TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
' አዲስ ስርዓተ ትምህርት በአማራ ክልል '

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በቅርቡ ተግባራዊ የሚኾን አዲስ የሥርዓተ ትምህርት ይፋ አድርጓል፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በቅርቡ ተግባራዊ የሚኾን አዲስ የሥርዓተ ትምህርት ይፋ አድርጓል፡፡

አዲሱን የሥርዓተ ትምህርት ይፋ ያደረጉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) ናቸው፡፡

በዚህም፦

- አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት በትምህርት ቤቶች አደረጃጀት ይለያል፦
° ከ1እስከ 6ኛ ያሉትን አንደኛ ደረጃ
° ከ7 እስከ 8 ያሉትን መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ፣
° ከ9 እስከ 12ኛ ያሉትን ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ በሚል ተደራጅቶ ወደ ሥራ እንዲገባ መወሰኑን አብራርተዋል፡፡

- የመምህራን ስልጠና ሥርዓትን በተመለከተ ከምልመላ ጀምሮ የስልጠና አይነት እና ጊዜ እንዲሻሻል ተደርጓል ብለዋል።

- ሥርዓተ ትምህርቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥነት እንዲኖረው የትምህርት ማዕቀፍ እንዲዘጋጅ መደረጉን ጠቁመዋል።

- ሁለተኛ ደረጃ ላይ የትምህርት አሰጣጥ የቀለም ትምህርት እና የሙያ ትምህርት ተብሎ በሁለት መንገድ ሊሰጥ ታስቧል፥ ትግበራውም በቀጣይ ዓመት ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል በተመረጡ ትምህርት ቤቶች፣ ከ7ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ባሉ ኹሉም ትምህርት ቤቶች ተግባዊ ለማድረግ ታቅዶ እየተሠራ ነው ብለዋል።

- የማስተማሪያ ቋንቋን በተመለከተ በአማርኛ፣ በአዊኛ፣ በኽምጣና እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች እንደሚኾን እና ሥርዓተ ትምህርቱም በዚሁ እንደሚዘጋጅ ገልጸዋል።

- የአርጎበኛ ቋንቋን ለማካተት የማጥናት ሥራ እየተሰራ እንደሆነ አንስተዋል።

- የግእዝ ቋንቋን በሥርዓተ ትምህርቱ ለማካተት ዝግጅት እየተደረገ እንደኾነም ጠቁመዋል።

(አሚኮ)

@tikvahethiopia
"...ግድያው ለሰው ልጅ ሕይወት ያለን ቸልተኝነት ያሳያል" - ሂዩማን ራይትስ ዋች

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች በደምቢ ዶሎ ከተማ በአደባባይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተገድሏል ላለው ወጣት ተጠያቂ የሆኑ የመንግሥት ባለስልጣናት እና የጸጥታ ኃይሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠየቀ።

የ17 ዓመት ወጣት የነበረው አማኑኤል ወንድሙ ከበደ ግንቦት 3 ቀን 2013 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተማ ሕዝብ በተሰበሰበበት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መገደሉን የመብት ተሟጋቹ ድርጅት አስታወቋል።

ሂዩማን ራይትስ ዋች እንዳለው የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ታዳጊውን በአደባባይ ከገደሉት በኋላ የታዳጊውን የቤተሰብ አባላት ጨምሮ ሌሎች ነዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን በመግለጫው አስታውቋል።

የሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር የሆኑት ሌቲሻ ባደር ፥ "ባለስልጣንት ወጣቱን መግደላቸው ለሰው ልጅ ሕይወት ያለውን ቸልተኝነት ያሳያል" ብለዋል።

የአካከባቢው ባለስልጣናትም ወጣቱን በአደባባይ መግደላቸው እና ቪዲዮ መቅረጻቸው ከሕግ በላይ እንደሆኑ እምነት እንዳላቸው ያሳያል ብለዋል።

የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርት : https://www.hrw.org/news/2021/06/10/ethiopia-boy-publicly-executed-oromia

#ቢቢሲ
@tikvahethiopia
#LiveUpdate

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛውን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ በጊዜ ሠሌዳው ቅደም ተከተል መሠረት በመከናወን ላይ ስላለው የመራጮች ድምጽ መስጫ ወረቀት ህትመት እና አጠቃላይ የቴክኒክ ሥራዎችን አስመልክቶ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ለሚዲያዎች መግለጫ ይሰጣል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የሚገኙ ሲሆን በሚነሱ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃዎችን የምንለዋወጥ ይሆናል። መልካም ቆይታ !

@tikvahethiopia
ዛሬ ሰኔ 3 በፋግታ ወረዳ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ በሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ።

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ፋግታ ወረዳ ዛሬ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ በአንዳንድ አከባቢዎች ሰብል ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ፋግታ ኮሙዩኒኬሽን ሪፖርት አድርጓል።

ዝርዝር የጉዳቱ መጠን እንዲሁም አካባቢዎቹ አልተገለፁም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ዛሬ ጥዋት የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤ አደም ፋራህ የጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መልዕክት ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሼል እና ለአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዩርሱላ ቮን ደር ላየን ማድረሳቸው መገለፁ ይታወሳል።

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩቴ የተላከ ደብዳቤን ስለማድረሳቸው ተሰምቷል።

ደብዳቤውን ለሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና የውጭ ንግድ እና ልማት ትብብር ሚኒስትር ሲግሪድ ካግ ነው ያስረከቡት።

ወ/ሮ ዳግማዊት ደብዳቤውን ባስረከቡበት ወቅት ከሚኒስትሯ ጋር በተለያዩ ጉደዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

በውይይታቸው ወቅትም በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣ በመጪው ሃገራዊ ምርጫ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር እና በኢትዮ ሱዳን የድንበር ውዝግብ ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡

@tikvahethiopia
"...ቱርክ በየትኛዉም ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጎን ትቆማለች" - አምባሳደር ያፕራክ አልፕ

በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ የህዳሴዉ ግድብ ሶስትዮሽ ድርድር እና የኢትዮ ሱዳን የድንበር ዉዝግብ በሠላማዊ መንገድ ሊፈታ ይገባል አሉ።

አምባሳደሩ ይህን ያሉት ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በሰጡት ቃለምልልስ ነው።

ቱርክ ከሱዳን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ግንኙነት ያላት አገር መሆኗን የገለፁት አምባሳደሩ ፥ ጦርነት ለሁለቱም አገራት ስለማይበጅ ልዩነታቸዉን በዉይይት እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

አምባሳደር ያፕራክ አልፕ አገራቸዉ በየትኛዉም ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆምም አስታዉቀዋል፡፡

አገራቸዉ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ልዉዉጥ ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እንደምትሰራም ገልፀዋል።

ቱርክ እና ኢትዮጵያ በርካታ ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት እንዳላቸዉ የገለፁት አምባሳደር ያፕረክ አልፕ፤ አሁን ላይ የአገራቱ አመታዊ የንግድ ልዉዉጥ 6 መቶ ሚሊዮን ዶላር ደርሷል ብለዋል፡፡

በሌላ መረጃ : ኢትዮጵያና ቱርክ በትራንስፖርቱ ዘርፍ በቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን መግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ከቱርኩ የትራንስፖርት እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር አዲል ካራይስማይሎግሉ ጋር ስምምነቱን መፈራረማቸውን በትዊተር ገጻቸው አሳውቀዋል።

#EthioFM #WeyzeroDagmawitMoges

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#LiveUpdate የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛውን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ በጊዜ ሠሌዳው ቅደም ተከተል መሠረት በመከናወን ላይ ስላለው የመራጮች ድምጽ መስጫ ወረቀት ህትመት እና አጠቃላይ የቴክኒክ ሥራዎችን አስመልክቶ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ለሚዲያዎች መግለጫ ይሰጣል። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የሚገኙ ሲሆን በሚነሱ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃዎችን የምንለዋወጥ…
#BREAKING

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ በገጠሙ የህትመት ችግር፣ የጸጥታ ሁኔታና የዳታ ችግር ምክንያት በሁለት ዙር እንደሚካሄድ አስታውቋል።

ሁለተኛው ዙር ምርጫም ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሆን ቦርዱ ወስኗል።

በሁለተኛ ዙር ምርጫ የተካተቱት አካባቢዎችን ዝርዝር ሲገለፅ እናሳውቃችኃለን።

በሌላ በኩል፥ የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ መራዘሙን ቦርዱ አስታውቋል።

የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ይደረጋል ተብሏል።

PHOTO : Tikvah-Family
@tikvahethiopia
#Update

በተሻሻለው የምርጫ 2013 ተመዝጋቢዎች ቁጥር ሪፖርት መሰረት አጠቃላይ የመራጮች ቁጥር 37,408,600 መድረሱን ያሳያል።

ከነዚህ ውስጥ 20,317,472 ወንዶች ሲሆኑ 17,091,128 ሴቶች ናቸው።

@tikvahethiopia
#BREAKING

የኢትዮጵያ ብሄራቂ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14/2013 የሚካሄደው 6ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ በሶማሌ ክልል እንደማይካሄድ አስታውቋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ፥ ለምርጫው በተያዘለት ጊዜ አለመካሄድ የህትመት ችግር እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩል ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ የቀረቡ ቅሬታዎችን በምክንያትነት አስቀምጠዋል።

የክልሉ የህዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤት እጩዎች ጷግሜ 1 ቀን 2013 ዓ/ም በሚካሄድ ሁለተኛ ዙር ምርጫ ይመረጣሉ መባሉን አል ዓይን ዘግቧል።

PHOTO: Tikvah-Family
@tikvahethiopia
#Update

ድምፅ መስጫ ወረቀቶች በድጋሚ ህትመት የሚያስፈልጋቸው የምርጫ ክልሎች ከላይ በዝርዝር የተገለፁት ናቸው።

#ምርጫ2013 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 6,069 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 280 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 273,678 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት 5 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,231 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,920,676 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ማክሮን በስራ ጉብኝት ላይ እያሉ በጥፊ ተመቱ። የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የስራ ጉብኝት ላይ እያሉ በጥፊ ተመቱ። ፕሬዚደንቱ በደቡብ ምስራቅ ፈረንሳይ #ደሮም_ከተማ ጉብኝት በማድረግ ላይ እያሉ ነው በጥፊ የተመቱት። ማክሮን በተከለለ አጥር ውስጥ የነበሩ ሰዎችን ሰላም ለማለት ጠጋ ሲሉ ነው ክስተቱ የተፈፀመው። ፕሬዚዳንቱ በጥፊ ሲመቱ “ Down with Macron-ism ” የሚሉ ቃላት…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፕሬዜዳንት ማክሮንን በጥፊ የመታው ግለሰብ ተፈረደበት።

የፈረንሳዩን ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በሥራ ጉብኝት ላይ እያሉ በጥፊ የተማታው ግለሰብ 18 ወራት እስር ተፈርዶበታል።

ዳሚኤን ታሬል የተባለው ግለሰብ ፕሬዝደንቱን መማታቱን ለፍርድ ቤት በሰጠው ቃል አምኗል። ዐቃቤ ሕግ ግለሰቡ ሆነ ብሎ የኃይል እርምጃ ወስዶ ፕሬዝደንቱን ተማትቷል ሲል ከሶታል።

በጥፊ የተማታው ግለሰብ "ማክሮኒዝም ይውደም" እያለ ነው ፕሬዝዳንቱን በጥፊ የመታቸው።

ፍርድ ቤቱ ግለሰቡ ላይ የ18 ወራት እስር ቢፈርድበትም 14ቱ በይርጋ የሚታይ ይሆናል ብሏል።

ማክሮንን በጥፊ በመማታት ጥፋተኛ የተባለው ግለሰብ የ4 ወራት እስሩን የሚጀምር ሲሆን በቀጣዮቹ 18 ወራት ውስጥ ጥፋት አጥፍቶ ቢገኝ የ18 ወራት ፍርዱ የጸና ይሆናል።

ማክሮንን በጥፊ የተማታው ዳሚኤን ታሬል ፕሬዝደንቱን ለምን እንደተማታ ሲጠየቅ፤ ከጓደኛው ጋር የፕሬዝደንቱን ጉብኝት መኪናቸው ውስጥ ሆነው እየጠበቁ ሳለ በሁሉም ዘንድ የሚወሳ ተግባር ለመፈጸም ማቀዱን ተናግሯል።

ግለሰቡ ኃይል የመጠቀም ሃሳብ አልነበረኝም ብሏል።

ፕሬዝደንቱ ላይ እንቁላል ወይም ክሬም ኬክ ለመወርወር አቅዶ የነበረ ቢሆንም ፕሬዝደንቱ ቀርበውት "ድምጼን [የምርጫ] ልሰጠው እንደምችል ሲገምተኝ በጣም ተበሳጨሁ" በማለት ተናግሯል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

Video Credit : AlexpLille

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሚቀጥለው ሳምንት የአሜሪካ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ሀገራት የሰብዓዊ ዕርዳታ እና ልማት አመራሮች በትግራይ ሁኔታ ላይ እንደሚመክሩ ተሰምቷል። ውይይቱ በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ እንደሆነ ይጠበቃል። ስብሰባው በትግራይ ክልል ባለው የሰብዓዊ ቀውስና ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ማዕቀፍ ውስጥ አስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ላይ…
#Update

ዛሬ በትግራይ ክልል ያለውን የሰብዓዊ ቀውስን በተመለከተ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት (EU) ከፍተኛ ባለስልጣናት በኦንላይን ውይይት አድርጋዋል።

የዛሬው ውይይት ቀደም ብሎ እንደተገለፀው በቀጥታ ተላልፏል።

በውይይቱ እነማን ተሳተፉ ?

- በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ፣
- የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር፣
- የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ
- የአውሮፓ ሕብረት የቀውስ አስተዳደር ኮሚሽነር ያኔዝ ሌነርቼክ
- የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ተሳታፊ ሆነውበታል።

እነንማን ምን አሉ የሚለውን በዚህ ያንብቡ : https://telegra.ph/Tigray-06-10

በሌላ በኩል በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ዛሬ በዚህ መድረክ ባሰሙት ንግግር ነገ የቡድን ሰባት (G7) አገራት ሰብሰባ እንደሚኖራው ገልጸው ፤ ከG7 አገራት አጀንዳዎች መካከል የኢትዮጵያ ጉዳይ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ጉዳይም የተባበሩት መንግሥታት (UN) የጸጥታ ም/ ቤት አጀንዳ መሆን አለበት ብለዋል። ፌልትማን ረሃብ የጦርነት መሳሪያ ተደርጎ መወሰዱ የተመድ የጸጥታ ምክር ቤት አጀንዳ ያደርገዋል ሲሉ ተደምጠዋል።

ተኩስ እንዲቆም፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደረስ እና የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ጫና ማድረጋችንን መቀጠል አለብን ብለዋል።

#BBC

@tikvahethiopia