#ማስጠንቀቂያ
የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ታሽጎ የሚሄድበትን ሳጥን ፦
- መክፈት
- ማንቀሳቀስ
- መቁረጥ
- ውስጡን ማየት ከፍተኛ የሆነ #ወንጀል ነው።
ምርጫ ቦርድ ለሁሉም ምርጫ አስፈፃሚዎች፣ ወረዳ ላይ ያሉ ዝቅተኛ እርከን ላይ የሚሰሩ የመንግስት አካላት (ይከፈት እንየው የሚሉ) በሙሉ ከፍተኛ #ማስጠንቀቂያ ሠጥቷል።
በማንኛውም ሁኔታ በምርጫ ክልሎች ላይ ችግር ተፈጥሮ ከተገኘ ወደድጋሚ ምርጫ እንደሚሄድ መታወቅ አለበት ብሏል ቦርዱ ፤ አክሎም የድጋሚ ምርጫ ለሀገር ሃብት ጠቃሚ ስላልሆነ፣ ቦርዱም ብዙ ገንዘብ ስለሚያባክን ከድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ጋር በተገናኘ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል።
#TikvahEthiopia #TikvahFamily
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#ምርጫ2013 ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦች በዛሬው ዕለት "የምርጫ ወቅት እና ሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት" ላይ ትኩረቱት ያደረገ አጭር ገለፃ በቀጥታ በቴሌግራም Voice Chat ይኖረናል። ገለፃው በዋነኝነት በዚህ ለሀገሪቱ ወሳኝ በሆነ ወቅት ላይ በሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት ሊፈጠር የሚችለውን ችግር በማስቀረቱ ረገድ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለን እንጠብቃለን። አቅራቢዎቹ : ከመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል…
Audio
AudioLab
#ሀሰተኛ_መረጃ_እና_ምርጫ2013
"የምርጫ ወቅት ላይ ስለሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እና እንዴት እነዚህን ሀሰተኛ መረጃዎችን መከላከል እንችላለን" በሚለው ጉዳይ ዛሬ በቀጥታ Voice Chat ለቲክቫህ ቤተሰቦች ገለፃ ተደርጓል/ለጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቷል።
ገለፃና ለጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ከCARD በፍቃዱ ኃይሉ ፤ ከኢትዮጵያ ቼክ ደግሞ ኤልያስ መሰረት ነበሩ።
ምናልባት በቀጥታ በVoice Chat ገለፃውን ማዳመጥ ሳትችሉ የቀራችሁ ቤተሰቦቻችን ከላይ የድምፅ ቅጂው ተያይዟል፤ አዳምጡት።

የነገ ምርጫ/የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን በተመለከተ ያሉት ሂደቶች ፦
- አንድ መራጭ የመራጮች ምዝገባ ካርዱና ለመራጮች ምዝገባ ያካሄደበትን መታወቂያ መያዝ አለበት።
- መራጩ ምርጫ ጣቢያ በደረሰበት ወቅት ሰልፍ ካለ መሰለፍ ይኖርበታል።
- በሰልፉ ላይ ምንም አይነት ቅደም ተከተል (በስም ፣ በፊደል ወይም በምርጫ ካርድ...) የለም።
- የሰልፍ ርቀት የሚያስጠብቁ፣ ሰልፉን ሁኔታ የሚያስተካከሉ አካላት የሚሉትን ማዳመጥ ይኖርበታል።
- መራጩ ተሰልፎ ተራው ሲደርስ ወደውስጥ ገብቶ መዝገቡ ላይ ስሙ መኖሩ ተረጋግጦ የድምፅ መስጫ ወረቀት ይሰጠዋል።
- የድምፅ መስጫ ወረቀት ሲሰጠው እጁ ላይ የቀለም ምልክት ይደረግበታል።
- በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚመርጠውን እጩ የሚመርጥበት የተሸፈነ ወይም ደግሞ የተከለለ (የድምፅ አሰጣጥ መከለያ) አለ እዛ ገብቶ ድምፁን ይሰጣል፤ መራጩ ተመልሶ ሲወጣ ባሉት ሳጥኖች ወስጥ ድምፁን ይከታል።

#Attention
በድምጽ መስጫ ቀን የተከለከሉ ተግባራት ምን ምን ናቸው ?
• ማንኛውም ሰው ከምርጫ ጣቢያው 200 ሜትር ዙሪያ መለስ ርቀት ውስጥ በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ፣ የጦር መሣሪያ ይዞ ወይም በሌላ በማናቸውም ፀጥታን በሚያደፈርስ ሁኔታ ውስጥ መገኘት የለበትም
• መራጭ ያልሆኑና ድምፅ የሰጡ ሰዎች በምርጫ ጣቢያው ውስጥ መገኘት የለባቸውም
• ማንኛውም ሰው ያለፈቃድ ወደምርጫ ጣቢያው በመግባት / በምርጫ ጣቢያው ግቢ ውስጥም ሆነ ውጭ የምርጫውን እንቅስቃሴ ማወክ ወይም ማደናቀፍ ወይም ምንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ እንቅስቃሴ ማድረግ የለበትም
ወደ ምርጫ ጣቢያ የማይገቡ ነገሮች ምንድናቸው?
• ማንኛውም ሰው እንደ በራሪ ወረቀት፣ ፖስተር እና በሌሎች አጭር ጽሁፍ መልክ የተዘጋጁ የምርጫ ቅስቀሳ ሰነዶችን ይዞ ወደ ምርጫ ጣቢያው መግባት አይችልም፡፡
• ማንኛውም ሰው የጦር መሳሪያ ወይም እንደጩቤ እንደ ሴንጢ የመሳሰሉ ስለትነት ያላቸውን ወይም እንደየአካባቢው ሁኔታ ለሀይል መጠቀሚያነት የሚውሉ እንደዱላ ፣ አለንጋ ፣ ቁራጭ እንጨት ወይም ብረት ወይም ሌላ ማንኛውንም ተቀጣጣይ ወይም የሚፈነዳ ጠጣር ወይም ፈሳሽ ነገር ይዞ ወደ ምርጫ ጣቢያ መግባት የለበትም።
• ከላይ የተዘረዘሩትን የተከለከሉ ነገሮች ወደምርጫ ጣቢያ ይዞ የመጣ መራጭ የምርጫ ጣቢያው የሰልፍ አስከባሪ በሚሰጠው መመሪያ መሰረት በአደራ አስቀምጦ መግባት አለበት።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ

#ምርጫ2013 #ኢትዮጵያ
እጅግ የተከበራችሁ የTikvah Ethiopia ቤተሰብ አባላት በሙሉ ነገ ሀገራችን ከምታደርገው 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጋር በተያያዘ መልዕክታችሁን በእነዚህ አድራሻዎች አስቀምጡ ፦
- በቴሌግራም Bot : @tikvahethiopiaBOT
- በድረገፅ www.tikvahethiopia.net
- በትዊተር በመልዕክት መቀበያ twitter.com/tikvahethiopia?s=09
- በኢሜል [email protected]
- SMS : +251919743630
ውድ አባላት በምርጫው ወቅት ምርጫ ቦርድ ያስቀመጣቸውን ደንቦች፣ ህጎች እና መመሪያዎች አክብራችሁ ሰላማዊ የሆነ ምርጫ ሂደት ይኖር ዘንድ ሀገራዊ ኃላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ አደራ እንላለን።
እያንዳንዱን የምርጫ ሂደት #በንቃት እንድትከታተሉ ይሁን።

#ምርጫ2013
ኢትዮጵያ 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማካሄድ ጀመረች።
ዛሬ ምርጫ በሚካሄድባቸውን የምርጫ ጣቢያዎች ከማለዳው 12:00 ጀምሮ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ጀምሯል።
ከተለያዩ ከተሞች የወጡ ፎቶዎችን መመልከት እንደቻልነው ፥ ህዝቡ በለሊት ተነስቶ ድምፁን ለመስጠት ሰልፍ ይዟል።
ወደ በኃላ ምርጫውን ተንቀሳቅሰው ለመመልከት ፍቃድ ያገኙ የቲክቫህ አባላት በየምርጫ ጣብያው በመገኘት ያለውን ሁኔታ በቀጥታ በVoice Chat በቀጥታ ያሳውቃሉ።
Photo Credit : AAPS

ምርጫ 2013 በሚመልከት የTikvah-Ethiopia አባላት በመልዕክት መቀበያ አድራሻዎች መልዕክታቸውን እያስቀመጡ ነው።
ከለሊት 11:30 ጀምረው ተሰልፈው ምርጫ ጣቢያ ከጥዋት 1 ሰዓት በኃላ የተከፈተበት ቦታ እንዳለ፣ በአዲስ አበባ እና በክልል ባሉ አንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ለምርጫው ቢገኙም ጣቢያዎች ዘግይተው መከፈታቸውን አሳውቀዋል።
አባላቶቻችን እስካሁን ባለው የተመለከቱት ችግር ምርጫው ይጀመራል ተብሎ ይፋ በተደረገበት ሰዓት አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው መራጮችን አለማስተናገዳቸውን ነው።
ከዚህ ባለፈ የኮቪድ-19 መከላከያ ፕሮቶኮል ያለማክበር ችግር እንዳለ አንስተዋል።
በፀጥታ እና በሰላም በኩል ግን ሂደቱን በተረጋጋ መንፈስ እየሄደ እንዳለ አባላት እያሳወቁ ነው።
የድምፅ መስጫ ሰዓቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ በሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫ ያለውን የምርጫ እንቅስቃሴ እየተከተልን እናሳውቃለን።
Photo Credit : Tikvah Family

በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ፦
- የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ መዘግየት ፣
- በድምፅ አሰጣጥ ላይ የሚታይ መደነጋገር፣
- ሰዓት አለማክበር፣
- የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል አለመጠበቅ፣
- ረጃጅም ሰልፎች (በፍጥነት አለመሄድ) ፣
- የሰልፍ ተራ አለመጠበቅ፣
- የምርጫ ቁሳቁስ መቀያየር
- ቀልጥፍ ያለ መስተንግዶ ክፍተት
- መራጮች ምርጫ ካርዳቸውን የወሰዱበትን መታወቂያ ሳይዙ መሄድ
- "እከሌን ምረጡ" የሚል ቅስቀሳ ለማድረግ መሞከር የመሳሰሉት ችግሮች ከመስተዋላቸው በዘለለ የምርጫ ሂደቱ #በሰላም እየተካሄድ መሆኑን ከአዲስ አበባና ከክልል የምርጫ ጣቢያዎች የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።
የ Tikvah - Ethiopia አባላት በተመለከቷቸው የምርጫ ጣቢያዎች እድሜያቸው የገፋ ዜጎች ፣ እናቶች አባቶች ድምፅ ለመስጠት ተሰልፈው ተመልከተዋል። ነፍሠ ጡሮች፣ ልጅ የታቀፉ እናቶች ተሰልፈው ድምፅ ሲሰጡ አስተውለዋል።
በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ በፀጥታ እና በሰላም ረገድ ምንም ጥቆማ ከአባላቶቻችን አልተላከም፤ ሁሉም ሂደት #በተረጋጋ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ገልፀውልናል።
Photo Credit : Tikvah Family (Addis Ababa)

ፎቶ : የኢትዮጵያ ስድስተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ መካሄድ ከጀመረ ሰዓታት ተቆጥረዋል፤ አሁንም የድምፅ መስጠት ሂደቱ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ቀጥሏል።
#TikvahFamily
@tikvahethiopia
#TikvahFamily
@tikvahethiopia
#LIVE
ውድ ቤተሰቦቻችን ሁለት በቀጥታ የሚሰራጩ ጉዳዮች ፦
- የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል እስካሁን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ተዘዋውሮ የተመለከተው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት (ከ4:30 ጀምሮ)
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ከስካይ ላይት ሆቴል ከስፍራው እናሰማችኃለን (ሰዓቱ ሲደርስ እንነግራችኃለን)