#ምርጫ2013
ከቲክቫህ አባላት የሚመጡት ፎቶዎች አሁንም በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች ረጃጅም ሰልፎች አለመቃለላቸውን የሚያሳይ ነው።
ከክልል ከተሞች በተመሳሳይ የሚላኩልን መልዕክቶች ሰልፎችን አለመቃለሉን የሚጠቁሙ ናቸው።
የተራዘመው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ሊያበቃ 1:30 ይቀራል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድምፅ መስጠት ይቻላል። በመላው ሀገሪቱ ውስጥ ምርጫ እየተካሄደ ባለባቸው ጣቢያዎች ሁሉ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እስከምሽቱ 3:00 ሰዓት ድረስ እንደሚቀጥል ምርጫ ቦርድ አሳውቋል። #Share #ሼር @tikvahethiopia
#ምርጫ2013
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፥ የምርጫ አስፈፃሚዎች እስከ ሶስት ሰአት ድረስ የሚመጣ ማንኛውን መራጭ እንዲያስተናግዱ መልዕክት አስተላልፏል።
ነገር ግን ፦
1ኛ. የመራጮች መዝገባቸው ላይ ያሉ ዜጎች መርጠው ያጠናቀቁባቸው
2ኛ. ለመምረጥ የተሰለፉ ዜጎች በተጠናቀቁበት ቦታዎች የምርጫ ጣቢያ መዝጋትና የቆጠራ ስራ መጀመር እንደሚችሉ ተገልጿል።
ቦርዱ በድምፅ አሰጣት ሂደት ወቅት ችግር ያጋጠማቸው ዜጎች በ " 778 " ነጻ የስልክ መስመር በመደወል ማሳወቅ ይችላሉ ብሏል።

"...አርሶ አደሩ ኪሳቸው ሲፈተሽ የተገኘው የምርጫ ቦርድ ማስተማሪያ ናሙና ወረቀት ነው" - የጋሞ ዞን ፖሊስ
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በቁጫ ምርጫ ክልል ተመሳስሎ የተሰራ/ፎርጅድ የድምጽ መስጫ ወረቀት ተገኘ ተብሎ የሚሰራጨው ዘገባ የተሳሳተ መረጃ ነው አለ የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ የሆኑት ምክትል ኮማንደር ደግፌ ደበላ ፥ በቁጫ ምርጫ ክልል ተመሳስሎ የተሰራ የሚመስል የድምጽ መስጫ ወረቀት በአንድ ምርጫ ጣቢያ ከአንድ መራጭ አርሶ አደር በፍተሻ ወቅት መገኘቱን አሳውቀዋል።
ኮማንደር ደግፌ ፥ ወረቀቱ በምርጫ ሂደቱ ላይ ችግር የሚፈጥር እንዳልሆነ ገልፀው፥ በአንድ አርሶ አደር ኪስ ውስጥ የተገኘው የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማስተማሪያ ናሙና ወረቀት መሆኑ መረጋገጡን ገልፀዋል።
የዞኑ ፖሊስ ምርመራ ማድረጉን የገለፀ ሲሆን ፥ ወረቀቱ ፎርጅድ ሳይሆን ከዚህ ቀደም ፓርቲዎች ለአባሎቻቸው ለማስተማሪያነት የተጠቀሙት የምርጫ ቦርድ ናሙና ወረቀት መሆኑን አዛዡ ማምሻውን አሳውቀዋል።

ወ/ሪት ብርቱካን በቅኝታቸው ወቅት ምን ገጠማቸው ?
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ጀሞ 28 ፣ 14 እና 42 ምርጫ ጣቢያዎች እንዲሁም በምርጫ ክልል19 ምርጫ ጣቢያ 16 ተገኝተው የምርጫውን እንቅስቃሴ መመልከታቸውን በፎቶ አስደግፈን አሳውቀናችሁ ነበር።
በእነዚህ የምርጫ ጣቢያ ያጋጠማቸውን በአጭሩ ፦
- ወረዳ አንድ ጀሞ 28 ፣ 14 እና 42 ምርጫ ጣቢያ ሁለት ታዛቢዎች ከህግ አግባብ ውጪ የምርጫ ማስፈጸም ሂደት ላይ በመገኘታቸው የታዛቢነት ባጃቸውን አስወልቀዋቸዋል፤
- የምርጫ አስፈጻሚዎቹ ለትምህርት የተዘጋጀውን የድምጽ መስጫ አምሳያ ወረቀት ለትምህርትነት መጠቀም ሲገባቸው ትክክለኛውን የድምጽ መስጫ ወረቀት ሲጠቀሙ በማየታቸው አስፈላጊውን እርምት ወስደዋል፤
- ምርጫ ክልል 19 ምርጫ ጣቢያ 16 በነበራቸው ቆይታ የምርጫ ታዛቢ ፈቃድ(ባጅ) ሳይኖራት ''የብልጽግና ታዛቢ ነኝ'' በሚል በምርጫ ጣቢያው የተገኘች ግለሰብን ለህግ አካላት አስረክበዋል።
ሌሎችም የምርጫ ቦርድ አባላት በተለያዩ አከባቢዎች ያለውን የምርጫ እንቅስቃሴ መመልከታቸውን ለማወቅ ችለናል።

#Update
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጫ ሂደት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል።
ቦርዱ የጨመረው ሰዓት ተጠናቋል።
በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ #የድምፅ_ቆጠራ ተጀምሯል።
Photo Credit : ኢፕድ

በቀጣይ ...
ምርጫ ቦርድ የዛሬውን ማጠቃለያ መግለጫ ከደቂቃዎች በኃላ ከስካይ ላይት ሆቴል ይሰጣል።
የቤተሰባችን አባላት በስፍራው ይገኛሉ።
የቦርዱን መግለጫ #በቀጥታ በቴሌግራም Voice Chat ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

#Live
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳና ሌሎችም የቦርዱ አመራሮች መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።
ከላይ ያለውን የ Voice Chat "Join" በማለት መከታተል ትችላላችሁ።

Audio
AudioLab
#የዛሬው_ማጠቃለያ_መግለጫ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አማራሮች የሰጡትን የዛሬ ማጠቃለያ መግለጫ በቀጥታ በ Voice Chat መከታተል ያልቻላችሁ የድምፅ ቅጂውን አያይዘነዋል።
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አማራሮች የሰጡትን የዛሬ ማጠቃለያ መግለጫ በቀጥታ በ Voice Chat መከታተል ያልቻላችሁ የድምፅ ቅጂውን አያይዘነዋል።
@tikvahethiopia
በሲዳማ ክልል ነገ የምርጫ ሂደቱ ይቀጥላል !
ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ፦
"... የህትመት ስራው ላይ የድምፅ መስጫ ወረቀቱ በ100 ተደርጎ መታሸግ ሲገባቸው በ50 ተደርገው በመታሸጋቸው በ19 የምርጫ ክልሎች ላይ የድምፅ መስጫ ወረቀቱ በ50% ቀንሶ እንዲደርስ ሆኗል።
ስለዚህ በዚህ የድምፅ መስጫ እጥረት ምክንያት በሁሉም የምርጫ ክልሎች የድምፅ መስጠት ሂደቱ ተቋርጧል።
ሆኖም ግን ችግሩን ለመፍታት ቀኑን ሙሉ ስንሰራ ቆይተናል ፤ የሚያስፈልጋቸውን ሰነዶች በሙሉ በየምርጫ ክልሉ (19) እንዲደርስ አድርገናል ፤ ከደረሰ በኃላ ግን ወደየጣቢያው ለማድረስ አንዳድን ቦታዎች ላይ ከመሰረት ልማት እና ከርቀት አንፃር እንዲደስር አድርጎ በዚሁ ቀን ምርጫውን አስቀጥሎ ማጠናቀቅ እንደማይቻል በመረዳታችን ቦርዱ 1162 የምርጫ አዋጁ በሚፈቅደው መሰረት ፤ ምርጫ ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ በሚቋረጥበት ጊዜ ለጊዜው ምርጫው እንዲቋረት አድርጎ ሁኔታዎች የሚስተካከልበት ሰዓት ወስዶ ሂደቱ እንዲቀጥል ማድረግ እንደሚችል በሚደነግገው መሰረት ነገ ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ በሲዳማ የምርጫ ክልሎች በሙሉ ሂደቱ ይቀጥላል።
ይህ በሚደረግበት ጊዜ የድምፅ መስጫ/ምርጫ ቁሳቁሶች በአግባቡ እንዲታሸግ ፣ቃለጉባኤ እንዲይዙ፣ ለሁሉም ምርጫ አስፈፃሚዎች መመሪያ ተሰጥቷል።
ቃለጉባኤ በታዛቢዎች ፣ በአስፈፃሚዎች ፣ በሲቪል ሶሳይቲ ታዛቢዎች ፣ በፖለቲከ ፓርቲ ታዛቢዎች ቃለጉባኤ ተይዞ በጥንቃቄ በየጣቢያው እንዲቆይ አድርገናል። ከዚህ የተላኩ ቁሳቁሶች በምርጫ ክልል በወረዳ ደረጃ እንዲቆዩ አድርገናል፤ ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግም ትዕዛዝ አስተላልፈናል።"

የምርጫው ሰላማዊነት ?
- ይሄ ነው የሚባል የከፋ የፀጥታ ችግር አላጋጠመም።
- አማራ ክልል አንድ የምርጫ ጣቢያ ላይ ግለሰቦች እርስ በእርስ ተጋጭተው (የታጠቁ ስለመሆናቸው ለቦርዱ የደረሰው መረጃ የለም) የምርጫው ሂደት ተቋርጦ ነበር።
- አማራ ክልል በ "ጎንጂ ምርጫ ክልል" አንድ ጣቢያ ላይ የአስተዳደር ሰዎች ገብተው አልወጣም በማለታቸው በምርጫ አስፈፃማዎች ላይ ስጋት በማደሩ አንድ አስፈፃሚ አከባቢውን ለቆ ሄዷል።
- ኦሮሚያ ክልል አንዳንድ ከዚህ ቀደም ችግር ነበረባቸው የተባሉ ቦታዎች ላይ ግጭት ባይኖርም አስፈፃሚዎች በስጋት ያልከፈቷቸው ጣቢያዎች ነበሩ (ምስራቅ ሀረርጌ አንድ የምርጫ ክልል ውስጥ (የተወሰኑ) ብዙ የማይባሉ የምርጫ ጣባያዎች ያልተከፈቱ ነበሩ) ፤ ናኖ የምዕራብ ሸዋ ምርጫ ክልል 2 የታጠቁ ሰዎች ሂደቱ ለመረበሽ ሞክረው ምርጫድ ተቋርጦ ነበር።
- በአጠቃላይ ምርጫው ሰላማዊነቱ ተረጋግጦ ፣ በመልካም ሁኔታ ያለቀ ምርጫ ነው፤ ከላይ ከተገለፁት ውጭ ያጋጠመ የከፋ ችግር የለም። በተለይ ግጭት ፣ ጉዳት ፣ የተጀመረ የምርጫ ሂደት የሚያስተጓጉል እና ሁሉን ነገር የሚለውጥ ችግር ገጥሟል ማለት አይቻልም።
(የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ)

#AddisAbaba
ስድስተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመታዘብ በCarter Center በኩል ወደ ኢትዮጵያ የመጣ አንድ አፍሪካ-አሜሪካዊ አዲስ አበባ በሚገኝ "ራዲሰን ብሉ" በተባለ በሆቴል ውስጥ በእራሱ ክፍል ህይወቱ አልፎ ስለመገኘቱ ኢትዮጵያ ቼክ አሳውቋል።
በማህበራዊ ሚዲያ ግለሰቡ እንደተገደለ ተደርጎ የወጣው መረጃ "ያልተረጋገጠ" ነው ተብሏል።
ምንም እንኳን እስካሁን ይፋዊ የምርመራ ሪፖርት ባይገኝም ለመረጃው ቅርበት የላቸው አካላት የግለሰቡ ህልፈት ከህመም ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስለጉዳዩ መረጃው እንደደረሰው ያሳወቀ ሲሆን ዝርዝር መረጃ ነገ ይፋ አደርጋለሁኝ ሲል ለ www.ethiopiaCheck.org የመረጃ ማጣሪያ አሳውቋል።

የምርጫ ውጤት በተመለከተ ፦
• ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ሰኔ 14 በሰጡት መግለጫ ፦
- ከዛሬ ጀምሮ ውጤት በየምርጫ ጣቢያው ደረጃ መገለፅ ይጀመራል።
- ቆጠራ ያጠናቀቁ ጣቢያዎች በሙሉ በምርጫ ጣቢያው የተገኘውን ውጤት ከዛሬ ጀምሮ መግለፅ ይጀምራሉ።
- ከነገ ጥዋት ጀምሮ እያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያ ያለውን ውጤት እና ቁሳቁስ ይዞ ወደየምርጫ ክልሉ ይሄዳል።
- ምርጫ ክልሎች ቢበዛ 5 ቀን ድረስ ውጤት ለማሳወቅ ይፈጅባቸዋል። ቦርዱ ግን በጊዜያዊነት ከስር ከስር ያሳውቃል።
- ነገና ከነገወዲያ ቦርዱ የሚገባለትን ውጤት ደረጃ በደረጃ ውጤቶችን እያረጋገጥ ይገልጻል።
- በ10 ቀን ውስጥ ውድድር በተደረገባቸው ምርጫ ክልሎች #ቢያንስ ጊዜያዊ ውጤት ምርጫ ቦርድ ያሳውቃል።
NB : የምርጫ ጣቢያዎች ስራቸውን አምሽተው ስለሚያጠናቅቁ እና ቆጠራው ጊዜ ስለሚፈጅ ወደምርጫ ክልል ዛሬ ለሊት ጉዞ እንዳያደርጉ በመመሪያ ደረጃ ተገልጿል።
ትክክለኛ የማንለው የምርጫ ውጤት አገላለፅ የትኛው ነው ?
• ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በሰጡት ማብራሪያ ፦
- ምርጫ ቦርድ ይፋ ሳያደርግ እና የምርጫው ሂደት እንዲሁም የምርጫ ቆጠራው ሳይጠናቀቅ እከሌ ነው ያሸናፈው፣ ይሄን ከተማ እንከሌ አሸነፈ ፣ይሄን ክልል እከሌ አሸነፈ ማለት አይቻልም።
- ቦርዱ ይፋዊ የውጤት ገለፃ ሳያደርግ ማንኛውም ግምታዊ መረጃ ፣ ቅድመ ውጤት ትንበያ ማድርግ አይቻልም።
- ሚዲያዎች ቦርዱ ይፋ የሚያደርገውን የምርጫ ውጤት ብቻ ነው መዘገብ ያለባቸው፤ ከዛ ውጪ የሚደረጉት ተቀባይነት አይኖራቸውም።
NB : ወደሌላ ችግር እንዳያመራ ምርጫ ቦርድ ይፋዊ የውጤት ገለፃ እንስኪያደርግ ማንኛውም አይነት ግምታዊ መረጃ ከማሰራጨት በመቆጠብ በትዕግስት መጠበቅ ያስፈልጋል።

#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ
በየምርጫ ጣቢያዎቹ ውጤት እየተለጠፈ ይገኛል፤ ነገር ግን በርካታ #ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ ነው።
ውድ አባላት ይፋዊና ቦርዱ ማህተም ያላረፈባቸውን ፤ በተለም ደግሞ በዘፈቀደ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎችን #በጥንቃቄ እንድትከታተሉ ይሁን።
ከምርጫ በኃላ ችግር የሚፈጥረው እንዲህ አይነት ጉዳይ ስለሆነ ሰላማዊ ሂደቱ እንዲጠበቅ አስተዋጽኦ አድርጉ።