TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 3,442 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 110 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 273,024 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት 4 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,213 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,888,214 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
#Tigray

በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ም/ቤት የቨርሞንት ክፍለ ሃገር ሴኔተር ፓትሪክ ሌሂ በትግራይ ጉዳይ መግለጫ አውጥተዋል።

መግለጫው ሲጀምር "በ1984 እአአ በኢትዮጵያ በተራዘመ ድርቅ ሳቢያ በስፋት በተከሰተው የምግብ እጥረትና በመንግሥት አድላዊ ፖሊሲዎች የተነሳ የደረሰውን ከባድ ረሃብ በዚያም ምክንያት ብዙዎቹ የትግራይ ተወላጆች የሆኑ ሰውነታቸው በረሃብ ያለቀ ፤ 1 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የተሰደዱበትን የሚዘገንን ቸነፈር በደንብ አስታውሰዋለሁ"

ቆይቶ ዝናብ መጣል ጀመረ። ስደተኞቹም ወደቀያቸው ተመለሱ። ይሁን እንጂ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሃገሪቱ በየጊዜው ግጭት እና የበቂ ምግብ ዕጦት ተለይቷት አያውቅም ሲሉም የዩናይትድ ስቴትሱ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል አክለዋል።

ዛሬ የትግራይ ህዝብ ዘግናኝ በሆነ ደረጃ ጭካኔ የተመላበት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጥቃት እየተፈጸመበት ነው ያሉት ሴኔተር ሌሂ ህዝቡ በአጣዳፊነት የሚያስፈልገው የምግብ እርዳታ እንዳይደርሰው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደራዊ ኃይሎች እንዲሁም ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች እየከለከሉ ናቸው" ብለዋል።

“የአሜሪካ እና ሌሎችም ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም የግጭቱ ተሳታፊ ወገኖች ግጭቱን አቁመው ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ የወሰዱት አንዳችም ትርጉም ያለው እርምጃ የለም" ሲሉ አክለዋል።

"ትግራይ ውስጥ የሚፈጸሙትን ግድያዎች፣ በግዴታ ከቀዬ ማፈናቀል፣ ወሲባዊ ጥቃቶች እና ሌሎችም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲሁም በውሃ አቅርቦት ስፍራዎችና በሆስፒታሎችና በመሰል የጤና ማዕከሎች ላይ የሚደርሰውን ውድመት የአሜሪካ መንግሥት አውግዟል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-06-07 #VOA

@tikvahethiopia
የሮይተርስ ምርመራ ሪፖርት :

ሮተርስ ዛሬ ይፋ ባደረገው የምርመራ ሪፖርቱ የማይካድራ ጭፍጨፋን የሕወሃት ኃይሎች እንደጀመሩት ገልጿል።

አማራ ተወላጆችን የጨፈጨፉት ሻምበል ካሳዬ መኻሪ የተባለ የሕወሃት አባል ያደራጃቸው ሚሊሻዎች እንደሆኑ ከምስክሮች አንደበት መስማቱን ሮይተርስ አሳውቋል።

ሚሊሻዎች እንዲሁም የከተማዋ ፖሊስ አባላት የአማራዎችን መኖሪያ ቀበሌዎች በመክበብ በገጀራ እና ጥይት በጅምላ እንደጨፈጨፉ ሪፖርቱ አብራርቷል፡፡

የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች እና መከላከያ ሠራዊት ወደ ከተማዋ የገቡት ከጭፍጨፋው በኋላ እንደሆነ ሪፖርቱ ይገልጿል።

የሮይተርስ ሪፖርት የአማራ ክልል ታጣቂዎች በትግራይ ተወላጆች ላይ የበቀል ርምጃ መውሰዳቸውን ጠቅሷል፡፡

የሮይተርስ የምርመራ ሪፖርት👇
https://www.reuters.com/investigates/special-report/ethiopia-conflict-expulsions/ #Wazema

@tikvahethiopia
"...በሰሜን የገጠመን ግጭት እስካሁን ከገጠሙን ከሁሉም የከፋው ነው" - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የኢፌድሪ ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ያለፉት ሦስት ዓመታት ዋና ዋና ንግግሮቻቸውን የያዘ ''ዐሻራ'' የተሰኘ መጽሐፍ የምረቃ ስነስርዓት እና በኢፕድ 80ኛ ዓመት በዓል ላይ ተገኝተው ነበር።

በዚህም ወቅት ላይ የ3 ዓመታቱን ፈተናዎች በተመለከተ ንግግር አድርገዋል፡፡

ከተናገሩት መካከል ፦

" ተደጋጋሚ ችግር ያሳለፍንባቸው ያለፉት ሶስት ዓመታት ፣ በፊት ከነበሩት 10 ዓመታት ጋር ሲነፃፀሩ ቢያንስ ከጂኦ ፖለቲካ አንፃር የከፉ ጊዜያት ናቸው።

በሰሜን የገጠመንን ግጭት አንዳንዶች ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት፣ ከካራማራው ጦርነት ጋር ሊያነፃፅሩ ይሞክራሉ ፣ ነገር ግን ወታደርም ስለሆንኩ ከሁሉም የከፋው ግጭት ነው።

ከጣልያን ጋር ስንዋጋ በጎራዴም ቢሆን እኛ ጎራዴያችንን ይዘን እነሱም በመሳሪያቸው ተዋግተናል። በኤርትራ እና ካራማራውም እኛም እነሱም ባለን ነው የተዋጋነው።

አሁን ግን የነበረው ውጊያ የኛን ትጥቅ እና የኛን መከላከያ በማፍረስ ነው ከኛ ጋር የነበረው ወጊያ።

ባለፉት ሶስት ዓመታት ብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆነን በሰላሙ ጊዜ ተጀምረው መጠናቀቅ ካልቻሉ 10 ትላልቅ የስኳር ፋብሪካዎች 7ቱን አጠናቀናል፤ ሌሎች ብዙ ፕሮጀክቶችንም እንዲሁ።"

#አልዓይን

ፎቶ : የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

@tikvahethiopia
የሔመቲ አቋራጭ መንገድ!

( #በጋዜጠኛ_ኤልያስ_መሰረት )

ሌ/ጀ መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ (ሔመቲ) የሚመሩትን የሚሊሺያ ጦር ይዘው የሱዳን መከላከያ ሀይልን መቀላቀል እንደማይፈልጉ አሳውቀዋል።

ዛሬ ከወደ ካርቱም የተሰማው ይህ ዜና ብዙ ቀጠናዊ 'እድሎችን' ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ይገመታል።

የአልበሽር መንግስት ከወደቀ ወዲህ ገሸሽ እንደተደረገ የተሰማው ሔመቲ የያዘውን ሀይል ይዞ በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳሰበ በይፋ ባይታወቅም ከግብፅ ጋር ደፋ ቀና እያለ ላለው የሱዳን መንግስት ሌላ ከባድ ራስ ምታት ሊሆን ይችላል።

በቀጠናው ስትራቴጂካል አሰፋፈር ለማስተካከል ለሚጥሩ ደግሞ ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነ ይታሰባል።

ከግመል ነጋዴነት ተነስቶ አሁን ሱዳን ውስጥ ከፍተኛ ሀይል በእጁ የያዘ ግለሰብ የሆነው ሔመቲ ሚሊሺያዎችን በቀላሉ ማንቀሳቀስ የሚችል፣ በፊት ከግመል፣ አሁን ደግሞ ከወርቅ ንግድ ሚሊዮኖችን ያፈሰ እንዲሁም የሱዳን ወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤት ምክትል ሀላፊ ነው። ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሀይል (RSF) የተባለውን ጦር ይመራል።

"አሁን ላይ ሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሽግግር ምክር ቤቱ ዋና ሀላፊ ቢኖራትም ሔመቲ በእጁ ከፍተኛ ሀይል ያለው ግለሰብ ነው" ይላሉ የቀጠናው ተንታኞች።

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ በህዳሴ ግድብ ዙርያ ሲያካሂዱት የነበረው ውይይት ካለ ስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ሔመቲ የዛሬ አመት ግድም አዲስ አበባ ተገኝቶ ነበር። ይህ ጉብኝት ሱዳን እና ግብፅ ውስጥ ያሉ አንዳንዶችን አሳስቦ ነበር።

ቀጠናዊ ሚዛን ለማስተካከል ለሚፈልግ ሁሉ ሔመቲ አሁን ላይ ተገኚ (free agent) ይመስላል ፤ እዚህ ላይ በኢትዮጵያ በዲፕሎማቶች ስራ እንደሚሰራበት ተስፋ ይደረጋል።

@tikvahethiopia
ኤርትራ የባይደንን አስተዳደር ወቀሰች።

የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ትግራይ ክልል ውስጥ ላለው ጦርነት ላለፉት 20 ዓመታት የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባርን ሲደግፉ የቆየ ያሉትን የአሜሪካ መንግስት አስተዳደር ተጠያቂ ማድረጉን APን ዋቢ አድርጎ ዶቼ ቨለ አስነብቧል።

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለሚካሄደው ጦርነት ኤርትራን ተጠያቂ ማድረጉም መሠረተ ቢስ ነው ሲሉ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡስማን ሳሌህ መግለጫ ሰጥተዋል።

ኡስማን ሳሌህ ትናንት ሰኞ ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በፃፉት እና በምክር ቤቱ በተሰራጨዉ ደብዳቤ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በክልሉ ጣልቃ በመግባት እና በማስፈራራት «ተጨማሪ ግጭትን እና አለመረጋጋትን ያስከትላል» ሲሉ ከሰዋል።

የአሜሪካው አሶሽየትድ ፕሬስ «በግምት ስድስት ሚሊዮን ሕዝብ ይኖርበት ከነበረዉ የትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት አንድ ሦስተኛውን አካባቢዉን ለቅቆ ሸሽቶአል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ በጦርነቱ እንደተገደሉም ይገመታል። በአሁኑ ወቅት የመንግሥት ወታደሮች ለበርካታ ግፎች ተጠያቂ ናቸው ከሚባሉት ከጎረቤት ኤርትራ ወታደሮች ጋር በትብብር ላይ ናቸዉ» ሲል ስለመፃፉ ዶቸ ቨለ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#AntonioGuterres #Tigray

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ በርካታ የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አካባቢዎች ረሃብ አፋፍ ላይ መሆናቸው ተናገሩ፡፡

ዋና ጸሃፊው የትግራይ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ እጅግ አስከፊ ወደ ሆነ ደረጃ መሸጋገሩ አይቀሬ ነው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

 የተጋረጠውን የረሃብ አደጋ ለመግታት ሰብአዊ እርዳታ ማዳረስ እንዲሁም በቂ ፈንድ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ዋና ጸሃፊው በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት አስታውቋል፡፡

"አሁን የሚከናወኑ ተግባራት ለበርካታ ሰዎች የመኖርና አለመኖር ጉዳይ መሆናቸውን መረዳት ተገቢ ነው"ም ነው ያሉት የተ.መ.ድ ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ፡፡

የጉተሬዝ ትግራይን የተመለከተ መግለጫ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በትግራይ ያሉ የግጭቱ ተዋናዮች ተኩስ እንዲያቆሙና ያልተገደበ የስብአዊ እርዳታ ተደራሽነት እንዲኖር ጥሪ እያደረገ ባለበት ወቅት መሆኑን አል ኣይን በድረገፁ አስነብቧል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ/ኦቻ/ እየተካሄደ ባለው ግጭት ሳቢያ በትግራይ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ አሳሳቢ መሆኑን እና በኢትዮጵያ ከ1970ዎቹ ወዲህ ከፍተኛ የረሀብ አደጋ እንዳንዣበበ ባለፈው ሳምንት አሳትውቋል።

#AlAIN

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ/ም !

" ኢህአዴግ " ስልጣን ከያዘ በኃላ ለ3ተኛ ጊዜ የተካሄደውን #የ1997ቱ ሀገር አቀፋዊ ምርጫ ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ ሳቢያ ሰኔ 1/1997 በመንግስት የተገደሉ ዜጎች ዛሬ 16ኛ ዓመት መታሰቢያቸው ነው።

በወቅቱ "ኢህአዴግ" ይህን መሰሉ አንባገነናዊ ተገባር የፈፀመው ስልጣኑን ለማስጠበቅ ፣ ስልጣኑን የሚያስጠብቀውም በመሳሪያ ኃይል እንጂ በህዝብ ድምፅ እንዳልሆነ የተቀናቃኝ ፖለቲካ ኃይሎች በተለያየ ጊዚያት ተናግረዋል።

ሰኔ 1 ቀን 1997 በግፍ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ ዜጎች ለነፃነት፣ ለዴሞክራሲ፣ ለፍትህ፣ ለሀገራዊ አንድነት ዋጋ የከፈሉ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፤ በየዓመቱም በዚህ ቀን ይታሰባሉ።

ፖለቲከኞች ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾ ይህን የሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም ክስተት ለሁሉም ትምህርት የሚሰጥ እና መቼም ቢሆን ሊደገም የማገባው ብዙ ትምህርትም ሰጥቶ ያለፈ እንደሆነ ይናግራሉ።

በወቅቱ (ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም) በግፍ የተገደሉ ፣ የቆሰሉ፣ ለእስርና እንግልት የተዳረጉ ዜጎች ኢትዮጵያን ያስተዳደር በነበረው "ኢህአዴግ" በሚባለው ፓርቲ ወቅት ሲሆን ፓርቲው ከዓመት በፊት በኢትዮጵያ ምድር ህልውና እንዳይኖረው ተደርጎ፣ ከስሟል።

በውስጡ የነበሩ ድርጅቶችም ከአንዱ (#ህወሓት) በቀር አንድ ላይ ተዋህደው ውህድ ፓርቲ ፈጥረው ኢትዮጵያን እያስተዳደሩ ነው።

Video Credit : Biniyam Hirut
@tikvahethiopia
የዓለም አቀፍ ዜና አውታሮች ድረገፆች ተቋረጡ።

ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች የሆኑት የፋይናንሻል ታይምስ ፣ የኒው ዮርክ ታይምስ እና የብሉምበርግ ኒውስን ጨምሮ የሌሎችም የዜና አውታሮች ድረገፆች አገልግሎታቸው ተቋረጠ።

የCNN እና የፈረንሳይ ሌሞንዴ ድረገፆችም 4 ሰዓት አካባቢ የስህተት ምልክት ታይቶባቸዋል። አልጀዚራ ድረገፅም ተመሳሳይ ችግር ገጥሞት ነበር።

የብሪታኒያው ዘጋርዲያን በድረገፁና በአፕሊኬሽኑ ላይ ችግር ገጥሞት እንደነበረ ገልጿል ሌሎች የብሪታኒያ የዜና አውታሮች ድረገፆች ወዲያው መስራት አቁመው ነበር።

በርከት ባሉት ዓለም አቀፍ ዜና አውታር ድረገፆች ላይ ምን እንደተፈጠረ እና ለምን እንደተቋረጡ ለጊዜው አልታወቀም።

#አልጀዚራ

@tikvahethiopia
የጀርመን ድጋፍ ለኢትዮጵያ :

ጀርመን 8.5 ሚሊዮን ዩሮ በኢትዮጵያ በግጭትና በአየር ንብረት ለውጥ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ህይወትን ለመታደግ ድጋፍ አድርጋለች።

የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ከጀርመን ህዝብ 8.5 ሚሊዮን ይሮ በኢትዮጵያ በግጭት እና በአየር ንብረት ለውጥ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ህይወትን ለመታደግ ያደረገዉን መዋጮ አወድሷል።

የተጠቀሰዉ ገንዘብ ከ2021 እስከ 2023 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ ሲሆን ድጋፉ ጀርመን ለምስራቅ አፍሪቃ ቀጠና በምታደርገዉ የገንዘብ ድጋፍ አካል ዉስጥ የተካተተ ነዉ።

ይህ ከጀርመን ህዝብ የተገኘዉ ርዳታ በትግራይ የዓለሙ የምግብ ፕሮግራም «WFP» የአስቸኳይ የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ ከሚሰጠዉ ድጋፍ ጋር የተያያዘ ነዉ።

ልገሳዉ እስከ 2.1 ሚሊዮን ሕዝብ የአስቸኳይ ጊዜ ርዳታ ምላሽን ለመስጠት አስተዋፅዖ ያደርጋል ተብሎአል።

በትግራይ ክልል በአጠቃላይ 5.2 ሚሊዮን ህዝብ ወይም ከጠቅላላው የትግራይ ህዝብ 91 በመቶ የሚሆነው አካባቢዉ ላይ በሚታየዉ ግጭትና ጦርነት ምክንያት አስቸኳይ የምግብ ርዳታን ፈላጊ ነዉ።    

ልገሳዉ በተጨማሪ በሃገሪቱ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለስደተኞች በሚሰጠዉ ርዳታ እና  በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ውስጥ በከፍተኛ የአየር ንብረት መዛባት ለተጎዱ ማህበረሰቦች ሕይወት አድን እና ሕይወትን የሚቀይር የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ርዳታን ለማድረስ ያለመ ነዉ።  

የዓለም የምግብ ድርጅት (WFP) እስከ ዓመቱ መጨረሻ በትግራይ ክልል ርዳታዉን ለማዳረስ 203 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያስፈልገዋል። ከዚህ በተጨማሪ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት በሶማሌ ክልል የሚደረገውን የምግብ ርዳታ ሥራ ለማካሄድ ተጨማሪ 97 ሚሊዮን ዶላር ይፈልጋል።

መረጃው የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዓለም አቀፍ ዜና አውታሮች ድረገፆች ተቋረጡ። ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች የሆኑት የፋይናንሻል ታይምስ ፣ የኒው ዮርክ ታይምስ እና የብሉምበርግ ኒውስን ጨምሮ የሌሎችም የዜና አውታሮች ድረገፆች አገልግሎታቸው ተቋረጠ። የCNN እና የፈረንሳይ ሌሞንዴ ድረገፆችም 4 ሰዓት አካባቢ የስህተት ምልክት ታይቶባቸዋል። አልጀዚራ ድረገፅም ተመሳሳይ ችግር ገጥሞት ነበር። የብሪታኒያው ዘጋርዲያን በድረገፁና በአፕሊኬሽኑ…
#Update

ዛሬ ለሠዓታት ተቋርጠው የነበሩት ዓለም አቀፍ የዜና አውታር ተቋማት ድረገፆች (የብሉምበርግ ኒውስ ፣ የፋይናንሻል ታይምስ ፣ የኒውዮርክ ታይምስ) መስራት ጀምረዋል።

ከዓለም ዜና አውታር ድረገፆች በተጨማሪ የዩናይትድ ኪንግደም (UK) መንግስት ድረገፅ gov.uk ፣ አማዞን መገበያያ፣ ሬዲት ተመሳሳይ ችግር ገጥሟቸው ነበር።

ችግሩ እጅግ በበርካታ የዓለም ክፍል የታየ ቢሆንም በርሊን ውስጥ ድረገፆቹ ሳይቋረጡ ሲሰሩ ነበር ብሏል ዘጋርዲያን።

አሁን ላይ ለሰዓታት ያህል ተቋርጠው የነበሩት ድረገፆች መስራት የጀመሩ ሲሆን ለችግሩ መፈጠር ምክንያቱ "ፋስትሊ" የተሰኘው የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ነው ሲል ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

" ፋስትሊ " ኩባንያ ድረ ገጾችን ከጥቃቶች የመከላከል አግልግሎት በመስጠት እንዲሁም በድረ ገጾች ላይ የጎብኚዎች ቁጥር ሲበዛ የድረ ገጹ ፍጥነት እንዳይቀንስ በመሥራት ይታወቃል።

የአንድ ኩባንያ ችግር የበርካታ ድረ ገጾች አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረጉ መነጋገሪያ ሆኗል።

ኢሴት በተሰኘ ኩባንያ ውስጥ የሳይበር ደህንነት ባለሙያ የሆኑት ጄክ ሞር፤ በርካታ መሠረት ልማት ፈሰስ የተደረገባቸው ድረ ገጾች በአንድ ኩባንያ እጅ ላይ እንዲወድቁ ማድረግ አግባብ አይደለም ሲሉ ስለመናገራቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia