ሳማንታ ፓወር ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የUSAID አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር፣ በትግራይ ክልል ረሃብን ለመከላከል የተሟላ እና ያልተገደበ ሰብዓዊ ተደራሽነት እንዲፈቀድ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ግፊት ማድረግ የጉዟቸው ዓላማ እንደሆነ አስቀድመው ገልጸዋል፡፡
ይሁን እና የሚያደርጉት ግፊት ስለሚያካትታቸው ነጥቦች የተባለ ነገር የለም፡፡
በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሳማንታ ፓወርን ወደኢትዮጵያ መምጣት ተከትክሎ መንግስት የኢትዮጵያን እውነት ማሳወቅ አለበት ያሉ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ የኃላፊዋን መምጣት እንዳልወደዱት ሲፅፉ ታይተዋል።
ፓወር በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለልስጣናት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
@tikvahethiopia

Photo : የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች እና የ5000 ሜትር ሴቶች የሜዳልያ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።
በ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ለሜቻ ግርማ ለሀገራችን ኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ማስገኘቱ ፤ በ5000 ሜትር ሴቶች ደግሞ ጉዳፍ ፀጋይ ለሀገራችን ኢትዮጵያ የነሃሳ ሜዳሊያ ማስገኘቷ ይታወቃል።

#Ethiopia
"... ትዕግስታችን የተሟጠጠ ለታ እንዴት ከእያንዳንዱ ከተማና መንደር ጠራርገን እንደምናስወጣቸው ታያላችሁ። ጦርነት ከሆነ ፍላጎታቸው ያገኙታል" - አቶ ዛዲግ አብርሃ
#ቢቢሲ
ከሰሞኑን ቢቢሲ ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳይን ቃለምልልስ አድርጎ ነበር።
በዚህ ወቅትም ያቀረቡት ቅድመ ሁኔታ ተቀባይነት አግኝቶ የተኩስ አቁሙ እንዲደረግና ሁሉን አቀፍ ፖለቲካዊ ውይይት ተደርጎ የሽግግር ሂደት መጀመር አለበት ብለዋል።
ጄነራል ጻድቃን ኃይሎቻቸው በአፋር እና አማራ ክልል ጥቃት መፈፀማቸውን የተናገሩ ሲሆን ጥቃቱ በትግራይ ክልል ላይ ያለውን መዘጋት (ብሎኬጅ) በመስበር " መውጫ መንገድ ለማግኘት እንዲሁም ቡድኑ ለተኩስ አቁም ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ መንግሥት እንዲቀበል ጫና ማሳደር ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ስለጉዳዩ ምን አለ ?
የኢትዮጵያ መንግስት ከህወሓት አመራሮች ጋር ድርድር እንደማያደርግ የኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሚኒስትር አቶ ዛዲግ አብረሃ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
አቶ ዛዲግ አብረሃ መንግሥት ከህወሓት አመራሮች ለድርድር እንደማይቀመጥ ገልጸዋል።
አሁን በሰሜኑ የአገሪቱ አካባቢ ያለውን ሁኔታ በሚመለከትም መንግሥት በተናጠል ተኩስ አቁም ውስጥ መሆኑን ጠቅሰው "አሁን በህወሓት በኩል የሚታየው ነገር ራስን አጋኖ ከማየት የመነጨ ነው" ብለዋል።
ነገር ግን መንግሥት ትዕግስቱ ሲሟጠጥ መንግሥት ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ "አቅማችንን ማየት ከፈለጋችሁ የተወሰኑ ሳምንታት መጠበቅ ይኖርባችኋል። ትዕግስታችን የተሟጠጠ ለታ እንዴት ከእያንዳንዱ ከተማና መንደር ጠራርገን እንደምናስወጣቸው ታያላችሁ። ጦርነት ከሆነ ፍላጎታቸው....ያገኙታል" ሲሉ ተናግረዋል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/Tigray-08-03

#Tigray
ወደ ትግራይ እርዳታ እንዲገባ #የጅቡቲው_መስመር በቂ በመሆኑ ተጨማሪ ኮሪደር እንደማይከፈት የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ።
የብሄራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ለአዲስ ዘመን በሰጡት ቃል በትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ ለሚሹ ተረጂዎች እርዳታ ለማቅረብ በሚል አንዳንድ ምዕራባዊያንና ተቋሞቻቸው በምዕራብ ትግራይ በኩል መተላለፊያ ኮሪደር ይከፈት የሚለው ግፊታቸው ተቀባይነት እንደሌለው አስገንዝበዋል።
የእርዳታ አቅርቦቶች በፌዴራል መንግስትና በአፋር ክልል ከፍተኛ ጥረት ለትግራይ ህዝብ እየደረሰ መሆኑንም ኮሚሽነሩ አሳውቀዋል።
በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው ህወሓት መንግስት ያሳለፈውን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ባለመቀበል በአማራ እና በአፋር ክልሎች ላይ ትንኮሳ እየፈጸመ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ ምትኩ ካሳ ፤ ለትግራይ ክልል ተረጂዎች የሚቀርብን እርዳታ የያዙ ከ170 በላይ ተሽከርካሪዎችን አግቶ በማቆየቱ በክልሉ ያሉ ተረጂዎች ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጠዋል ብለዋል።
ይህንንም ሁኔታ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም አንዳንድ ምዕራባዊያን አገራት እና ተቋሞቻቸው ከሱዳን ቀጥታ እርዳታ ለማስገባት በሚል በምዕራብ ትግራይ በኩል መተላለፊያ ኮሪደር ይከፈት የሚል ጥያቄዎችን ማቅረባቸውን ገልፀዋል።
እነሱ ይህንን ይበሉ እንጂ መንግስት ለተረጂዎቹ እርዳታ ለማቅረብ የጅቡቲው መስመር በቂ መሆኑን በማሳወቅ ተጨማሪ ኮሪደር እንደማይከፈት ማሳወቁን በዚህም የጸና አቋም እንዳለው አስታውቀዋል። (ኢፕድ)

ድል ለሀገራችን !
ዛሬ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሀገራችን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው ውድድሮች ይካሄዳሉ።
የመጀመሪያው ውድድር ቀን 8:00 ላይ የሚካሄድ ሲሆን የወንዶች 5,000 ሜትር #ማጣርያ ነው። በዘህም ውድድር ጌትነት ዋለ ፣ ንብረት መላክ እና ሚልኬሳ መንገሻ ሀገራችንን ይወክላሉ።
ቀን 9:25 ላይ ደግሞ የሴቶች 800 ሜትር #ፍፃሜ የሚካሄድ ሲሆን ሀብታም አለሙ ብቸኝነት ሀገራችንን ኢትዮጵያ ትወክላለች።
ድል ለሀገራችን !
@tikvahethsport

TIKVAH-ETHIOPIA
"ጥላሁን ያሚ በሞት ይቀጣልኝ" -ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን በመግደል ወንጀል የተከሰሰው ጥላሁን ያሚ በሞት ይቀጣልኝ ብሏል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር ለመስማት የተሰየመ ሲሆን በዚህ ጊዜ ዐቃቤ ህግ ተከሳሹ የቀደመ ባህሪው 2 የወንጀል ሪከርድ እንዳለበት አስረድቷል፡፡ በዚህም…
#BREAKING
አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ገድሏል የተባለው ጥላሁን ያሚ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ፡፡
በግድያው ተባብሯል የተባለው 2ኛ ተከሳሽ ከበደ ገመቹ ደግሞ በ 18 አመት ፅኑ እስራት የተቀጣ ሲሆን በወቅቱ ለፀጥታ አካል መረጃ ባለማሳወቅ ጥፋተኛ የተባለው 3ኛ ተከሳሽ አብዲ አለማየሁ ደግሞ በ 6 ወር ቀላል እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡
የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው፡፡
የመረጃ ባለቤት ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እየወጡ ነው።
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የማስወጣት ስራ ከተጠናቀቀ በኃላ በኣክሱም ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎችን የማስወጣት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
በዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸው ሲከታተሉ ከቆዩ ተማሪዎች መካከል፤ ግማሽ ያህሉ ትላንት ምሽት በአፋር ክልል ወደሚገኘው ሰመራ ዩኒቨርስቲ መግባታቸውን ተማሪዎችን ዋቢ አደርጎ "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል።
ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በኣክሱም ዩኒቨርስቲ ተመድበው ሲማሩ የቆዩ ተማሪዎች ብዛት 3,500 እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ትላንት 1,820 ተማሪዎች አፋር ገብተዋል ተብሏል።
ተማሪዎቹ አፋር እና ትግራይን በምታዋስነው “መዝአለት” በተባለች አነስተኛ ወረዳ ላይ ሲደርሱ ተማሪዎቹን ለማስመለስ የተቋቋመው ቴክኒካል ኮሚቴ አባላት ተቀብለዋቸዋል።
የአብኣላ ከተማ ነዋሪዎችም ተማሪዎችን የጫኑ ከ20 የሚበልጡ አውቶብሶች ትናንት ማምሻውን ከተማውን ሲያቋርጡ መመልከታቸውን ለድረገፁ ተናግረዋል።
በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ያሉ የዓይን እማኞችም የኣክሱም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በ28 አውቶብሶች ተጭነው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ትላንት ደርሰዋል ብለዋል።
ተማሪዎችን ለማስመለስ የተቋቋመው ኮሚቴ በኣክሱም ዩኒቨርስቲ ያሉ ተማሪዎችን በሁለት ዙር ለመመለስ 60 አውቶብሶችን አዘጋጅቶ ሲጠባበቅ እንደነበር ተነግሯል።
የማስመለስ ሂደቱን ከተቻለ በሁለት ቀን ለማጠናቀቅ እቅድ እንዳለ ተጠቁሟል።
የመረጃ ባለቤት ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

ድል ለሀገራችን ! ዛሬ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሀገራችን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው ውድድሮች ይካሄዳሉ። የመጀመሪያው ውድድር ቀን 8:00 ላይ የሚካሄድ ሲሆን የወንዶች 5,000 ሜትር #ማጣርያ ነው። በዘህም ውድድር ጌትነት ዋለ ፣ ንብረት መላክ እና ሚልኬሳ መንገሻ ሀገራችንን ይወክላሉ። ቀን 9:25 ላይ ደግሞ የሴቶች 800 ሜትር #ፍፃሜ የሚካሄድ ሲሆን ሀብታም አለሙ ብቸኝነት ሀገራችንን ኢትዮጵያ ትወክላለች።…
#Tokyo2020 🇪🇹 #ETHIOPIA
የ5,000 ሜትር የወንዶች ማጣርያ የመጀመሪያ ምድብ ተካሂዷል።
በዚህም መሰረት በማጣርያው የተወዳደሩት ጌትነት ዋለ እና ንብረት መላክ ወደ ቀጣዪ ዙር ማለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።
አትሌት ጌትነት ዋለ ዘጠነኛ በመሆን አትሌት ንብረት መላክ ደግሞ አስራ አራተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

የውጤት መግለጫ : የ5000 ሜትር የወንዶች ማጣሪያ የመጀመሪያ ምድብ ተካሂዶ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ማለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።
በውድድሩ የተሳተፉ ከአንድ እስከ አምስተኛ ደረጃን የያዙ አትሌቶች በቀጥታ ወደቀጣይ ውድድር ማለፍ የቻሉ ሲሆን ኢትዮጵያን የወከሉት አትሌቶች 9 እና 14 ደረጃን ይዘው ነው ያጠናቀቁት።
አትሌቶቻችን የገቡበት ሰዓት ፦
- አትሌት ጌትነት ዋሌ 13:41.13 (9ኛ ደረጃ)
- አትሌት ንብረት ማላክ 13:45.81 (14ኛ ደረጃ)

#ምድብ_2
የውጤት መግለጫ : በሁለተኛው ምድብ የተወዳደረው አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ ውድድሩን ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።
በሁለቱ ምድቦች በማጣርያው የተመዘገበውን ሰዓት ተከትሎ ከ ስድስተኛ ደረጃ በኋላ ያጠናቀቁ አትሌቶች በ ምርጥ ሰዓት የተሻለ የሆነው ወደ ፍፃሜው የሚያልፍ አትሌቶች የሚገለፁ ይሆናል።
በ5,000 ሜትር ውድድር ከአንድ እስከ አምስት የወጡ አትሌቶች በቀጥታ የሚያልፉ ይሆናል።
የ5,000 ሜትር የፍፃሜ ውድድሮች በመጪው አርብ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል።

#ምድብ_2 የውጤት መግለጫ : በሁለተኛው ምድብ የተወዳደረው አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ ውድድሩን ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል። በሁለቱ ምድቦች በማጣርያው የተመዘገበውን ሰዓት ተከትሎ ከ ስድስተኛ ደረጃ በኋላ ያጠናቀቁ አትሌቶች በ ምርጥ ሰዓት የተሻለ የሆነው ወደ ፍፃሜው የሚያልፍ አትሌቶች የሚገለፁ ይሆናል። በ5,000 ሜትር ውድድር ከአንድ እስከ አምስት የወጡ አትሌቶች በቀጥታ የሚያልፉ ይሆናል።…
አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።
ኢትዮጵያን ወክለው በ5 ሺህ ሜትር ውድድር ከተሳተፉ ሶስቱ አትሌቶች መካከል ሚልኬሳ መንገሻ ብቻ በተሻለ ሰዓት ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።
አትሌት ሚልኬሳ በሁለተኛው ምድብ ውድድሩን በ6ኛ ደረጃ ቢያጠናቅቅም የተሻለ ሰዓት አስመዝግቦ ነው ወደፍፃሜ ያለፈው።
በመጀመሪያው ምድብ የተወዳደሩት ጌትነት ዋለ እና ንብረት መላክ ወደ ፍፃሜ ማለፍ አልቻሉም።
Photo Credit : AMAN

አትሌት ሀብታም አለሙ 6ኛ ወጥታለች።
በቶኪዮ ኦሎምፒክ የ800 ሜትር ውድድር ሀገራችን ኢትዮጵያን የወከለችው አትሌት ሀብታም አለሙ በፍፃሜው ውድድር ስድስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
ሀብታም ስድስተኛ ደረጃን ይዛ ባጠናቀቀችበት የዛሬው ውድድር የአመቱን ምርጥ ሰዓቷን ማስመዝገብ ችላለች።
@tikvahethsport
በቶኪዮ ኦሎምፒክ የ800 ሜትር ውድድር ሀገራችን ኢትዮጵያን የወከለችው አትሌት ሀብታም አለሙ በፍፃሜው ውድድር ስድስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
ሀብታም ስድስተኛ ደረጃን ይዛ ባጠናቀቀችበት የዛሬው ውድድር የአመቱን ምርጥ ሰዓቷን ማስመዝገብ ችላለች።
@tikvahethsport
ድል ለሀገራችን !
አትሌት ለተሰንበት ግደይ፣ ሌሊሳ ዴሲሳን ፣ አትሌት ሹራ ቂጣታን ጨምሮ ሌሎች ተጠባቂ የኢትዮጵያ ተወዳዳሪዎችን ያቀፈው የመጨረሻው የሀገራችን ልዑካ ዛሬ ምሽት ወደ ጃፓን ይበራል።
ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንደተገኘው መረጃ ዛሬ ወደጃፓን የሚያቀናው ልዑካ በ15 አባላት ያሉት ነው።
በውድድር ቅደም ተከተላቸው መሰረት በማራቶን በሁለቱም ፆታ የሚሳተፉ አትሌቶች፣ በ10000 ሜትር ሴቶች የሚሳተፉ አትሌቶች፣ አመራሮችና አሰልጣኞች የሚጓዙ ይሆናል፡፡
በዚህም መሰረት በዚህ ምሽት የሚጓዘው የልዑካን ቡድን ፦
1.አቶ ቢልልኝ መቆያ የአትሌቲክስ ቴክኒክ ቡድን መሪ
2. አሰልጣኝ ሃጂ አዴሎ የማራቶንን አሰልጣኝ
3. አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ የማራቶን አሰልጣኝ
4. አሰልጣኝ ቶሌራ ዲንቃ የረጅም ርቀት አሰልጣኝ
5. አሰልጣኝ ኃይሌ እያሱ የረጅም ርቀት አሰልጣኝ
• ማራቶን ሴቶች ፦
6. አትሌት ትዕግስት ግርማ
7. አትሌት ብርሃኔ ዲባባ
8. አትሌት ሮዛ ደረጄ
9. አትሌት ዘይነባ ይመር (ተጠባባቂ)
• ማራቶን ወንዶች ፦
10. አትሌት ሹራ ቂጣታ
11. አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ
12. አትሌት ሲሳይ ለማ
• 10,000 ሜትር ሴቶች ፦
13. አትሌት ለተሰንበት ግደይ
14. አትሌት ፅጌ ገ/ሰላማ
15. አትሌት ፀሃይ ገመቹ
መረጃው የተገኘው ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው።
ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ !

የሶማሌ ክልል ተፈጥሯል በተባለው የዋጋ ግሽበት ላይ ሥ/አስፈጻሚ ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ።
ሰሞኑን በመላው የሱማሌ በክልል አከባቢዎች የምግብ ዋጋ እየጨመረ መምጣቱንና አግባብነት የሌለው የዋጋ ግሽበት መፍጠሩ ተገልጿል።
ለዋጋ ንረት ዋና ዋና ምክንያቶች የተባሉት:-
1. በክልሉ የሚመረተው የምግብ ምርቶች በጣም ዝቅተኛ መሆን
2. ህዝቡ የሚጠቀምበት ምግቦች ከውጭ የሚገቡ በመሆናቸውና ለክልሉ ነጋዴዎች በኢትዮጵያ ገንዘብ የማይሸጡለትና ከፍተኛ ዶላር የሚጠይቁ በመሆናቸው
3. የሶማሌ ክልል ነጋዴዎች ብሔራዊ ባንክ የሚሰጠውን የውጭ ምንዛሬ ለማግኘትና የዶላር ምንዛሬ ተመን ለመቀበል የብሔራዊ ባንክ የምንዛሬ ጊዜን ለመጠበቅ ትዕግስት የሌላቸው መሆናቸውና በርካታ ነጋዴዎች የሚመረጡትን የጥቁር ገበያ ምንዛሬ ላይ ከፍተኛ የሀገሪቱ ብርና አነስተኛ የዶላር ገንዘብ በማጋጠሙ የዋጋ ግሽበት ችግር ፈጥራል።
4. በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰጩና አገሪቱ እየፈረሰች ነው እየተበታተነች ነው..የሚሉት ሀሰተኛ መረጃዎች ሰምቶ ትንሽ ብር ያላቸው ሰዎች ወደ ዶላር በመቀየራቸውን የዋጋ ግሽበቱ ምክንያት ሆኗል።
ችግሩን ለመፍታት የተወሰነው የውሳኔ ፦
1. በአስቸኳይ የመንግስት ምግብ አስመጪ ድርጅት ማቋቋም።
2. የፌዴራል መንግሥት በክልሉ ከቀረጥ ነፃ ምግብ እንዲገባ ፈቅድ እንዲሰጥ መጠየቅ።
3. ነጋዴዎች እንደተለመደው ሱቆቻቸውን ወይም መጋዘኖቻቸውን መዝጋት እንደለለባቸውምና የምግብ እቃዎችን በመደኛ ዋጋ መሸጥ እንዳለባቸው እንዲሁም ከመደኛ ውጭ ምግብን በስህተት እየሸጡ የተገኘ ሁሉ በህግ መጠየቅ።
4. የምንዛሬ ተመንና የገንዘብ ምንዛሬ ጭማሪና ለውጥ እንዲደረግ ተግባራት ላይ የተሳተፉ ባንኮች፣ የገንዘብ አስተላላፊ ኩባንያዎችና ግለሰቦች በአስቸኳይ እርምጃ መውሰድ።

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 6,297 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 467 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ አራት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 191 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።