TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Eid_al_Adha

በዓለም ላይ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች የዛሬውን የኢድ አል አደሃ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ሲያከብሩት ውለዋል።

ከላይ በተለያዩ ሀገራትና አካባቢዎች የነበረውን የበዓል ድባብ የሚያሳዩ ፎቶዎችን እንድትመለከቷቸው ልከንላችኃል።

ፎቶዎቹ ፦
- በአል አቅሳ መስጊድ (እየሩሳሌም)
- በታላቁ ካምሊካ መስጊድ (ቱርክ፤ ኢስታንቡል)
- በኢራቅ (ኪርኩክ)
- በኬንያ (ናይሮቢ)
- በየመን (ሰንዓ)
- በአፍጋኒስታን (ሄራት)
- በሱማሊያ (ሞቃዲሾ) የነበረውን የበዓል ድባብ የሚያሳዩ ናቸው።

የፎቶ ባለቤቶች : AFP , AP , Anadolu , EPA , Reuters

@tikvahethiopia
#Tokyo2020

ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ !

በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ 🇪🇹 አትሌቲክስ ቡድን የመጀመሪያው ዙር ተጓዥ ቡድን ዛሬ ምሽት ወደቶኪዮ ይበራል። አትሌቶቻችን በሰላም እንዲገቡ እንመኛለን። በመጪው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ የሀገራችንን ስም በዓለም መድረክ ከፍ እንደሚያደርጉ ባለሙሉ ተስፋ ነን።

Photo Credit : EPA

@tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ወቅታዊ እና የሰብዓዊ ድጋፍ ሁኔታ ፦

የትግራይ ክልል ከአፋር ክልል እና አማራ ክልሎች ጋር በሚያዋስኑት አካባቢዎች ግጭቶች ስለመቀጠላቸው ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ከቀናት በፊት የህወሓት ታጣቂዎች ወደአፋር ክልል ዘልቀው ጥቃት ስለመፈፀማቸው መግለፃቸው አይዘነጋም።

በየአካባቢው ስላሉ መረጃዎች በመከላከያም ሆነ በሌሎች አካላት ዝርዝር መረጃ ባይሰጥባቸውም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተለያየ ያልተረጋገጡ መረጃ በስፋት ይሰራጫሉ።

መሬት ላይ ስላለው የወታደራዊ እንቅስቃሴ የተለያዩ አክቲቪስቶች እና የማህበራዊ ሚዲያዎች ከሚያሰራጩት መረጃ ውጭ በግልፅ እና በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።

ከዚህ ቀደም ፌዴራል መንግስት የተኩስ አቁሙን እያከበረ ትንኮሳ ሲፈፀምበት አስፈላጊውን የኃይል እርምጃ እንደሚወስድ ማሳወቁ አይዘነጋም።

ከትላትና በስቲያ ከሳምንታት በኃላ ወደሚዲያ ብቅ ያሉት የኢትዮጵያ ጦር ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ፥ ሰራዊቱ የሚሰጠውን ግዳጅ ለመወጣት በአስተማማኝ ቁመና ላይ መሆኑን ሲናገሩ ተደምጠዋል።

TPLF የትግራይ ህዝብ ማዕከሌ ነው የሚል ከሆነ እስካሁን ህዝቡን ያሰቃየው እንደሚበቃው አውቆ ለ3ኛ ዙር ቆም ብሎ እንዲያስብ ፤ መንግስት ያመቻቸውን የተናጠል የተኩስ አቁም እሱም ተግብሮ የሚፈልገውን ፖለቲካዊ ጥያቄ መደራደር እንዳለበት እንመክራለን ብለዋል ጄኔራሉ።

ከዚህ ውጭ በቅድመ ሁኔታ ተሽቆጥቁጦ ሰላም ሊመጣ እንደማይችል መታወቅ አለበት ፤ ቅድመ ሁኔታ ደርድሮ እዚህ ውስጥ ተገብቶ ነው የምደራደረው የሚለው ተቀባይነት አይኖረውም ሲሉም ተደምጠዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-07-21

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲስ ስታንዳርድ በጊዜያዊነት ታግዷል፤ ለምን ? አዲስ ስታንዳርድ ትላንት በፌስቡክ ገፁ ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለጃከን አሳታሚ የተሰጠውን ፈቃድ በጊዜያዊነት ማገዱን ገልጿል። ባለሥልጣን መ/ቤቱ ፈቃዱን ያገደበት ምክንያት አላብራራም ብሏል ፤ የሚዲያ ሥራዎቹንም ከሐምሌ 8/2013 ጀምሮ በጊዜያዊነት ማቆሙን የጃከን አሳታሚ አሳውቋል። ኩባንያው በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ላይ በሰፈረው…
አዲስ ስታንዳርድ ላይ የተጣለው ጊዜያዊ እገዳ ተነስቷል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በአዲስ ስታንዳርድ የበየነ መረብ ሚዲያ ላይ የጣለውን ጊዜያዊ እገዳ ማንሳቱን ተሰምቷል።

ባለሥልጣኑ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ውይይት ማድረጉን ተከትሎ ነው እገዳውን ለማንሳት መወሰኑን ያስታወቀው።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ፣ ሁለቱ አካላት ባደረጉት ውይይት መግባባት ላይ መድረሳቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል፡፡

:አዲስ ስታንዳርድ' በሕወሓት የሚመራውን ኃይል “የመከላከያ ኃይል” ብሎ እውቅና እስከመስጠት በመድረስ የሽብር ቡድኑ አጀንዳ ማራመጃ መድረክ ሆኗል” በሚል ሚዲያውን በጊዜያዊነት ማገዱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

እገዳው መነሳቱን በማስመልከት በድረገጹ መግለጫ ያወጣው አዲስ ስታንዳርድ፣ አስቀድሞም እገዳ የተጣለበት ከሕግ አግባብ ውጭ መሆኑን ገልጿል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ግን ከሚዲያው ጋር በተያያዘ ያሉ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች ቀጣይ መዘዛቸው ስለማይታወቅ እገዳ አንስቶ ለመወያየት መምረጡን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መሀመድ ተናግረዋል፡፡

አዲሱ የሚዲያ ዐዋጅ በቅርብ ጊዜ የወጣ ከመሆኑ ባለፈ ዐዋጁ በሚደነግገው መሰረት ገና ቦርድ አለመቋቋሙን የገለጹት አቶ መሀመድ፣ ተቋሙ በሽግግር ላይ ከመሆኑ እና ሀገሪቱም ካለችበት ሁኔታ አንጻር በባለስልጣኑ ውሳኔዎች ዙሪያ የሚፈጠሩ ክፍተቶች እንደሚኖሩ አምነው በመነጋገር እየተሸሻሉ እንደሚሄዱ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን በአዲስ ስታንዳርድ ላይ ጊዜያዊ እገዳ ከጣለ በኋላ፣ ሁሉም ሚዲያዎች ከ "ሕወሓት" ጋር በተያያዘ የትግራይ መከላከያ ኃይል እና የትግራይ ክልል መንግስት የሚል ስያሜ እንዳይጠቀሙ የሚያስጠነቅቅ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል ሲል የዘገበው የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tokyo2020 ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ ! በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ 🇪🇹 አትሌቲክስ ቡድን የመጀመሪያው ዙር ተጓዥ ቡድን ዛሬ ምሽት ወደቶኪዮ ይበራል። አትሌቶቻችን በሰላም እንዲገቡ እንመኛለን። በመጪው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ የሀገራችንን ስም በዓለም መድረክ ከፍ እንደሚያደርጉ ባለሙሉ ተስፋ ነን። Photo Credit : EPA @tikvahethiopia
#Ethiopia 🇪🇹 #TokyoOlympics2020

በቶኪዮ 2020 (2021) በአትሌቲክሰ ሃገራችንን ከሚወክለው የልኡካን ቡድን መካከል የመጀመሪያ ዙር ተጓዥ የሆኑት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትና የቡድኑ ኦፊሻል ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉና የፌዴሬሽኑ አቃቤ ነዋይ እንዲሁም የአትሌቲክስ ቡድኑ መሪ የሆኑት ዶ/ር በዛብህ ወልዴ ትላንት ምሽት ወደ ጃፓን ቶኪዮ መጓዛቸውን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA🇪🇹

"..እንደ አንድ ትልቅ አገር ለማሸነፍ ተዘጋጅተናል" - ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዜዳንት የሆኑት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ በቶኪዮ ኦምፒክ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው ቡድን ውጤት ለማስመዝግበ በጣም ጥሩ የሚባል ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል።

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጡት ቃል ፥ "አንዳንድ ችግሮች አይታጡም ግን ዝግጅታችን በጣም ጥሩ ነው" ብለዋል።

አክለውም ፤ " ዓለም ለማሸነፍ ይዘጋጃል። እኛም እንደ አንድ ትልቅ አገር ለማሸነፍ ተዘጋጅተናል" ሲሉ ተናግረዋል። "ፈጣሪ ከረዳን ጥሩ ውጤት እናመጣለን ብለን እናስባለን" ያሉት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ "እንደ ልባችን እንዳንሰራ የረበሸን ነገር ኮቪድ-19 ወረርሸኝ ነው" ብለዋል።

በሌላ በኩል የረዥም ርቀት ዋና አሰልጣኝ የሆኑት ኮማንደር ሁሴን ሺቦ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል፥ "ሀገራችን ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ አትሌቶቻችንም፤ እኛም በአካልም በአእምሮም ዝግጁ ሆነናል" ብለዋል።

አሰልጣኝ ኮማንደር ሁሴን ፤በውድድር ላይ 4 ቡድን ማለትም የሴቶች እና የወንዶች 5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር ውድድሮችን እንደሚመሩ ተናግረው አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃን ለመያዝ አቅደን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

በተመሳሳይ ኢትዮጵያን ወክለው ቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ የሚወዳደሩ አትሌቶች የሀገሪቱን ስም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ለማድረግ እና ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ እንደተዘጋጁ ተናግረዋል።

ፎቶ ፋይል ፦ በ @tikvahethsport , Getty Image, ልዩ ስፖርት (ሃይለእግዚያብሄር ኣድሃኖም)

@tikvahethiopia
ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ ሀሙስ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለፅ ሰልፍ እንደሚያደረጉ ተገልጿል።

ሰልፉ በመስቀል አደባባይ እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን በእለቱ ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከለሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ የሚዘጉ መንገዶች፦

• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎፒያ አደባባይ
• ከመገናኛ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ
• ከ4 ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻወልዴ ችሎት/ ፓርላማ መብራት
• ከቸርችር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ እና አገር አስተዳደር መብራት ወይሚ ኢሚግሬሽን
• ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ
• ከተክለ ሀይማኖት፣በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ የኋላ በር
• ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ
• ከሳሪስ በጎተራ አጎና ሲኒማ እና አራተኛ ክፍለ ጦር
• ከጦር ኃይሎች፣ ልደታ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ
• ከጦር ኃይሎች፣ ልደታ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ፣ ሜክሲኮ ለገሀር መብራት የሚወስደው ለገሃር መብራት አካባቢ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳስቧል።

NB : ፖሊስ ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር የገለፀ ሲሆን የፕሮግራሙ ተዳሚዎች ይህን ተገንዝበው ለፍተሻ እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲስ ስታንዳርድ ላይ የተጣለው ጊዜያዊ እገዳ ተነስቷል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በአዲስ ስታንዳርድ የበየነ መረብ ሚዲያ ላይ የጣለውን ጊዜያዊ እገዳ ማንሳቱን ተሰምቷል። ባለሥልጣኑ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ውይይት ማድረጉን ተከትሎ ነው እገዳውን ለማንሳት መወሰኑን ያስታወቀው። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ፣ ሁለቱ አካላት ባደረጉት ውይይት መግባባት ላይ መድረሳቸውን ለአሜሪካ…
#Update

ላለፉት ቀናት ስራውን አቆርጦ የነበረው 'አዲስ ስታንዳርድ' የበየነመረብ ሚዲያ ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ወደ ስራው መመለሱን ገልጿል።

ዓመታትም በኦንላይን ሚዲያነት የሰራው 'አዲስ ስታንዳርድ' ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ከሚባሉት በጣም ጥቂት #በእንግሊዘኛ ቋንቋ የመረጃ ማቅረብ አገልግሎት የሚሰጥ ድረገፅ ነው።

ከሰሞኑን የኢመብባ "አዲስ ስታንዳርድ" በሕወሓት የሚመራውን ኃይል “የመከላከያ ኃይል” ብሎ እውቅና እስከመስጠት በመድረስ የሽብር ቡድኑ አጀንዳ ማራመጃ መድረክ ሆኗል” በሚል ሚዲያውን በጊዜያዊነት ማገዱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በኃላ ሁለቱ አካላት ውይይት አድርገው መግባባት ላይ ደርደው እገዳው ተነስቷል።

አዲስ ስታንዳርድ፣ አስቀድሞም እገዳ የተጣለበት ከሕግ አግባብ ውጭ መሆኑን ከእገዳው መነሳት በኃላ ባወጣው መግለጫ ገልፆ ነበር።

ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ድረገፁ ወደቀደመ መደበኛ አገልግሎቱ ተመልሷል።

@tikvahethiopia