TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ጉዳይ የዛሬው የG7 ስብሰባ ትልቁ አጀንዳ እንደነበር ተሰምቷል። ከG7 ስብሰባ ጋር በተገናኘ የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዜዳንት ቻርልስ ሚሼል በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። የ7 ወራቱ ግጭት ፣ ጭካኔ ፣ ብሔርን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎችን ከመቼውም ጊዜ ወደ ከፋ ሰው ሰራሽ ረሃብ እየወሰደ…
G7 ስብሰባ ተጠናቀቀ።

የG7 ሀገራት መሪዎች ላለፉት 3 ቀናት ሲያደረጉ የነበሩትን ስብሰባ ዛሬ አጠናቀዋል። በስብሰባው መጠናቀቅ በኃላም ባለ 70 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

ከዚህ ቀደም መረጃዎችን እንደተለዋወጥነው ከG7 ስብሰባ አጀንዳዎች መካከል የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ጉዳይ አንዱ እኛ ዋነኛው ነበር።

የG7 ሀገራት ስብሰባው ማጠቃለይ ስለትግራይ ምን አሉ ?

- ትግራይ ውስጥ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

- በ100 ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ መጋለጥ፣ በክልሉ የቀጠለው ግጭት፣ አጠቃላይ እየተፈጠረ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ አሳስቦናል ብለዋል።

- ጠብ ጫሪነት ተግባራት በፍጥነት እንዲቆሙ ፣ በሁሉም አካባቢዎች የእርዳታ ድርጅቶች ያልተገደበ እንቅስቃሴ እንዲፈቀድላቸውና የኤርትራ ወታደሮች በአፋጣኝ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

- በትግራይ ክልል ተፈጽመዋል ያሏቸውን ፆታዊ ጥቃቶችን ፣ አሰቃቂ ግድያዎችን እና ድርጊቶችን አውግዘዋል።

- የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የፈጸሙ አካላት ለፍትህ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።

- በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የተጀመረውን ምርመራ በደስታ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል። 

- ሁሉም ወገኖች ለቀውሱ ብቸኛ መፍትሔ የሆነውን ተዓማኒ የፖለቲካ ሒደት እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

- የኢትዮጵያ መሪዎች ብሔራዊ እርቅ እና መግባባት የሚፈጥር ሰፊ እና አካታች የፖለቲካ ሂደት እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከስልጣናቸው ተነሱ።

እስራኤልን ለ12 ዓመታት የመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በዛሬው እለት ከስልጣናቸው ተነስተዋል።

ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከስልጣናቸው የተነሱት የሀገሪቱ ከኔስት (ፓርላማ) ጥምረት የፈጠሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመሰረቱትን መንግስትን መቀበሉን ተከትሎ ነው።

የግራ ዘመሙ የያማኒያ ፓርቲው ናፍታሊ ቤንት የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስፍራውን ተረክበዋል።

ናፍታሊ ቤንት በዛሬው ዕለት ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሲሆን፣ እስከ 2023 ድረስ እስራኤልን የሚመሩ ይሆናል።

ከ2023 በሁዋላም ስልጣኑን ለያዴህ አቲድ ፓርቲ መሪው ያኢር ላፒድ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስፍራውን የሚያስረክቡ ይሆናል። ይህም ጥምር መንግስት የመሰረቱት ፓርቲዎች ስልጣን ለመጋራት በደረሱት ስምምነት መሰረት እንደሚፈጸም ተነግሯል።

ኔታንያሁ ከስልጣናቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በርካታ እስራኤላውያን አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን እየገለጹ ነው።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

'ከሀሰተኛ ምስሎች ተጠንቀቁ'

የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ምን እንደሚመስሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለማስተማሪያ ባዘጋጃቸው ወረቀቶች አሳይቷል።

ከዚህ ውጪ በሌላ ይዘቶች የሚሰራጩ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች #ሐሰተኛ እና ለማደናገር የሚፈበረኩ ናቸው።

ውድ የቲክቫህ አባላት የምርጫው መቃረብ ተከትሎ የሀሰተኛ መረጃ ዝውውር ከወትሮው በርከት ሊል ስለሚችል አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ አደራ እንላለን።

የምርጫ ጉዳይ መረጃዎችን ቀጥታ ከ "ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ" ውጭ ካልሆነ ለሰው ከመናገራችሁ እና ከማጋራታችሁ በፊት ደጋግማችሁን እንድታጣሩ/እንድታረጋግጡ ይሁን።

www.tikvahethiopia.net

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #SaudiArabia #Attention "...የአካል ወይም ንብረት ጉዳት የደረሰባችሁ ዜጎች ያላችሁን ማስረጃ በመያዝ ለቆንስላ ጽ\ቤቱ ማቅረብ ትችላላችሁ" - በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ የሳዑዲ ዓረቢያ የፀጥታ ኃይሎች በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ተከትሎ ዜጎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ…
#Update

በሳዑዲ ዓረቢያ የህግ አስከባሪ አካላት ተይዘው የነበሩ ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ከእስር እንዲፈቱ መደረጉ ተገፀ።

የሳዑዲ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነ እና ዜጎችም ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ መሰራጨቱ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ ከተለያዩ ከተሞች በህግ አስከባሪ አካላት የተያዙ የነበሩና ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ያላቸው ከጅዳና መካ ከተሞች ከአርባ በላይ ኢትዮጵያውያን ከጂዛን ዘጠና አራት ከመዲና ስድስት መቶ እንዲሁም ከአብሃ ሰላሳ ስምንት ኢትዮጵያውያን የበጅዳ የሚገኘድ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ\ቤቱ ባደረገው ክትትል እንዲፈቱ መደረጉ ተነግሯል።

ጉዳዩን አስመልክቶም የቆንስላ ጽ\ቤቱ ከሚመለከታቸው የሳዑዲ መንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በቅርበት እየተነጋገረ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን በተለይ በህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ አማካኝነት ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርስ ማንኛውም የማዋከብና እንግልት ምክንያት እንዲገለፅለትና ይሄው በአስቸኳይ እንዲቆም የቆንስላ ጽ\ቤቱ በኦፊሴል ጉዳዩ ለሚመለከተው የሳዑዲ መንግስት ተቋም እንዳመለከተ አሳውቋል።

ቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ፥ በቀጣይ ቀናት በጉዳዩ ላይ ተገቢውን ክትትል በማድረግ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ እንደያደርግ እና እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

#ኢትዮጵያውያን አሁንም ቢሆን ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዲቀጥሉ የጥንቃቄ መልዕክት ተላልፏል።

መረጃው የኢፌድሪ ቆንስላ ፅ/ቤት (ጅዳ) ነው።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

“... ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ተደርጓል” - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

ኢትዮጵያ የምታካሂደው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፌዴራል እና የክልል የደህንነትና የፀጥታ መዋቅር በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገለፀ።

ይህን የገለፁት የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ናቸው።

የፌዴራል እና የክልል የደህንነት እና የፀጥታ አካላታ ግብረሐይል በወቅታዊ የሀገሪቷን ደህንነት የሚገመግም እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጥ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።

በዚሁ ወቅት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ቀጣዩ የምርጫና ድህረ ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

የፌዴራል እና ክልል የፀጥታ እና ደህንነት አካላት የጋራ ግብረ ሀይል የሀገረቷን ወቅታዊ የደህንነት ሁኔታ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሏል። #ኢብኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ምርጫ2013 “... ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ተደርጓል” - አቶ ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ የምታካሂደው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፌዴራል እና የክልል የደህንነትና የፀጥታ መዋቅር በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገለፀ። ይህን የገለፁት የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ናቸው። የፌዴራል እና የክልል የደህንነት እና የፀጥታ አካላታ ግብረሐይል…
"...ከደህንነት መስሪያ ቤቱ ክትትል አያመልጡም" - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

ኢትዮጵያ የምታካሂደውን ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫው እና የሁለተኛውን ዙር የህዳሴውን ግድብ ሙሌት ለማስተጓጎል የሚሰሩ የውጭና የውስጥ ጠላቶች መኖራቸውን የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ።

አቶ ተመስገን ይህን በኡሀን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው የፌዴራል እና የክልል የደህንነት እና የፀጥታ አካላታ ግብረሐይል ውይይት ላይ ነው።

ዳይሬክተሩ ፥ ምርጫውን እንዲሁም 2ኛውን ዙር የግድቡን ሙሌት ለማሰናከል የሚሰሩ የውጭና የውስጥ ጠላቶች አሉ ነገር ግን ከደህንነት መስሪያ ቤቱ ክትትል አያመልጡም ብለዋል።

ምርጫው ሆነ እና የግድቡ ሙሌት ያለምንም ችግር እና መስተጓጎል በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በምርጫ 2013 ይወዳደራሉ። እንደ ሀሩን ሚዲያ /Harun Media/ ዘገባ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በመጭው ምርጫ #በግል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ይወዳደራሉ። ለዚህም ምዝገባ የሚያስፈልገውን የ2,500 ሰው ድጋፍ በማሰባሰብ በእጩነት መመዝገባቸው ታውቋል። በሌላ በኩል፦ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) እንደሚወዳደሩ ሀሩን ሚዲያ…
#ምርጫ2013

ከጥቂት ቀናት በኃላ በሚደረገው ምርጫ 2013 በግል ይወዳደራሉ ተብለው ከሚጠበቁ ተወዳዳሪዎች መካከል ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በግል ምክንያት በምርጫው መቀጠል እንደማይችሉ አሳወቁ።

ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ይህ ያሳወቁት ዛሬ ለ'ጅማ ከተማ ነዋሪዎች' በይፋዊ ማህበራዊ ገፃቸው ላይ ባሰራጩት አጭር የፅሁፍ መልዕክት ነው።

የኡስታዝ አህመዲን ጀበል ሙሉ መልዕክት ፦

"ዘንድሮ በሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጅማ ከተማ እንድወክላችሁ ሽማግሌ ከመላክ አንስቶ በተለያዩ መንገዶች እጩ እንድሆን በመጠየቅና ለእጩነት የሚጠበቀውን ፊርማ በራሳችሁ ተነሳሽነት በመፈረምና በማስፈረም የምርጫ ቅስቀሳ እንድጀምር፣ ለቅስቀሳውም «የሚጠበቅብንን ሁሉ ለመወጣት ከጎንህ ነን» በማለት ላሳደራችሁብኝ እምነትና አክብሮት ከልብ እያመሰገንኩ፤ በግል እጩነት ተመዘግቤ በነበረው በምርጫው በራሴ የግል ምክንያት ልቀጥል አለመቻሌን ላላሳወቅኳችሁ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ሳሳውቃችሁ ከታላቅ አክብሮት እና ይቅርታ ጋር ነው"

@tikvahethiopia
የኢትዮ-ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው አካላት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መግለጽ ይችላሉ ተባለ።

ይህ የተገለፀው ዛሬ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ይርጋና የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ብሩክ ታዬ በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው።

የፍላጎት መግለጫው ከነገ ጀምሮ ለአንድ ወር ክፍት ይሆናል ተብሏል።

ሰነዱን ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው አካላት ከሰኔ 8 ቀን 2013 ጀምሮ ከተቋማቱ ድረ ገጾች ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

በፍላጎቱ ላይ በመመስረት ከአንድ ወር በኋላ ዓለም አቀፍ ጨረታ ይወጣል ተብሏል።

በቀጣይ የኢትዮ ቴሌኮም 5 በመቶ ድርሻ #ለኢትዮጵውያን እንደሚሸጥ ይፋ ተደርጓል። (ኢዜአ)

@tikvahethiopia
የአረብ ሊግ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በህዳሴ ግድብ ላይ ሊመክሩ ነው።

በመጪዉ ማክሰኞ በዶሃ ኳታር በህዳሴዉ ግድብ በተመለከተ የአረብ ሊግ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባ ያካሂዳሉ።

በተመለከተ የአረብሊግ ዋና ጸሃፊ ረዳት አምባሳደር ሂሳም ዘኪ የዶሃዉ ስብሰባ የፌብሩዋሪ 8 ቀን 2021 የካይሮ የሊጉ ስብሰባ ቀጣይ መሆኑን ለአልጀዚራ በሰጡት ምላሽ ገልጸዋል።

የአረብ ሊግ አቋም ለግብፅና ለሱዳን ፖለቲካዊ ድጋፍ መስጠት መሆኑንም አንስተዋል።

በመጪዉ ማክሰኞ ሶስተኛ ዉሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅና የቋሚ መልዕክተኞች ስብሰባ መካሄዱን ገልጸዋል።

ግብፅ እና ሱዳን ችግሩን ለመፍታት ያደረጉትን ጥረት በመደገፍ ጉዳዩ ወደ ጸጥታዉ ምክር ቤት ለማቅረብ አረብ ሊግ እንደሚደግፍም አስረድተዋል።

የአረብ ሊግ ኢትዮጵያን ከአቋሟ ማስቀየር እንደማይችልና አሜሪካ እንዲሁም ምዕራባዊያን እንዲሁም አዉሮፖዊያን ኢትዮጵያን ከአቋሟ ሊያስቀይሩ አለመቻላቸዉን ይህም የዉሃዉ ምንጭ አገር በመሆኗ አረብ ሊግ ኢትዮጵያን ሊያስገድድ እንደማይችል ረዳቱ ገልጸዋል።

ከአልጀዚራ ቻናል
ትርጉም፦አብራር ሙክታር

@tikvahethmagazine
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#GERD🇪🇹

"...በሚመጣው ነገር ሁሉ መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን" - የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት

የመከላከያ ሰራዊት አባላት የታላቁ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር ሙሌት እንዲሁም አጠቃላይ ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን መስዋእትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ገለፁ።

የሰራዊቱ አባላት ይህን ሲገልፁ የተሰማው ሀገር መከላከያ ባሰራጨው የ1 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ርዝማኔ ባለው ቪድዮ ላይ ነው።

የመከላከያ አባላት የግድቡ ስራ ለሰከንድም ሳይቆም ይሰራል፣ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌትም ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

"እኛ በህይወት እስካለን የግድባችን ስራ ለሰከንድ አይደናቀፍም" ብለዋል።

ሁሉም #ኢትዮጵያዊ ከጫፍ ጫፍ ሆ ብሎ በመነሳት የገነባው ግድብ መሆኑን የተናገሩት የሰራዊቱ አባላት ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ለሚመጣው ነገር ሁሉ ቀድመን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን በዚህም ህዝቡ በምንም መልኩ ሊጠራጠር አይገባም ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
#Update

በዛሬው ዕለት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ፀረ-ሽብር ችሎት በእነ አቶ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ብይን ሰጥቷል።

የእነ አቶ እስክንድር ነጋ ጠበቆች እነ አቶ አስክንድር በ6ኛው አገራዊ ምርጫ እጩ ሆነው በመቅረባቸው ምክንያት ያለመከሰስ መብታቸውን ፍ/ቤቱ አረጋግጦ ከእስር እንዲፈቱ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበው ነበር።

ፍርድ ቤት ፥ የወንጀል ክሱ የተመሠረተው እጩ ሆነው ከመመዝገባቸው በፊት ስለሆነ ጥያቄውን አልተቀበልኩትም በማለት በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ብይን ሰጥቷል።

ጠበቆቹ በብይኑ ላይ ቅሬታ ስላደረባቸው ይግባኝ ለጠቅላይ ፍ/ቤት በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ።

መረጃው የባልደራስ ፓርቲ / የህግና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኃላፊ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ነው።

@tikvahethiopia
#Update

እናታችን ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና (እዳዬ) በኮቪድ-19 ተይዘው በጳውሎስ ሆስፒታል በጽኑ ሕሙማን ክፍል ሕክምና ላይ እንዳሉ መገለጹ ይታወሳል።

በርካታ የቲክቫህ ቤተሰቦች አሁን ጤናቸው በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል፥ ጠይቁልን ባላችሁን መሰረት የጤናቸውን ሁኔታ ከማህበሩ ጠይቀናል።

ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና እናታችን አሁንም በሆስፒታሉ ጥሩ ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የተገለጸልን ሲሆን አሁንም ድረስ ኦክስጅን ተገጥሞላቸው እንደሚገኙ ተረድተናል።

ሆስፒታል ከገቡበት ቀናት ጋር ሲነጻጸር አሁን ላይ ጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብለናል። አሁንም ሁሉም በየእምነቱ በጸሎት እንዲያስባቸው ማህበሩ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#GERD

ሱዳን በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ጊዜያዊ ውል ማድረግ እንደምትፈልግ አስታወቀች።

ሱዳን ያስቀመጠችው ቅድመ ሁኔታ ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ሁለተኛውን ዙር የግድቡን ሙሌት ካካሄደችም በኋላም ቢሆን ድርድሩን ለማስቀጠል የሚጠይቅ መሆኑን የሀገሪቱ የውሃ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

በዚህም ሱዳን ቀደም ሲል ከስምምነት በተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ መፈራረምን ጨምሮ ቅድመ ሁኔታውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የሚደረግ ጊዜያዊ ስምምነት እንደምትቀበል የውሃ ሚንስትሩ ያሴር አባስ ዛሬ ካርቱም ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

በህዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገው ድርድር እንዲቀጥል እና ድርድሮቹ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ እንዲከናወን የሱዳን ፍላጎት መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ሦስቱ ሃገራት አስቀድሞ በአብዛኞቹ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ «ከመግባባት ደርሰዋል» ነገር ግን ከአንዳች አስገዳጅ ስምምነት አልተደረሰም ሲሉ ሚንስትሩ አክለዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ሁለተኛውን ዙር የግድቡን ሙሌት ከፊታችን ባሉት የክረምት ወራት ለማከናወን መዘጋጀቱን ማስታወቁ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ፣ግብጽ እና ሱዳን በአፍሪቃ ህብረት አደራዳሪነት ባለፈው የሚያዝያ ወር በኪንሻሳ ካደረጉት እና ያለስምምነት ከተለያዩበት ድርድር ወዲህ አልተገናኙም።

(ዶቼ ቨለ)

@tikvahethiopia
በልደታ ክ/ከተማ ቦንብ ፈንድቶ በአንድ ሰው ላይ የአካል ጉዳት ማድረሱን ፖሊስ አስታወቀ።

በፍንዳታው ዙሪያ ያሉ መረጃዎችን ለማወቅ ምርመራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ሰኔ 7ቀን 2013 ዓ.ም በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዮ ቦታው ዮርዳኖስ ሆስፒታል መግቢያ ፊት ለፊት ለጊዜው ምንነቱ ባልተረጋገጠ ምክንያት ከቀኑ 8፤30 አካባቢ ኤም 7.5 የሚባል ፕላስቲክ ቦንብ ፈንድቶ ቦንቡን ይዞት በነበረው ግለሰብ የግራ እጁ ላይ ከባድ ጉዳት አድርሶበታል፡፡

ከፖሊስ መምሪያው በተገኘው መረጃ መሰረት ግለሰቡ በአካባቢው በጎዳና ላይ ኑሮን በማድረግ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ብረታ ብረቶችን በመልቀም የሚተዳደርና ከሶስት ቀን በፊት ስብርባሪ ብረቶችን ሲለቅም ቦንቡን እንዳገኘው የሰጠውን ቃል ዋቢ አድርጎ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ግለሰቡ ለህክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የተላከ ሲሆን በፍንዳታው ዙሪያ ያሉ መረጃዎችን ለማወቅ ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን እና የምርመራው ውጤቱን ወደፊት እንደሚያሳውቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃዎችን ከተገቢው ቦታ ለማግኘት የሚያደርጋቸው ጥረቶች የሚበረታቱ ሲሆን አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ከጸጥታ አካላት ጋር ያለውን ተባባሪነት አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

(የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን)

@tikvahethiopia