርስ የመተባበር፣ የመረዳዳትና የጀግንነት መልካም እሴቶችን አጉልተው ለማሳየት ይጠቀሙበታል።

በዓሉ ሴቶች ያላቸውን የፈጠራ፣ የመደራደር፣ የውሳኔ ሰጭነት ብቃት በተግባር የሚያሳዩበትና መልካም ስሜታቸውን የሚገልጹበትም ነው።

በተጨማሪም በህዝቡ ውስጥ ያሉትን ጉድለቶች በስነ ቃልና በዘፈን መልክ እንዲስተካከሉ የሚነቅፉበት፣ ማህበረሰቡ መድልዎን እንዲጠየፍ፣ የሴቶችን መብት የሚጋፋ የአስተዳደር መዋቅር አሊያም ወንድ ካለ እንዲስተካከል መልዕክት የሚያስተላልፉበት ጭምር ነው።

‘አሸንዳ በዓል ለትግራይ ህዝብ ባህል የመሰረት ድንጋይ ተደርጎ ይወሰዳል፤ በዓሉ ማንነትን አጉልተው የሚያሳዩ እሴቶች አሉት።

አሸንዳ ለሴቶች መብት አጥብቆ የሚታገል፣ መከባበርንና መረዳዳትን አብዝቶ የሚሰብክ ፣ ሰዎች ባላቸው የሃብት መጠን ሳይሆን በሰውነታቸው ብቻ ክብር እደሚገባቸው በስነ ቃልና በዘፈን መልክ ያስየምታል።

@tikvahethiopia