TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 5,916 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 511 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ ስምንት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 123 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia
ባለፉት ቀናት በሱዳን ጉብኝት ያደረጉት የUSAID ኃላፊ ሳማንታ ፖውር ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

ፖወር ወደኢትዮጵያ መግባታቸው በይፋ በሚዲያ ሳይታወቅ እና እሳቸው ሆነ ተቋማቸው ሳያሳውቁ ነው ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው መግለጫ የሰጡት።

ለመሆኑ በመግለጫቸው ምን አሉ ?

- ከሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና ከዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

- በትግራይ ክልል ካለው ግጭት ጋር በተያያዘ የሰላም አማራጮች መታየት እንዳለባቸው ፣ ግጭት መቆም እንዳለበት ፣ ሁሉም ተፋላሚ ኃይሎች ወደ ድርድር መምጣት እንዳለባቸው ከሰላም ሚኒስትር ጋር መነጋገራቸውን ገልፀዋል።

- የትግራይ ያለው የውጥ ግጭት ሊፈታ የሚችለው በሰላማዊ አማራጭ ብቻ መሆን እንዳለበት መነጋገራቸውን አሳውቀዋል።

- የአሜሪካ መንግስት ይሁን ሌሎች አካላት የሚሰጡት መገልጿቸው ሃሳቦች መፍትሄ ከማፈላለግ ሃሳብ ጋር የተያያዙ ናቸው ብለዋል።

- ለውጣዊ ግጭት ወታደራዊ አማራጭ መፍትሄ እንደማይሆን፣ ሁሉም አካላት ግጭቱን አስቸኳይ አቁመው ውይይት መጀመር እንዳለባቸው ተናግረዋል።

- ግጭቱ እየሰፋ መሄዱን ተናግረው ሰላማዊ መፍትሄ ካልተበጀለት ይበልጥ እየተስፋፋ በርካታ ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

- በአፋር እና አማራ ክልል ህወሃት በፈፀመው ጥቃት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸው አንስተዋል።

- ዓለም አቀፍ ህጎች መከበር እንዳለባቸው፣ ንፁሃን ለአላስፈላጊ ጉዳት መዳረግ እንደሌለባቸው ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰራተኞች ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተናግረዋል።

- ከሰሞኑ የአሜሪካ መንግስት ይፋ ካደረገው 149 ሚሊዮን ዶላር የሰብዓዊ ድጋፍ በተጨማሪ በዛሬው ዕለት 45 ሚሊዮን ተጨማሪ በጀት ለኮቪድ ወረርሽኝ ለመከላከል ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል ለኢትዮጵያ ይፋ አድርገዋል።

#VOA

@tikvahethiopia
ሳማንታ ፖወር በኢትዮጵያ ማንን አገኙ ?

የUSAID ኃላፊ ሳምንታ ፓወር ሱዳን እንደነበሩ ቢታወቅም በይፋ በሚዲያ ሳይገለፅ ፣ በመንግስትም የተባለ ነገር ሳይኖር እንዲሁም እሳቸው ሆነ ተቋማቸው USAID ያሉት ነገር ሳይሆር ዛሬ አዲስ አበባ ሆነው መግለጫ ሰጥተዋል።

ትላንት ነው ኢትዮጵያ የገቡት።

ፓወር በኢትዮጵያ ቆያታቸው ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተዋል።

እሳቸው እንዳሳወቁት ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና ከሰላም ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚል ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ሳማንታ ፓወር ዛሬ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ለማግኘት እና ለመወያየት ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከከተማ ውጭ እንደሆኑ እንደተነገራቸው ገልፀዋል።

ሳማንት አሁን ላይ ቆይታቸውን ያጠናቀቁ ይመስላል አብረዋቸው ያሉ ባልደረቦቻቸው እንደገለፁት ዛሬ ለሊት ወደአሜሪካ ይበራሉ።

ሳማንታ ፓወር የተለያዩ አሉባልታዎች ሊወሩ እንደሚችል ያነሱ ሲሆን የተሳሳቱ መረጃዎች በሚሰራጭበት ጊዜ መወያያት ብቸኛው መፍትሄ ነው ብለዋል።

ሳማንታ ፓወር ከአሜሪካ በተነሱበት ወቅት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይን ጨምሮ ከሌሎችም ባለስልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩ አስበው ነበር የመጡት።

የጉብኝታቸው ዋነኛ አላማ በትግራይ ክልል ረሃብን ለመከላከል የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት ከፍ እንዲል ለማድረግ በመንግስት ላይ ጫና ለማሳደር ነበር።

የመረጃ ባለቤት ፦ ጋዜጠኛ ኬኒዲ አባተ

@tikvahethiopia
ማርቲን ግሪፊትድ በትግራይ ቆይታቸው ምን ታዘቡ ?

(በቢቢሲ)

አዲሱ የተባበሩት መንግሥታት የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ በትግራይ ክልል ለሁለት ቀናት ጉብኝት አድርገዋል። ግሪፊትስ በትግራይ ስለተማለከቱት ሁኔታ ቢሯቸው መግለጫ አውጥቷል።

ግሪፊትስ በትግራይ ቆይታቸው ፦

- በትግራይ ክልል የተመለከቱት የጥፋት መጠን ልባቸውን እንደሰበረው ገልፀዋል። አስከፊ የሰብዓዊ ሁኔታ መመልከታቸውን ተናግረዋል።

- በጦርነቱ ህይወታቸው ከተመሰቃቀለ ዜጎች ጋር መወያየታቸው ገልፀዋል።

- በጦርነቱ ምክንያት የነበራቸውን ሁሉ ያጡ ሰዎች ማግኘታቸውን፣ መኖሪያቸውንና የእርሻ መሬታቸውን እንዲሁም መንደሮቻቸውንና ከተማቸውን ጥለው የተሰደዱ፣ በሃውዜን ቤታቸው ተቃጥሎ ሰብላቸው የተዘረፈ ቤተሰብ ማግኘታቸውን፣ እስካሁን ድረስ መጠለያም ሆነ ምግብ የሌላቸው ቤተሰቦችን ማግኘታቸው ገልፀዋል፤ "ይህን ማየትም ሆነ የጥፋቱን መጠን መመልከት ልብ ይሰብራል" ብለዋል።

- በትግራይ ጉብኝታቸው ወቅት አሰቃቂ ጥቃት የደረሰባቸውን ግለሰቦችን አነጋግረዋል ፤ የዜጎች መሰረታዊ ልማት የሆኑ እንደ ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታልና ውሃ አገልግሎቶች ስልታዊ በሆነ መንገድ እንዴት እንደወደሙም በአይናቸው መመልከታቸውን ገልፀዋል።

- በመቐለ እና ፍሬወይኒ ውስጥ ለሳምንታት ያህል የተደፈሩትን ጨምሮ አሰቃቂ የሚባሉ ወሲባዊ ጥቃቶች የተፈፀመባቸውን ሴቶችን ማናገራቸው ገልፀዋል። እነዚህ ሴቶች ሁለንተናዊና ሁሉን አቀፍ አገልግሎቶች ቢሹም "አብዛኛው የጤና ማዕከላት አገልግሎት እየሰጡ አይደለም ብለዋል።

- የመገናኛ ተደራሽነት፣ ነዳጅና እና የባንክን የመሳሰሉ መሰረታዊ አገልግሎቶች መቋረጥ አስከፊውን ሁኔታ እያባባሰው መሆኑን ተናግረዋል።

https://telegra.ph/BBC-08-05

@tikvahethiopia
ግሪፍቲስ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ማንን አገኙ ?

የተባበሩት መንግሥታት የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ በኢትዮጵያ የስድስት ቀናት ጉብኝት አድርገው ነበር።

በዚህ ጉብኝታቸው ፦

- ከፌደራል መንግሥቱ
- ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንት
- ከአፍሪካ ሕብረት
- ከሰብአዊ እና ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ጋር ገንቢ ስብሰባዎች አካሂደዋል።

ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም የሰላም ሚኒስትሯን ጨምሮ ከሌሎች ቁልፍ የመንግሥት በለሥልጣናት ጋር ስብሰባ አድርገዋል።

በስብሰባው ሰብአዊ እርዳታ ሁኔታና የረድዔት ድርጅቶች ለኢትዮጵያውያን እርዳታ በሚያቀርቡበት ወቅት የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ላይ ለመወያየት ዕድል አግኝተው ነበር ተብሏል።

ግሪፊትስ ከኢትዮጵያ ጉብኝታቸው በኃላ በትዊተር ገፃቸው፦

- ከዶክተር አብይ ጋር ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

- ወደ ትግራይ ተጉዘው ድጋፍ የሚፈልጉ ዜጎችን አነጋግረዋል።

- እየሰፋ የመጣው ግጭት መቆም እንዳለበት ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች እንዲደርስ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ አንስተዋል።

- የእርዳታና የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች ለተቸገሩ ሰዎች የሚደርሱበትን ሁኔታ ለማሻሻል ከመንግስት ጋር መሥራት አለብን ብለዋል።

- በቀን መቶ የጭነት መኪናዎችን ለማስገባት ጠንክረን እየሠራን ነው ይህ እንደሚሆን የኢትዮጵያ መንግስት አረጋግጦልናል ብለዋል።

- እርዳታ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ መድረስ እና የእርዳታ ሰራተኞች ጥበቃ እንዲደረግላቸው በግል መሥራቴን እቀጥላለሁ ብለዋል።

- በሰብአዊ ፍላጎት ውስጥ ላሉ ኢትዮጵያዊ ዜጎች ሁሉ እርዳታ እንዲደርሳቸው -በትግራይ ፣ በአማራ ፣ በአፋር፣ በማንኛውም ክልል- ቅድሚያ የምሰጠው ጉዳይ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#Tokyo2020 🇪🇹 #Ethiopia

ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ !

ዛሬ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሀገራችን አትሌቶች ውድድራቸውን ይካሂዳሉ ።

ቀን 8:00 ላይ የ ወንዶች 1,500 ሜትር #ግማሽ_ፍፃሜ ውድድር የሚካሄድ ሲሆን ታደሰ ለሚ እና ሳሙኤል አባተ በ ርቀቱ የሚሳተፉ አትሌቶቻችን ናቸው።

ድል ለሀገራችን !

ፎቶ :- ከግራ ወደ ቀኝ ታደሰ ለሚ እና ሳሙኤል አባተ

@tikvahethsport
#USAID-ኢትዮጵያ ባለው መጋዘን 58 ሺ ሜትሪክ ቶን እህል እንዳለው ሳማንታ ፓወር በትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል።

እህሉ በትግራይ ክልል እንዲሁም በሌሎች የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ዜጎችን ሊመግብ የሚችል ነው ብለዋል።

ፓወር የእርዳታ እህሉ ተረጂዎች ጋር ለማድረስ ምቹ እና ያልተገደበ ሁኔታ ሊፈጠር ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
ሱዳን ኢትዮጵያ አንድ ሺህ ሜጋዋት ሃይል እንድትሸጥላት ጠየቀች።

ሱዳንን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል ለመግዛት ፍላጎት አሳይተዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የኮርፖሬት ፕላኒንግ ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም ሲዓ ተናግረዋል።

በቅርቡ ሱዳን አንድ ሺህ ሜጋዋት ሃይል እንደምትፈልግ ማሳወቋን ተከትሎ ባለፈው ወር የተቋሙ ሠራተኞች ወደ ካርቱም አቅንተው እንደነበረና የሱዳን ባለሙያዎችም በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ውይይቱ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ለኬንያ የኤሌትሪክ ሃይል አቅርቦት 500 ኪሎ ዋት መሸከም የሚችል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ እየተጠናቀቀ መሆኑን የገለጹት አቶ አንዱዓለም፤ የኬንያ ፓርላማ ተወካዮች በቀጣዩ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በጉዳዩ ላይ ውይይት እንደሚያደርጉም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ከኬንያ አልፎ ታንዛኒያ እስከ ደቡብ አፍሪካ ሁለት ሺ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ የሚያስችል መሠረተ ልማት ያነሱት ኃላፊው ሶማሌላንድም ከኢትዮጵያ ሃይል ለማግኘት እንድትችል በዓለም ባንክ ድጋፍ ኢስት አፍሪካ ፖወር ፖሊሲ ከሚባል ተቋም ጋር ጥናት እየተደረገ መሆኑ አመልክትዋል።

ደቡብ ሱዳንም ሃይል እንዲቀርብላት በደብዳቤ ፍላጎቷን መግለጿን ጠቁመው፤ ይህን ተከትሎ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ማከናወን የሚያስችል ጥናት ለማድረግ የባለሙያዎች ቡድን በቅርቡ ወደ ደቡብ ሱዳን እንደሚያቀና ተናግረዋል።

(ENA)

@tikvahethiopia
ICRC ወደ ትግራይ ህገወጥ ገንዘብ እና ቁስ አዘዋውሯል ?

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከላይ በምስሉ የሚታየው ገንዘብ ህገወጥ በሆነ መንገድ የዓለም አቅፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ወደ ትግራይ ሲያስገባ አፋር ላይ በተደረገ በፍተሻ መያዙን የሚገልፁ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።

ICRC ዛሬ በዚሁ ጉዳይ መግለጫ አውጥቷል።

በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ትክክለኛ እንዳልሆነ ገልጿል።

ምስሉ የዓለም አቅፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ 5 ተሽከርካሪዎች ባካተተው ኮንቮይ ከሁለት ሳምንት በፊት በአፋር ክልል በነበረው ፍተሻ ወቀት የተነሳ መሆኑን አሳውቋል።

በምስሉ የሚታየው ቁስ በሙሉ የአስቸኳት ጊዜ እርዳታ እና የህክምና ቁሶችንም የሚያካትት ሲሆን የሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግስት አካላት በቅድሚያ እንዲያውቋቸው ተደርገውና ፍቃድ ተገኝቶባቸው የተጓጓዙ ናቸው ብሏል።

ቁሳቁሶቹና ገንዘቡ ድርጅቱ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚያደርገው ለሚሰጠው የሰብዓዊ አገልግሎት ተግባር የሚውል መሆኑን ገልጾ ሁሉም ቁሳቁሶች መቐለ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ መድረሱን አመልክቷል።

ICRC ጥሬ ገንዘብ ያጓጓዘው የባንክ አገልግሎት ባለመኖሩ መሆኑንም አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Tokyo2020 🇪🇹 #Ethiopia

በ1,500 ሜትር ወንዶች የግማሽ ፍፃሜ በመጀመሪያው ምድብ የተካፈለው አትሌታችን ታደሰ ለሚ ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ ለ ፍፃሜው ማለፍ #ሳይችል ቀርቷል።

በ1,500 ሜትር የግማሽ ፍፃሜ ውድድር የመጀመሪያውን አምስት ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁ አትሌቶች በቀጥታ ለፍፃሜው ውድድር የሚያልፉ ይሆናል።

የ1,500 ሜትር የፍፃሜ ውድድር በመጪው ቅዳሜ ከ ቀኑ 8:40 ላይ የሚካሄድ ይሆናል።

*ፈጣን ሰዓት የሚያስመዘግቡ 2 አትሌቶች የ ፍፃሜ ውድድሩን የሚቀላቀሉ ይሆናል።

@tikvahethsport
#Tokyo2020 🇪🇹 #Ethiopia

በ1,500 ሜትር የግማሽ ፍፃሜ በ ሁለተኛው ምድብ የተካፈለው አትሌታችን ሳሙኤል አባተ አስራ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ለፍፃሜው ማለፍ #ሳይችል ቀርቷል።

በሁለተኛው ምድብ አሸናፊ የሆነው ኬንያዊው አቤል ኪፕሳንግ የኦሎምፒክ ሪከርድን የግሉ ማድረግ ችሏል።

የ1,500 ሜትር የፍፃሜ ውድድር በመጪው ቅዳሜ ቀን 8:40 ላይ የሚካሄድ ይሆናል ።

@tikvahethsport
#ዝግጅት_ጥቆማ

ልባም ህይወት !

በኒውሮ ሊንጉስቲክ ፕሮግራሚንግ ፕሪክቲሼኔር የሚሰጥ - "መጥፎ እና ጥሩ ሀሳብ ወደ አእምሮአችን እንዴት ይመጣል?"

ፕሮግራሙ ሀምሌ 30/2013 ዓ/ም ከምሽት 12 እስከ 1:45 የሚካሄድ ሲሆን ፕሮግራሙ በነፃ የሚሰጥ ነው።

በስልክ ቁጥር 0911624348 ወይም 0911280510 ስም በቴክስት በመላክ ቦታ መያዝ እንደሚቻል አዘጋጆቹ ለቲክቫህ አሳውቀዋል።

22 ወደ መገናኛ በሚወስደው መንግድ ብሉ በርድ ሆቴል አጠገብ ነው ፕሮግራሙ የሚካሄደው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የUSAID አስተዳዳሪ የሆኑት ሳማንታ ፓወር ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት ሰብዓዊነት አሳስቦኝ ነው ሲሉ መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ፡፡

አምባሳደሩ ዛሬ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ስለሳማንታ ፓወር ጉብኝት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ዲና ሳማንታ “ሰብዓዊነት አሳስቦኝ ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት" ሲሉ መናገራቸውን እንደሚወራው "መንግስት ለመቀየር እንዳልመጡ ፤ ይልቁንም ሰብዓዊነት እንደሚያሳስባቸው” መናገራቸውን ገልፀዋል።

ሲመጡ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይን እና ምክትላቸውን አቶ ደመቀን ለማግኘት አቅደው የነበሩት ሰማንታ ፓወር 2ቱንም ሳያገኟቸው ቀርተዋል። በዚህ ጉዳይ አስተያየታቸውን የሰጡት አምባሳደር ዲና ፥ “በነበረባቸው የስራ ጫና (ዶ/ር ዐቢይና አቶ ደመቀ)” ምክንያት ፍላጎታቸው ተሳክቶ ሳያገኟቸው ቀርተዋል ብለዋል።

ምንም እንኳን እነሱን ማግኘት ባይችሉም ከእርሳቸው ተቋም ተግባር ጋር በሚገናኙ ስራዎች ዙሪያ የተሰማሩ የመንግስት ባለስልጣናትን እንደሚያገኙ ተነግሯቸው አግኝተዋል ሲሉ አክለዋል።

ሳማንታ ፓወር ካገኟቸው ባለስልጣናት መካከል ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የሚገኙበት ሲሆን "ህወሃት" የተጀመረውን ሃገራዊ ለውጥ ረግጦ መውጣቱን ለሳማንታ መናገራቸውን ገልፀዋል።

ፓወር፥ “አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በጣም ዋጋ ትሰጣለች” ያሉ ሲሆን ጉዳዩ እዚህ ደረጃ መድረስ አልነበረበትም ስለማለታቸውም ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ድርድርና ውይይትን በተመለከተ የተጠየቁት አምባሳደር ዲና ምናልባት በመጪው መስከረም ወር መጨረሻ በሚመሰረተው አዲስ መንግስት ሁሉን አቀፍ (All inclusive) ውይይት እንደሚደረግና ምናልባት የህወሓት አባል የነበሩ ሰዎች ወደዚህ ውይይት ሊመጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
የተፈናቃዮች ጥሪ :

በወልዲያ ከተማ በአምስት መጠለያ ጣቢያዎች ከራያ ቆቦ እና አካባቢዋ የተፈናቀሉ ዜጎች ይገኛሉ።

በወልድያ ከተማ የሚገኙት ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸው መጠየቃቸውን #አሚኮ ዘግቧል።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር በ5 መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ ሁሉም እገዛ እንዲያደርግ ጠይቋል።

ወልዲያ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች የከተማው ህዝብ ላደረገላቸው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ወደ ቀያቸው እስኪመለሱ የሚደረግላቸው የሰበዓዊ ድጋፍ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የወልድያ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ሙሀመድ ያሲን የከተማዋ ነዋሪዎችና ወጣቶች ተፈናቃዬቹን ለመደገፍ ላደረጉት ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል።

ከንቲባው ባለሀብቶችና የእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ህወሓት በአፋር እና አማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ከ225 ሺህ በላይ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው በሁለቱ ክልል መንግስታት መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia