TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ 1931 ዜጎቿን ወደ አገራቸው መልሳለች። በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ 40 ሺህ ዜጎችን በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ መገለፁ አይዘነጋም። በዚህ መሰረትም ትላንት 1,252 ከሪያድ እና 679 ከጂዳ በአጠቃላይ 1931 ዜጎች በስድስት በረራዎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው። @tikvahethiopia
#Update
ከሳዑዲ አረቢያ 2,257 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳሳወቀው በትናትናው ዕለት 2,257 ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
@tikvahethiopia
ከሳዑዲ አረቢያ 2,257 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳሳወቀው በትናትናው ዕለት 2,257 ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Somali የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 አመት የ8ኛ ክፍል ፈተናዎችን በክልሉ ለሚገኙ ዞኖች፣ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ማከፋፈል ጀመረ። በሶማሌ ክልል የ2013 አመት የ8ኛ ክፍል ፈተናን ከሰኔ 21 እስከ ሰኔ 23 ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል። በክልሉ በሚገኙ 735 ትምህርት ቤቶች 44,144 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል። የሶማሌ ክልል…
#Update
በሶማሌ ክልል የ2013 አመት የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ተጀመረ።
ዛሬ በተጀመረው የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ735 የፈተና መስጫ ማዕከላት 44,144 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።
ፈተናው ሰኔ 23 የሚጠናቀቅ ሲሆን በፈተናው ፈታኞች ፣ ተቆጣጣሪዎች ፥ ፖሊሶችን ጨምሮ 2,778 የሚሆኑ አካላት ተሳታፊ መሆናቸውን የሶማሌ ክልል ብዙሃን መገናኛ ድርጅት አሳውቋል።

#ምርጫ2013
378 የምርጫ ክልሎች የምርጫ ውጤት አስረከቡ።
ከየክልሎቹ የሚሰበሰቡ የምርጫ ድምጽ ውጤቶች ርክክብና ጉብኝት ተደረገ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው የመገናኛ ብዙሀን ጉብኝት በአጠቃላይ ከየምርጫ ክልሎች ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚመጡ የምርጫ ውጤቶች ርክክብ ሒደት እና በአሁኑ ሰአት የውጤት አሰባሰብ ሒደቱ ተጎብኝቷል።
በመረጃ ርክክቡም የሚጠበቁ መስፈርቶችን መሠረት በማድረግ ከየምርጫ ክልሎች በሚጠበቀው መልኩ መሆኑ እየተረጋገጠ ርክክብ ተደርጓል።
378 የምርጫ ክልሎችም የምርጫ ውጤት አስረክበው የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

እየከፋ የመጣው የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ስርቆት :
በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ በሁምቦ ላሬና ቀበሌ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ የኃይል ማስተላለፍያ ታወርና ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ላይ የስርቆት ወንጀል በመፈፀሙ በአካባቢው የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ተቋርጦ መሰንበቱን የኢትይጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
የስርቆት ወንጀሉ የተፈፀመው ከወላይታ ሰብስቴሽን ተነስቶ ለሦስት የደቡብ ዞኖች አገልግሎት በሚሰጥ የኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ መስመር ላይ ሲሆን በዚህም ሁለት ታወሮች ወድቀዋል፣ 20 ታወሮች ደግሞ ብረታቸው ተገንጥሎ ተወስዷል፡፡
የኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ መስመሩን ጠግኖ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎችን ሳይጨምር 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጭ ይጠይቃል ተብሏል፡፡
የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ስርቆቱ በተቋሙና በኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ላይ ከፍተኛ ኪሳራ የሚያደርስ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ችግሩ የተከሰተባቸውን የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች በእንጨት ምሶሶ በመስራት ለተቋረጠባቸው ለ3ቱ ዞኖች አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ብሏል፡፡
የወላይታ ዞን ዓቃቤ ህግ በከፍተኛና በዝቅተኛ ኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ የሚፈፀማን የስርቆት ወንጀል ለመከላከል በርካታ ጥረቶችን እያደረገ ሲሆን በእዚህም ደርጊቱን የፈፀሙ 5 ግለሰቦች ከ3 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ማድረጉን አስታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪ በስርቆት ወንጀል የተጠረጠሩ 32 ግለሰቦችን በ11 መዝገቦች ላይ ክስ መመስረቱ ተገልጿል፡፡ #ኢፕድ

#BREAKING
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፌዴራል መንግስት ሰብዓዊነትን መሰረት ባደረገና ተጨማሪ ጉዳት በማያስከትል መልኩ #የተኩስ_አቁም_ስምምነት እንዲያደርግ ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ እንዳስታወቁት፥ ክረምት እየገባ በመሆኑ የትግራይ ክልል አርሶ አደር ተረጋግቶ የእርሻ ስራውን እንዲያከናውን፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ለተረጂዎች ያለምንም ችግር እንዲደርስ ወቅቱን የሚመጥን ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርግ ተጠይቋል ብለዋል።
ዶ/ር አብርሃም በላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጥያቄውን ባለፈው ሳምንት በይፋ ማቅረቡን ገልፀዋል።
ይህ ጥያቄ የቀረበው የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ከክልሉ ህዝብ ተወካዮች ፣ ከቢሮ እና ዞኖች አመራር አባላት፣ በተለያየ ቦታ ከሚገኙ የትግራይ ተወላጆች፣ ከትግራይ ምሁራን፣ ከባለሀብቶችና ከሃይማኖት አባቶች ጋር ተከታታይ ምክክር ካደረገ በኋላ ነው ብለዋል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/ENA-06-28-2
#ኢዜአ
@TIKVAHETHIOPIA

#Mekelle
መቐለ ከተማ የቀድሞው የክልሉ ገዢ (ህወሓት) ታጣቂዎች መግባት ጀምረዋል የሚል መረጃ ከተሰራጨ በኋላ ነዋሪዎች ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑ ተሰምቷል።
ነዋሪዎች የሞተር ሳይክሎች እና የመኪኖች ጥሩምባ እያሰሙ በመቐለ ጎዳናዎች ሲዘዋወሩ ታይተዋል።
በመቐለ ርችት እየተተኮሰ መሆኑን እንዲሁም የትግራይ ክልል ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልቡ የከተማዋ ነዋሪዎች በጎዳናዎች ሲዘዋወሩ መታየታቸውን ተገልጿል።
ከዚህ ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የፌድራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን ለቀው መውጣት መጀመራቸው ተሰምቷል።
የከተማዋ መደበኛ እንቅስቃሴ ከቀኑ ስድስት ሰዓት በኋላ ነው መቀዛቀዝ የጀመረው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከመቐለ ወደ ኲሃ አቅጣጫ ሲጓዙ መታየታቸውን ተሰምቷል።
የትግራይ ቴሌቭዥን ከዛሬ ጀምሮ ሥርጭቱ የተቋረጠ ሲሆን በትግራይ ክልል ሌሎች አካባቢዎች የቴሌኮም ግልጋሎት አይሰራም።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ከተማው የሚያደርገው ጉዞ ተቋርጧል።
የክልሉ መንግሥት ዋና መቀመጫ የሆነችው መቐለ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር የሆነችው ሕዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ነበር።
ዘገባው የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (ከመቐለ) ነው።

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ከደቂቃዎች በፊት በሰበር ዜና አማፅያን ወደፊት እየገፉ መምጣታቸውን ተከትሎ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደሮች ለቀው ወጥተዋል ብሏል።
እስካሁን እየወጡ ስላሉት መረጃዎች በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት በኩል የተባለ ነገር የለም።

#BREAKING የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፌዴራል መንግስት ሰብዓዊነትን መሰረት ባደረገና ተጨማሪ ጉዳት በማያስከትል መልኩ #የተኩስ_አቁም_ስምምነት እንዲያደርግ ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ እንዳስታወቁት፥ ክረምት እየገባ በመሆኑ የትግራይ ክልል አርሶ አደር ተረጋግቶ የእርሻ ስራውን እንዲያከናውን፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ለተረጂዎች…
#BREAKING
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን የተኩስ አቁም ስምምነት ጥያቄ የፌዴራል መንግሥት በአዎንታዊነት እንደተቀበለው ባወጣው መግለጫ አስታወቀ !
* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን የተኩስ አቁም ስምምነት ጥያቄ የፌዴራል መንግሥት በአዎንታዊነት እንደተቀበለው ባወጣው መግለጫ አስታወቀ !
* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
#Update
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የቀድሞው የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት መቐለ ከተማን መቆጣጠሩን ማምሻውን አስታውቋል።
የህወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ "የትግራይ ዋና ከተማ መቐለ በቁጥጥራችን ሥር ነች" ሲሉ #ለሬውተርስ ተናግረዋል።
የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ከመቐለ እንደዘገበው ደግሞ በከተማው የሚገኘው ኤፍ.ኤም መቐለ ራዲዮ ጣቢያ ተቋርጦ የነበረ ሥርጭቱን ጀምሯል።
የራዲዮ ጣቢያው ከዚህ ቀደም ይደመጡ ያልነበሩ፣ የትግራይ ኃይሎችን የሚያወድሱ ሙዚቃዎች በማሰማት ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል።
" የትግራይ መከላከያ ኃይል (TDF) " ተብሎ የሚጠራው ታጣቂ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ መቐለ ከተማ መግባቱን የከተማዋ ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።
የመቐለ አስተዳደር በሚገኝበት አካባቢ እንዲሁም "አዋሽ ካምፕ" ተብሎ የሚጠራው የቀድሞ የሰሜን ዕዝ የጦር ሰፈር አካባቢ ታጣቂዎቹ ታይተዋል።
ሁለት የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት በመቐለ የተለያዩ ቦታዎች ማምሻውን አልፎ አልፎ የተኩስ ይሰማ ነበር።
የተሽከርካሪዎች ጥሩምባ እንዲሁም የርችት ተኩስ አሁንም እየተሰማ እንደሚገኝ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ከመቐለ ዘግቧል።

#Ethiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን አለፈ።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጤና ሚኒስቴር ዛሬ ይፋ ያደረገው ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነ አጠቃላይ የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር 2,003,226 ደርሰዋል።
በሌላ መረጃ ፦ ባለፉት 24 ሰዓታት 3,144 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 39 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የአንድ ሰው ህይወት አልፏል፤ 573 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር መነጋገራቸውን አሳወቁ።
የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የተፈጠረው ክስተት እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ገልፀዋል።
ጉተሬዝ አሁንም ቀውሱን መፍቻ ምንም የወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ አሳውቀዋል።
ጉተሬዝ ፥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ተነጋግሬያለሁ ያሉ ሲሆን ውጤታማ የሆነ የተኩስ አቁም ተግባራዊ ይደረጋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።
የሲቪል ዜጎችን ደህንነት መጠበቅ፣ በችግር ላይ ላሉ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ እና ለችግሩ ፖለቲካዊ መፍትሄ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።

#FDREDefenseForce
የመከላከያ ሚኒስቴር የ33ኛ ዙር ምልምል ወታደሮችን በአሁኑ ሰዓት በማስመረቅ ላይ ይገኛል።
በብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ት/ቤት ሲሰለጥኑ የነበሩ ወታደሮች የተሰጣቸውን ስልጠና አጠናቀዋል።
ተመራቂዎቹ ከመደበኛው ሠራዊቱ ጋር በመቀላቀልከ ውስጥ እና ከውጭ የሚቃጣን ወረራ በመመከት እንዲሁም የኢትዮጵያን አንድነት አጠናክው ያስቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል የሀገር መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት