TIKVAH-ETHIOPIA
የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውስኔ መራዘም ቅሬታ አስነሳ። የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ዉሳኔ የመራዘሙን ውሳኔ እንደማይቀበሉ የካፋ እና የዳውሮ ዞኖች ገለጹ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ዉሳኔ እንዲራዘም መወሰኑን ተከትሎ ከካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ዉሳኔውን ተቃውሟል። የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳሻው ከበደ በሰጡት መግለጫ ''ለህዝበ ውሳኔው አስፈላጊዉ ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ…
"...ቦርዱ የህዝበ ውሳኔውን ቀን ለማራዘም ያሳለፈውን ውሣኔ ዳግም ሊመለከተው ይገባል" - የደቡብ ምዕራብ ክልል አደራጅ ዓብይ ኮሚቴ
የደቡብ ምዕራብ ክልል አደራጅ ዓብይ ኮሚቴ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝበ ውሳኔ ቀን ለማራዘም ያሳለፈውን ውሣኔ ዳግም እንዲመለከት ጠይቋል።
ዓብይ ኮሚቴው ይህንን የጠየቀው የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ተከትሎ በአዲስ አበባ ያካሄደውን አስቸኳይ ስብሰባ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው።
ኮሚቴው የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሣኔው ቀደም ብሎ በተያዘለት ጊዜ ከ6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ጋር እንዲፈፀም ጠይቋል።
የመንግስት ውሣኔና አቅጣጫ ተከትሎ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ህዝበ ውሣኔው በተቀመጠለት የጊዜ ሠለዳ እንዲካሄድ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን አስታውሷል።
የምርጫ ቦርድ ውሳኔ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው ብሏል።
የአካባቢው ህዝቦች የዘመናት ጥያቄያቸው ላይ ውሳኔ ለማሳረፍ የምርጫውን ቀን እየተጠባበቁ ይገኛልም ነው የተባለው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሪፌረንደሙን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ለማስፈፀም ላሳየው ተነሳሽነት እና የተግባር እንቅስቃሴ ዓብይ ኮሚቴው ምሥጋና ማቅረቡን www.waltainfo.com ዘግቧል።
ትላንት የካፋ ፣ የዳውሮ እንዲሁም የቤንች ሸኮ ዞኖች የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ተቃውመው መግለጫ ማውጣታቸው አይዘነጋም።
የዳውሮ፣ ካፋ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ቤንች ሸኮ ዞኖችና ኮንታ ልዩ ወረዳ በአንድ ላይ የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል እንዲመሰርቱ መወሰኑ ይታወሳል።
@tikvahethiopia

#EthioTelecom
ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊ በሆነ መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ የገነባቸውንና ጎብኚዎች በእንጦጦ ፓርክ የዳታ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸውን ስማርት ማማ (smart pole) የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
ስማርት ማማው የጎብኚዎችን ፍሰት መሰረት በማድረግ የፓርኩን ተፈጥሯዊ ገጽታውን በጠበቀ እና ለዕይታ ማራኪ በሆነ ዲዛይን የተተከለ ሲሆን በቀጣይም በፓርኩ ውስጥ ለሚከናወነው የ5ኛው ትውልድ (5G Technology) ኔትወርክ ዝርጋታ ዝግጁ እንዲሆን መደረጉ ተጠቅሷል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ በቀጣይ ኢኮ ቱሪዝም በሚካሄድባቸው የተለዩ ስፍራዎች ጋር የሚመሳሰሉ የካሞፍላጅ ማማዎች (Camouflage Towers) እንደሚተከሉ ተጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም በእንጦጦ ፓርክ እንደ ማሳያ ተደርጎ የቀረበው ይህ ዘመኑ ያፈራው ቴክኖሎጂ በቀጣይም የዘመናዊ ከተሞችን (Smart City) አስቻይ መሠረተ ልማቶችን ማለትም ለቴሌኮም አገልግሎት ፣ ለመንገድ መብራት ፣ ለአየር ንብረት ልኬት፣ ለትራፊክ ማኔጅመንት ፣ ለደኅንነት ካሜራ ፣ ለማስታወቂያ ስክሪን እና አማራጭ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያን በአንድ ላይ ማቀናጅት የሚያስችሉ ስማርት ማማዎችን ከተለያዩ የማንግስት እና የግል ተቋማት ጋር በመተባበር የሚተክል መሆኑን አስታውቋል፡፡
ምንጭ፦ ኢትዮ ቴሌኮም
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

ነገ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች !
የመስቀል አደባባይና እስከ ማዘጋጃ ቤት ድረስ የተከናወነው የመንገድ ግንባታ ምረቃ ምክንያት በማድረግ ሰኔ 6/2013 የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
የምረቃ ስነ ስርዓቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፦
- ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን የላይኛው አደባባይ
- ፒያሳ ጣሊያን ሰፈር መግቢያ
- ሱማሌ ተራ አካባቢ የሚገኘው አደባባይ
- አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ
- ጎላ ሚካኤል
- ጥቁር አንበሳ ሼል
- ሜትሮሎጂ
- ጎማ ቁጠባ
- ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ
- ለገሃር ጉምሩክ መብራት
- ቡናና ሻይ
- ገነት መብራት
- 4ኛ ክፍለ ጦር (ጥላሁን አደባባይ)
- ቂርቆስ መታጠፊያ
- አጎና ሲኒማ
- ኦሎምፒያ
- ኡራኤል አደባባይ
- ባምቢስ መታጠፊያ
- ካዛንቺስ ሼል
- ፍልውሃ ሸራተን አካባቢ መስጊድ
- ኦርማ ጋራዥ
- ንግድ ማተሚ ቤት
- ራስ መኮንን ድልድይ
- አፍንጮ በር ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ብሏል የከተማው ፖሊስ።
አሽከርካሪዎች ይህን ተገንዝበው አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀሙ ተብሏል።

#Tigray
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ጉዳዮች ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ ትግራይ ክልል ውስጥ የኤርትራ ኃይሎች የትግራይ ህዝብ ለረሃብ እንዲጋለጥ እያደረጉ ነው ሲሉ ከሰዋል።
ሎውኮክ ይህን ያሉት ከሮይተርስ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ወቅት ነው።
ኃላፊው ፥ የኤርትራ ወታደሮች እና የአከባቢው ተዋጊዎች ሆን ብለው ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ ባሉ አካባቢዎች ለሚገኙ ከ 1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሰብዓዊ አቅርቦት እንዳይደርስ እያገዱ ነው ብለዋል።
"በእርግጠኝነት ምግብ እንደ ጦር መሳሪያነት እያገለገለ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ፣ የተባበሩት መንግስታት እና የእርዳታ ድርጅቶች ከመጋቢት ወር ጀምሮ ለ3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ለሚጠጉ የትግራይ ነዋሪዎች ምግብና ሌሎች ድጋፎችን ማድረሳቸውን OCHA ገልጿል፤ ነገር ግን አብዛኛው እርዳታ በመንግስት ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች የሚከናወን ነው ሲሉ ሎኮክ ተናግረዋል።
የተመድ ሰብዓዊ ጉዳዮች ኃላፊ በሆኑት ማርክ ሎውኮክ ለቀረበው ክስ የኤርትራ መንግስት አሁናዊ ምላሽ ባይሰጥም ከዚህ ቀደም የኤርትራ ጦር ትግራይ ውስጥ ሰብዓዊ ድጋፎችን ይዘርፋል፤ ያግዳል መባሉን በተመለከተ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገ/መስቀል "የፈጠራ ወሬ ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተው ነበር።
የሮይተርስ ሙሉ ዘገባ👇
https://www.reuters.com/world/africa/exclusive-un-official-accuses-eritrean-forces-deliberately-starving-tigray-2021-06-11/

የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ጉዳይ የዛሬው የG7 ስብሰባ ትልቁ አጀንዳ እንደነበር ተሰምቷል።
ከG7 ስብሰባ ጋር በተገናኘ የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዜዳንት ቻርልስ ሚሼል በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
የ7 ወራቱ ግጭት ፣ ጭካኔ ፣ ብሔርን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎችን ከመቼውም ጊዜ ወደ ከፋ ሰው ሰራሽ ረሃብ እየወሰደ ነው ብለዋል።
መላው የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ችግሩን ለማስወገድ እንዲንቀሳቀስ ጥሪ እናቀርባለን ሲሉ ፅፈዋል።

ምክትል ጠ/ሚና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዛሬ በቪድዮ መልዕክት አሰራጭተዋል።
በመልዕክታቸውም በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በመጠቀም የተለያዩ አካላት በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር የሚያደርጉት ጥረት ኢትዮጵያን አሳዝኗል ብለዋል።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ የሚያስፈልጋት ጠንክራ ድጋፍ መሆኑን በመግለፅ፥ የኢትዮጵያን ህዝቦችና የግዛት አንድነት አንዲሁም ትስስርን በሰብዓዊነት ሽፋን ዝቅ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተቀባይነት የለውም ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍን ከፍ ለማድረግ፣ ማህበራዊ ትስስርን መልሶ ለመገንባት እና መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ከሁሉም አጋሮቿ ጋር ለመስራት ዝግጁ ናት ሲሉም ተደምጠዋል።
በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ወገኖች በሰብዓዊነት ሽፋን የኢትዮጵያን ህዝቦች እና የግዛት አንድነት እና ትስስር ለማዳከም ተልእኮ ይዘው ሲሰሩ ማየት 'የሚያሳዝን ተግባር ነው' እነዚህ ግለሰቦች እና አጋሮቻቸው ከዚህ ተግራቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል።
አቶ ደመቀ፥ "ኢትዮጵያ በራሷ ዜጎች ላይ ረሃብን እንደ ጦር መሣሪያነት እየተጠቀመች ነው" በሚል በሀገሪቱ ላይ የተለጠፉ ክሶች መሰረተ ቢስ ናቸው ብለዋል፤ እንደዚህ አይነት ክሶች በምንምን ስሌት ሰላምንና መረጋጋትን ለመፍጠር አይረዱም።
የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ አካላት በትግራይ ውስጥ በነጻነት እንዲሰሩ የሚያስችሉ አሰራሮች መዘርጋቱን ገልፀው፥ “አንዳንድ ተዋንያን ግን በሰብዓዊ ዕርዳታ ሽፋን የሽብርተኞችን ቡድን ለማስታጠቅ መሣሪያዎችን በድብቅ ለማስገባት መሞከራቸውን የሚያመለክቱ ተዓማኒ #ማስረጃዎች እንዳሉ ተናግረዋል፤ይህ አይነቱ ድርጊትት ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
#AlAIN

ዛሬ ጥዋት የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤ አደም ፋራህ የጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መልዕክት ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሼል እና ለአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዩርሱላ ቮን ደር ላየን ማድረሳቸው መገለፁ ይታወሳል። የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩቴ የተላከ ደብዳቤን ስለማድረሳቸው ተሰምቷል። ደብዳቤውን…
#Update
ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን መልዕክትን ለተለያዩ ሀገራት /ተቋማት እያደረሱ መሆኑን በተለያዩ መረጃዎች ተለዋውጠናል።
ለማስታወስ ያህል ፦
- የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ለኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩቴ የተላከ ደብዳቤን አድረሳዋል።
- የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድን የተላከ መልዕክት ለአውሮፓ ህብረት የስራ ሃላፊዎች አድርሰዋል።
- የውሀ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ከጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ አድርሰዋል።
በዛሬው ዕለት ደግሞ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የተመራ ልዑክ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መልእክት ለፈረንሳይ ፕሬዚደንት አድርሷል።
መልእክቱን የተቀበሉት የፈረንሳይ ፕሬዚደንት የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ አማካሪ ሚንስትር ፍራንክ ፓሪስ ናቸው።
ሚኒስትሯ መልዕክቱን ባስተላለፉበት ወቅት በሀገሪቱ ውሥጥ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ ከእሳቤው ጀምሮ ሂደቱና ውጤቶቹ ላይ ያተኮረ ገለጻ አድርገዋል።
በትግራይ ስላሉ የሰብዓዊ ድጋፍ እና የመልሶ ማቋቋም ተግባራት ላይ ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸው ታውቋል።
መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።

#Ethiopia #COVID19
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 5,405 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 136 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 274,028 አድርሶታል።
በ24 ሰዓት 2 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,237 ደርሷል።
የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,936,566 ደርሰዋል።

ነገ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ! የመስቀል አደባባይና እስከ ማዘጋጃ ቤት ድረስ የተከናወነው የመንገድ ግንባታ ምረቃ ምክንያት በማድረግ ሰኔ 6/2013 የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። የምረቃ ስነ ስርዓቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፦ - ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን የላይኛው አደባባይ - ፒያሳ ጣሊያን ሰፈር መግቢያ - ሱማሌ ተራ አካባቢ የሚገኘው አደባባይ -…
የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ነገ ይመረቃል።
2.6 ቢሊዮን ብር ወጥቶበት የተገነባው የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ነገ እንደሚመረቅ ይጠበቃል።
ፕሮጀክቱ እስከ ማዘጋጃ ቤት የሚዘልቅ የመንገድ ግንባታን ያካተተ ነው።
በተለይ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት በተጀመረበት ወቅት በአንዳንድ አካላት ከፍተኛ የሆነ ቅራኔ እና ተቃውሞ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቀርቦ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።
ከሰሞኑ በተሰራጨው የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ "ቃልን በተግባር" በተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ላይ ጠ/ሚስትሩ ይህንን ጉዳይ አንስተውት ነበር።
ጠ/ሚኒስትሩ ፥ ስራው ሲጀመር ቅራኔዎች እና ተቃውሞዎች እንደነበሩ አስታውሰዋል። አሁን ላይ ስራው ተሰርቶ መጠናቀቁን በመግለፅ ሁሉም ዜጋ ቦታውን የመጠበቅ ፣የማሳመር፣ የማስዋብ፣ ከዚህም የተሻለ ቦታ የመስራት ኃላፊነት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
መስቀል አደባባይ ፥ የህዝብ በዓላት ፣ የሙዚቃ ኮንሰርት ፣ ሃይማኖታዊ በዓላት፣ የመንግስት ፕሮግራሞች፣ የተለያዩ አይነት ትርዒቶች ሊታዩበት በሚያስችል መልኩ የተሰራ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።
እስከ 1 ሚሊዮን ሰዎችን ማስተናገድ የሚችልበት አቅም እንዲኖረው መደረጉን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የመስቀል አደባባይ ፓርኪንግ እጅግ ሰፊ እና ለአይንም ማራኪ ሆኖ የተሰራ እስከ 1450 ገደማ መኪና መያዝ የሚችል መሆኑን ገልፀዋል።
Photo Credit : Tikvah Family