TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ምርጫ2013

በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ፦

- የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ መዘግየት ፣
- በድምፅ አሰጣጥ ላይ የሚታይ መደነጋገር፣
- ሰዓት አለማክበር፣
- የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል አለመጠበቅ፣
- ረጃጅም ሰልፎች (በፍጥነት አለመሄድ) ፣
- የሰልፍ ተራ አለመጠበቅ፣
- የምርጫ ቁሳቁስ መቀያየር
- ቀልጥፍ ያለ መስተንግዶ ክፍተት
- መራጮች ምርጫ ካርዳቸውን የወሰዱበትን መታወቂያ ሳይዙ መሄድ
- "እከሌን ምረጡ" የሚል ቅስቀሳ ለማድረግ መሞከር የመሳሰሉት ችግሮች ከመስተዋላቸው በዘለለ የምርጫ ሂደቱ #በሰላም እየተካሄድ መሆኑን ከአዲስ አበባና ከክልል የምርጫ ጣቢያዎች የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

የ Tikvah - Ethiopia አባላት በተመለከቷቸው የምርጫ ጣቢያዎች እድሜያቸው የገፋ ዜጎች ፣ እናቶች አባቶች ድምፅ ለመስጠት ተሰልፈው ተመልከተዋል። ነፍሠ ጡሮች፣ ልጅ የታቀፉ እናቶች ተሰልፈው ድምፅ ሲሰጡ አስተውለዋል።

በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ በፀጥታ እና በሰላም ረገድ ምንም ጥቆማ ከአባላቶቻችን አልተላከም፤ ሁሉም ሂደት #በተረጋጋ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ገልፀውልናል።

Photo Credit : Tikvah Family (Addis Ababa)

@tikvahethiopia
ፎቶ : የኢትዮጵያ ስድስተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ መካሄድ ከጀመረ ሰዓታት ተቆጥረዋል፤ አሁንም የድምፅ መስጠት ሂደቱ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ቀጥሏል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#LIVE

ውድ ቤተሰቦቻችን ሁለት በቀጥታ የሚሰራጩ ጉዳዮች ፦

- የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል እስካሁን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ተዘዋውሮ የተመለከተው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት (ከ4:30 ጀምሮ)

- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ከስካይ ላይት ሆቴል ከስፍራው እናሰማችኃለን (ሰዓቱ ሲደርስ እንነግራችኃለን)

@tikvahethiopia
Live stream finished (3 minutes)
Audio
AudioLab
#ምርጫ2013

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ፦
- ሰሚት 2 የምርጫ ጣቢያ፤
- ወረዳ 5 ምርጫ ጣቢያ 1፤
- ምሥራቅ በር ምርጫ ጣቢያ፤
- ወረዳ 5 ምርጫ ጣቢያ 6 እና ምርጫ ጣቢያ 4.1 ተዘዋውረን የምርጫ ሂደቱን ተመልከትናል።

በቀጥታ Voice Chat መከታተል ያልቻላችሁ የድምፅ ቅጂው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
የፖሊስ ሪፖርት :

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በአገር አቀፍ ደረጃ እስከአሁን ባሰባሰበው መረጃ መራጩ ህዝብ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላማዊና በተረጋጋ መንገድ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል።

በቀጣይ ተመሳሳይ መረጃ ከፌዴራል ፣ ከክልልና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እያሰባሰበ ተአማኒነት ያለው መረጃ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
ፎቶ : ይህ አ/አ አያት ዞን ሁለት የሚገኝ ምርጫ ጣቢያ ነው። መራጩ ዜጋ ከጥዋት ጀምሮ ተሰልፏል፤ ሰልፉ ግን የሚጠበቀውን ያህል ንቅንቅ አላለም።

ሌሎችም ጣቢያዎች ላይ ቀደም ብለን እንዳሳወቅነው ተመሳሳይ ሁኔታ ይታያል፤ ይህ ሁናቴ መራጩን ዜጋ እያሰላቸ ነው #መፍትሄ ይፈልጋል።

(የቲክቫህ አባላት)

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

(ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ/ም)

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከደቂቃዎች በኃላ በዛሬው ቀን ስላለው የምርጫ እንቅስቃሴ የመጀመሪያ ዙር መግለጫ ይሰጣል።

መግለጫውን የሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላት በቦታው ተገኝተዋል።

ውድ አባላት በመግለጫው ላይ የሚነሱትን ዋና ዋና ጉዳዮችን የምንልክላችሁ ይሆናል።

ከዚህ ባለፈ በቀጥታ መግለጫውን በ Voice Chat መከታተል እንደምትችሉ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
Live stream started
👆ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እየሰጡ የሚገኙትን መግለጫ በቀጥታ በ Voice Chat ያዳምጡ።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
Live stream finished (25 minutes)
መግለጫ
TIKVAH-ETHIOPIA
#መግለጫ1

ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከደቂቃዎች በፊት የሰጡትን መግለጫ በቀጥታ በVoice Chat ላይ ማዳመጥ ላልቻላችሁ እና ላመለጣችሁ የድምፅ ቅጂው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
"የሰማያዊ ሳጥን ስርቆት"

ደቡብ ክልል ኦባደብረፃሃይ የምርጫ ክልል አንድ ጣቢያ ላይ ሰማያዊ ሳጥን መሰረቁን የምርጫ ቦርድ ሰብሰባዊ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አሳውቀዋል።

ይህንን ጉዳይ ፖሊስ እያጣራው መሆኑን በመግለፅ ምርጫ ቦርድ በፍጥነት ምን ማድረግ እንደሚችል በማወቅ እርምጃ ይውሳዳል ብለዋል።

እስካሁን ድረስ ቦርዱ እርምጃ ያልወሰደ ሲሆን አንድ ጣቢያ ብቻ ስለሆነ ቦርዱ ፈጣን እርምጃ ይወስዳል ሲሉም ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
"እስካሁን ያጋጠመ የፀጥታ ችግር የለም" - ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እስካሁን ባለው ሂደት አንድም ቦታ የፀጥታ ችግር እንዳልገጠመ አሳውቀዋል።

በአምቦ አንድ የምርጫ ክልል አንድ ጣቢያ አስፈፃሚዎች በደረሳቸው መረጃ ተደናግጠው ከአካባቢው ገለል ማለታቸውን ነገር ግን ምን ችግር እንዳልነበር ገልፀዋል።

ወ/ሪት ብርቱካን በጣቢያው የምርጫ ሂደቱ "እናስቀጥላለልን ብለን ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል።

ከዚህ ውጭ ምርጫው እየተደረገባቸው ባሉ ቦታዎች ሁሉ በሰላም መራጮች ድምፅ እየሰጡ እንደሆነ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia