TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Hawassa

ሃምሌ 19 በድምቀት ለሚከበረው የሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በበዓሉ ዙሪያ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ከሀይማኖት አባቶችና የበዓሉ ዝግችት ኮሚቴ ጋር ከቀናት በፊት ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ ትኩረት አድርጎ የነበረው የእንግዶች አቀባበል፣ የትራፊክ ፍሰት ማስተናበር፣ የፀጥታ ሁኔታ እና ሌሎች በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ነበር።

ዛሬ ጥዋት ደግሞ የሐዋሳ ከተማ እና የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ከለብ ደጋፊዎች የንግስ በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ የጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል።

የቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ መላከ ሠላም አባ ኃ/ጊዮርጊስ ማህጽነት የሁለቱ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

በአሉ እስኪጠናቀቅ እንግዶችን በመቀበል በማስተናገድ የተለመደውን ትበብር እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ዛሬ ከተካሄደው የፅዳት ዘመቻ ጋር በተያያዘ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ደስታ ዳንኤል በሰጡት አስተያየት "የጽዳት ዘመቻ አንድነትን መከባባርን የሚያመለክት ነው" ሲሉ ገልፀዋል።

Photo Credit : Hawassa City Administration (3)
ተጨማሪ ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
"እናቴ በጭንቀት ታማለች"

ከሳምንታት በፊት የታሰሩት የአውሎ ሚዲያ ጋዜጠኞች እና ሰራተኞች እስካሁን ያሉበትን እንደማያውቁ ቤተሰቦቻቸው ዛሬ በስልክ ሪፖርት አድርገውልናል።

እስር ላይ ካሉ የአውሎ ሰራተኞች መካከል የአንድ ታሳሪ የቤተሰብ አባል የሆነች እንስት ጋዜጠኞቹና የሚዲያ ሰራተኞቹ የት እንዳሉ ቤተሰብ ባለማወቁ ለከፍተኛ ጭንቀት መዳረጋቸውን ገልፃለች።

ቤተሰብ ስላለበት ሁኔታ እንደሚከተለው አስረድታለች፦

" ... ያሉበት አይታወቅም ይህ ነው አስጨናቂው ነገር ፤ ቢታወቅ እና ብንጠይቃቸው መልካም ነበር። ማንም ሰው ሊታሰር ይችላል ምንም ችግር የለውም፤ መንግስት የያዘው ነገር ከሆነ አያስፈራም። ምግብ እስከሰጠን፣ ልብስ እስከሰጠን ድረስ፣ መጎብኘት እስከቻልን ድረስ፣ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብታቸው እስከተጠበቀ ድረስ ችግር የለውም መንግስት የራሱን መልስ እስከማሰጥ እንጠብቃለን። ነገር ግን ያሉበትን ባለመታወቁ ለቤተሰብ ከፍተኛ ጭንቅ ነው። ለምሳሌ እናቴ ታማለች። የሌሎቹም ልጆች ያሏቸው ልጆቻው ያልቀሳሉ፣ እናት አባቶችም ያለቅሳሉ እነሱ ያሉበት ባለመታወቁ የብዙዎቹ ቤተሰቦች ህይወት ተመሰቃቅሏል"

በታሰሩ በነጋታው ወደ ፌዴራል ፖሊስ ሄደው እንዳገኟቸው እዛ እንደሆኑ ታውቆ እንደነበር የገለፀችልን የታሳሪ ቤተሰብ አባሏ፣ "ፖሊስ አጣርቶ ይለቃቸዋል በሚል ቤተሰብ ወደቤት ተመለሰ በነጋታው ግን የሉም ተባልን"

የት ሄዱ? የት ተወሰዱ? ስለሚለው ጉዳይ ምንም ነገር አይገልፁልንም፤ ፈተናቸዋልም ብለውናል ፤ ፈተናቸዋል ማለታቸው ደግሞ ይበልጥ ቤተሰብን ጭንቀት ውስጥ ከቶታትል ስትል አስተድታለች።

መንግስት ስላሉበት ሁኔታ ለቤተስቦች ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቃለች።

* በጋዜጠኞቹ እና ሰራተኞቹ ጉዳይ አካልን ነፃ የማውጣት አቤቱታ ለፍ/ቤት ቀርቦ ለሰኞ ተቀጥሯል።

@tikvahethiopia
#AFAR

"...እነሱ ለሚፈፅሙት እያንዳንዱ ድርጊት አፀፋዊ ምላሽ መስጠት ለኛ በጣም ቀላል ነው ፤ ይህንንም እናደርገዋለን" - አቶ አወል አርባ

ትግራይ ክልልን ከአፋር ክልልና አማራ ክልል በሚያዋስኑ አካባቢዎች ስላለው መሬት ላይ ያለ ሁኔት በግልፅ በዝርዝር ባይታወቅም አሁንም ድረስ ወታደራዊ ግጭቶች ስለመኖራቸው የሚገልፁ ጥቆማዎች አሉ።

በአካባቢው ላይ ባለው ግጭት ምክንያት ሺዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተፈናቅለዋል።

የአፋር ክልል ፕሬዜዳንት የሆኑት አቶ አወል አርባ በወቅታዊ የክልሉ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ አወል አርባ ፥ በአሁን ሰዓት ህወሓት አጠቃላይ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ዓላማ አንግቦ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል።

"እኛ ኢትዮጵያን ከመራን ኢትዮጵያዊ ነን፤ ኢትዮጵያን ካልመራን ግን ኢትዮጵያዊ አይደለንም ስለዚህ ኢትዮጵያን አፍርሰን እራሳችን መንግስት እንሆናለን የሚል ዓላማ ይዘው የመጡት አሁን ሳይሆን በ1968 ጫካ በነበሩበት ወቅት የፃፉት መፅሃፍ በግልፅ ምስክ እንደሆነና ዶክመቱም በታሪክ ድርሳናት እጅ ይገኛል" ሲሉ ተደምጠዋል።

አቶ አወል ፥ ሽብርተኛ ተብሎ ለተፈረጀው ህወሓት ለሚፈፅመው እያንዳንዱ ድርጊት አፀፋዊ ምላሽ መስጠት እንችላለን ፤ መንገዶችን በህፃናት ለማዘጋት ሞክረዋል፤ እነሱ ላደረጉት ተግባር አፀፋ መስጠት ለኛ ቀላል ነው ይህንንም እናደርገዋለን ብለዋል።

የአፋርን ህዝብ ሰብዓዊነት የጎደለው ትግባርን በመፈፀም አንበረክከዋለሁ ማለት የማታሰብ ነው ያሉት ፕሬዜዳንቱ አፋር በታሪኩ የሽንፈት ታሪክ አጋጥሞት አያውቅም በአሸባሪነት የተፈረጀውን 'ህወሓት' በተባበረ ክንድ እንፋለመዋለን ፤ ዳግም ላይመለስ የሚገባውን ዋጋ በሚገባው ቋንቋ እንሰጠዋለን ሲሉ ዝተዋል ።

ያንብቡ : telegra.ph/Afar-07-24

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 4,873 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 213 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ ሁለት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 98 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia
#Tokyo2020

የ12 ዓመቷ ሶሪያዊ ታዳጊ በቶኪዮ ኦሎምፒክ !

በዘንድሮው የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል ሶርያ ትገኝበታለች።

በውድድሩ ላይ በእድሜ ትንሿን ተወዳዳሪ የምታሳትፈው ሶርያ ስትሆን ተወዳዳሪዋ የ12 ዓመቷ ሄንድ ዛዛ ናት ፤ ዛዛ በጠረጴዛ ቴኒስ ነው ሀገሯን ሶሪያ ወክላ በዓለም አቀፉ ውድድር የሚትፋለመው።

የቶኪዮ በእድሜ ትንሿ ተወዳዳሪ ሄንድ ዛዛ በ ኦሎምፒክ የ መጀመሪያ ጨዋታዋ ብትሸነፍም ሌሎች ሕፃናት “ ሕልማቸውን እንዲከተሉ ” ታበረታታለች።

በልጅነቷ በሀገሯ በጦርነት የተጎዳችው ዛዛ ወደ ውድድሩ ለመድረስ “ብዙ የተለያዩ ችግሮችን” ማለፍ እንደነበረባት ተናግራለች።

የቶኪዮ መረጃዎችን ይከታተሉ : @tikvahethsport
Audio
AudioLab
በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን፤ አሙሩ ወረዳ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች በሚደርስባቸው ''ዛቻና ማስፈራሪያ'' ወፌና ኢላሞ ከሚባሉ የገጠር ከተሞች ተሰደው በአጋምሳ ከተማ በሚገኝ ት/ቤት ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጸውልናል።

* የድምፅ ፋይሉን ያዳምጡ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
AudioLab
በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን፤ አሙሩ ወረዳ የሚገኙ የአማራ ብሔር ተወላጆች በሚደርስባቸው ''ዛቻና ማስፈራሪያ'' ወፌ እና ኢላሞ ከሚባሉ የገጠር ከተሞች ተሰደው በአጋምሳ ከተማ በሚገኝ ት/ቤት ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጸውልናል።

በቁጥር 11 ሺ ይሆናሉ የተባሉት ነዋሪዎች ወደ አማራ ክልል በመሰደድ ላይ እያሉ ተከልክለው በትምህርት ቤቱ መጠለላቸውን ችግራቸውን ለማስረዳት ወደ አዲስ አበባ ሰላም ሚኒስቴር የመጡት ሼህ ሀሰን መሐመድ ይናገራሉ።

ከእነዚህ ከተሞች በተጨማሪ በብዙ ሺ የሚቆጠር ህዝብ በገጠር እንደሚገኝም አስረድተዋል።

ጉዳዩን ለማስረዳት ወደ አዲስ አበባ የመጡት አራት ሆነው እንደሆነ የሚገልጸው ካሳነው አህመድ ከአከባቢው 40 አባወራ አስቀድመው መውጣታቸውንና አሁን ላይ በዛህ ለሚገኙ ወገኖቻቸው ለማመልከት እንደመጡ ይናገራል።

''አሁን ላይ ህይወታቸውን በእንዴት እንደሚያመልጡና እንደሚያተርፉ ለማመልከት ነው የመጣነው'' ሲል በጹሑፍ ለሰላም ሚኒስቴር ማስገባታቸው፤ ሆኖም የሚያናግራቸው እንዳላገኙ ይናገራል።

በወረዳው የኦነግ ሸኔ ኃይል በምን ደረጃ ይገኛል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም ''አከባቢው ላይ ወዲያ ወዲህ ሲል የሚታየው "ኦነግ ሸኔ" ነው መሳሪያ እናከፋፍላለን እስከማለትም ደርሰዋል'' ሲል ምላሹን ያስቀምጣል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-25

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ትግራይ ክልልን ከአማራ እና አፋር ክልል በሚያዋስኑ አካባቢዎች ግጭቶች መቀጠላቸውን የሚያመላክቱ ጥቆማዎች እየወጡ ነው።

በአካባቢው ስላለው ሁኔታ ተጨባጭ የሆነ መረጃ ማግኘት አዳጋች ሆኗል ፤ ዝርዝር መረጃም ማግኘት አልተቻለም።

በግጭቱ ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እየተፈናቀሉ ናቸው።

ከቀናት በፊት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ ፥ "ህወሓት" በአፋር ላይ ክፍቶታል ያሉትን ጥቃት የክልሉ ሕዝብ ተጥቅ አንግቦ ራሱን እንዲከላከል ጥሪ አቅርበው ነበር።

ርዕሰ መስተዳዳሩ ማንኛውም አፋር ባለው የጦር መሳርያ ምድሩን ያስጠብቅ ዘንድ ነው ጥሪ አቅርበው የነበረው፤ ይህም በአለም አቀፍ ሚዲያዎች ተዘግቦ ነበር።

ዛሬ ደግሞ የአማራ ክልል ር/መስተዳደር የሆኑት አቶ አገኘሁ ተሻገር በክልሉ ውስጥ የማንኛውም የመንግሥትን መሳሪያ የታጠቀ፣ የግል መሣሪያ የታጠቀ፣ ለግዳጅ ብቁ የሆነ ወጣት ሁሉ ከነገ ጀምሮ ለህልውናው ዘመቻ እንዲዘምት የክተት ጥሪ አስተላልፈዋል።

አቶ አገኘሁ ከተናጠለ ተኩስ አቁሙ በኃላ የህወሓት ቡድን በራያ፣ በወልቃት ፣ በዋግ እንዲሁም በጠለምት ግንባሮች ጥቃት መክፈቱን የገለፁ ሲሆን ሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የክልል ልዩ ኃይሎች በጥምረት በወሰዱት የማጥቃት እርምጃ በቡድኑ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሱበት እንደሆነ ተናግረዋል።

በትግራይ ክልል የነበረው ግጭት በጀመረበት ወቅት ክልሉን ሲያስተዳድር የነበረው እና በህ/ተ/ም/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የ ''ህወሓት ቡድን" የትግራይ ህዝብ ባለው የጦር መሳሪያ ሁሉ ወጥቶ እንዲታገል ጥሪ ሲያቀርብ እንደነበር አይዘነጋም፤ አሁን ላይ ደግሞ የአፋር እና አማራ ክልል መሪዎች ለህዝባቸው የክተት አዋጅ አውጀዋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

'MIND ETHIOPIA' በኢትዮጵያ ሁሉን አካታች ሀገራዊ ምክክር እንዲኖር በቅርቡ ሀገራዊ የውይይት መድረክ እንደሚያዘጋጅ ማስታውቋል።

MIND ETHIOPIA የሰላም ሚኒስቴርን ጨምሮ 8 የሀገር ዓቀፍ ድርጅቶች ጥምረት ነው።

ሀገሪቱ አሁን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ሀገራዊ ምክክር በ1 ቀን ተደርጎ የሚቆም ሳይሆን ሒደት እና ቀጣይነት ያለው መሆኑን MIND ETHIOPIA ገልጿል፡፡

የዴስቲኒ ኢትዮጵያ አስተባባሪና የMIND ETHIOPIA አባል የሆኑት አቶ ንጉሱ አክሊሉ ፥ "ኢትዮጵያ ተለዋዋጭ የፖለቲካ ሁኔታ ያላት በመሆኑ ሁሉን አካታች ሀገራዊ የምክክር መድረክ ለማድረግ ጠንካራ ሒደቶች እና ሕዝባዊ ድጋፍ ያስፈልጋል፤ ለዚህም ከሀገር ውስጥ እስከ ዴያስፖራው ማሕበረሰብ ድረስ በመነጋገር ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው" ብለዋል።

አቶ ንጉሱ አክለው ፥ ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ዓመታት የገጠሟት የማንነት ፤ የድንበር፤ የሕገ መንግስት ብሎም የታሪክ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች በጠረጴዛ ዙሪያ መፈታት እንዳለባቸው ገልጸው ለዚህም ከወር በኋላ ትልቅ ሀገራዊ የምክክር መድረክ እንደሚኖር አስታውቀዋል፡፡

ሀገራዊ ምክክርን ' በሕግ አግባብ ' ከሚፈቱ ግጭቶች መለየት እንደሚገባ አስገንዝበዋል አቶ ንጉሱ ስለማስገንዝበባቸው አሀዱ ሬድዮ በድረገፁ ላይ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ 'MIND ETHIOPIA ' ኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካዊ ንግግር እና እርቅ እንዲፈጠር እያደረገ ያለው ጥረት ደግፋለሁ ብሏል።

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ጄፍሪ ፊልትማን ፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እና የUSAID ተወካዮች ከ 'MIND ETHIOPIA' ጋር መወያየታቸው ታውቋል።

ውይይቱ የነበረው 'MIND ETHIOPIA' በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ንግግር እንዲጀመር እና በብሄራዊ እርቅ እንዲሰፍን በሚያደርገው እንቅስቃሴ ዙሪያ እንደነበር ተሰምቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ItsMyDam🇪🇹 ዛሬ ይፋ በተደረገው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ማድረጊያ የድረገፅ ፕላትፎርም ዜጎች ድጋፍ ማድረግ ጀምረዋል። Mygerd.com የተሰኘው ድጋፍ ማድረጊያ ድረገፅ ይፋ በተደረገ በደቂቃዎች ውስጥ 36 ሰዎች ባደረጉት ልገሳ ስለማድረጋቸው ታውቋል። በዚህም 1,899 የአሜሪካ ዶላር ሊሰበሰብ ችሏል። አምስትሰዎች ለሌሎች በማስተዋወቅ ዘመቻውን ስለመቀላቀላቸው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ…
#ItsMyDam🇪🇹

Mygerd.com ይፋ መደረጉ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያሉ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ህዳሴ ግድብን በገንዘብ እንዲደግፉና አሻራቸውን ዕድል ፈጥሯል።

እስካሁን 291 ሰዎች ባደረጉት ስጋፍ 23,410 የአሜሪካ ዶላር ተሰብስቧል፡፡ 28 ሰዎች ደግሞ ለሌሎች በማስተዋወቅ ዘመቻውን ተቀላቅለዋል፡፡

ድጋፉ ቀጥሏል፡፡ ግድቡም ይጠናቀቃል።

#የኢኤኃ

@tikvahethiopia
#Somali

በሶማሌ ክልል መዲና ጅግጅጋ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመው የበደር የትራንስፖርት ማህበር በዛሬው እለት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሀግብር ተካሄደ፡፡

ማህበሩ በከተማ ትራንስፖርትና በመካከለኛ ሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት ዘርፍ የሚሰማራ ሲሆን በቅድሚያም አገልግሎቶቹን በጅግጅጋ ፤ ቱጉጫሌ ፤ ደገሀቡርና ድሬዳዋ ከተሞች እንደሚጀምርም ነው የተገለፀው፡፡

#SRTV

@tikvahethiopia
PHOTO : 2ኛው የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ የቶኪዮ ተሳታፊ ቡድን ጃፓን ገባ።

ቡድኑ ትላንት ምሽት ወደ ቶኪዮ፣ ጃፓን የተጓዘ ሲሆን #ቶኪዮ በሰላም ደርሷል።

በድኑ ቶኪዮ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ፦
- ዶ/ር ሂሩት ካሳው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር፣
- ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ የኢአፌ ፕሬዝዳንት፣
- የኢትዮጵያ ኦምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ
- የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዋና ፀሀፊ አቶ ዳዊት አስፋው
- ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር
- ዶ/ር በዛብህ ወልዴ የኢአፌ አቃቤ ንዋይ የአትሌቲክስ ቡድን መሪ ኤርፖርት ተገኝተው ለቡድኑ አቀባበል አድርገውለታል።

#EAF #DrFethWeldesenbet

@tikvahethiopia