TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የፖሊስ ሪፖርት : በውጭ አገር ታዛቢው የአሟሟት ሁኔታ ላይ ምርምራ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ፖሊስ "ትናንት በራዲሰን ብሉ ሆቴል አሜሪካዊ ዜጋ በመኝታ ክፍሉ ሕይወቱ አልፎ ተገኝቷል" ብሏል። የሆቴሉ የጽዳት ሠራተኛ ትናንት ጠዋት አንድ ሠዓት ገደማ አሜሪካዊው ያረፈበትን የመኝታ ክፍል ለማጽዳት ስትገባ ያየችውን ነገር ለፖሊስ ጥቆማ መስጠቷን ፖሊስ ገልጿል።…
#Update

"ራዲሰን ብሉ ሆቴል" ውስጥ ሞተው የተገኙት ግለሰብ ታዛቢ አለመሆናቸውን ምርጫ ቦርድ አሳወቀ።

ዛሬ የአዲስ አበባ ፖሊስ ሟቹ ኪስ ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልዩ የምርጫ ታዛቢ ወረቀት (ባጅ) እና ሌሎችም ቁሳቁሶችን አግኝቻለሁ ሲል ለኢዜአ መናገሩ ይታወሳል።

ከደቂቃዎች በፊት ወቅታዊ መግለጫ የሰጡት የምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን አማካሪ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ፥ ግለሰቡ የካርተር ሴንተር አለም አቀፍ ታዛቢ እንዳልሆኑ ተናግረዋል።

ግለሰቡ እንደማንኛውም ድጋፍ ሰጪ አለም አቀፍ ተቋም በታዛቢነት ሳይሆን በእንግድነት ከቦርዱ ባጅ መውሰዳቸውን ገልፀዋል።

ግለሰቡ የተሰጣቸው "የልዩ የእንግድነት ባጅ" ነው ያሉት ሶሊያና በዚህ የልዩ ባጅ የምርጫ ሂደቱን የመከታተል ነገር ግን የመታዘብ ስራ ከማይሰሩ አጋር ድርጅቶች የሚሰጥ ባጅ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

ወ/ሪት ሶሊያና ፥ ከካርተር ሴንተር ምርጫውን ለመታዘብ የመጣ ታዛቢ የለም ብለዋል።

"አሟሟታቸውን ቦርዱ ሰምቷል በዚህም አዝኗል ፤ አማሟታቸው በመንግስት ፖሊስ እና በሌሎች ተቋማት እየታየ እንደሆነ ሰምተናል ነገር ግን ከምርጫው ጋር ምንም ግንኙነት የለውም" ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Exclusive

ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ከምርጫ 2013 ጥቂት ቀን አስቀድመው በይፋዊ ማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ላይ በግል ምክንያት ምርጫውን መቀጠል እንደማይችሉ መግለፃቸው ይታወሳል።

ትላንት በተደረገው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ ግን ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በተወዳደሩበት ጅማ አካባቢ የመራጮችን ድምፅ ስለማግኘታቸው በምርጫ ጣቢያ ላይ በተለጠፈ ውጤት መግለጫ ወረቀት ላይ ለማየት ተችሏል።

ይህን ጉዳይ የ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እንዴት እንደማያየው ? የጠየቅናቸው የቦርዱ የኮሚኒኬሽን አማካሪ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ይህን አጭር ምላሽ ሰጥተውናል ፦

"እኛ ጋር አጠቃላይ የተመዘገቡ 148 የግል ተወዳዳሪዎች አሉ፤ ከማንኛውም ተወዳዳሪነት ለመውጣት የግልም ሆነ የፓርቲ ተወዳዳሪ እጩነቴን ትቻለሁ የሚል "እጩነት መተው" የሚባል ፎርም አለ እሱ ተሞልቶ መቅረብ አለበት።

እኔ እስከማውቀው ድረስ በኡስታዝ አህመዲን ጀበል የቀረበ የእጩነት መተው ማመልከቻ የለም እኛ ጋር ፤ ባሎቱ ላይ አሉ ፤ ድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ አሉ ተቆጥሮ ይቀጥላሉ።"

NB : ወ/ሪት ሶሊያና ቦርዱ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተመስርቶ ህጋዊ ውሳኔ እንደማይወስድ ገልፀዋል። እጩነት የህጋዊ ሂደት ነው ፤ በእጩነት መመዝገብ እና መሰረዝ ህጋዊ ነው ፣ እጩነትን መተውም ህጋዊ ነው እያንዳንዱ የራሱ ሂደት አለው ከዛ አንፃር እጩነትን መተው በሚል ቦርዱ ጋር የገባ ነገር እንደሌለ ገልፀዋል። በዚህ መሰረት ለምርጫ ክልሎች / ጣቢያዎች ምንም አቅጣጫ አልተሰጠም ፤ ድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ እንዳሉ እንደማንኛውም እጩ ነው ኡስታዝ አህመዲን ጀበል የተስተናገዱት ብለዋል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሲዳማ በ19 ጣቢያዎች ድምጽ እየተሰጠ ነው። በሲዳማ ክልል "በድምጽ መስጫ ወረቀት እጥረት" ምክንያት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ተቋርጦባቸው በነበሩ ጣቢያዎች ዛሬ ምርጫ እየተካሄደ ነው። የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በተቋረጠባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ከ5 ሰዓት ጀምሮ ነው ድምጽ እየተሰጠ የሚገኘው። የድምጽ መስጫ ወረቀት በሂሊኮፍተር እንዲደርስ ተደርጎ ነው የዛሬው ምርጫ የቀጠለው። የድምጽ አሰጣጡ እስከ ምሽት…
"...ለሊቱን ቆጠራው ተከናውኖ ውጤቱ ነገ ጠዋት ለህዝብ ይፋ ይደረጋል" - አቶ ፍሬው በቀለ

ከ5 ሰዓት ጀምሮ በሲዳማ ክልል የቀጠለው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ምሽት 12 ሰዓት ላይ በሰላም ተጠናቋል።

ምርጫው ለዛሬ ያደረው በ "ድምፅ መስጫ ወረቀት እጥረት" ምክንያት መሆኑ ይታወቃል።

በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ እና ደቡብ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍሬው በቀለ ለኢዜአ እንደገለጹት ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ በ19ኙ የምርጫ ክልሎች ስር በሚገኙ 1 ሺህ 998 ጣቢያዎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ሲካሄድ ቆይቶ ተጠናቋል።

በጣቢያዎቹ ሌሊቱን ቆጠራውን በማከናወን ውጤቱን ነገ ጠዋት ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ አቶ ፍሬው ለኢዜአ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ፣ ትግራይ ክልል የተነሳው ግጭት እንሆ 8 ወር አስቆጥሯል።

ግጭቱ የሺዎችን ህይወት እንደቀጠፈ፣ ሺዎችንም እንዳሰደደ ቤት ፣ በርካቶች አካል እንዳጎደለ፣ በርካታ ሴቶችን ለፆታዊ ጥቃት እንደዳረገ፣ በርካታ ህፃናትን በአካልም በስነልቦናም እንደጎዳ፣ እንደተመድ ሪፖርት መቶ ሺዎችን ለረሃብ እንዳጋለጠ ይታመናል።

የፌዴራል መንግስቱ የትግራይ ሁሉንም ከተሞች በቁጥጥሩ ስር ካደረገ በኃላ በተለያዩ ጊዜያት ከዚህም ከእዚያም የግጭት ሪፖርቶች ይወጡ እነደነበር የአደባባይ ሃቅ ነው።

ከሰሞኑን ጠቅላላ ምርጫ ሲደረግ ፣ የኢትዮጵያን ጉዳይም የሚከታተሉ የዓለም ሚዲያዎችም ፊታቸውን ወደምርጫው ሲያዞሩ ጠንከርና ከበድ ያለ ግጭት በትግራይ የተለያዩ ቦታዎች እንደነበሩ ተሰምቷል።

ከባድ ግጭት እንደነበረም የሀገር መከላከያ ሰራዊትም ያረጋገጠው ጉዳይ ነው።

ከፌዴራሉ የፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ የገባው በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የህወሓት ኃይል በርካታ የክልሉን ከተሞችን መያዙን እየገለጸ ነው። የመከላከያ ሠራዊት ቡድኑ አገኘሁ ያለውን ድል "ሐሰተኛ ዜና" ሲል አጣጥሎታል።

የሠራዊቱ ቃል አቀባይ ኮ/ል ጌትነት ከሰሞኑ ከባድ ውጊያ እንደነበረ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል፥ የህወሓት ኃይሎች ከተሞችን ፣ የጦር መሳሪያዎችን ወይም ወታደሮችን ማርከናል ያሉትን ግን ሐሰት ነው ብለዋል።

"የኢትዮጵያ መንግሥት ምርጫ በማካሄድና በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ሥራ በበዛበት ጊዜ ሽብርኛው ህወሓት፣ ታዳጊዎችን በማሰለፍ በሽብር ተግባራት ላይ ተሰማርቶ ነበር" ሲሉ ገልፀዋል ኮሎኔሉ።

የተካሄደው ዘመቻ የቡድኑን መሪዎች ለመያዝ እንደነበር አስረድተዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-Crisis-06-23

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ምርጫው በ2 ዙር መደረጉ በመንግስት ምስረታ ላይ የሚያመጣው ተፅእኖ አለ ?

በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ምርጫው በ2 ዙር መደረጉ አዲስ በሚመሰረተው መንግስት ላይ ተፅእኖ ይኖረው ይሆን ሲሉ ይጠይቃሉ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከቀናት በፊት ለቲክቫህ በሰጠው ምላሽ ምርጫ 2013 በሁለት ዙር መደረጉ በመንግስት ምስረታ ላይ የሚያመጣው ተፅእኖ የለም።

የቦርዱ የኮሚኬሽን ኃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በሰጡት ማብራሪያ ምርጫው በ2 ዙር መደረጉ በመንግስት ምስረታ ላይ ምንም የሚፈጥረው ተፅእኖ እንደሌለ አሳውቀዋል።

ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ "ምርጫው በሁለት ዙር ተደርጎ የሚጠናቀቀው መስከረም ከመግባቱ በፊት ነው ፤ የአዲሱ መንግስት ምስረታ ደግሞ መስከረም መጨረሻው ሳምንት ላይ ስለሆነ ከዛ በፊት ምርጫና ውጤቱ ስለሚያልቅ የመንግስት ምስረታ ላይ የሚያመጣው ችግር የለም" ብለዋል።

ሰኞ ብዙ የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫው ስለተካሄደ መንግስት የሚመሰርተውን አካል ማወቅ እንደሚቻል ገልፀዋል።

ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ፥ "ሰኔ 14/2013 ዓ/ም ምርጫ ሳይደረግ በቀሩት ክልሎች ማን ይወክለናን የሚለውን ለመወሰን በተለይ የክልል መቀመጫቸውን ምክንያቱም በዚያኛው ጊዜ የፌዴራል መቀመጫን ነው የምናስበው ፤ የክልል መቀመጫ የሚያሸንፉ ሊኖሩ ስለሚችሉ የክልል መቀመጫቸውን አይተው እዛ ላይ ማነው ክልሉን የሚያስተዳድረው የሚለውን ለመለየት ጠቃሚ ነው፥ በተጨማሪ መራጮች ወኪሎቻቸውን ልከው ለመደራደር ለመከራከር ይጠቅማቸዋል ፤ ነገር ግን ምርጫው በሁለት ዙር መደረጉ በመንግስት ምስረታ ላይ የሚፈጥረው ችግር የለም" ሲሉ አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EMA የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንትና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለሚዲያዎች የሰጡት ቃለምልልስ ከምርጫ በፊት እንዳይሰራጭ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አሳሰበ። ቃለምልልሱ በዚህ በጥሞና ወቅት መተላለፍ የለበትም ብሏል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ እድሪስ ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፥ ምንም እንኳን ቃለ መጠይቁ የመንግስት የስራ ክንውኖች ላይ ያተኮረና…
#Update

የታገደው የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ቃለምልልስ ዛሬ ይሰራጫል ተብሏል።

የ "ጥሞና ወቅት" ላይ እንዳይተላለፍ የተባለው የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ቃለ ምልልስ ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት ላይ ነው በተለያዩ ሚዲያዎች ይተላለፋል የተባለው።

ቃለምልልሱ ዛሬ እንደሚተላለፍ የሰማነው ከጠ/ሚር ፅ/ቤት ይፋዊ ከሆነው የፌስቡክ ገፅ ላይ ነው።

ይህ ቃለምልልስ ፥ ከምርጫ በፊት እንዳይሰራጭ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አሳስቦ እንደነበር አይዘነጋም።

በወቅቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ቃለ መጠይቁ የመንግስት የስራ ክንውኖች ላይ ያተኮረ እና የምርጫ ቅስቀሳ እንዳልሆነ በመግለፅ ነገር ግን በጥሞና ወቅት ሊተላለፍ አይገባም ሲል ማሳሰቢያ ሰጥቶ ቃለምልልሱን ለማሳተላለፍ ማስታወቂያ ሲያስነግሩ የነበሩ ሚዲያዎች በሙሉ ማስታወቂያውን አቁመው ነበር።

@tikvahethiopia
"Maal Mallisaa"

ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ከመሞቱ በፊት ሰርቶ ያጠናቀቀው 3ኛ አልበሙ ሊወጣ እየተጠናቀቀ መሆኑ ተሰምቷል።

የአዲሱ አልበም ማስታወቂያዎች በመዲናችን አዲስ አበባ እየተለጠፉ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የአልበሙን መውጣት በሚጠባበቁት ዘንድ ልዩ ትኩረትን ስቧል።

የአልበሙ ስያሜ "Maal Mallisaa" እንደሚሰኝም ታውቋል።

የአዲሱ አልበም መውጫ ቀን መቼ ነው? የሚለው ለጊዜው ትክክለኛው ቀን አልታወቀም።

ድምፃዊ ሃጫሉ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ምሽት መገደሉ ይታወሳል።

ከወራት በፊት #Grammy_Award እ.አ.አ 2020 - 2021 የዓለም የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ካጣቸው አርቲስቶች እና የሙዚቃ ሰዎች ዝርዝር ዉስጥ የሀገራችን ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን አካቶት እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

Photo Credit : Haacaaluu Hundeessaa (FB Page)

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በ 'ድምጽ መስጫ ወረቀት እጥረት' ምክንያት በጋምቤላ ክልል ባሉ በተወሰኑ ጣቢያዎች ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ተቋርጦ የነበረው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ትላንት ተካሂዷል።

የድምፅ ቆጠራው ተጠናቆ ጊዜያዊ ውጤቱ በየምርጫ ጣቢያ ለህዝብ ይፋ እየተደረገ ነው።

ጊዜያዊ ውጤቱ ይፋ እየተደረገ ያለው በሰባት ምርጫ ክልሎች ስር በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች እንደሆነ ተገልጿል።

ድምጽ የተሰጠባቸው ሳጥኖች ወደምርጫ ክልሎች በመጓጓዝ ላይ ይገኛሉ።

መረጃው የኢዜአ ነው።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሰንገን ኦባሳንጆ የሚመራው በኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢዎች ቡድን የምርጫ ትዝብቱን #የመጀመሪያ ሪፖርት ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ያቀርባል።

ሪፖርቱን #በቀጥታ በቴሌግራም Voice Chat መከታተል የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
Live stream started
#LIVE

በኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢዎች ቡድን ሪፖርቱን ከስካይ ላይት ሆቴል እያቀረበ ነው።

ከላይ ያለውን Voice Chat 'Join' በማለት በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
Live stream finished (52 minutes)
TIKVAH-ETHIOPIA
#LIVE በኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢዎች ቡድን ሪፖርቱን ከስካይ ላይት ሆቴል እያቀረበ ነው። ከላይ ያለውን Voice Chat 'Join' በማለት በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ። #TikvahFamily @tikvahethiopia
የAU የመጀመሪያ /ቀዳሚ የምርጫ 2013 ትዝብት ሪፖርት👆

በኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን የምርጫ 2013 የመጀመሪያ/ቀዳሚ ሪፖርት ዛሬ አቅርቧል።

ሪፖርቱን የቡድኑ መሪ ኦሊሰንገን ኦባሳንጆ በንባብ አሰምተዋል።

ቡድኑ በ5 ክልሎችና 2 ከተሞች የምርጫውን አባላቱን ልኮ ምርጫውን መታዘቡን አስታውቋል፡፡

በአንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች እንግልትና ወከባ ፤ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ከጸጥታ ጋር ተያይዞ ስጋቶች ፣ የተቃዋሚ ፓርቲ ወኪሎችን የማዋከብና የማንገላታት ችግሮች ፣ የቁሳቁስ እጥረት ችግር ምርጫው ላይ ጫና ፈጥሮ እንደነበር አሳውቋል።

ከዚህ በተረፈ ግን ምርጫው ሰላማዊ ፣ ተአማኒ በሆነ ሁኔታ መከናወኑን ገልጿል።

የምርጫ ውጤት በሚመለከተው አካል ይፋ እስኪሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲጠባበቅ ቡድኑ ጥሪ አቅርቧል።

ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia