የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች የምክር ቤት ተገኝተው ምን አሉ ?
- የክልሎች በጀት
- የኢኮኖሚ ሁኔታ
- የፋይናንስ ዘርፍ
- ገቢን ማሳደግ
- ፕሮጀክቶች
- የክልሎች በጀት
- ቱሪዝም
- ሕዳሴ ግድብ
- የትግራይ ሁኔታ
- ወታደሮችን የማውጣት ውሳኔው
- የዓለም-አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ዘገባ
- የሀገር መከላከያ በጀት
በአጭር በአጭሩ ያንብቡ : https://telegra.ph/PMO-07-05
NB : የጠ/ሚኒስትሩን የም/ቤት ቆይታ ድጋሚ በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ይተላለፋል ተብሎ ይታሰባል፤ በቴሌቪዥን ጣቢው የዩትዩብ አድራሻም ይገኛል፤ በስራ መደራረብ ጊዜ ለማታገኙ ከላይ የተያያዘው ሊንክ በአጭር በአጭሩ ማንበብ ትችላላችሁ።
@tikvahethiopia

#Tigray
"...ትግራይ ክልል የሚሄድ ማንኛውም ትራንስፖርት በመቋረጡ ደም ለማቅረብ አስቸጋሪ ሆኗል" - አቶ ያረጋል ባንቴ
የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ወደ ትግራል ክልል የሚላከው የደም አቅርቦት መቋረጡን ለአሀዱ ሬድዮ 94.3አስታውቋል።
ባንኩ በጤና ተቋማት በህክምና ላይ ላሉ ዜጎችና ግጭት ባለባቸው ቦታዎች ደም ለሚያስፈልጋቸው ክልሎች ደም በማቅረብ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ያረጋል ባንቴ እንደተናገሩት ወደ ትግራይ ክልል የሚሄድ ማንኛውም ትራንስፖርት በመቋረጡ ደም ለማቅረብ አስቸጋሪ ሆኗል ብለዋል።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ክልሉን ለቆ ከመውጣቱ አስቀድሞ መቐለ ለሚገኘው ደም ባንክ ለ2 ዓመት የሚያገለግል ደም ማቅረባቸውን የገለፁት አቶ ያረጋል አክሱም ላይ ምን አልባት የተወሰነ እጥረት ሊያጋጥም ይችላል ብለዋል። በሌሎች አካባቢዎች ግን ያን ያህል ችግር እንደሌለ አሳውቀዋል።
አቴ ያረጋል ፥ በክልሉ በጤና ተቋማት በህክምና ላይ ላሉ ህሙማን እንዲሁም ግጭት ከተከሰተ ተጨማሪ የደም አቅርቦት ስለሚያስፈልግ ዜጎች በበጎፍቃደኝነት እንዲለግሱ የማድረግ ስራ መሰራት አለበት ብለዋል።
በኢትዮጵያ የማይመከር ቢሆንም የመጨረሻ አማራጭ የሚሆነው የቤተሰብ ምትክ ደም ፈልጎ መጠቀም እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
በግጭቶች እና ጦርነቶች ጉዳት የሚደርስበት ካለ ፍላጎቱ ስለሚጨምር አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ባለሙያዎች ወደ ትግራይ ክልል እንዳይሄዱ የተደረገ ሲሆን ችግሩ ረጅም ጊዜ የሚዘልቅ ከሆነ የሚያሳስብ መሆኑ ገልፀዋል።
የመንግስትን አቅጣጫ በመከተል ወደፊት ተግባራዊ የሚሆኑ የሚሻሻሉ ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡
መረጃው አሐዱ ኤፍ ኤም 94.3 ነው።

#ምርጫ2013
(ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ/ም)
ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል።
መግለጫውን የሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላት በቦታው ተገኝተዋል።
መግለጫውን በVoiceChat መከታተል እንደምትችሉ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

#Live
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን አማካሪ የሆኑት ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ::
ከላይ በVoice Chat ‘Join’ የሚለውን በመጫን መከታተል ትችላላችሁ::
ፎቶ : ፋይል

Audio
AudioLab
የኢትዮጵየ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን መግለጫ በቀጥታ መከታተል ላልቻላችሁ ቤተሰቦቻችን ከመግለጫው ማብራሪያ የተሰጠበትን ክፍል ብቻ የድምፅ ቅጂውን አያይዘነዋል።
@tikvahethiopia
@tikvahethiopia
#ምርጫ2013 አጫጭር መረጃዎች ፦
- ምርጫ ቦርድ የተጠቃለለ የምርጫ ውጤት በዚህ ሳምንት አሳውቃለሁ ብሏል። ከዚህ ቀደም ለቦርዱ ያልደረሱ 30 የምርጫ ውጤቶች አሁን ላይ ተጠቃለው ገብተዋል።
- የቁጫ ምርጫ ክልል የድምጽ ቆጠራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባሉበት በአዲስ አበባ እየተደረገ ነው።
- ኦሮሚያ ክልል ነገሌ የምርጫ ክልል ድምፅ ባልተሰጠባቸው 30 የምርጫ ጣቢያዎች በቀጣይ ሀሙስ ድምጽ ይሰጣል።
- የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ምርጫ በተወዳደሩበት ኦሮሚያ ክልል ጎማ ቁጥር 2 በሰፊ ድምፅ አሸንፈዋል።
- ዛሬ ይፋ በተደረጉ የተረጋገጡ የምርጫ ውጤቶች የአብኑ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተወዳደሩበት በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ምርጫ ክልል ማሸነፋቸው ተገልጿል።
- ከምርጫው ቀን አንስቶ ከቆጠራ እና ድመራ ጋር በተያያዘ በ153 የምርጫ ክልሎች 31 ፓርቲዎች፣ 7 የግል ተወዳዳሪዎች በጽሁፍ፣ ስልክና በSMS አቤቱታ አቅርበዋል። ምርጫ በተካሄደባቸው በሁሉም ክልሎች ቅሬታ ቀርቧል።
• በአማራ ክልል 49 ምርጫ ክልሎች፣
• በደቡብ ክልል 40 ምርጫ ክልሎች
• በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ምርጫ ክልሎች
• በአፋር ክልል በ21 ምርጫ ክልሎች በርካታ ቅሬታ የቀረቡባቸው ናቸው።
#SolainaShimeles #NEBE

#Ethiopia
የ24 ሰዓት የኮቪድ ሪፖርት :
• የላብራቶሪ ምርመራ - 4,165
• ቫይረሱ የተገኘባቸው - 68
• ህይወታቸው ያለፈ - 1
• ከበሽታው ያገገሙ - 131
አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 276,503 የደረሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 4,332 ህይወታቸው ሲያልፍ 261,156 ሰዎች አገግመዋል። ክትባት የተከተቡ ዜጎች 2,047,751 ደርሰዋል።

#UPDATE
የእናታችን ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና የቀብር ስነሥርዓት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣ የፌዴራል ባለስልጣናት ፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ነገ ማክሰኞ ሰኔ 29/2013 ዓ.ም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤቴክርስቲያን ይፈፀማል።
የፕሮግራሙ ሂደት ባጭሩ፦
• ከ2:30 እስከ 5:00 አበበች ጐበና የሕፃናት ክብካቤ እና ልማት ማህበር ሽኝት ይደረጋል ።
• ከ5:00 እስከ 6:00 ስዓት ወደ መስቀል አደባባይ ሽኝት ይደረጋል፣
• ከ6:00 እስከ 8:00 ስዓት ልዩ ልዩ ዝግጅት ከተደረገ በኋላ ከ8:00 ስዓት ጀምሮ ወደ መቅደስ ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ሽኝት ተደርጎ የቀብር ሥነ-ስርዓታቸው በክብር ይፈፀማል።

ዛሬ ፋይናሻል ታይምስ "Fighting and food shortages fray hopes for Ethiopia’s ceasefire" በሚል በትግራይ ጉዳይ ሰፋ ያለ ፅሁፍ ይዞ ወጥቷል።
ፅሁፉ የኢትዮጵያ መከላከያ የትግራይ ከተሞችን ከለቀቀ በኃላ ህወሓትም የትግራይ ከተሞችን ከያዛቸው በኃላ ያለውን ሁኔታ የሚዳስስ ነው።
በዚህ ዘገባ ላይ ከዚህ ቀደም በዓለም አቀፍ ሚዲዎች ላይ ያልተሰማ አዲስ መረጃ ተካቶበታል ይኸውም "ህወሓት ሱዳን ውስጥ 30,000 ተዋጊ ኃይል አለኝ" ማለቱ ነው።
ፋይናሻል ታይምስ የአንድ ስማቸው ያልተገለፀ የህወሓት ከፍተኛ ኃላፊ ነገሩኝ ብሎ እንዳስነበበው፥ ህወሓት ተቀዳሚ ስራው በምዕረብ ትግራይ በኩል ያሉ ተቀናቃኞችን ማስወጣት/ምዕራባዊ የትግራይ ቦታዎች መቆጣጠር እንደሆነ ገልጿል።
ቡድኑ ለዚህ ምንም አይነት የወታደራዊ አቅም ችግር እንደሌለበት ለፋይናሻል ታይምስ የገለፀ ሲሆን አሁን ላይ ዋነኛ ዓላማው ትግራይን ከሱዳን ጋር የማያገኛኘውን ኮሪደር ለማስከፈት መሞከርና ማስከፈት ነው ብሏል።
ህወሃት ሱዳን ውስጥ ውጊያውን ለመቀላቀል የሚጠባበቁ 30 ሺ ታጣቂዎች አሉኝ ማለቱን ፋይናሻል ታይምስ አስነብቧል።
አንድ ስማቸውን ያልተገለፀ የሱዳን ባለስልጣን በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት አስተያየት ሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በሚደረገው ጦርነት ለመሳተፍ ፍላጎት እንደሌላት ገልፀዋል።
በዚህ ዘገባ ላይ ስለታጣቂዎቹ ዝርዝር መረጃ አልቀረበም ፣ እንዴትስ ይህን ያህል ቁጥር ያለው ታጣቂ ሱዳን ውስጥ ሊኖረው እንዳለው አላመለከተም።
ከዚህ ቀደም የፌዴራል መንግስት በ" ማይካድራ ጭፍጨፋ" የተሳተፉ በርካታ ታጣቂዎች ከተፈናቀሉ ሰዎች ጋር ተመሳስለው ወደሱዳን ገብተው እንደነበር ክስ ሲያሰማ ነበር።
ያንብቡ : telegra.ph/Update-07-06-2

የስም ቅያሬ የተደረገለት "ትግራይ ቴሌቪዥን" ጣቢያ !
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር "ትግራይ ቴሌቪዥን" በሚል ስያሜ የሚታወቀው ጣቢያ "ይሓ ቲቪ" የሚል ስያሜ እንዲሰጠው ያቀረበለትን ጥያቄ መቀበሉን ኢዜአ ዘግቧል። "ይሓ ቲቪ" በቅርብ ቀናት ውስጥ ስርጭቱን ይጀምራል ሲል ዘገባው አክሏል።
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር "ትግራይ ቴሌቪዥን" በሚል ስያሜ የሚታወቀው ጣቢያ "ይሓ ቲቪ" የሚል ስያሜ እንዲሰጠው ያቀረበለትን ጥያቄ መቀበሉን ኢዜአ ዘግቧል። "ይሓ ቲቪ" በቅርብ ቀናት ውስጥ ስርጭቱን ይጀምራል ሲል ዘገባው አክሏል።
@tikvahethiopia
#Tigray
በኢትዮጵያ የ UNHCR ቃል አቀባይ ኔቨን ክሬቨንኮቪክ ፥ "ከኦንላይን እና ከሌሎች ምንጮች" በትግራይ ክልል ሽረ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ስደተኞች መገደላቸውን የሚገልፅ ሪፖርት ደርሶናል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግሩ።
ቃል አቀባዩ ለቢቢሲ በላኩት ኢሜኤል፥ " የደረሱንን ሪፖርቶች በልዩ ትኩረት እንመለከተዋልን ፤ ወዲያውኑ ሽረ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞችን ፣ ባልደረቦቻችንና ሰራተኞቻችን አግኝተናል" ብለዋል።
አክለው፥ “እስካሁን የደረሱን ማናቸውም ክሶች ማረጋገጥ አልቻልንም ነገር ግን የእነዚህን ዘገባዎች ትክክለኛነት ለመገምገም የሚረዱ ተገቢ መረጃዎችን መሰብሰባችንን እንቀጥላለን” ሲሉ ገልፀዋል።
የመብት ተሟጋቾች ብዙ ስደተኞች በአካባቢው ሚሊሻዎች በጭካኔ መገደላቸውን የሚገልጹ ሪፖርቶች እየደረሱን ነው ብለዋል።
ነገር ግን ባለፈው ሳምንት የሀገር መከላከያ ከትግራይ መውጣቱን ተከትሎ በክልሉ ያሉት የግንኙነት መስመሮች በመቋረጣቸው ሪፖርቶቹን ማረጋገጥ አስቸጋሪ አድርጎታል።
የኤርትራ ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የተለያዩ የአስክሬን ምስሎችን በማጋራት በመቶች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ትግራይ ውስጥ መገደላቸው እየገለፁ ነው።
በሌላ በኩል በስደተኞች ጉዳይ የተለያዩ ፅሁፎች በማጋራት ሚታወቁት ሜሮን እስጢፋኖስ በማይአይኒ 6 ኤርትራውያን መገደላቸውን የሚገልፁ እንዲሁም 300 መገደላቸውን የሚገልፁ ሪፖርቶችን ከሰሙ በኃላ ለማጣራት ጥረት አድርገው የደረሱበትን ማምሻውን ገልፀዋል።
ሜሮን ከጥቂት ቀናት በፊት ማይ አይኒ ካምፕ 2 ስደተኞች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መጠቃታቸውን እንደሰሙ፤ ነገር ግን ጉዳቱ ቀላል እንደነበር ገልፀዋል። አክለው፥"ከUNHCR ባልደረቦች እንደሰማሁት ሽሬ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተገደሉ የተባለው የተሳሳተ መረጃ ነው" ሲሉ ፅፈዋል።

#GERD
ኢትዮጵያ የሁለተኛው ዙር የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመሙላት ሂደት መጀመሩን እንዳሳወቀቻት ግብፅ ገለፀች።
የግብፅ የውሃና መስኖ ሚኒስቴር የ2ኛው ዙር ሙሌት መጀመሩን "ኢትዮጵያ በይፋ ለግብፅ አሳውቃለች" ሲል ዛሬ መግለፁን ሮይተርስን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡት ይገኛል።
የህዳሴ ግድብ ሁለተኛው የውሃ ሙሌት ሂደት ስለመጀመሩ ኢትዮጵያ ለግብፅ በይፋዊ ደብዳቤ እንዳሳወቀቻት በግብፅ ባሉ ሚዲያዎች በስፋት በሰበር ዜና እየተዘገበ ነው።
በኢትዮጵያ መንግስት በኩል እስካሁን በይፋ የተሰማ ነገር የለም።
ቀደም ብሎ በተያዘው ፕሮግራም የተ.መ.ድ. ፀጥታው ምክር ቤት የፊታችን ሀሙስ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያመክራል ተብሎ ይጠበቃል።
በሐምሌ ወር የምክር ቤቱ ሰብሳቢ የሆኑት በተ.መ.ድ. የፈረንሳይ አምባሳደር ኖኮላስ ደ ሪቪዬር ከሰሞኑ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ኢትዮጵያ ፣ ግብጽ እና ሱዳን የገጠማቸውን አለመግባባት በውይይት እንዲፈቱ ከማድረግ/ማግባባት ውጪ ም/ቤቱ ሌላ መፍትሄ እንደማይኖረው መግለፃቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ሪጅን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎትን አሰጀመረ !
በደቡብ ሪጅን የተጀመረው የ4ጂ አድቫንስድ አገልግሎት ሀዋሳ፣ ሻሸመኔ እና ቡሌ ሆራን ጨምሮ 12 ከተሞችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።
አገልግሎቱ የኢንተርኔት እና ሌሎች በኩባንያው የሚቀርቡ አገልግሎቶች በተሻለ ፍጥነት ለማግኘት ያስችላልም ነው የተባለው።
ኩባንያው ከፍተኛ የኢንተርኔት አጠቃቀም በሚታይባቸው 103 ከተሞች የ4ጂ .ኤል.ቲ.ኢ አገልሎትን ለማሰፋፋት እየሠራ የሚገኝ ሲሆን እሰከአሁን ባደረጋቸው የኔትወርክ ማስፋፊያ ስራዎች 65 ከተሞችን ተጠቃሚ አድርጓል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሰራ አሰፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ በአዲስ አበባ ከተማ ተወሰኖ የቆየውን የ4ጂ አገልግሎት ወደ ክልሎች በማስፋፋት ለሀገሪዊ ጥቅል ዕድገት እንዲያግዝ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ከ3ጂ አንፃር በ14 እጥፍ በተሻለ ፍጥነት አገልሎት ለማገኘት የሚያሰችል እንደሚሆን ተናግረዋል።
127 ዓመት እድሜ ያለው ኢትዮ ቴሌኮም በርካታ ማሻሻያዎች በማድረግ ለደንበኞች የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
ኩባንያው በአጠቃላይ በመላ ሀገሪቱ 55 ነጥብ 4 ሚሊዮን ደንበኞች ሲኖሩት ከዚህ ውስጥ 25 ነጥብ 5 ሚሊዮን ያህሉ የኢንተርኔት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል።
#ኢብኮ