TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
2 ዓለም አቀፍ የእርዳታ ቡድኖች የኢትዮጵያ መንግስት በከፊል / በሙሉ ስራቸውን እንዳቋረጠባቸው እና የስራ ፍቃዳቸውን እንደነጠቃቸው ትላንት አሳወቁ።

ቡድኖቹ የDoctors Without Borders - MSF (የደች ቅርንጫፍ) እና Norwegian Refugee Council (NRC) ሲሆኑ ሐምሌ 23/2013 ዓ/ም ጀምሮ መንግስት ስራ እንዳያከናውኑ እንዳገዳቸው ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስት አንዳንድ የእርዳታ ድርጅቶች በስም ሳይገልፅ ሀገርን በማፍረስ ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ እና አንዳንዶቹንም ከሀገር እስከማባረር የሚደርስ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ በጥብቅ አስጠንቅቆ ነበር። አሁን ላይ በMSF እና NRC ስራቸውን በከፊል እና በሙሉ መንግስት እንዳስቆማቸው ለገለፁበት አቤቱታ ምላሽ አልሰጠም።

MSF ባወጣው መንግለጫ ለእግዱ ዝርዝር ማብራሪያ እና ምክንያት ከባለስልጣናት ለማግኘት ሂደት ላይ መሆኑን አሳውቋል። NRC በበኩሉ ከባለስልጣናት ጋር ውይይት እያደረኩ ነው ብሏል።

@tikvahethiopia
#USA

የአሜሪካ መንግስት ወደትግራይ እርዳታ እንዲገባ ሁሉም ኃይሎች ግጭት ማቆም አለባቸው ብሏል።

ለተፈጠረው ችግር ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ የለውም ያለው የአሜሪካ መንግስት በአስቸኳይ TPLF ኃይሉ ከአማራ እና አፋር ክልል እንዲያስወጣ፣ የአማራ ክልል መንግስት ኃይሎቹን ከምዕራብ ትግራይ ክፍል እንዲያስወጣ ፣ የኤርትራ መንግስትም በአቸኳይ እና በቋሚነት ኃይሎቹን ከኢትዮጵያ እንዲያስወጣ ጠይቋል።

የኤርትራ ጦር ከየትኞቹ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ነው በቶሎ የሚያስወጣው የሚለውን በውል አልተጠቀሰም።

ሁሉም ወገኖች ያልተገደበ የሰብዓዊ ድጋፍ ለተጎዱ ሰዎች እንዲደርስ ማፋጠን አለባቸው የትግራይ የንግድ ብሎኬጅ ሊያበቃም ይገባል ሲል የአሜሪካ መንግስት አቋሙን ገልጿል።

በደጋሚ የአሜሪካ መንግስት የግጭት ተሳታፊዎች ግጭት አቁመው በድርድር ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም እንዲደርግ ንግግር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

የአሜሪካ መንግስት ይህን ያለው በUSAID ኃላፊ ሳማንታ ፓዎር አማካኝነት ነው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የኢትዮጵያ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል ከተባበሩት መንግስታት የእርዳታና ሰብአዊ ጉዳዬች አስተባባሪ ሚስተር ማርቲን ግራፊት ጋር ውይይት አካሄዱ።

ወ/ሮ ሙፈርያት ፤ በውይይቱ ሂደት መንግሥት ላለፉት ስምንት ወራት በትግራይ ክልል ያከናወነውን የሰብአዊ እርዳታ ተግባራት በዝርዝር እንዲሁም በመንግስት የተወሰደውን የሰብአዊ ተኩስ አቁም ውሳኔን ተከትሎ የተዘረጉ የአሰራር ስርዓቶች ሂደቱን ለማሳለጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ላይ ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸውን በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው አሳውቀዋል።

በተጨማሪ ፥ "መንግስት የወሰደውን የሰብአዊ የተናጥል ተኩስ አቁም ውሳኔ ወደ ጎን በማለት ህወሓት በአማራ ክልል እና በአፋር ክልል የሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ በእብሪት በከፈተው ጥቃት ለተፈናቀሉ ዜጎቻችን እርዳታ የማቅረብ አስፈላጊነት ላይ ውይይት አካሂደናል" ብለዋል።

@tikvahethiopia
ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ !

ዛሬ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሀገራችን አትሌቶች ውድድራቸውን ይካሂዳሉ።

ቀን 7:00 ላይ የሴቶች 1,500 ሜትር #የግማሽ_ፍፃሜ ውድድር የሚካሄድ ሲሆን ፍሬወይኒ ሀይሉ እና ለምለም ሀይሉ በርቀቱ የሚሳተፉ አትሌቶቻችን ናቸው።

ቀን 8:00 ላይ ደግሞ የሴቶች 3,000 ሜትር መሰናክል #ፍፃሜ ሲካሄድ መቅደስ አበበ እና ዘርፌ ወንድማገኝ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳሊያ ለማስገኘት ይፋለማሉ።

ድል ለሀገራችን !

@tikvahethsport
#UN

የተመድ (UN) የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ የሆኑት ማርቲን ግሪፊትስ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢዎች ለትግራይ ተዋጊዎች ያደላሉ እንዲሁም ያስታጥቃሉ ማለታቸው "አደገኛ" ብለውታል።

ኃላፊው የእርዳታ ድርጅቶች ላይ የተቃጣው "መሠረተ ቢስ ወቀሳ" ሊቆም ይገባል ማለታቸውን ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል። "ማስረጃ ካለ በማስረጃ ሊደገፉ ይገባል፤ እውነት ለመናገር ግን ይህ አካሄድ አደገኛ ነው" ብለዋል ኃላፊው።

የህወሓት ኃይል በምዕራብ ደቡብ በኩል ወደ አጎራባቾቹ አማራ ክልል እና አፋር ክልል በመግባት ወደ 200 ሺህ ሰዎችን አፈናቅለዋል ብለዋል ኃላፊው።

54 ሺህ ሰው የተፈናቀለው በአፋር ክልል መሆኑን ተናግረዋል።

ምንም እንኳን ኃላፊው ይህንን ይበሉ እንጂ ከቀናት በፊት ከአፋር እና ከአማራ ክልል መንግስታት በተገኘው መረጃ ህወሓት በአፋር ክልል እና አማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ከ225,000 በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።

ከአማራ ክልል ከ150 ሺህ በላይ ዜጎች ከአፋር ክልል ደግሞ ከ76 ሺህ በላይ ዜጎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች አንዳንዶቹ ወደዘመዶቻቸው ተጠግተው ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
#Update

የአማራ ክልል መንግስት ህወሓት ወደ ክልሉ ዘልቆ በመግባት በከፈተው ጦርነት የተፈናቀሉ ሰዎች 200 ሺህ መድረሳቸውን አሳውቋል።

ክልሉ ይህን ያሳወቀው በኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አቶ ግዛቸው ሙልነህ አማካኝነት ነው።

ህወሓት በወረራቸው አካባቢዎች የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ቁሳዊ ውድመት እየደረሰ መሆኑንም ኃላፊው ለኢፕድ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

አቶ ግዛቸው ቡድኑ እየፈፀመ ነው ያሉት ቁሳዊ እና ሰብዓዊ ውድመት ወጣቶችን አፍኖ መውሰድ፣ ንፁሃንን መግደል፣ ሴቶችን መድፈር፣ ከፍተኛ ሀብት እና ንብረትን ዘርፎ ወደ መሃል ትግራይ መቐለ መውሰድ ይገኙበታል።

እስካሁን ድረስ ባለው 200 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውንም አቶ ግዛቸው አመልክተዋል።

ከዚህ ባለፈ የቡድኑ ተዋጊ ኃይል ወደአማራ ክልል ዘልቆ ሲገባ ዳግም እንዳይወጣ ተደርጎ እየተመታ ነው ፤ ህወሓት ህፃናትን ፣ ሴቶችን፣ አዛውንቶችን ፣ የሃይማኖት አባቶችን ወደጦርነት እየማገደ ነው የትግራይ እናቶችና የትግራይ ህዝብ ድርጊቱን ያውግዝ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

በትላንትናው ዕለት 79 የሀገራችን ዜጎች ከየመን፣ ሰንዓ ወደ አገራቸው ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

በየመን የሚገኙ የኢትዮጵያን ዜጎችን ወደ አገራችው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ያስታወሰው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትላንት 79 ዜጎችን ከሰንዓ በማስወጣት ወደ አገራቸው እንደሚለሱ መድረጉን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
157 ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ መኪናዎች መቐለ ገቡ።

ትናንት ሐምሌ 27 ቀን 2013 ዓ.ም. 157 ሰብዓዊ ዕርዳታ የያዙ የጭነት መኪናዎች መቐለ የወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ ገፅ አሳውቋል።

መኪናዎቹ የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ አስፈላጊ መገልገያዎችን የያዙ መሆናቸው ተገልጿል።

ድጋፉ ከዓለም የምግብ ድርጅት (WFP) ፣ እንደ ዩኒሴፍ (UNICEF) እና ዩ.ኤን .ኤፍ.ፒ.ኤ (UNFPA) ካሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች (UN) ፣ እንዲሁም ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍን ለማቅረብ ከሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተገኘ ነው ተብሏል።

Photo : File

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
2 ዓለም አቀፍ የእርዳታ ቡድኖች የኢትዮጵያ መንግስት በከፊል / በሙሉ ስራቸውን እንዳቋረጠባቸው እና የስራ ፍቃዳቸውን እንደነጠቃቸው ትላንት አሳወቁ። ቡድኖቹ የDoctors Without Borders - MSF (የደች ቅርንጫፍ) እና Norwegian Refugee Council (NRC) ሲሆኑ ሐምሌ 23/2013 ዓ/ም ጀምሮ መንግስት ስራ እንዳያከናውኑ እንዳገዳቸው ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስት…
#Update

1ኛ MSF HOLLAND 2ኛ NORWEGIAN REFUGEE COUNCIL እና 3ኛ AL MAKTOUME FOUNDETION የተባሉ የውጭ ድርጅቶች የኢፌድሪ የሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ኤጀንሲ በሰጣቸው ፍቃድ በህጋዊነት በተለያዩ የሰብዓዊ ስራዎች ተሰማርተው እየሰሩ የቆዩ ድርጅቶች ሲሆኑ የድርጅቶቹን እንቅስቃሴ በተመለከተ ፍቃድ ሰጪው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በሚያደርገው ክትትል መሰረት ድርጅቶቹ ከተቋቋሙለት አላማ ውጭ በመንቀሳቀስ፤

- አንደኛ- 1ኛ እና 2ኛ የተጠቁት ድርጂቶች የተለያዩ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ እና በሌሎች ዘዴዎች ሲያሰራጩ በመገኘታቸው፣

-ሁለተኛ - 3ቱም ድርጅቶች ስልጣን በተሰጠው አካል የስራ ፍቃድ ያልተሰጣቸውን የውጭ ሃር ዜጎች ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ከስድስት ወር በላይ ቀጥረው ሲያሰሩ በመገኘታቸው፤

- ሶስተኛ- 1ኛ የተቀመጠው ድርጅት ስልጣን በተሰጠው አካል ፍቃድ ያልተሰጣቸው የሳተላይት የሬድዬ መገናኛ መሳሪያውችን ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባ የድርጂቱ ሰራተኞች አፍራሽ ለሆኑ አላማ ሲጠቀሙበት እና ይዘው ሲንቀሳቀሱ በጸጥታ አካላት ቀጥጥር ስር በመዋላቸው

- አራተኛ- 3ኛ የተጠቀሰው ድርጅት የትምህርት ሚንስቴር የኮቪድ-19 ፕሮቶኮልን ባለማክበር ፣ የበጀት አጠቃቀም ግልጽነት የጎደለውና በትምህርት ቤቱ ስም የሚመጣን በጀት ከአላማው ውጭ እየተጠቀመ በመሆኑ እንዲሁም በሰራተኞች አስተዳደር ችግር የታየበት በመሆኑ ምክንያት፤

ድርጅቶቹ ከተቋቋሙት አላማ ውጭና የሃገርን ጥቅም በሚጻረር መልኩ ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው እንዲታረሙ በተደጋጋሚ ከድርጅቶቹ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ቢደረግም ሊያስተካክሉ ስላልቻሉ አጠቃላይ ምርመራ ተደርጎ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ አጠቃላይ የድርጅቶቹ እንቅስቃሴ ለ3 ወራት #ታግዷል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tokyo2020 በ1,500 ሜትር ለፍፃሜ ለማለፍ በተካሄደው ውድድር በመጀመሪያው ምድብ የተወዳደረችው ፍሬወይኒ ሀይሉ 3:57.54 በሆነ ሰዓት 2ኛ ደረጃን በመያዝ ለ ፍፃሜው አልፋለች። @tikvahethsport
#ምድብ2

በ1500 ሜትር ለፍፃሜ ለማለፍ በተካሄደ በ2ኛው ምድብ ውድድር ኢትዮጵያን ወክላ የተወዳደረችው #ለምለም_ሀይሉ ዘጠነኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

ለምለም ወደ ቀጣዪ ዙር ማለፍ ሳትችል ቀርታለች።

በዚህ ምድብ በተደረገው ውድድር ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ኔዘርላንድን ወክላ የተሳተፈችው #ሲፋን_ሀሰን ቀዳሚውን ደረጃ በመያዝ ለፍፃሜው አልፋለች።

የ1500 ሜትር ፍፃሜ ውድድር የፊታችን አርብ ከቀኑ 9:50 ጀምሮ ይደረጋል።

@tikvahethsport
አንዲት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከባሮ ድልድይ ዘላ ህይወቷ አለፈ።

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የተቋሙ ተማሪ የነበረች ወጣት ባልታወቀ ምክንያት ከባሮ ድልድይ በመዝለል ህይወቷ ማለፉን ገልጿል።

የሎጆስቲክስ ትምህርት ክፍል ሶስተኛ ዓመት ተማሪ የነበረችው ተማሪ ቀመሪያ ኃይሉ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም ከቀኑ 12:00 ሰዓት አካባቢ ከባሮ ድልድይ ወደ ወንዙ በመዝለል ህይወቷ ማለፉ ነው የተገለፀው።

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ፣ የክልሉ ፖሊስ፣ የአቦል ወረዳ አመራሮችና ነዋሪዎች ያደረጉትን ፍለጋ ተከትሎ የሟቿ አስክሬን በአቦል ወረዳ "ፒኝኬው ቀበሌ" መገኘቱን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

More: @tikvahuniversity
#Tokyo 🇪🇹

በ 3 ሺህ ሜትር መሰናክል በተካሄደ የ ፍፃሜ ውድድር ዩጋንዳዊቷ ቼሙታይ የ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች ።

ኢትዮጵያዊቷ መቅደስ አበበ ውድድሯን በ አራተኛነት እንዲሁም ዘርፌ ወንድማገኝ በ ስምንተኛነት ውድድራቸውን አጠናቀዋል ።

አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ የገባችበት 9:16.41 ሰዓት የ ግሏ ምርጥ ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል ።

ሁለቱም በ ርቀቱ የተሳተፉት አትሌቶቻችን መቅደስ አበበ እና ዘርፌ ወንድማገኝ የመጀመሪያ የ ኦሎምፒክ ተሳትፏቸው ነበር ።

@tikvahethsport
ኤርትራውያን ስደተኞችን ሰላም ወዳለበት የማዘዋወር ስራ...

የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ስደተኞቹን የተሻለ ሰላም ወዳለባቸው አካባቢዎች ለማዘዋወር የአደጋ ግዜ እቅድ ማዘጋጀቱን አሳውቋል።

ድርጅቱ ይህን ያሳወቀው ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ነው።

በማይጸብሪ በሚገኙት ማይ አይኒ እና አዲ ሃሩሽ መጠለያ ጣቢያዎች ያሉ ስደተኞችን በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ዳባት ከተማ እየተገነባ ወደሚገኘው አዲስ ጣቢያ እንደሚዘዋወሩ ተገልጿል።

በ91 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባው የመጠለያ ካምፕ 25 ሺ ስደተኞችን ለማስተናገድ አቅም አለው።

የስደተኞችን ደህንነት በተመለከተ የተጠየቁት የUNHCR የኢትዮጵያ ቃል አቀባይ ነቨን ከርቨንኮቪክ ስደተኞቹ "የሰብዓዊ እርዳታ ተቋርጦባቸው በማያቋርጥ ፍርሃት ውስጥ እየኖሩ ይገኛሉ" ብለዋል።

ከማይ አይኒ ካምፕ ለUNHCR በቅርቡ በደረሰ ሪፖርት ቢያንስ 1 ስደተኛ በካምፑ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መገደሉን ያመለከተ ሲሆን ሐምሌ 14 ሌላ ስደተኛ መገደሉን የሚያመላክት ሌላ ሪፖርት ለUNHCR ደርሶ እንደነበር አሳውቀዋል።

የድርጅቱ ሠራተኞች ላለፉት 3 ሳምንታት ከስደተኞች መጠለያ ካምፖች ጋር ያላቸው ግንኙነት ሙሉ በሙሉ መቋረጡን አስረድተዋል።

"ወጥመድ ውስጥ የገቡ ስደተኞች አስቸኳይ የሕይወት አድን እርዳታ ያስፈልጋቸዋል" በማለት ስለ ስደተኞቹ ገልጸዋል።

ወደ 24,000 የሚሆኑ ኤርትራዊያን ስደተኞች ማስፈራራትና እንግልት እየገጠማቸው እንደሆነም ገልጸዋል።

More : telegra.ph/BBC-08-04

Source : BBC

@tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ለማድረግ የሚያገለግል የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ።

ይፋ የተደረገው መተግበሪያ" Its My Dam" የተሠኘ ስያሜ ያለው ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ነው ይፋ የተደረገው።

የገቢ ማሰባሰቢያ መተግበሪያውን ወደ ሥራ ለማስገባት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

መተግበሪያዉ ከ1 ዶላር ጀምሮ እስከ 10 ሺህ ዶላር ድረስ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ነው።

Photo Credit : EEP

@tikvahethiopia
#USA : አሜሪካ 1,210,550 ዶዝ የጆንሰን እና ጆንሰን ኮቪድ-19 ክትባት ለኢትዮጵያ ለግሳለች።

በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በተገኘው መረጃ ልገሳው ከዚህ ቀደም ከተለገሱት 453,600 ክትባቶች ተጨማሪ ነው።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ፥ “ልገሳው የኢትዮጵያ ህዝቦች የኮቪድ -19ን ወረርሽኝ ለመከላከል የሚያደርጉትን ትግል ያግዛል" ብለዋል።

በተጨማሪም፤ "የኮቪድ -19 ክትባቶችን ለኢትዮጵያ በማድረስ የህይወት አድን ስራ ላይ በመሳተፋችን ክብር ይሰማናል" ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ የቅርብ የጤና አጋር እንደመሆናችን ሕይወትን ለማዳን እና ወረርሽኙን ለማጥፋት ቁርጠኛ ነን” ሲሉ ተናግረዋል።

ከክትባቱ ጋር በተያያዘ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በትዊተር ገፃቸው የአሜሪካን ድጋፍ እንደሚያደንቁ ገልፀው ፤ ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመዋጋት እና የኮቪድ-19 ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ትቀጥላለች ብለዋል።

ዶ/ር ሊያ COVAX፣ UNICEF ፣ CDC Africaን ድጋፉን ስለመቻቹና ስለደገፉ አመስግነዋል።

@tikvahethiopia